2005 ኮንዶምኒየም ተመዝጋቢዎች ድምፅ

2005  ኮንዶምኒየም ተመዝጋቢዎች ድምፅ Ethiopia’s condominium housing program watchers

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ አቤቱታና ጥሪ!የኮየ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች መከራ እስከመቼ?በኮየ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ከ60 ሺህ በላይ ነዋሪ ባለበት ሰፊ መንደር) ያለው አንድ ብቸ...
14/02/2026

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ አቤቱታና ጥሪ!
የኮየ ፈጬ ኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች መከራ እስከመቼ?

በኮየ ፈጬ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ከ60 ሺህ በላይ ነዋሪ ባለበት ሰፊ መንደር) ያለው አንድ ብቸኛ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አገልግሎት አሰጣጥ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ዛሬም እንደ ትላንቱ ደንበኞች ለሰዓታት በሰለቸ ሰልፍ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።

1. ከአስር በላይ መስኮቶች ቢኖሩም፣ አገልግሎት የሚሰጡት ግን አንድ ወይም ሁለት መስኮቶች ብቻ ናቸው።

2. አንድ ደንበኛ ተራውን ለማግኘት ጉርሻ pageከ3 እስከ 4 ሰዓታት እንዲጠብቅ ይገደዳል።

3. በተለይ ልዩ እንክብካቤ የሚሹ እርጉዝ እናቶች እና አዛውንቶች ለረጅም ሰዓት በሰልፍ እንዲቆሙ መደረጉ የባንኩን የስነ-ምግባር መመሪያ የማይመጥን ነው።

4. ለዚህ ሁሉ ህዝብ አንድ ቅርንጫፍ ብቻ መኖሩ ጫናውን መቋቋም የማይችል አድርጎታል።

ባንኩ "የሁልጊዜም ታማኝ ረዳት" ነኝ እንደሚለው ከሆነ፣ ይህንን የአገልግሎት ዝግመትና የሰራተኞችን መዘናጋት በአስቸኳይ ሊፈትሽ ይገባል።

13/02/2026

የ2005 እና 1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች

#ኮንዶሚኒየም # ተመዝጋቢዎች #የነዋሪዎችድምጽ #ኮንዶሚኒየም #ቤት

13/02/2026

የ2005 እና 1997 ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች

#ኮንዶሚኒየም # ተመዝጋቢዎች #የነዋሪዎችድምጽ #ኮንዶሚኒየም #ቤት #2005 #1997

13/02/2026

ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ብሶት
#የነዋሪዎችድምጽ #ኮንዶሚኒየም #ቤት

13/02/2026

ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ብሶት
#የነዋሪዎችድምጽ #ኮንዶሚኒየም #ቤት

13/02/2026
13/02/2026

ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ብሶት
#የነዋሪዎችድምጽ #ኮንዶሚኒየም #ቤት

11/02/2026
በውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ተደረገ‼️የተሰጠው መግለጫ ከስር ቀርቧል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርም መደረግ ከጀመረበት ሀምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ፤ የውጭ ም...
11/02/2026

በውጭ ምንዛሪ መመሪያዎች ላይ ማሻሻያ ተደረገ‼️

የተሰጠው መግለጫ ከስር ቀርቧል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሟላ የማክሮኢኮኖሚ ሪፎርም መደረግ ከጀመረበት ሀምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ፤ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማጎልበት የሚያስችሉ የተለያዩ የውጭ ምንዛሪ ማሻሻያዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የውጭ ምንዛሪ ገበያን የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ በውጭ ምንዛሪ መመሪያ ላይ የሚከተሉትን ማሻሻያዎች ማድረጉን ያሳውቃል፡፡

1. የአገልግሎት ላኪዎች ከወጪ ንግድ የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ሙሉ በሙሉ በሪቴንሽን ሂሳባቸው ያለ ምንም የጊዜ ገደብ እንዲይዙ ተፈቅዷል፡፡

2. ባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ላላቸው ደንበኞቻቸው ለውጭ ሀገር ክፍያ የኤሌክትሮኒክ ግብይትን ጨምሮ የሚያገለግል ዓለምአቀፍ ካርድ ማዘጋጀት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

3. ማንኛውም የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ ያለው የባንክ ደንበኛ ሕጋዊ ስነዱን ሂሳብ ለከፈተበት ባንክበማቅረብ፤ የውጭ ምንዛሪ ሂሳቡን በመጠቀም ለትዳር አጋሩና ለልጆቹ የትምህርት፤የህክምናና የጉዞ ወጪ ክፍያ ማድረግ ይችላል፡፡

4. ማንኛውም ለትርፍ የተቋቋመ ድርጅት የውጭ ምንዛሪ ምንጩ ከወጪ ንግድ የሚገኝን የውጭምንዛሪ ሳይጨምር በእርዳታ/ስጦታ አለያም ከሌላ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የተገኘ መሆኑ ከተረጋገጠ የተንቀሳቃሽ፣ የቁጠባና የጊዜ ገደብ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላል፡፡

5. ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የውጭ ምንዛሪ የቁጠባ ሂሳብ ለመክፈት ይጠየቁት የነበረው አነስተኛ 100 የአሜሪካ ዶላር እንዲቀር ተደርጓል፡፡

6. ድርጅቶች የመዋእለ ነዋያቸውን ሁኔታ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እያስመረመሩ ከሀገር ውጭበሌላ ሀገር መዋእለ ነዋያቸውን ፈሰስ ማድረግ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

7. ማንኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነዋሪ የሆነ ግለሰብ ወደ ሀገር ይዞት የተመለሰውን የትኛውንም ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ያለ ጉምሩክ ሰነድ በባንኮችና ሕጋዊ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በኩል ወደ ብር መመንዘር አለያም ወደ የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ በማስገባት ተቀማጭማድረግ ይችላል፡፡

8. ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ ሰነድ ለባኮች በማቅረብ መጠኑ ከ3,000 የአሜሪካ ዶላር ያልበለጠ የውጭምንዛሪ ከሀገር ውጭ ለሚኖሩ ዘመዶቻቸው እገዛ እንዲውል ከሀገር ወደ ውጭ ማስተላለፍ የሚችሉበት ሥርዓት ተፈቅዷል፡፡

9. ባንኮች የፎርዋርድ የውጭ ምንዛሪ ግብይት ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ ማካሄድ እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

10. የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተሮች፣ ኤምባሲዎችና በሀገር ውስጥ የሚሰሩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የተራድኦ ድርጅቶችን ጨምሮ ያለ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ በባንኮች የውጭ ምንዛሪ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡

11. ድርጅቶች ወደ ሀገር ውስጥ የሚያመጡት የውጭ ብድር (በገንዘብና በዓይነት) እና የስፕላዬርብድርን የማጽደቅ ሥራ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መስፈርቶችን በተከተለ መልኩ ሙሉ በሙሉ በባንኮች እንዲከናወን ተፈቅዷል፡፡

12. ማንኛውም በወጪ ንግድ ላይ የተሰማራ ላኪ ድርጅት ከማንኛውም የውጭ አካል የቅድመ ክፍያ ስምምነት ላይ በመድረስ እና በሁለቱ ወገኖች የተደረሰውን የስምምነት ሰነድ ለላኪው ድርጅት ደንበኛ ባንክ በማቅረብ የቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላል፡፡

13. በተጨማሪም የውጭ ምንዛሪ ገቢ ለወደፊት የወጪ ንግድ ክፍያ እንደ ቅድመ ክፍያ የሚቆጠረው (ሀ) ስምምነቱ ገዥውን ለማመላከት ታስቦ “ቅድመ ክፍያው ለወደፊት ወጪ ወይም ገቢ ንግድ የሚውል" ወይ (ለ) ወደፊት ወደ ውጭ የሚላኩ ሸቀጦችን ከዘረዘረ ወይም የደረሰኝ ቁጥሩ ከተጠቀሰ አለያም የግብይት የውል ስምምነት ሰነድ ቁጥር በሚላከው የውጭ ምንዛሪ ደረሰኝ ላይ ከተጠቀሰ ይሆናል፡፡

14. ባንኮች ከካፒታላቸው ከ10 በመቶ ያልበለጠ ለግሉ ዘርፍ የውጭ ሀገር ብድር ዋስትና መስጠት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

15. ባንኮች የውጭ ተቋም በሚሰጠው የማረጋገጫ ደብዳቤ እና ደንበኛው በሚያቀርበው ጥያቄ ላይበመመርኮዝ በአንድ ጉዳይ ከ20,000 የአሜሪካ ዶላር ወይም ከተመጣጣኝ የሌላ ሀገር ገንዘብ ያልበለጠ የውጭ ምንዛሪ ለህክምናና ለትምህርት ያለ ቪዛ እና የአውሮፕላን ትኬት ቅድመ ክፍያ ማከናወን ይችላሉ፡፡

16. ያለምንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማረጋገጫ የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ መመሪያ መሰረት አስፈላጊውን ሰነድ ለባንካቸው በማቅረብ እንዲሁም ባንኮች በመመሪያው መሰረት የቀረበው ሰነድ መሟላቱን በማረጋገጥ በትርፍ ክፍፍል መልክያገኙትን የውጭ ምንዛሪ ከሀገር ማስወጣት እንዲችሉ ተፈቅዷል፡፡

17. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎችን የገንዘብ ፍሰትና ካፒታል የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በፈቃድ አሰጣጥ ወቅት የሚይዘውን ተቀማጭ ገንዘብ፤ (አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ በሥራ ላይ ለሆኑ ቢሮዎች 30 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ቢያንስ ለስድስት ወራት በሥራ ላይ ላሉ ቢሮዎች 15 ሚሊዮን ብር) ተመላሽ ያደርጋል፡፡

18. የውጭ ምንዛሪ ግብይት ቢሮዎች በእጃቸው የሚይዙት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ቀደም ሲል ከነበረው የካፒታላቸው 10 በመቶ ወደ 25 በመቶ ተሻሽሏል፡፡ ከዚህ በላይ የሆነ ትርፍ የውጭምንዛሪ ገንዘብ ለባንኮች መሸጥ አለበት፡፡

19. ሁሉም የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች አስፈላጊውን ሰነድ በመጠየቅ ለቪዛ፣ ለጋስፖርትና ለፈቃድ እድሳት ጥሬ የውጭ ምንዛሪ ሽያጭ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል፡፡

Via National Bank of Ethiopia

ሁሌ ይመረቃል ለተመዝጋቢ ግን እይደርስም
09/02/2026

ሁሌ ይመረቃል ለተመዝጋቢ ግን እይደርስም

09/02/2026

ዋናው ጥያቄ አሁን ሚሰሩት ቤቶች በትክክል ለተመዝጋቢዎች ይተላለፋሉ ወይስ ??

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 2005 ኮንዶምኒየም ተመዝጋቢዎች ድምፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share