Hanos Media and Promotion

Hanos Media  and Promotion we are informing and entertaining you

follow us. https://web.facebook.com/story.php?story_fbid=122112153387175713&id=61585271393204&rdid=Bd4GScnkCFlVB54m #
30/01/2026

follow us. https://web.facebook.com/story.php?story_fbid=122112153387175713&id=61585271393204&rdid=Bd4GScnkCFlVB54m #

የሕወሓት ጦር አሰላለፍ እና አመራር መረጃ ተገኘ.

ወያኔ መገንጠልን ግቡ ላደረገ ጦርነት በአራት አቅጣጫ ጦሩን እያንቀሳቀሰ ነው።

ከጥር 18 ቀን ጀምሮ አፍላ ውጊያ ከተነሳባቸው የምስራቅና ምዕራብ ጠለምት አካባቢዎች በተጨማሪ በሌሎች ወሳኝ ግንባሮች full-scale war ለመክፈት የሰው ኃይል፣ ሎጀስቲክና የመረጃ ቅንጅቶችን እያደረገ ነው።

በጠለምት ቀጠናዎች እስካሁን በታወቀ መረጃ 3 "አርሚ" አስገብቷል። (አርሚ 11፣ 13፣ 35) ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ ይችላል። ከዋልድባ መድሐኒዓለም ታችኛውን ገፅ፣ የወልቃይት አናት እና የጠገዴ መሻገሪያ የአርማ ደጋ ወሳኝ በር ትላንት ይዘዋል።

ይህኛው ኃይል ወደወልቃይት እና ወደ ጠገዴ ወሳኝ ክፍሎች ሰብሮ ለመግባት የተዘጋጀ ነው።

በሽራሮ በኩል ተከዜን ተሻግሮ ወደቃፍታ ሁመራ፣ በደደቢት ወደ ቆራሪት አቅጣጫ በ human wave attack ለመግባት አስቧል።

ከሽሬ ሲንቀሳቀስ ያደረው የሰው ኃይል ለዚህ አብነት ነው።

በሱዳን ያለው ታጣቂ ኃይል ከመቼውም ጊዜ በላይ የትጥቅ አቅም ፈጥሯል። "አርሚ 70" በ3 ኮሮችና አንድ ኮማንዶ ክፍለጦር ከመዋቀሩ ባሻገር ለዚሁ ዘመቻ ሌሎች ስልጠናዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። ይህን የወልቃይት አስተዳደር ጠንቅቆ ያውቃል!

- ድንበር አካባቢ ሸረሪና ላይ ያለው ኮር 701 አዛዡም ኮ/ል ፀጋይ ኃይል እንዲጨመረው ተደርጓል።

- መሃል ሱዳንና ዋድ መደኒ ላይ ሆነው የአልቡርሃንን ጦር ደግፈው ሲዋጉ የቆዩት በዮሐንስ እና በመብራህቶም የሚመሩት ኮር 702 እና ኮር 703 ተንቀሳቅሰዋል።

- ወዲ ነጮ ተብሎ የሚጠራው 1 ክፍለጦር ኮማንዶም በተመሳሳይ ከ ዋድ መደኒ ወደ ጠረፍ ኃይል እንዲያንቀሳቅስ ተደርጓል።

- የአርሚ 70 ከፍተኛ አመራሮች

1. ጄኔራል ሙዘይ መኮንን አዛዥ
2. ግደይ ሃይሉ (ወዲ ፊውዳል) ምክትል
3. ምሩፅ - መረጃ
4. ተወልደ - ሎጀስቲክስ

ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚወስዱት በነ ፍስሐ ማንጁስ ከሚመራው አዲሱ ኮማንድ ነው።

የህወሓት ቡድን ለታጣቂ ኃይሉ ለዚሁ ዘመቻ ዝግጅት ያደረገው የአመራር ምደባ ፦

የሕወሓት ታጣቂ ዋና አዛዥ ብርጋዴየር ጀኔራል ኃይለ ሥላሴ ግርማይ (ወዲ እምበይተይ)፣

የዘመቻ መምፈሪያ ኃላፊው ደግሞ ሜጀር ጀኔራል ዩሓንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ)፣

