Berekah Tube

Berekah Tube የነቃ ትውልድ!

⛔️የከባድ መኪና ሹፌሮች "የቸርች ማሰርያ ኩፖን" በግዳጅ እንዲገዙ እየተደረገ መሆኑ ተዘገበ~~~~~~~~የከባድ መኪና ሹፌሮች  በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ በደሎች እየደረሱባቸው መሆ...
13/12/2025

⛔️የከባድ መኪና ሹፌሮች "የቸርች ማሰርያ ኩፖን" በግዳጅ እንዲገዙ እየተደረገ መሆኑ ተዘገበ
~~~~~~~~
የከባድ መኪና ሹፌሮች በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለያዩ በደሎች እየደረሱባቸው መሆኑን በከፍተኛ ምሬት እየተናገሩ ቆይተዋል፡፡ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለሚመለከተው አካል አቤት ቢሉም መንግስት ምንም እንኳን የምችለዉን ማሻሻያ ለማድረግ እየሰራሁ ነው ቢልም እስካሁን ድረስ መፍትሄዎችን እንዳላገኙና ለመስራትም እጅግ እየተቸገሩ መሆኑን ፣ይህንንም ተከትሎ በራሳቸዉና በቤተሰቦቻቸው ህይወት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን ይገልጻሉ፡፡

እነዚህ የከባድ መኪና ሹፌሮች ከሚያነሷቸው ችግሮች መሃል የደህንነት ስጋቶች፣ የስራ ክብደት እና የደሞዝ አለመመጣጠን፤ የመሰረተ ልማት አለመሟላትና ያንንም ተከትሎ የጉዞ መስተጓጎል፣ አስተዳደራዊ በደሎች የሚጠቀሱ ሲሆኑ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በየአርቴፊሻል ኬላው በአንድ ጉዞ ዉስጥ ብቻ በተደጋጋሚ በሚጠየቁት ገደብ አልባ ገንዘብ እጅግ መማረራቸዉን ሲገልጹ ይሰማሉ፡፡ ይህ በእንዲሁ እያለ እነሆ አሁን ደግሞ የፕሮቴስታንቶችን ቸርች ማሰርያ እየተባሉ በግዳጅ ኩፖን እንዲገዙ እየተደረጉ መሆኑን የ የተሰኘውና ሹፌሮች የሚደርስባቸዉን በደሎች የሚያጋልጠው ገጽ ከእነማስረጃው ለጥፎት እንዲህ ይነበባል!👇
_____________
"ትናንት ከሰበታ እና ቱሉቦሎ መሀል ያለወ ወረዳ ላይ ማለትም ኢሉ ወረዳ ወይንም ተጂ ከተማ ላይ የጴ'''''ንጤ ቸርች ማሰሪያ እያሉ ትራፊኮችና መንገድ ትራንስፖርቶች የ500 ብር ኩፖን ካልገዛቹ ብለው እያስቆሙ የግድ እየተቀበሉን ነው የሚል መልዕክት ደርሶናል ብለን ስላጋራን ብዙዎች ጉዳዩ መፈፀሙ ሳታውቁ ስትዘልፉን ነበር። ለማንኛውም ኩፖኑ ይሄው ያኔ ያላጋራነው ጉዳዩን አይተው እንዲታረሙ ነበር ለማንኛውም ማንም በግዳጅ የሚያደርገውን ነገር የማውገዝ የማሳወቅ የማሳየት ግዴታ ስላለብን እንዲህ ያለውንም አናልፍም። ማውገዝ ካለባችሁ እኛን ችግሩን ያሳየነውን ሳይሆን ችግሩን የፈጠረውን አካል ነው። በግዴታ መሆኑን ነው ልክ አይደለም ያልን መዋጮውን አይደለም። እንመዝን"

☪️☪️☪️
13/12/2025

☪️☪️☪️

አሜሪካዊው ቄስ ከእስልምና በፊት እና ከእስልምና በኋላ
11/12/2025

አሜሪካዊው ቄስ ከእስልምና በፊት እና ከእስልምና በኋላ

እስልምና ውበት ነው!❤Islaamummaan bareedina!❤
05/12/2025

እስልምና ውበት ነው!❤
Islaamummaan bareedina!❤

''ትምህርት የሞተው ብረሃኑ ነጋ ሲሾም ነው'' ዶ.ር ዳኛቸው አሰፋኤርትራ በረሃ ላይ ብረት ይዞ ኮማንደር ነኝ እያለ ሲያዋጋን የነበረ ሰው አምጥተህ ትምህርት ሚንስትር ስታደርገው ነው ትምህር...
