Horizon Podcast

Horizon Podcast Reset�Restart�Refocus�Coming Soon�

MIDROC Investment Group ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሀገር ‎‎የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ መንበር ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ኢትዮጵያ ከአደጉት የዓለ...
17/09/2026

MIDROC Investment Group ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሀገር

‎የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀ መንበር ሼይኸ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ኢትዮጵያ ከአደጉት የዓለም ሀገራት ተርታ እንድትሰለፍ ሚድሮክ የበኩሉን አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛል አሉ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቤተሰብ ቀንን በዛሬው እለት ያከበረ ሲሆን ‎​መርሃግብሩ ላይ በዙም የቀጥታ የቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤትና ሊቀመንበር ሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ምኞቴ ኢትዮጵን ከአደጉ ሀገራት ተርታ ተሰልፋ ማየት ነው ብለዋል።

‎​ይህንን እውን ለማድረግ ሚድሮክ አሁን እየሰራቸው ካሉት የልማት ሥራዎች በተጨማሪ ባለ 10 ኮከብ ሆቴል በመገንባትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ሥራዎች በመሥራት ተቋሙ ለሀገር ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅዖ የበለጠ ለማጉላት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

‎​በኢትዮጵያ የግሉና የመንግሥት ዘርፍ ተናበው በመሥራት የዋጋ ንረትን መከላከል እንዳለባቸው የጠቆሙት ሼይኸ መሀመድ፤ ለሕዝቧ ምቹ የሆነች፣ ለጠላቶቿ የማትንበረከክና በአለት ላይ የጸናች ሀገር ለመገንባት በአንድነት መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

‎​ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለፉት ስድስት ዓመታት ያስመዘገበው ውጤት በጣም የሚያኮራ መሆኑን በመግለጽ ለተቋሙ ሠራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

‎​በተለይም ሚድሮክ አሁን ላይ ከ80 ሺህ በላይ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ጠቁመው፣ ይህንን ቁጥር በእጥፍ ለማሳደግ መሥራት እንዳለበት አሳስበዋል።

‎​በተጨማሪም ሁሉም የሚድሮክ አመራርና ሠራተኛ የልማት ሠራዊት በመሆን ተቋሙ ቀጣይነት ያለው ዕድገት እንዲያስመዘግብ በባለቤትነት ስሜት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ- የሀገር ሀብት

  Abiy Ahmed Ali ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይ...
12/09/2026

Abiy Ahmed Ali

ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል።

‎በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ ናት።

‎በተጨማሪም በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ይኖርብናል።

‎የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው።

Office of the Prime Minister-Ethiopia

#ኢትዮጵያ

የፅናት ተምሳሌት – FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
08/09/2026

የፅናት ተምሳሌት – FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

  ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️ "ወደ መሠረት መመለስ‼️" እና "ብርሃን እየቀበሩ በጨለማ መኖር‼️" በሚሉ መሪ ቃሎች  በዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ አዳራሽ ያሰናዳነው  ልዩ የመድረክ ዝግ...
31/08/2026



ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️ "ወደ መሠረት መመለስ‼️" እና "ብርሃን እየቀበሩ በጨለማ መኖር‼️" በሚሉ መሪ ቃሎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ፓን አፍሪካ አዳራሽ ያሰናዳነው ልዩ የመድረክ ዝግጅት በዚህ መልኩ ተጠናቋል::

በመጀመሪያ ከዓመታት ጥበቃ በኋላ ይህ እንዲሆን ለፈቀደው አላህ (ሱወ) ክብር እና ምስጋና በሚገባው ልክ ይድረሰው 🙏🙏🙏

በመቀጠል ውድ ግዝያችሁን ሰውታችሁ ከጎኔ ለቆማችሁ ሁሉ አላህ በጉዳያችሁ ሁሉ ይቁምላችሁ 🙏🙏
በተለያዩ ጉዳዮች በአካል ያልተገኛችሁም በእናንተ ዱዓ ነውና የተሳካው እናተንም አላህ ያክብርልኝ:

በአላህ ፍቃድ ቀጣይ ፕሮጀክቴን ይፋ አድርጋለሁ አብረንም እናሳካዋለን‼️‼️

ነሐሴ 24 2018

"የሀገራችን ዓሊሞች አስተምሮ፣ ተጋድሎ እና እስላማዊ ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫዎቻችን ናቸው‼️
ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️