የስልጠና ኃላፊ ብርጋዴየር ጀኔራል ምገበይ ኃይሌ ሲሆኑ፤

የሕወሓት ወታደራዊ መረጃ ኃላፊ በመሆን የተመደቡት ደግሞ ሜጀር ጀኔራል ማሾ በየነ ናቸው፡፡

ሌተናል ጀኔራል ፍስሃ ኪዳኑ (ፍስሐ ማንጁስ) የጊዜዊ አስተዳደሩን ሀብት፣ የውጭ ክፍልና የውጭ ግንኙነት በሀብት፣ በመረጃና በግንኙነት የመምራት ኃላፊነት ይዟል።

እነዚህ ለአብነት የተጠቀሱ ወታደራዊ አመራሮች የውጊያ ዝግጁነትን ከማረጋገጥ ባለፈ የውጊያ ጭንቅላት ሆነው እንደሚያገለግሉ በፖለቲካ አመራሩ ዘንድ ታምኖባቸዋል፡፡

በእስካሁኑ አሰራር የታጣቂ ቡድኑ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ታደሰ ወረደ እንደሆነ ቢታወቅም፣ ይህ አዲሱ ኮማንድ ታደሰን ያንሳፈፈ ሆኗል፡፡ በኮሚቴ ይወሰኑ ከነበሩ አሰራሮች ሰውየውን ማሸሽ ከጀመሩ ሰነባብቷል።

በሌላ በኩል የጦርነቱ ቅድመ ዝግጅት ቁልፍ ጉዳይ የሆነው፣ የሕወሓት ጀኔራሎች የጦርነት ወታደራዊ ኮማንድ ማዕከል ሆና የተመረጠችው ቦታ አዲ ፀፀር (ሽራሮ አካባቢ) ነች።

በተጨማሪም፣ ከባባድ መሳሪያዎቻቸውንም ከቦታ ወደ ቦታ እያንቀሳቀሷቸው እንደሆነ ተጠቁሟል። ቡድኑ ቀላል ሮኬቶችን ጨምሮ መድፎችንና ታንኮችን አንቀሳቅሷል።

ወደ አዲ ፀፀር እና የጭላ ወስዶ ያከማቻቸው ከባድ መሳሪያዎችም አሉ።

የጦርነቱ ዋና ዓላማ መገንጠልን ግቡ ያደረገ እንደሆነ ይህም የአማራ ታሪካዊ ርስቶች በመውረር ለማሳካት እንደታሰበ ከዝግጅታቸው መረዳት ይቻላል፡፡

በሱዳን ባለው የሰው ኃይል ስምሪት ገብረሂወት ( ወዲ ዝራብእ ) ፣ ሃጎስ እና አረጋዊ የሚባሉት ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሳ የተዋረድ አመራሮች ናቸው።

አርሚ 70 ሱዳን ውስጥ በሶስቱም ማሰልጠኛዎቹ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ታጣቂዎችን ዝግጁ አድርጓል። ወያኔ በሱዳን በኩል ውጊያ ለመክፈት የሚጠብቀው አገዛዙ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን መግለጫና ይዘት ነው። ቀጣናዊ ሁኔታዎችንና ተለዋጭ ክስተቶችን አጢኖ ከዛ በፊትም ሊጀምረው ይችላል።

❔ የምትደግፉት ክለብ ስንተኛ ደረጃ ነዉ ❔Hanos Media  and Promotion Ethiopian Music Black is Stronge ፈጣን ስፖርት
25/01/2026

❔ የምትደግፉት ክለብ ስንተኛ ደረጃ ነዉ ❔
Hanos Media and Promotion
Ethiopian Music
Black is Stronge
ፈጣን ስፖርት

ዜና ችሎት :- የሞት ፍርድ ተፈረደባት::በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳሽ የነበረችው ሰንበቴ ታደሰ ጥፋተኛነቷ በፍርድ ቤት ተረጋግጦ በሞት እንድትቀጣ ተወሰነባት።ውሳኔው የተሰጠው በትናንት...
24/01/2026