20/11/2025

''ትምህርት የሞተው ብረሃኑ ነጋ ሲሾም ነው'' ዶ.ር ዳኛቸው አሰፋ

ኤርትራ በረሃ ላይ ብረት ይዞ ኮማንደር ነኝ እያለ ሲያዋጋን የነበረ ሰው አምጥተህ ትምህርት ሚንስትር ስታደርገው ነው ትምህርት እንደወደቀ እኔ አውቄለሁ እናንተ እንደፈለጋችሁ።

የሽምቅ ውጊያ ሳዋጋ ከረምኩ የሚል ሰው የትምህት ሚንስትር የምናደርግ ሰዎች ነን ያሳዝናል። እስኪ ወደ ሗላ መለስ ብለን በአፄ ሀይለስላሴ ጊዜ የትምህት ሚንስትር እነማን ነበሩ፣ መጀመሪያ አፄ ሀይለስላሴ ለሁሉም ስልጣን ሲሰጡ የትምህት ሚንስተርነቱን ለ20 አመታት ለማንም አልሰጡም።

እውነት እላችሗለሁ የሚገርም ነገርኮ ነው፣ እኔ በግል ወቀሳ ማንም ላይ ላደርግ አልመጣሁም ሲሉ ተደምጠዋል ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ

19/11/2025
"በትምህርት ሚኒስቴር  በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ የማራቅ ዘመቻ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል"📎 የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋየኢትዮጵያ እ...
18/11/2025

"በትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው ሙስሊሙን ከትምህርት ገበታ የማራቅ ዘመቻ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል"

📎 የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትምህርት ሚኒስትር በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው ሙስሊም ተማሪዎች ከትምህርት የማራቅ ዘመቻ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቋል፡፡

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ እንዳሉት ሙስሊም ተማሪዎች በአለባበሳቸው ምክንያት በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ያለው በደል የሀገራችንን ተከባብሮ የመኖር እሴት የመናድ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

አክለውም ሂጃብም ሆነ ኒቃብ የሙስሊም ሴቶች መግለጫ መሆኑን በማንሳት አንዱን ፈቅዶ አንዱን መከልከል እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡

ሀገር ወዳድ የሆነው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በትምህርት ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ጊዜ እየተፈፀመ ያለውን በደል በትግስት ማሳለፉን አንስተው የሚመለከተው የመንግስት አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

17 አባላት ያሉት ኮሚቴ የሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን በደል እንዲያጠራ መቋቋሙንም ገልፀዋል፡፡

ቻይና የኢትዮጵያ ዕዳ መክፈያ ጊዜ የሚያራዝም አወቃቀር ለመደገፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ****የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ዕዳ መክፈል አቅቶት ከአበዳሪ ተቋማትና ሀገራት ...
16/10/2025

ቻይና የኢትዮጵያ ዕዳ መክፈያ ጊዜ የሚያራዝም አወቃቀር ለመደገፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
****
የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ዕዳ መክፈል አቅቶት ከአበዳሪ ተቋማትና ሀገራት ጋር ያልተሳካ ድርድር እያደረገ ባለበት ጊዜ ከቻይና መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ አግኝቷል።

የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያ እዳ ክፍያ ጫና ያቃልላል የተባለ አዲስ የክፍያ አወቃቀር መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች አበዳሪዎች ጋር ያላት ግንኙነት የበለጠ ውጤታማ እንድትሆን የሚያስችል ትልቅ እድገት ነው ብሎታል ኤምባሲው።

የመግባቢያ ሰነዱ የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም አዳዲስ የትብብር እና የጋራ ዕድገት ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።

©️ማለዳ ሚዲያ

በቄሶች ቡራኬ የሚላከው ፋኖ «የአሁኑ ጭፍ*ጨፋ አላረካንም፤ ተጨማሪ መስጂዶችን መድ'ፈር፤ ተጨማሪ ኢማሞችን መግ*ደል፤ ተጨማሪ የመጅሊስ አመራሮችን መረ'ሸን፤ ወሎን መውረ'ር…» ይጠበቅብናል ...
06/10/2025

በቄሶች ቡራኬ የሚላከው ፋኖ «የአሁኑ ጭፍ*ጨፋ አላረካንም፤ ተጨማሪ መስጂዶችን መድ'ፈር፤ ተጨማሪ ኢማሞችን መግ*ደል፤ ተጨማሪ የመጅሊስ አመራሮችን መረ'ሸን፤ ወሎን መውረ'ር…» ይጠበቅብናል እያለ ነው።

(ዘ-ሐበሻ) ምሽቱ የመካነ ሰላም ከተማን ጸጥታ አልብሷት ነበር። በታላቁ የኑር መስጂድ ውስጥ፣ ምዕመናን የቀኑን የመጨረሻ ጸሎት (የኢሻ ሰላት) አድርሰው ወደ ፈጣሪያቸው ሰላምን፣ ጤና፣ ፍቅር...
