Glance of Jan

Glance of Jan Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Glance of Jan, Social Media Agency, Ethiopia, Addis Ababa.

የግሎባል ሱሙድ ፍሎቲላ ቅሌትበዋናነት በአለም አቀፍ የአከባቢ መብት ተቆርቋሪነት፤ እንዲሁም በኋላ ላይም በሰብአዊ መብት ተቆርቀሪነት በምትታወቀዉ ሲዉዲናዊቷ “ግሬታ ዙንበርግ” የፊት አዉራሪነ...
29/09/2025

የግሎባል ሱሙድ ፍሎቲላ ቅሌት

በዋናነት በአለም አቀፍ የአከባቢ መብት ተቆርቋሪነት፤ እንዲሁም በኋላ ላይም በሰብአዊ መብት ተቆርቀሪነት በምትታወቀዉ ሲዉዲናዊቷ “ግሬታ ዙንበርግ” የፊት አዉራሪነት እየተመራ በጋዛ ላይ የተጣለዉን የባህር ላይ ከበባን ለመስበር በማሰብ በስሩ ከ55 በላይ ጀልባዎችን እና ከ44 የዓለማችን አገራት የተዉጣጡ በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር፡ “ግሎባል ሱሙድ ፍሎቲላ”/Global Sumud Flotilla/ በሚል ስያሜ እ.ኤ አ. ነሐሴ 31, 2025 ከስፔና የባርሴሎና ወደብ የተነሳዉ ቡድን በዉስጡ የደቡብ አፍሪካዉ ተወዳጅ መሪ የነበሩት የኔልሰን ማንዴላ የልጅ ልጅ “ማንድላ ማንዴላ” እና የፈረንሳይዋን ታዋቂ ተዋናይት “አዴሌ ሀኤኔል” እና ሌሎች ብዙ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በዉስጡ ያቀፈ ነዉ፡፡

ዛሬ ሰኞ መስከረም 29, 2025 ጉዞ ከጀመሩ 29ነኛ ቀናቸዉን የያዙ ሲሆን ምናልባትም ነገ ወደ ጋዛ ሰርጥ የዉሃ ክልል ይደርሳሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መላዉ አለምም እስራኤል ምን አይነት ምላሽ ልትሰጥ ትችላለች በሚል ስጋት ጉዳዩን በአይነቁራኛ እየተከታተለ ይገኛል፡፡

ታዲያ ይህ ብዙ የተባለለት የተጓዦች ቡድን መንገድ ላይ ከእስራኤል በኩል እየገጠመን ነዉ ካሉት የድሮን ቅኝት፣ ቦንብ እና የኬሚካል ጥቃት ተግዳሮቶች ባለፈ ትልቅ ቅሌት ገጥሞታል፡፡
ይህ በዋናነት “በሰብዓዊነት ተልዕኮ ስም” የተሰባሰበዉ ቡድን በዋናነት በአራት ክፍሎች የተቧደነ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ልክ እንደስማቸዉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሲሆኑ፤ ሁለተኛዉ ቡድን ደግሞ አፍቃሪ ሀማስ ናቸዉ፡፡ በሶስተኛዉ ቡድን ዉስጥ የሚካተቱት ደግሞ አክራሪ እስልምናን የሚያቀነቅኑ ሲሆኑ በአራተኛዉ ጎራ ዉስጥ እራሳቸዉን የሚከቱ ደግሞ ለግብረሰዶማዉያን መብት እንታገላለን የሚሉ ናቸዉ፡፡

ግብረሰዶማዊነትን አጥብቀዉ በሚቃወሙ አክራሪ እስላማዊ ቡድኖች እና ዘግየት ብሎ ከቱኒዚያ ወደብ ቡድኑን በተቀላቀለዉ እራሱን “የኮሚኒስት ፍናፍንቶች ተዋጊ”/Communist q***r fighter/ በማለት በሚጠራዉ በቱኒዚያዊዉ ሰይፍ አያዲ መካከል በተፈጠረዉ አተካራ የተነሳ በተጓዦቹ መካከል መቃቃርን ፈጥሯል፡፡

