ራስ ጋይንት የገብርየ ልጅ

ራስ ጋይንት የገብርየ ልጅ Communicated

"አዎጅ" "አዎጅ" በል" የስማህ ላስማ አስማ"የአማራ ክልል የአብክመ ፍርድ ቤት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደርስራተኞችን ጥቅም፣የስራ ልምድ፣ ሳያስከብር በቸልተኝነትመመልከቱ የዘመኑን የፍትህ ...
10/03/2025

"አዎጅ" "አዎጅ" በል" የስማህ ላስማ አስማ"
የአማራ ክልል የአብክመ ፍርድ ቤት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደር
ስራተኞችን ጥቅም፣የስራ ልምድ፣ ሳያስከብር በቸልተኝነት
መመልከቱ የዘመኑን የፍትህ ደረጃ ምን ላይ እደደረስ የሚያሳይ
ነው። እኛ የፍ/ቤት የአስተዳደር ስራተኞች በአሽባሪነት የተፈረጅን
የማፊያ ስብስብ ወይንም የፖለቲካ ቀስቃሺ ፓርቲ ሳንሆን
እራበን፣ጠማን፣ በምንስራው ልክ ይከፈለን፣የስራችን ጥቅሙና
አግባብነቱ ይታወቅልን፣ እደማንኛውም የኢትዮጵያ የመንግስት
ስራተኞች ጥቅማችንና መብታችን ይከበርልን ብለን የምንጠይቅ
ሚስኪንና ሀገር ወዳድ፣ህዝብ አገልጋይ ዜጎች ነን።
ቢሆንም ግን የዳኞች አስተዳደር ጉባኤና የፍርድ ቤት ሺማምንቶች
የራሳቸውን ጥሩ ኑሮ ከነ ደመወዙ እየበሉ፣ለልጆቻቸው ቤታቸውን
እየስሩ፣ልጆቻቸውን እያስተማሩ የእኛን የመብት ጥያቄ በአግባቡ
መዝኖ አለመመለስ የስግብግብነት እጁን ያረዘመ የታወረ የፍትህ
ስርዓት ላይ እየዎኘን መሆኑን በግልፅ ያሳየናል።
በአጠቃላይ ከፍትህ ተቋም እየስራን ፍትህ ያጣን፣ ድምፃችን
የታፈነ፣ ብሎም የተረገጥን በመሆናችንና ፍርድ ቤት ማለት
በሚዛን የተወከለ ሁሉም እኩል የሚስፈርበት ቢሆንም የፍርድ
ቤት የአስተዳደር ስራተኞችን ስንመለከት ጥግ የሌለው በደል
እየደረስብን ይገኛል።
የአብክመ ፍርድ ቤት በስሩ የሚገኙትን የአስተዳደር ስራተኞች
የሞራላዊ ድሺቀት፣በኑሮ ማበሳቆል፣ የበይ ተመልካች
ማድረግ፣የመብት ጥያቄወችን ማፈንና መርገጡን " አዎጅ"
"አዎጅ" "አዎጅ" ብለን ቀስቅስን በጋራ በቃ ልንለው ይገባል!!
ስራችንን በቅንነት እየስራን መብታችንን እንጠይቅ። ለዳኞች ብቻ
የተቋቋመውን ኢትዮጵያዊ ግብረ ስናይ ድርጅት የሆነውን የፍርድ
ቤት የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በቃህ ልንለው ይገባል።
"ፍትህን እየደገፍን ፍትህ እንጠይቃለን "

3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረ...
06/06/2023

3 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ናቸው። ለፈተና በቂ ዝግጅት ስላላደረጉ ለመሸወድ ፈለጉ። በዚህም ምክንያት አንድ መላ ዘየዱ። ራሳቸውን ግሪስ ቀቡና ራሳቸውን በሚገባ በማቆሸሽ ከሌክቸረሩ ፊት በመቅረብ እንዲህ ሲሉ ምክንያታቸውን አቀረቡ፦

ኢንስትራክተር በጣም እናዝናለን፤ ፈተናውን ለመፈተን የማያስችል እንከን ገጥሞናል። ምክንያታቸውን አስከተሉ፦

አንድ ሰርግ ላይ ታድመን ነበር፤ እናም ከፕሮግራሙ በኋላ በመመለስ ላይ እያለን በመንገዳችን ላይ መኪናችን ብልሽት ገጠማት። የመኪናችንን ብልሽት ለመጠገን እንደምትመለከተን በአስቀያሚ ሁኔታ ቆሽሸናል።

