27/10/2024
የመከላከያ ሠራዊት መዝሙር
የኩሩ ሕዝቦች መኖሪያ የሕብረ ብሄር ቡቃያ
የሰላም ተምሳሌት ዓርማ የቀለሞች ሕብር ኢትዮጵያ
በደም አሻራሽ አትመው ሕዝቦች ለሰጡን አደራ
ለሕገ-መንግስታችን ክብር ታጥቀን ቆመናል በጋራ
የአበው የአርበኝነት ቅርስ የነፃነት ገድል ፋና
ወደ ትውልድ ተሻግሮ ወረሶት ፀንቷል እንደገና
ምድራዊ ፈተና በዝቶ ዙሪያው ቢነድ በጎመራ
ጥስ ነው እናልፈዋለን የማይሞት ታሪክ ልንሰራ
ሕዝብ ነው ኃያል ክንዳችን ሰላም ልማት ነው ቋንቋችን
የመፈቃቀድ አንድነት እኩልነት ነው ዜማችን
የማንጨበጥ ነበልባል እሳት ነን ለጠላታችን
ፍሙ ከርቀት ይፋጃል ብረት ያቀልጣል ክንዳችን
ኢትዮጵያ በእኛ ደም ደምቃ በአፅማችነሰ ፍላፅ ተማግራ
እንደታፈረች እንድትኖር ከዘመን ዘመን ተከብራ
ከመሞት በላይ እንሙት ደማችን ሺ ጊዜ ይፍሰስ
አየር አፈሯ ይባረክ ምን ጊዜም ስሟ ይታደስ።