በዚህም ሳያበቃ ግንባር ቀደም የጉዞ አስተባባሪዎች ከሆኑት መካከል አንዱ የሆነዉ፤ ካሊድ ቦኡቼማ ሲናገር “የልዑካኑ ዋና መርሕ የነበረዉ ለፍልስጤማዉያን ድምጽ ለመሆን ታስቦ የተጀመረዉ ዘመቻ የተለየ ፍላጎት ባላቸዉ አካላት ተጠልፋል” በማለት ጉዞዉን አቋርጦ ወጥቷል፡፡
ካሊድ ቦኡቼማን ተከትለዉ ብዙኋኑ “በተራማጅ የባህል አጀንዳ አራማጆች”/Culturally Progressive Agenda/ አላማችን ተጠልፏል በማለት በተለያየ ጎራ ተቧድነዋል፡፡

ይህንን ቅሌት ተከትሎ ሲዉዲናዊቷ አክቲቪስት ግሬታ ዙንበርግ ከዋና አስተባባሪ የማኔጅመንት ቡድን ዉስጥ ተወግዳ፤ በጉዞ ዉስጥ እንደ ተራ በጎ ፈቃደኛ ግለሰብ ብቻ እየተሳተፈች እንደምትገኝ ተገልጿል፡፡

በነገራችን ላይ የፍልስጤማዉያንን መብት እና የሁለት አገርነት መፍትሄን በመደገፍ በምዕራቡ አለም በሚደረጉ የተቃዉሞና የድጋፍ ሰልፎች ላይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች፣ የግራ ዘመም ፖለቲካ ደጋፊዎች እና የግብረሰዶማዊያን መብት ተማጋቾችን በጥምረት መመልከት የተለምደ ትዕይንት ሆኗል፡፡

እንዴት በእነዚህ 3ት ኃይሎች መካከል ጥምረት ሊፈጠር ቻለ? በመካከላቸዉ የሚያዛምዳቸዉ አንዳች የጋራ አጀንዳ ይኖር ይሆን? የሚለዉ እንቆቅልሽ፤ እስካሁን ድረስ በመላዉ አለም በሚገኙ ህዝቦች ያልተፈታ ሚስጥር ሆኗል፡፡

እናንተስ ይህንን ጉዳይ ልብ ብላችኋል? በጉዳዩ ላይ ያላችሁስ መረዳትና ምልከታ ምንድነዉ?

ሰላም ሰንብቱ!

ይህ በዋናነት “በሰብዓዊነት ተልዕኮ ስም” የተሰባሰበዉ ቡድን በዋናነት በአራት ክፍሎች የተቧደነ ነዉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ልክ እንደስማቸዉ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች ሲሆኑ፤ ሁለተ.....

የስሎቫኪያ ፓርላሜንት በአብላጫ ድምጽ፤ በአገራቸዉ ተቀባይነት ያለዉ ሕጋዊ ጸታ ወንድ ና ሴት ብቻ ናቸዉ ሲል የህገመንግስት ማሻሻያ አደረገ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸዉ ልጆችን ...
27/09/2025

የስሎቫኪያ ፓርላሜንት በአብላጫ ድምጽ፤ በአገራቸዉ ተቀባይነት ያለዉ ሕጋዊ ጸታ ወንድ ና ሴት ብቻ ናቸዉ ሲል የህገመንግስት ማሻሻያ አደረገ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸዉ ልጆችን በጉዲፈቻ ወስዶ ማሳደግ የሚከለክል ህግ አጽድቋል፡፡

Slovakia has changed its constitution, enshrining into law recognition of only two sexes – male and female.
The legal change, which passed in a knife-edge vote in the central European nation's parliament, also restricts adoption to married heterosexual couples and prohibits surrogate pregnancies.

የስሎቫኪያ ፓርላሜንት በአብላጫ ድምጽ፤ በአገራቸዉ ተቀባይነት ያለዉ ሕጋዊ ጸታ ወንድ ና ሴት ብቻ ናቸዉ ሲል የህገመንግስት ማሻሻያ አደረገ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸዉ ....