#ሌክቸረሩም ከምክንያተቸው በመነሳት ተረዳቸውና ወደቤታቸው እንዲመለሱ ለፈተና ዝግጅት 3ት ቀን ሰጣቸውና አሰናበታቸው።

ከ3ት ቀን በኋላ ለተዘጋጀላቸው ፈተና በበቂ ሁኔታ አጥንተውና ተዘጋጅተው መጡ።

ሌክቸረሩ አንድ ውሳኔ ወሰነና እንዲህ አደረገ ...

ሶስቱም ተራርቀው የተለያየ ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ። ተማሪዎቹም በጣም ተራርቀው ተቀመጡ፤ የፈተና ወረቀትም ተሰጣቸው። ጥያቄዎቹ የሚከተሉት ነበሩ፦

ጥያቄ ቁጥር 1 - ማን ነበር ያገባው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 2 - የት ነበር የሠርግ ፕሮግራሙ የተካሄደው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 3 - መኪናዋ የተበላሸችበት ትክክለኛ ቦታ የት ነው ? (25 % ማርክ)

ጥያቄ ቁጥር 4 - የተበላሸችው መኪና ሞዴሏ ምን አይነት ነው ? (25% ማርክ)

ከጥያቄዎቹ መጨረሻም #ማስጠንቀቂያው እንዲህ ይላል - መልሳችሁ የግድ ተመሳሳይ መሆን አለበት !!!
_______

Africa 10 ን ላይ - ተወስዶ የተተረጎመ

18/09/2022
ይኸ ነገር እዚያ ማዶ ብናየው ምን እንል ነበረ!በውቢቷ ባህርዳር ከተማ እየተገነባና በመጠናቀቅ ላይ ያለው አዲሱ የአባይ ድልድይ!
18/09/2022

ይኸ ነገር እዚያ ማዶ ብናየው ምን እንል ነበረ!

በውቢቷ ባህርዳር ከተማ እየተገነባና በመጠናቀቅ ላይ ያለው አዲሱ የአባይ ድልድይ!

ከአምሳለ በቀቀን እንውጣ!በቀቀን ሰው የሚናገረውን ደግማ መናገር የምትችል የወፍ ዝርያ ነች፡ ይህች ወፍ ቃሉን ትድገመው እንጅ ትርጓሜውን አታውቀውም፡፡የዘመናችን የፌስ ቡክ ጦረኞች የአማራ ታ...
09/09/2022

ከአምሳለ በቀቀን እንውጣ!

በቀቀን ሰው የሚናገረውን ደግማ መናገር የምትችል የወፍ ዝርያ ነች፡ ይህች ወፍ ቃሉን ትድገመው እንጅ ትርጓሜውን አታውቀውም፡፡

የዘመናችን የፌስ ቡክ ጦረኞች የአማራ ታሪካዊ ጠላት የሆነው አጥፊው የትህነግ ቡድንና ደጋፊወቹ በአማራ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጆ ሃገር ለማፍረስ እየዳከረና ህዝብን አፈናቅሎ ሃብት ንብረቱን እየዘረፈ ለጦርነት ስልቱ ይመቸው ዘንድ የአማራን ህዝብ በተለመደ ቅጥፈቱ ለማዘናጋት ያደረገውን ንግግር በበጎ አይቶ የህወሃትን ጥፋት ለማቃለል ሲጥሩ ተስተውሏል፡፡

ህወሃት የአማራ ጠላት ነው፡፡ ተንኮልና ውሸት አብሮት የኖረው ይህ አሸባሪ ቡድን ለትግል የተነሳሳውን የአማራን ወጣት ስነ ልቦና ለመግዛት የጀመረው የአማራና ትግሬን ወዳጅነት ስብከት እየተቀበሉ የትህነግን የጥፋት ፍላጎት ሰማሳካት የሚጥሩ አንቂ ነን ባይ ፌስ ቡከረኞች የትህነግን አላማ ልትረዱት ይገባል፡፡ ከትህነግ በፊት የብዙ ሽህ ዓመታት ወዳጅና ጎረቤት ሆነው የኖሩት የትግራይና የአማራ ሕዝብ ሠላም የሚረጋገጠው በህወሃትና እሱ ጠፍጥፎ በሰራቸው አሻንጉሊቶቹ ሞትና መቃብር ብቻና ብቻ ነው!!

ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ በቆራሪት በኩል አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያገናኘዉን የተከዜን ድልድይ በከባድ መሳሪያ ሰብሮታል። ከታች ያለዉን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑhttps:/...
08/09/2022

ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ በቆራሪት በኩል አማራ ክልልን ከትግራይ ክልል የሚያገናኘዉን የተከዜን ድልድይ በከባድ መሳሪያ ሰብሮታል። ከታች ያለዉን የቴሌግራም ሊንክ ይጫኑ
https://t.me/+OST9tm0FHXE3Mjc8

 # # # የአመቱ ምርጥ ፎቶ
08/09/2022

# # # የአመቱ ምርጥ ፎቶ

07/09/2022

በሁለት አመት ውስጥ በተደረገው ውጊያ የተሰዋ እንጂ የተማረከ አንድ ፋኖ የለም !!

አትገረምም አንተ !!

የማስመሰል ስራ ቢቀርባችሁ ምነው!የደሀ ልጅ ተመዝብሮ ካለቀ በኋላ በዚህ መልኩ አቀነባብረው ፃፏት።ገንዘብ ያለው ከፍሎ  የሌለው ተቀድሮ ብድር ያጣው በወለድ ገንዘብ ተበድሮ ተከፈለ በኋላ ጃን...
07/09/2022

የማስመሰል ስራ ቢቀርባችሁ ምነው!

የደሀ ልጅ ተመዝብሮ ካለቀ በኋላ በዚህ መልኩ አቀነባብረው ፃፏት።
ገንዘብ ያለው ከፍሎ የሌለው ተቀድሮ ብድር ያጣው በወለድ ገንዘብ ተበድሮ ተከፈለ በኋላ ጃንጥላ መስለው ለማስመሰል ዘብ ብለው መጡ።

ይህ ደብዳቤ እውነት ከሆነ የከፈሉትን መልሱላቸው ተብሎ ይፃፍ ነበር።
@@@ # # # #ሸር ላይክ አድርጉ
ለተጨማሪ መረጃ https://t.me/+OST9tm0FHXE3Mjc8
# # # like ያድርጉ #

በመዲናዋና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ አደጋዎች የ115 ሰወች ሕይወት አልፏል  አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ ...
07/09/2022

በመዲናዋና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ አደጋዎች የ115 ሰወች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ በ2014 ዓ.ም በተከሰቱ 511 ድንገተኛ አደጋዎች የ115 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ከደረሱት አደጋዎች መካከል 362 የእሳት ሲሆኑ 149 የጎርፍ፣ የኮንስትራክሽን፣ የወንዝና የኩሬ አደጋዎች ናቸው፡፡

በደረሱት አደጋዎች ምክንያትም የ115 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በ200 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ሕይወታቸው ካለፈው 115 ሰዎች መካከል 14ቱ በእሳት አደጋ ምክንያት መሆኑን አስታውሰው÷ ቀሪዎቹ 101 ሰዎች ደግሞ በተለያየ ድንገተኛ አደጋ ነው ሕይወታቸው ያለፈው ብለዋል፡፡

በደረሱት አደጋዎች ምክንያት 577 ሚሊየን 780 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል ያሉት አቶ ንጋቱ÷ በአንጻሩ በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ 39 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ማዳን መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከደረሱት አደጋዎች መካከል የ137 አደጋዎች መንስኤ መታወቁን ጠቁመው÷ 63 በኤሌክትሪክ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

በአጠቃላይ አብዛኛዎቹ አደጋዎች ያጋጠሙት በጥንቃቄ ጉድለት መሆኑንም ነው ባለሙያው የገለጹት፡፡

ሰሞኑንም የበዓል ወቅት እንደመሆኑ ከፍተኛ የኃይል አጠቃቀም እንደሚኖር ጠቁመው÷ ህብረተሰቡ ከምግብ ማብሰል ጋር ተያይዘው ለሚሠሩ ሥራዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ቴሌግራም፦https://t.me/+OST9tm0FHXE3Mjc8

Address

Dubai
WWW.FB.COM

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ራስ ጋይንት የገብርየ ልጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share