Ethio Digital-ኢትዮ ዲጂታል

Ethio Digital-ኢትዮ ዲጂታል እግዚአብሔር ይነሳ፥ ጠላቶችም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።
መዝሙር 68:1

Let the Lord arise, let his enemies be scattered, and let them that hate him flee before him. Psalm 68:1
(1)

22/01/2026

ሰላምን መርጠናል!

"የሰላም አማራጭን ተቀብለናል፤ ሰላምን መርጠናል ፤ ወደ ሰላም ኑ" አስጨነቅ ታደለ የብርጌድ አዛዥ የነበረ

📍ደብረ ማርቆስ
#ጦርነትአያስፈልግም
#የሰላምአማራጭ
#አማራ #ሰላም #ሰው #ኢትዮጵያ

22/01/2026

ሰበር ዜና የፋኖ ትግል ፣ በህወሓት ፣በሻቢያ ፣በግብፅ ተጠልፏል ‼️ ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው
#አማራ #ኢትዮጵያ #ሰላም #ሰው

22/01/2026

"የአማራ ህዝብ ከዚህ በላይ ጦርነት የሚሸከምበት ትክሻ የለውም" ኮሎኔል ፈንታሁን ሙሀባው🎯
#አማራ #ኢትዮጵያ #ሰላም #ሰው

20/12/2025
17/12/2025
ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!📌ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መ...
21/11/2025

ሴት ተማሪዎች አርቴፊሻል ነገር ማድረግ አይችሉም!

📌ሴት ተማሪዎች የጥፍር፣ የፀጉርና የከንፈር ቀለም መቀባት፣ ቅንድብ መቀንደብና መኳኳል፣ አላስፈላጊ ጌጣ ጌጦችን አድርጎ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ የሚከለክል መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጀ፡፡

| ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ሥነ ምግባር ለመቆጣጠር ያዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ማንኛውም ተማሪዎች ከተፈጥሮ ጸጉራቸው በስተቀር አርቴፊሻል ፀጉር መቀጠል አይችሉም ተብሏል፡፡

ከዚህ ባለፈም በትምህርት ቤት ውስጥ አላስፈላጊ የሆኑ የኢትዮጵያዊነት ባህልን የማይገልፁ በዓላት በተለይም እንደ ክሬዚ ዴይ፣ ኦልድ ዴይ፣ ቤቢ ዴይ፣ ቶማቶ ዴይ፣ ከለር ዴይ፣ ቫላንታይን ዴይ እና ሌሎችም የበዓል ቀናቶች ተብለው የሚከበሩ በዓላት ማክበር በመመሪያው ተከልክሏል፡፡

በትምህርት ቤት የደንብ ልብስ በተገቢ መንገድ መልሰብ ሲል ባወጣው መመሪያ ስር ሴቶች ጉርድ ቀሚስ ከባት በታች የሆነ ቁመት ያለው ለብሶ መገኘት አለባቸው ተብሏል፡፡

ከደንብ ልብስ ውጪ ቢሆን ከአካባቢው ባህል ጋር የማይቃረን አለባበስ መልበስ ይጠበቅባቸዋል ይላል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ትምህርት ቤት ውስጥ መፈፀም የተከለከሉ ድርጊቶች ብሎ ከዘረዘራቸው መካከል ደግሞ የትምህርት ቤቱን መምህራን፣ የትምህርት አመራር፣ ሠራተኞችና ሌሎች የትምህርት ማህበረሰብ አካላትን መዝለፍ፣ መስደብ፣ ማንቋሸሽና አካላዊ ጥቃት መፈጸም ቅጣት የሚያስከትል ተግባር ነው ተብሏል፡፡

ተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም ሞባይል እና የሙዚቃ ማዳመጫ መሣሪያዎችን ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይዞ መገኘት ረቂቅ መመሪያው ከልክሏል፡፡

በቃል፣ በምልክትም ሆነ በጽሑፍ ፀያፍ ነገሮችን መግለፅ፤ ጨዋነት የጎደላቸውን እንዲሁም ሐይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ምስሎችና ጽሑፎች በትምህርት ቤት ውስጥ ይዞ መገኘትና ማሰራጨት አይፈቀድም፡፡

በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የማንኛውንም ዓይነት የኃይማኖት አምልኮ ሥርዓትና የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን ማካሄድ ይከለክላል፡፡

ማንኛውም ተማሪ አገራዊ እሴት ያልሆኑና መጤ የሆኑ ነገሮችን በሰውነት ላይ ምልክት ማድረግ፤ ከአገራዊ እሴት ጋር የሚቃረኑ አሉታዊ መጤ ምልክቶችን በሰውነት ላይ መነቀስ፣ ማሳየት፣ ማድረግ፣ መጠቀም ፍፁም የተከለከለ ነው ብሏል ረቂቅ መመሪያው፡፡

ከ9 እስከ 12ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አንድ ተማሪ በሥነ-ምግባር ጉድለት እጅ ከፍንጅ ከተያዘና የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያውክ ሆኖ ከተገኘ ውሳኔ እስኪሰጠው ከትምህርት ቤት ሊታገድ እንደሚችልም በመመሪያው ሰፍሯል፡፡

ተማሪዎች ተደጋጋሚ ጥፋት አጥፍተው ሲገኙ በተለይም ከ7 እስከ 12ተኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች እስከ 1 ዓመት ድረስ እንደ ጥፋቱ መጠን ታይቶ ከትምህርት ሊታገዱ ይችላልም ሲል ረቂቅ መመርያው አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የትምህርት አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበ ረቂቅ ደንብ ተሰናድቷል፡፡

በዚህ ረቂቅ ደንብ ትምባሆ(ሲጋራ፣ ሺሻ)፣ ጫት፣ አልኮል የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ ዝርያ ያላቸው አደገኛ ህገ ወጥ መድኃኒቶች እና ሱስ አስያዥ ዕፆች ትምህርት ቤት አካባቢ መሸጥም ሆነ ይዞ መገኘትን ይከለክላል።

የአልኮል መሸጫ እና ማከፋፈያ ቤቶች፣ የሲጋራ መሻጫ ሱቆች፣ ሺሻ ቤቶች፣ ጫት መሸጫና መቃሚያ ቤቶች፣ ጭፈራ ቤቶች፤ ቁማር ቤቶች፤ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች እና የሰውነት መታሻ ወይም ማሳጅ ቤቶች በትምህርት ቤቶች በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ መክፈት አይቻልም፡፡

ፊልም ማጫዎቻ ቤቶች፣ ፕሌይ ስቴሽን ቤቶች፣ ዲ.ኤስ.ቲቪ ቤቶች፣ ከረንቡላ፣ ፑል፣ ጆተኒ፣ ቢንጎ እና የስፖርት ቁማር መጫወቻ ቤቶችም በትምህርት ቤት አቅራቢያ መክፈትን ከልክሏል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።

28/10/2025

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር በልዩ ዘመቻዎች ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በምስል፡-Source: FBC
25/10/2025

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን አከባበር በልዩ ዘመቻዎች ሃይል ማሰልጠኛ ማዕከል በምስል፡-

Source: FBC

25/10/2025

ኮይሻ

25/10/2025

#

Address

Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Digital-ኢትዮ ዲጂታል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share