በኢራን ሰሜናዊ ምዕራብ ከፍል የሚገኘዉና የእስያ አህጉር ትልቁ የጨዉ ሐይቅ የሆነዉ “ኡርሚያ”/Urmia/ ሙሉ ለሙሉ ደረቀ፡፡ትልቁ ጨዋማ የዉሃ አካል የሆነዉ የኡርሚያ ሐይቅ በእስያ ከፍለ አ...
24/09/2025

በኢራን ሰሜናዊ ምዕራብ ከፍል የሚገኘዉና የእስያ አህጉር ትልቁ የጨዉ ሐይቅ የሆነዉ “ኡርሚያ”/Urmia/ ሙሉ ለሙሉ ደረቀ፡፡

ትልቁ ጨዋማ የዉሃ አካል የሆነዉ የኡርሚያ ሐይቅ በእስያ ከፍለ አህጉር ዉስጥ ተወዳዳሪ የሌለዉ ሐይቅ ነበር፡፡ ምድራችን ከተፈጠረችና በአከባቢዉ የሰዉ ልጆች ሰፍረዉ ታሪክን መመዝገብ ከጀመሩ አንስቶ ላለፉት 4000 ዓመታት የነበረ ሐይቅ በሚያሳዝን ሁኔታ ደርቋል፡፡

እ.ኤ.አ የዘመን አቆጣጠር በ1980ዎቹ 140ኪ.ሜ ርዝመትና 55ኪ.ሜ ስፋት የነበረዉ ሐይቅ በዚህ አመት በ2025 እ.ኤ.አ ደረቅ ምድረበዳ ሆኗል፡፡
የአከባቢ መብት ተቆርቋሪዎችና በአገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ተቃማዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለክስተቱ ተጠያቂ ያደረጉት መንግስትን ሲሆን፤ በአከባቢ ላይ የሚከተለዉ ፖሊስ ለተፈጠረዉ ድርቅ መንስኤ ነዉ ብለዋል፡፡

መንግስት ግን ለተፈጥሮዉ አደጋ መንስኤ ነዉ በማለት እንደ ምክንያትነት ያስቀመጠዉ፡ ከ10,000 በላይ የሚሆኑ በተለይም ለእርሻ ተብለዉ የተቆፈሩ የከርሰ ምድር ጥልቅ ጉድጓዶች የአገሪቱን ዉሃ ጨርሶታል ብለዋል፡፡

ይህንን ተግባር የሚቃወሙ ቡድኖች ግን፤ የአገሪቱን 10 በመቶ ጂ.ዲ.ፒ/GDP/ መሸፈን የማይችለዉ የግብርና ኢንደስትሪ መተኪያ የሌለዉን የተፈጥሮ ሀብት ሲያጠፉ መንግስተ በቸልታ መመልከቱ ዛሬ ላይ ለሆነዉ ሁሉ ሙሉ ኃላፊነት መዉሰድ አለበት በማለት ይከሳሉ፡፡

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የሆኑት "ማሱድ ፔዝሺካህን"/Masoud Pezeshkian/ በሐምሌ ወር ስለሁኔታዉ ሲናገሩ፡ የግብርናዉ ዘርፍ በአመት 43 ሚለየን ኪዩቢክ ዉሃ ይጠቀማል፡፡ ይህ ደግሞ ተፈጥሮ መተካት ከምትችለዉ በላይ ነዉ በማለት የችግሩን ክብደት አስረድተዋል፡፡
በዚህም ሳያበቁ 15,000,000 ሚሊየን ህዝብ የሚኖርባትን የአገሪቱን ዋና ከተማ ቴህራንን በዉሃ እጥረት ምክንያት ወደ ሌላ ስፍራ የማዘዋወር እቅድ እንዳለ አስረድተዋል፡፡

የኡርሚያ ሐይቅ መድረቅ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ወደ ቀዉስ ዉስጥ ከመክተት ባለፈ፤ የደረቀዉ ሐይቅ ጨዋማ ስለነበር ጨዉ በአዉሎነፋስ እየተገፋ ወደ ሚታረሱ የእርሻ መሬቶች በመሄድ የገበሬዎችን ህይወት ለመከራ ዳርጓል፡፡

ማጠቃለያ፡ “አስተዋይ የሆነ ልብ ይበል” ለ4000 ዓመታት የነበረ የዉሃ አካል እነደዘበት ሲጠፋ ጊዜዉን ለመረዳት መሞከር ተገቢ ነዉ፡፡

ኘሬዚዱንት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር የምረጡኝ ቅስቀሳ  በሚያደርጉ ጊዜ፣ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ወጣቱ ድምፁን ለትራምፕ እንዲሰጥ የአንበሳ ድርሻውን የተወ...
11/09/2025