አክባሪያችሁ ዑስማን መሐመድ ሐምዛ ፕሮዱዩሰር እና ዳይሬክተር

#ክብርለሀገሬዓሊሞች

#ብርሃንእየቀበሩበጨለማመኖር

#ዓድዋ #ኢትዮጵያ
#ዓድዋበልኩሲተረክ

Horizon Podcast Osman Hamza
Osman Hamza Addis Mieraf Forum - አዲስ ምዕራፍ ፎረም
First hijrah foundation

30/08/2026

ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂኡን😭😭😭

ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ አላህ ቀብርህን ኑር ያድርግልህ🙏🙏 አላህ ጀነተል ፊርዶውስን ይወፍቅህ🙏🙏

First hijrah foundation Osman Hamza Addis Mieraf Forum - አዲስ ምዕራፍ ፎረም

30/08/2026

ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️ በዓድዋ ድል ሙዚየም

የፈርስት ሂጅራ መሥራችና በመሪነት ያገለገሉት ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ወደ አኺራ ተሻገሩ😭በአሜሪካን ሀገር ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ያሰባሰበው የ First hijrah foundation  የኢትዮጵያው...
30/08/2026

የፈርስት ሂጅራ መሥራችና በመሪነት ያገለገሉት ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ወደ አኺራ ተሻገሩ😭

በአሜሪካን ሀገር ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ያሰባሰበው የ First hijrah foundation የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ማኅበረሰብ ድርጅት መሥራችና ለአርባ ዓመታት በመሪነት ያገለገሉት ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ቅዳሜ ሌሊት ወደ አኺራ መሻገራቸውን ፋውንዴሽኑ አስታውቋል::

ሐጂ ነጂብ ከፈርስት ሂጅራ መሥራችነት ባሻገር ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መብት መከበር በተለያዩ መልኩ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ሚሊንየም መባቻ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄ በማንበብ ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያቀርቡ፣ በ2004 በነበረው የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴ ወቅት በሚዲያዎችና በሰላማ ሰልፎች ላይ በመገኘት የድምጻችን ይሰማ ድምጽ በመሆን የመንግሥትን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማክሸፍ ግንባር ቀደም ሚና ነበራቸው።

የሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ሰላተል ጀናዛ በኒውሃምፕሻየር MCC መስጂድ ኦገስት 30/2016 በ1:30 PM ይሰገዳል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው የሚፈፀመው Al Firdaus Memorial gardens ይሆናል። ቤተሰብ የሚሰባሰበው ደግሞ በፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን እንደሚሆን ተገልጿል።

ሐጂ ነጂብ ሙሐመድ የአራት ልጆች አባትና የአምስት የልጅ ልጆች አያት ነበሩ።

( Horizon Podcast እና Addis Mieraf Forum - አዲስ ምዕራፍ ፎረም በሐጂ ነጂብ ሙሐመድ ኅልፈት የተሰማንንን ሐዘን እየገለጽ ፣ አላህ (ሱ.ወ) ለእርሳቸው ጀነትን ለቤተሰብና ለመላው ሙስሊም ማኅበሰብ መጽናናትን እንዲለግሥ ይመኛል።)

ዘገባው የ Minber TV / ሚንበር ቲቪ ነው

  ለውድ የ    ዝግጅት ታዳሚያን በሙሉ በቅድሚያ የዝግጅታችን ታዳሚ ለመሆን ስለመረጣችሁን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን 🙏🙏 በመቀጠል ነገ ወደ ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ሲመጡ :-1.  መግቢያ በነፃ...
29/08/2026



ለውድ የ ዝግጅት ታዳሚያን በሙሉ በቅድሚያ የዝግጅታችን ታዳሚ ለመሆን ስለመረጣችሁን እጅግ አድርገን እናመሰግናለን 🙏🙏 በመቀጠል ነገ ወደ ዓድዋ ዜሮ ዜሮ ሲመጡ :-

1. መግቢያ በነፃ ስለሆነ ምንም ዓይነት የትኬት ሽያጭ እንደሌለ ልብ ይበሉ

2. ወደ ዝግጅቱ ሲመጡ መኪና ይዘው የሚመጡ ከሆነ መኪናዎን በዓደዋ ድል መታሰቢያ ግራውንድ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ እንዲያቆሙ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

3. ምናልባት በእግር ኳስ ተጫዋቾች እና ስፖርት በሚሰሩ ስፖርተኞ መንገድ ሊዘጋ ስለሚችል በመጠቀም አማራጭ መንገዶችን ይጠቀሙ

4. አየሩ ቅዝቃዜ ሊሆን ስለሚችል ጥላ እንዲሁም አለባበስዎን ምቹ ያድርጉ።

"የሀገራችን ዓሊሞች አስተምሮ፣ ተጋድሎ እና እስላማዊ ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫዎቻችን ናቸው‼️
ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️

