24/01/2026
የ3ኛው የባንክ ባለሙያዎች የፉትሳል እግር ኳስ ውድድር ግብዣ በተመለከተ
በቡሄ ትሬዲንግ አዘጋጅነት የሚካሄደው በከተማችን በሚገኙ በግልና በመንግስት የፋይናንስ ተቋማት የባንክ ባለሙያዎች (ቡድኖች) መካከል የሚደረገው የፉትሳል የእግር ኳስ ውድድር ከጥር 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በዘመናዊው የ7 ዴይስ የፉትሳል ሜዳ ዘወትር እሁድ ከ 4 እስከ 6 ሰዓት ይከናወናል።
በዚሁ መሰረት የ3ኛውና የ2018 ዓ.ም ውድድር ምዝገባ እየተከናወነ ይገኛል፤ በመሆኑም በአይነቱ ፍፁም አዝናኝና አስደሳች በሆነው “የባንኮች የፉትሳል የእግር ኳስ ውድድር” ላይ እንደ ተቋም የባንካችሁ የሰራተኞች ቡድን እንዲሳተፍ በታላቅ አክብሮት ተጋብዟዋል።
የውድድሩ መርሀ ግብርና ሽልማትን በተመለከተ፦
1. የዋንጫ ሽልማት
2. የከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት (1ኛ እና 2ተኛ)
3. የኮከብ ተጨዋች ሽልማት
4. የኮከብ ጎል አግቢ ሽልማት
5. የምርጥ ተጫዋች ሽልማት
6. የተጫዋቾች ማሊያ እና ቁምጣ በአዘጋጁ የሚቀርብ ይሆናል
7. ውድድር የሚካሄደው ቦታ፦ አዲስ አበባ ተግባረዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘመናዊው የ7 ዴይስ የፉትሳል ሜዳ
8. የቡድን አባላት ብዛት ፦ 15
9. መመዝቢያ፦ 20,000 (ሀያ ሺ ብር ብቻ)
ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስልክ ቁጥር እና የቴሌግራም ግሩፕ ላይ መመዝገብ ይቻላል።
1. +251962267710
በቴሌግራም ለመመዝገቢያ፦ https://t.me/bankersfutsal Registration issues ላይ ሙሉ ስም፣ የተቋም (ባንክ) ስም እና ስልክ ቁጥር በመሙላት መመዝገብ ይቻላል።
ከታላቅ አክብሮት ጋር ://t.me/BOHETRADINGPLC