ኘሬዚዱንት ትራምፕ ለሁለተኛ ጊዜ ለፕሬዚዳንትነት ለመወዳደር የምረጡኝ ቅስቀሳ በሚያደርጉ ጊዜ፣ ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን በመጠቀም ወጣቱ ድምፁን ለትራምፕ እንዲሰጥ የአንበሳ ድርሻውን የተወጣው ቻርሊ በጥላቻ በታወሩ ቡድኖች፣ በዩኒቨርስቲ ውስጥ ውይይት እያደረገ ሳለ በጥይት ተመትቶ ሕይወቱ አልፏል።
ውድ ህይወቱን ለእውነት አሳልፎ ሰጥቷል።
ነፍስህ በሰላም ትረፍ ቻርሊ!!!

The prominent US rightwing activist has died after being attacked at a public event in UtahCharlie Kirk succumbs to gun...
10/09/2025

The prominent US rightwing activist has died after being attacked at a public event in Utah

Charlie Kirk succumbs to gunshot wound – Trump
Charlie Kirk, founder of Turning Point USA ©
Charlie Kirk, a major supporter of Donald Trump and the executive director of the Turning Point USA organization, has died after he was shot while delivering a talk at Utah Valley University, the US president has announced.

The 31-year-old activist and influencer was shot in the neck while taking questions from a crowd gathered on the grounds of the university. Kirk was reportedly shot from a building about 200 yards from where he stood, having addressed the crowd for some 20 minutes, a university spokesperson told New York Times.

“The Great, and even Legendary, Charlie Kirk, is dead. No one understood or had the Heart of the Youth in the United States of America better than Charlie. He was loved and admired by ALL, especially me, and now, he is no longer with us,” Trump wrote on his Truth Social

❗️❗️❗️GERD Inauguration: Dam to Help Africa 'Emerge From Economic Slavery,' Says Ethiopian Minister🇪🇹🌍 The Grand Ethiopi...
09/09/2025

❗️❗️❗️GERD Inauguration: Dam to Help Africa 'Emerge From Economic Slavery,' Says Ethiopian Minister

🇪🇹🌍 The Grand Ethiopian Renaissance Dam, the largest in Africa, is a crucial step for the continent to achieve economic and policy freedom, according to Ethiopian Minister of Industry Melaku Alebel.

"The GERD, like the Victory of Adwa, helps Africans move away from the idea that ‘we can't,’ and ‘we can't stand without support,’ toward securing their economic and policy freedom," Alebel told Sputnik Africa at the inauguration ceremony.

🤝 The dam's power generation is essential for trade and industrial development, enabling Ethiopia to share electricity with neighboring countries like Kenya, Djibouti, and Sudan, the minister emphasized.

"This dam is not only ours; it belongs to the region and the continent," Alebel stated, adding that the facility can foster economic and political community, strengthen diplomatic ties, and contribute to Africa's overall progress.

የቡርኪናፋሶ ምክር ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያግደዉን ህግ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡ ሕጉም የቤተሰብ ህግ በመባል የተሰየመ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ ከ2 እስከ 5 አመት ድረ...
04/09/2025

የቡርኪናፋሶ ምክር ቤት የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያግደዉን ህግ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡ ሕጉም የቤተሰብ ህግ በመባል የተሰየመ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ግለሰብ ከ2 እስከ 5 አመት ድረስ በእስር እንዲቀጣ ይፈረድበታል፡፡
የወቅቱ የአገሪቱ መሪ ኮሎኔል ኢብራሒም ትራኦሬ፡ እ.ኤ.አ በ2022 ወደ ስልጣን ሲመጡ ለሕዝባቸዉ ለመፈጸም ቃል ከገቡት አጀንዳዎች ዉስጥ ተቀዳሚዉ ሲሆን፤ ቃላቸዉንም በተግባር ማረጋገጥ ችለዋል፡፡

In the new law, those found guilty of homosexuality could face a two- to five- year prison sentence.
The draft law was unanimously passed on Monday by 71 unelected members of the country’s transitional government, which has been in place since the military seized power under the leadership of the now President Ibrahim Traore

https://youtu.be/27s5KLVdrmQ
03/09/2025

https://youtu.be/27s5KLVdrmQ

In the new law, those found guilty of homosexuality could face a two- to five- year prison sentence.The draft law was unanimously passed on Monday by 71 unel...

https://youtu.be/zhVzMYsO78k
02/09/2025

https://youtu.be/zhVzMYsO78k

This video talks about the recent arguments on social media in Ethiopia. It tries to elaborate and clarify. by citing from history. ከሠሞኑን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ያ...