ዜና ችሎት :- የሞት ፍርድ ተፈረደባት::

በከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ተከሳሽ የነበረችው ሰንበቴ ታደሰ ጥፋተኛነቷ በፍርድ ቤት ተረጋግጦ በሞት እንድትቀጣ ተወሰነባት።

ውሳኔው የተሰጠው በትናንትናው ዕለተ አርብ ጥር 15/2018 ዓ.ም በጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መሆኑ ተገልጿል።

እንደ ፍርድ ቤቱ መግለጫ፣ ተከሳሿ በ2017 ዓ.ም በኮቸሬ ወረዳ ውስጥ በተፈፀመ ከባድ የወንጀል ድርጊት ተከሳሽ ሆና ቀርባ ነበር። ክሱ በ1997 ዓ.ም የወጣው የወንጀል ህግ አንቀጽ 539/1(ሀ) መሠረት ቀርቦ ተመርመሯል።

ተከሳሿ በችሎቱ ፊት ወንጀሉን እንዳልፈፀመች በመከራከር ቆይታ አድርጋ ቢሆንም፣ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች የቀረቡ ማስረጃዎች በፍርድ ቤቱ በቂ መሆናቸው ተገምግሟል። ተከሳሿም ተጨማሪ መከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንዳልቻለች በፅሁፍ አሳውቃለች።

በዚህ መሠረት፣ ፍርድ ቤቱ ድርጊቱ ከፍተኛ ክብደት ያለው እና ሕጉን በግልፅ የሚጥስ መሆኑን በመግለጽ፣ ተከሳሿ በሞት እንድትቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።

ከችሎቱ ታዳሚዎች መካከል አንዳንዶቹ፣ ውሳኔው ሕግን ለማስከበር እና ለማስጠንቀቅ አስፈላጊ መልዕክት አለው ሲሉ አስተያየታቸውን ገልጸዋል።

Via የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት – ህዝብ ግንኙነት

"ከአርሰናል ጋር ያለን ጨዋታ በእርግጠኝነት ከባድ እንደሚሆን ይታወቃል፤ ሆኖም እኛ በጥሩ ብቃት ላይ እንገኛለን። ወደ ኤምሬትስ የምናመራው ሶስቱንም ነጥቦች ይዘን ለመውጣት ነው። በመልሶ ማጥ...
24/01/2026

"ከአርሰናል ጋር ያለን ጨዋታ በእርግጠኝነት ከባድ እንደሚሆን ይታወቃል፤ ሆኖም እኛ በጥሩ ብቃት ላይ እንገኛለን።

ወደ ኤምሬትስ የምናመራው ሶስቱንም ነጥቦች ይዘን ለመውጣት ነው። በመልሶ ማጥቃት ስራቸውን በአግባቡ የሚወጡ ፈጣን የክንፍ ተጫዋቾች ስላሉን፣ የእነሱን ተከላካይ ክፍል ሰብሮ መግባት ለእኛ ፈተና አይሆንም።" ፓትሪክ ዶርጉ

ደርብ  ዘነበ++++++++++++++++++ደርብ ዘነበ በጎንደር የተወለደ ከሙዚቀኛ  ቤተሰብ የተገኘ ድንቅ ችሎታ ያደለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው፡፡ደርብ አባቱ አኮርዲዎን ተጫዋች አጎቶቹም ሙዚቀ...
24/01/2026