አክባሪያችሁ ዑስማን መሐመድ ሐምዛ ፕሮዱዩሰር እና ዳይሬክተር

📅 ቀን፦ ነገ እሁድ ነሐሴ 24 /2018
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:30 (ግማሽ ቀን)
📍 ቦታ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ

ለበለጠ መረጃ እና ድጋፍ ለማድረግ፦📞 +251955616161📞 +251987999997📞 +251972115454

#ክብርለሀገሬዓሊሞች

#ብርሃንእየቀበሩበጨለማመኖር

 ‼️  ‼️
28/08/2026

‼️
‼️

አስቸጋሪ ግን የራስ መንገድ‼️✍️✍️ 📖🎥 📽️🎥 👇👇“የአሁኑስ ይሳካ ይሆን ⁉️...አይሰረዝም ግን ⁉️...ለመሆኑ ይህን ያህል ዋጋ ለምን ትከፍላለህ‼️ ቢቀርብህስ... ❔❕አትተወውም...❔❗...
27/08/2026

አስቸጋሪ ግን የራስ መንገድ‼️
✍️✍️ 📖🎥 📽️🎥 👇👇

“የአሁኑስ ይሳካ ይሆን ⁉️...አይሰረዝም ግን ⁉️...ለመሆኑ ይህን ያህል ዋጋ ለምን ትከፍላለህ‼️ ቢቀርብህስ... ❔❕አትተወውም...❔❗"....

👇👇👇

በቅርብም በሩቅም ካሉ ወገኖቼ በተደጋጋሚ የምሰማቸው፣ አንዳንዶቹ ከትክክለኛ ስጋት፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ተስፋ ከመቁረጥ የሚሰነዝሯቸው ጥያቄዎች ናቸው። እውነት ነው❗ የአንድ ትልቅ ፕሮጀክት ዝግጅት በተደጋጋሚ መሰረዝ ፣ ቀናትን ማሸጋገር ከገንዘብና ሞራል ኪሳራው ባሻገር በአጋሮችና በተስፋ በሚጠባበቁ ታዳሚዎች ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም። ልብን ይሰብራል፣ ጉልበትን ያዝላል። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ማቆም ያልቻልኩት እና ተስፋ ያልቆረጥኩት የጀመርኩት ጉዞ የግል ዝናን ለመሸመት ወይም ቁሳዊ ትርፍን ለማሳደድ ስላሆነ ነው።

እኔ በኩሌ አዲስ ምዕራፍ ፎረም የተሰኘው የሐሳብ ሜዳ የመድረክ ዝግጅትን እና የፊልም ጥበብን እንደመሳሪያ በመጠቀም ዘጋቢ / ጥናታዊ ፊልሞችን የማመርተውን ጨምሮ መሰል ኃይማኖታዊ ፣ ሀገርዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮዮች ላይ ትኩረት አድርጌ የምሰራው በሙስሊም ኢትዮጵያውያን እየተሰተዋለ የሚገኘውን የሁሉን ነገር ተቀባይነት፣ የራዕይና አንድነት ማጣት እንዲሁም ሥር የሰደደ የማንነት ቀውስ ችግር ተቋማዊ እና ምሁራዊ መፍትሔ ይሻል ብዬ ስለማምነው::

የፊልም ኢንደስትሪ (የሲኒማ ጥበብ) ደሞ የአንድን ሀገር ባህል፣ ታሪክ እና ማንነት ለዓለም ለማስተዋወቅ እንዲሁም ከፍተኛ የኢኮኖሚ ገቢ ለማስገኘት ያለውን ትልቅ አቅም ሳንዘጋ....

እኔ የማላቆመው.... "ከራስ ለራስ የተሰጠ አደራ❗" በምለው እና ከ1400 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው ትውልድ ተሻጋሪ የሆነውን የሀገር በቀል እስላማዊ እውቀት ምርት እና የሊቃውንቶቻችንን (የዓሊሞቻችንን) ዘመን አይሽሬ ስብዕና ከተቀበረበት ፈልፍሎ የማውጣት ታላቅ የትውልድ አደራ ፤ ታሪክን ሰንዶ ለትውልድ ማሻገር ❗ “ቢቀርብህስ❔❕” ተብሎ የሚተው የትርፍ ጊዜ ሥራ ሳይሆን ፤ የሕሊና እና የትውልድ ዕዳ ነው❗ ብዬ ስለተቀበልኩት ነው::

