06/09/2026
ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው የሙዚቃ አልበም ሊያወጡ ነው‼
ልደቱ እንደገለፀው "እኔ የኪነ-ጥበብ ሰው ባልሆንም፣ ትንሽ አንዳንድ ዝንባሌዎች አሉኝ እና አንድ 'ሀሳብን በዜማ' የሚል አንድ አልበም በ AI ሰርቻለሁ። እና በውስጡ 12 ዘፈኖችን የያዘ ነው። ይሄ አልበም የፖለቲካ ፍልስፍናዬን፣ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች፣ በሌሎች የሕይወት ዘርፎችም ያለኝን እይታ የምገልጽበት ነው እና ለአዲሱ ዓመት ከመስከረም 1 ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት በየእለቱ ቀን አንድ አንድ ዘፈን እለቃለሁ።" በማለት ገልጿል።
ፖለቲከኛው በመጨረሻም እዚህ ላይ በመድረሱ ብዙዎች እየተነጋገሩበት ነው።
እርሶስ የአቶ ልደቱን ተግባር እንዴት አገኙት?