06/10/2025

(ዘ-ሐበሻ) ምሽቱ የመካነ ሰላም ከተማን ጸጥታ አልብሷት ነበር። በታላቁ የኑር መስጂድ ውስጥ፣ ምዕመናን የቀኑን የመጨረሻ ጸሎት (የኢሻ ሰላት) አድርሰው ወደ ፈጣሪያቸው ሰላምን፣ ጤና፣ ፍቅርን፣ ወዘተ.. እየለመኑ ነበር። ይህች የተቀደሰች ስፍራ፣ የሰላምና የእምነት ማዕከል፣ በቅጽበት ወደ ሰቆቃና የሽብር አውድማነት እንደምትቀየር በወቅቱ ማንም አላሰበም ነበር።

ነገር ግን ይህ የሰዓታት ጸጥታ፣ በድንገተኛ የሽብር ጩኸትና በተተኮሱ ጥይቶች ተሰበረ። ታጣቂዎች መስጂዱን ከበው፣ በእጃቸው በያዙት የስም ዝርዝር መሰረት፣ የማህበረሰቡ መሪዎችና አባቶች ናቸው ያሉዋቸውን አምስት ንጹሃን አማኞችን ለይተው በግፍ ገደሏቸው። በጸሎት ላይ የነበሩ እጆች፣ ሳይጨርሱ ተቆረጡ፤ ወደ ፈጣሪ ያነሱ አይኖች፣ ሳይመለሱ ጨፈኑ።

በድር የተሰኘው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ድርጅት ባወገዘበትና ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው፣ ጥቃቱ ድንገተኛ ሳይሆን በቂ ዝግጅት ተደርጎበትና ታቅዶበት የተፈጸመ ዘግናኝ ወንጀል ነው ይላል። ድርጅቱ እንደሚለው፣ ከጥቃቱ ቀናት በፊት በማህበራዊ ሚዲያ "በኑር መስጂድ የመከላከያ ሰራዊትና ባለስልጣናት መሽገዋል" የሚል የሀሰት ውንጀላ ሲሰራጭ ነበር። ይህ፣ ንጹሃኑን ለጥቃት ለማመቻቸት የተነዛ የጥላቻ ዘመቻ እንደነበር ድርጅቱ ያምናል።

ይህ የመካነ ሰላም ጥቃት፣ በክልሉ ለዓመታት ሲፈጸሙ የነበሩና ፍትህ ያላገኙ የጥቃት ሰንሰለቶች የመጨረሻው አሳዛኝ ምዕራፍ ነው። ከዚህ ቀደም በሞጣ፣ በጎንደር፣ በቆቦና በሌሎች አካባቢዎች ሙስሊሞች ላይ የተፈጸሙት ግድያዎችና የንብረት ውድመቶች ተጠያቂነት ባለማግኘታቸው፣ ነብሰ ገዳዮች ዛሬም በድፍረት ወንጀላቸውን እንዲቀጥሉ እንዳደረጋቸው ድርጅቱ በምሬት ይገልጻል። የእነዚያ ንጹሃን ደም "ፍትህ" እያለ ሲጮህ፣ መልስ ባለማግኘቱ ሌላ ደም ፈሰሰ።

ከትላንት ወዲያ ምሽት የተገደሉት የአምስቱ አባቶች የቀብር ስነስርዓት ትናንት ተፈጽሟል። ቤተሰቦቻቸው ልብ በሚሰብር ሀዘን ውስጥ ሆነው፣ የሀገሪቱ የሰላም ችግር ወደ ሃይማኖት ግጭት እንዳያመራ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

በድር በመግለጫው ማጠቃለያ ላይ ይህ ጥቃት በሀገሪቱ ላይ የከፋ የሃይማኖት ግጭት ለመጫር የታለመ እኩይ ተግባር መሆኑን በመግለጽ፣ መንግስት ወንጀለኞቹን በአስቸኳይ ለህግ እንዲያቀርብና በክልሉ የሚገኙ ሙስሊሞች ራሳቸውን የሚከላከሉበት ሁኔታ እንዲመቻች አጥብቆ ጠይቋል። የሟቾቹ ቤተሰቦች ፍትህን፣ የማህበረሰቡ አባላት ደግሞ ለነገው ህይወታቸው ዋስትናን ይሻሉ። የኑር መስጂድ ጸጥታ ግን ዛሬ ላይ የሀዘንና የስጋት ጸጥታ ሆኗል።

☪️የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በመካነሰላሙ ጭፍጨፋ ዙሪያ መግለጫ አወጣ  !!
06/10/2025

☪️የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት በመካነሰላሙ ጭፍጨፋ ዙሪያ መግለጫ አወጣ

!!

 ደቡብ ወሎዎችም ግዕዝ እንዲጫንብን አንፈቅድም ብለዋል!
12/09/2025



ደቡብ ወሎዎችም ግዕዝ እንዲጫንብን አንፈቅድም ብለዋል!

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Berekah Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Berekah Tube:

Share