ደርብ ዘነበ
++++++++++++++++++
ደርብ ዘነበ በጎንደር የተወለደ ከሙዚቀኛ ቤተሰብ የተገኘ ድንቅ ችሎታ ያደለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው፡፡ደርብ አባቱ አኮርዲዎን ተጫዋች አጎቶቹም ሙዚቀኞች ናቸው። በልጅነቱ "ያዳመጠውን ሁሉ ከልብ ያስፈነደቀ፤ በመሰንቆ አገራረፉ ማንንም ያስደነቀ ፤ በግጥም አጣጣሉ ሴት ወንዱን ያሳቀ"ተብሎ ስለተሞገሰው አሰፋ አባተ ብዙ ሰምቷል። ሰምቶም ወዶታል፤ አድንቆታል። "በልጅነቴ ጀምሮ ስለአሰፋ አባተ ሰዎች ይነግሩኝ ነበር። ከሙዚቃውም ከሰውዬውም ፍቅር ነበረኝ" የሚለው ደርብ "አሰፋ አባተን እንዴት አድርጌ በሙዚቃ ላምጣው?" የሚል ሐሳብ እንደነበረው ይናገራል። ደርብ እንዳደነቀው አሰፋ አባተ ሁሉ መሰንቆ ይጫወታል። የወደደውን የማትበላ ወፍ የተሰኘ ሙዚቃ መልሶ ሲዘፍን ግን አላማው መዝፈን ብቻ አልነበረም። "ማሲንቆ በእኔ ትውልድ እንዲመለስ ፈልጌ ነበር። ማሲንቆን ማስተዋወቅ እፈልግ ነበር" ይላል ደርብ ለዲ ደቭሊው በአንድ ወቅት በሰጠው ቃለ ምልልስ፡፡
"ባንቺው መጀን" በተባለው የወሎ ሙዚቃ ወሎን ከታች ከበረሃው እስከ ጦሳ ተራራና አምባሰል ተራራዎች ድረስ አስቃኝቶን በአንቺው መጀን እንል ዘንድ በሀሳብ ወሎ ወስዶ ያደርሰናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ በተጫወተው የአሰፋ አባተ "የማትበላ ወፍ" ተለይቶ የሚታወቀው ደርብ ዘነበ ከእነዚህ ስራዎች በኋላ ጠፍቶ ሰነባብቶ እንደገና በመመለስ
በሚኖርበት አውስትራሊያ Drums and Lions እና Dereb The Ambassador የተሰኙ ሁለት አልበሞች ሠርቷል።
በአልበሙ የተካተቱት "የኢትዮጵያ ሙዚቃ ወርቃማ ዘመናት" ተብለው በሚቆጠሩት 1960ዎቹ እና 70ዎቹ የተሠሩ ናቸው። አልበሙ ግን በኢትዮጵያ ገበያ አልተሸጠም። የጥላሁን ገሠሠ፣ ማሕሙድ አሕመድ፣ አለማየሁ እሸቴ እና ሙላቱ አስታጥቄ እና የደርብ የራሱ ባሕላዊ ሥራዎች ተካተውበታል። ደርብ ዘነበ እንደገና የሠራው የአሰፋ አባተ "የማትበላ ወፍ" የተባለ ሙዚቃ Drums And Lions በተሰኘ አልበሙ ውስጥ የተካተተ ነው።

ድሉ የአርሰናል ነው🙄Arsenal 4  United 2  ይጠናቀቃል። አቶ ፔፕ ጋርዲዮላም ቀበሮ የበሬ እንትን ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደዋለችው ይሆናል💪
24/01/2026

ድሉ የአርሰናል ነው🙄
Arsenal 4 United 2 ይጠናቀቃል። አቶ ፔፕ ጋርዲዮላም ቀበሮ የበሬ እንትን ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል እንደዋለችው ይሆናል💪

እስቲ ማን ሂሳብ ላይ ጎበዝ እንደሆነ ደግሞ እንይ 🙄𝟵𝟵.𝟵% ሰዎች በፍጹም መልሱን አልመለሱትም ⛔⛔⛔
24/01/2026

እስቲ ማን ሂሳብ ላይ ጎበዝ እንደሆነ ደግሞ እንይ 🙄

𝟵𝟵.𝟵% ሰዎች በፍጹም መልሱን አልመለሱትም ⛔⛔⛔

🎙 “ አርሰናልን ለመግጠም ጓጉቻለሁ “ ማይክል ካሪክ ‎‎የማንችስተር ዩናይትዱ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ለአርሰናል ጨዋታ " በጣም ጓጉቻለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።‎‎“ አርሰናል ምርጥ ቡ...
23/01/2026

