05/04/2026
🌿 ሆሳዕና በአርያም፦ መድኃኒት ወይም "አቤቱ አሁን አድን!" 🌿
"ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው!" (ማቴ. 21፥9)
የሆሳዕና በዓል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ በትሕትና በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት፣ ሕፃናትና አእሩግ በዝማሬ የተቀበሉበት ታላቅ የደስታ ዕለት ነው።
📖 የበዓሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት፦
የዳዊት መዝሙር (117÷25-26)፦ “አቤቱ እባክህ አሁን አድን... በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፡፡”
የዘካርያስ ትንቢት (9÷9)፦ “እነሆ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያ... ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል፡፡”
🌴 የዘንባባ (የጸበርት) ትርጉም፦
ዘንባባን በግንባራችን ማሰርና መያዝ ጥንታዊና ታሪካዊ ትርጉም አለው፡-
የይስሐቅ ልደት፦ ሣራ ይስሐቅን በወለደች ጊዜ ዘመዶቿ በደስታ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ጎብኝተዋታል።
የእስራኤል ነፃነት፦ እስራኤላውያን ከግብፅ አገዛዝ ወጥተው ባሕረ ኤርትራን ሲሻገሩ በደስታ እግዚአብሔርን ያመሰገኑበት ምልክት ነው።
🙏 በዓሉን በምግባር እናክብር!
"እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል" እንዳለው ጌታችን፤ እኛም በዝማሬና በምስጋና እናክብረው። ከበዓሉ ደስታ ጎን ለጎን ምስጋና ከማይለያቸው ገዳማውያን አባቶቻችን ጋር እንቁም፤ ገዳማትን እንደግፍ።
🇪🇹 ለገዳማት ድጋፍ ለማድረግ፦
ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000442598391
አቢሲኒያ ባንክ፦ 141029444
📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0938644444 / 0918077957
መልካም የሆሳዕና በዓል!
🌴🌴🌴✨✨✨
#ሆሳዕና