16/04/2026
ዳስ ጣል /አንሳዉ/!
አዲስ አበባ አዶ ሸገር
የሁሉ አይደል ሞላዉ ሀገሩ
በፍቅር ጠርተን ከዳር እስከዳር
መሐል ገቡና አቆሙን ከዳር ።
ባቆዩት ሀገር ጀግኖች በአንድነት
እንዴት ይገፋል ኢትዮጵያዊነት ።
ለካ እንዲህ ነዉ ማለቅ
እህ እያሉ ነዶ
ሀገር የሞተበት የት ያለቅሳል ሂዶ ።
ባሳደገኝ ቀዬ ባደኩበት መንደር
ባይተዋር ሰዉ ሁኜ
እንደሌለዉ ሀገር
ያቆምኳትን ሀገር ተፈትኜ በእሳት
እንዴት አቀርቅሬ ባንዴራዬን ላንሳት ።
አባይ ለዘዴዉ ባፍ ይቀድማል
አምኖ መከዳት እንዴት ያማል
ወርቅ ያበረደ ደርሶት አለት
እንዴት ይችላል ዝም ማለት
ከነገ ዛሬ ይሻል ባልኩኝ
የራሴን እንባ ተነጠኩኝ ። share Like Follow