🎙 “ አርሰናልን ለመግጠም ጓጉቻለሁ “ ማይክል ካሪክ

‎የማንችስተር ዩናይትዱ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ለአርሰናል ጨዋታ " በጣም ጓጉቻለሁ “ ሲሉ ተናግረዋል።

‎“ አርሰናል ምርጥ ቡድን ነው “ ያሉት ማይክል ካሪክ “ ብዙ ጥራት ያላቸው ተጨዋቾች አሏቸው ትልቅ ፈተና ነው “ ብለዋል።

‎ጨዋታውን በቀላሉ እንደማይመለከቱ የገለፁት አሰልጣኙ “ ነገርግን በጥሩ መልኩ መመልከት አለብን " ሲሉ ገልጸዋል።

‎ስለ ቡድናቸው ያነሱት ካሪክ “ አንድ ጨዋታ ብቻ ምርጥ ቡድን አያደርግም ነገርግን ጥሩ መሰረት ይሆነናል “ ሲሉ ስለ ደርቢው ድል ተናግረዋል።

‎“ በቡድኑ ውስጥ ጥሩ ድባብ አለ ነገርግን ከፊታችን ምን እንዳለ እናውቃለን በራስ መተማመን እና በትኩረት መካከል ሚዛን ማግኘት አለብን " ሲሉ ጨምረው ተናግረዋል።

‎" የትኛውም ውሳኔዬ የአጭር ጊዜ አይደለም ፤ ክለቡ በጥሩ ሁኔታ ላይ ሆኖ የማስረከብ ሀላፊነት አለብኝ። “ ማይክል ካሪክ

ባህር ዳር እና ሰባር ጊዮርጊስ በዓል.......ባህር ዳር በታላቁ የጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ከዓባይ ወንዝ መውጫ ላይ የተመሰረተች ሁሉም ሰው ለመኖር እና ለመጎብኘት በቀዳሚነት የሚመርጣትና የ...
23/01/2026

ባህር ዳር እና ሰባር ጊዮርጊስ በዓል.......
ባህር ዳር በታላቁ የጣና ሐይቅ ደቡባዊ ጫፍ ከዓባይ ወንዝ መውጫ ላይ የተመሰረተች ሁሉም ሰው ለመኖር እና ለመጎብኘት በቀዳሚነት የሚመርጣትና የሚመኛት ውብ ከተማ ናት፡፡
የባህር ዳር ስያሜ እና አመሰራረት ከጣና ሐይቅ እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ በአፈ ታሪክ በጣና ደሴቶች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ተሰርተው ሲጠናቀቁ የኪዳነ ምህረት ጽላት ይቀራል፡፡ የሀይማኖት አባቶችም የቀረውን ጽላት የት መትከል እንዳለባቸው በወቅቱ የነበረውን ንጉሥ ያማክራሉ፡፡
ንጉሡም ቀሪው ጽላት ከባሕሩ ዳር ወይም ከሐይቁ ዳር እንዲተክሉ በማዘዛቸው የኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አሁን የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል በሚገኝበት ቦታ ተተከለች፡፡ ቤተ ክርስቲያኗ ከባሕሩ ወይም ሐይቁ ዳር መተከሏን ተከትሎም አካባቢው ባሕር ዳር ተብሎ መጠራት እና በከተማነት መልማት ጀመረ፡፡
ለባህር ዳር ከተማ ስያሜ እና ምልክት በሆነው የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ከሁለት ቀናት በኋላ ዝርወተ አጽሙ ሰባር ጊዮርጊስ ክብረ በዓል በድምቀት ይከበራል፡፡ የጥርን በባህር ዳር ዋና ድምቀት በሆነው በዚህ ክብረ በዓል ታቦተ ሕጉ ከመንበሩ በመውጣት በጣና ሐይቅ ላይ በጀልባ እና በታንኳ ታጅቦ አካባቢውን ይባርካል፡፡
ሁላችሁም በዚህ ድንቅ ክብረ በዓል ትታደሙ ዘንድ ተጋብዛችኋል፡፡
Visit Amhara

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hanos Media and Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share