አዎ❗ መንገዱ አልጋ ባልጋ እንዳልሆነ እገነዘባለሁ :: የመረጥኩትም “አስቸጋሪ ግን የራስ መንገድ” ነው‼️ በሰፊውና በብዝሁኅኑ ማኅበረሰብ ዘንድ የተለመደው እና ተቀባይነት ያለው መንገድ እኔ የያዛኩት መንገድ እንዳልሆነም እረዳለሁ :: አስቸጋሪው መንገድ ግን እውነትን ይዞ መሰናክሎችን መጋፈጥ ነው። ዝግጅቶቼ በተደጋጋሚ መሰረዛቸው እና መራዘማቸው እኔን ለመስበር ሳይሆን፣ ታሪኩን የሚመጥነውን ትዕግስትና ጽናት እንድለማመድ ያደረገን የጥበብ እጅ እንደሆነ አምናለሁ። የሚሰረዘውና የሚቀያየረው የቀን አቆጣጠር እንጂ በልቤ የተጻፈውን ራዕይ መቼውንም አይሰርዘውም❗

ያለቲፎዞ እና ጭብጨባ እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁኔታ ዕውቀትን ማምረትና ማስረጽን ከሀገሬ ዓሊሞች ተምርያለሁ ፤ ፈተናን አሸንፎ በጽናት መቆምን ደግሞ ከዓድዋ ድል ጀግኖች አባቶቼ ወርሻለሁ‼️ ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️ ወደ መሠረት መመለስ‼️ እና "ብርሃን እየቀበሩ በጨለማ መኖር" በሚሉ ግዙፍ መሪ ቃሎች የመልካም ስብዕና አርዐያዎቻችንን ታሪክ እና ቅርሰውርስ ሕያው የምናደርግበት ፤ ጅምር እና አዳዲስ ሥራዎችን የምናስተዋውቅበት እና የምናስቀጥልበትን ልዩ የመድረክ ዝግጅት በታሪካዊው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መደረጉም ሌላው የጽናታችን ማሳያ ነው። ይህ ስፍራ በራሱ ምስክር ነው—ድል የሚገኘው በፈተናዎች ውስጥ አልፎ ለቆመ ብቻ እንደሆነ ይነግረናልና‼️

“ይሳካል ወይ⁉️” ለምትሉኝ ሁሉ መልሴ አጭር ነው፦ አዎ‼️ በአላህ (ሱወ) ፈቃድ እንዲሁም በእናንተ ዱዓና ጽናት ይህ ዝግጅት በታላቅ ድል ይሳካል‼️ ምክንያቱም ብርሃን እየቀበሩ በጨለማ የመኖር ዘመን አብቅቶ፣ ወደ መሠረታችን የምንመለስበት ግዜ አሁን ስለሆነ::

ውድ የታሪክና የእውቀት ወዳጆች፤ ይህ የሁላችንም ነው። ባለፉት አስቸጋሪ ግዝያቶች አብራችሁኝ ለነበራችሁ እያመሰገንኩኝ በፈተናዎች ቀን አብራችሁኝ እንደነበራችሁ ሁሉ፣ በድል እና ደስታዬ ቀን አብራችሁኝ እንድንትቆሙ በአክብርዎት ስጋብዛችሁ በታላቅ ኩራት ነው።

ክብር ለሀገሬ ዓሊሞች‼️

"የሀገራችን ዓሊሞች አስተምሮ፣ ተጋድሎ እና እስላማዊ ቅርሶቻችን የማንነታችን መገለጫዎች ናቸው‼️

አክባሪያችሁ ዑስማን መሐመድ ሐምዛ ፕሮዱዩሰር እና ዳይሬክተር

📅 ቀን፦ እሁድ ነሐሴ 24/2018
⏰ ሰዓት፦ ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:30 (ግማሽ ቀን)
📍 ቦታ፦ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አዳራሽ

ኑ! መሰናክሎችን በአንድነት አልፈን ታሪካችንን በጋራ እንዘክር❗

#ክብርለሀገሬዓሊሞች

#ብርሃንእየቀበሩበጨለማመኖር


Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት
Ustaz Abubeker Ahmed/ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ.
Engr/Ustaz Bedru Hussein - በድሩ ሁሴን
Ahmedin Jebel-አሕመዲን ጀበል
Ustaz Yassin Nuru / ياسين نورو
የታላቁ አንዋር መስጂድ ወጣት ጀመዓ
First hijrah foundation

Address

Piazza Adwa Victory Museum
Addis Ababa
5313

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Horizon Podcast posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share