21/09/2026
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት፣በታሪካዊቷ ደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው በታላቁ ደብር የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በንጽህና፣ በታማኝነትና በፍጹም ትጋት ሲያገለግሉ የቆዩት፣አባታችን አበ ሰላም ቄሰ ገበዝ ቆሞስ አባ ፍሰሐ አበበ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
አባታችን በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ረጅም ዘመናትን በብዙ አይነት መንፈሳዊ አገልግሎት አሳልፈዋል።
ለሕዝበ ክርስቲያኑ ትልቅ መጽናኛ፣ለቤተ ክርስቲያንም የዕድሜ ጠገብ ምሰሶ በመሆን የኖሩ ታላቅ አባት ነበሩ።
አባታችን ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም፣ የሰሩት መልካም ሥራና የዘለቀው መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ትልቅ አርአያ ሆኖ በልባችን ይኖራል።
የዕረፍታቸው ዜና ቤተሰቦቻቸውን፣ መንፈሳዊ ልጆቻቸውን እና አጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑን በእጅጉ ያሳዘነ ሲሆን፤ ሥርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በመስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም በአንሳስ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ይፈጸማል።
አምላከ ቅዱሳን የአባታችንን ነፍስ በሰማያዊ መኖሪያ ከቅዱሳን አባቶችን ጋር ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለመንፈሳዊ ልጆቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን።
እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን! አሜን።
ዜና ተዋሕዶ - 11/1/2019 ዓ.ም