01/09/2025

ከሠሞኑን የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎችን ያጥለቀለቁ፡ በዋናነት አገርን፣ ባህልን፣ ኃይማኖትን እና ሕዝብን በጅምላ እንዲሁም እራስን በተናጠል፤ የማጥላላት እና “ላለመሠልጠናችን” ተናጋሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ፡ ግንባር ቀደም ምክንያቶች ስለመሆናቸዉ በየፖድካስቱ ላይ እየተሰጡ ያሉ ትንታኔዎችን ስመለከት፤ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ለመረዳት የራሴን ጥረት ማድረጌ አልቀረም፡፡

የተናጋሪዎቹ አይን አዉጣነትና አላዋቂነት ሳያንስ፤ እነርሱን ደግፈዉ “እኛ ለመረዳት አቅሙ ስለሌለን እንጂ እነርሱ ሊሉ የፈለጉን እንደዚህና እንደዚያ ነዉ” በማለት የሚያዝጉን ደግሞ ተጨማሪ የልብ ድካሞች ናቸዉ፡፡

አጠቃላይ ሁኔታዉን እና ድግግሞሹን ስመለከት አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡

በህዳር 26፡ 2004 ዓ.ም / December 6, 2011/ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ከፍተኛዉ ኮሚሽነር፤ የአለም የሰብዓዊ መብት ቀንን/ UN Office of the High Commissioner for Human Rights, marking Human Rights Day/ በማስመልከት በስዊዘርላንድ ጄኔቫ ከተማ አለም አቀፍ ጉባኤ አዘጋጅቶ ነበር፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ ተናጋሪ ከነበሩት ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል በጊዜዉ የኦባማ አስተዳደር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ሒላሪ ክሊንተን ስለ አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ለተሰብሳቢዎቹ ረዘም ያለ ዲስኩር አድርገዉ ነበር፡፡

በንግግራቸዉ መካከል የጠቀሱት አንድ አረፍተ ነገር ግን የሰሞኑን “ኢ-አማኒያን” ነን ባዮችን እና ስለ “ሴክሹዋል ኢነርጂ” አብዝተዉ እያደነቆሩን ያሉ ወገኖቻችንን አስታወሰኝ፡፡

ስቴት ሴክረታሪ ሒላሪ ሮድሐም ክሊንተን ለጉባኤተኞቹ የሚከተለዉን ተናገሩ

Hillary Clinton- U.S Secretary of State...
“… The 3rd and perhaps most challenging issue arises when people cite religious or cultural values as a reason to violate or not to protect the human rights of LGBT citizens.”

ሒላሪ ክሊንተን፡ - የቀድሞ የአሜሪካን የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር…
“…የግብረሶዶማዉያንን መብት ለማስከበር በምናደርገዉ ትግል ዉሰጥ ትልቅ ተግዳሮት የሆነብን ህዝቦች ኃይማኖታቸዉን እና የባህል ዕሴቶቻቸዉን በመጥቀስ እነዚህን ማህበረሰቦች ለመቀበል አለመፈለጋቸዉ ነዉ፡፡”

ታዲያ በታዳሚዎቹ ላይ “ያሰብነዉን እንዳናሳካ እንቅፋት የሆኑብን ባህልና ኃማኖት ናቸዉ” በማለት በሰብዓዊ መብት ስም ሲመጸዳደቁ የነበሩት ሒላሪ ክሊንተን ዛሬ መታሰቢያቸዉ የለም፡፡
እንዲያዉም 47ኛዉ ፕሬዚደንት ሆነዉ ወደ ነጩ ቤተመንግስት በድጋሚ የተመለሱት ዶናልድ ትራምፕ፡ የሩሲያ ቅሌት በሚባለዉና የተለያዩ የሙስና ጉዳዮችን በመጥቀስ የእርጅና እድሜያቸዉን በእስር ቤት እንዲያሳልፉ ለአቃቤ ህግ ምርመራ እንዲጀመር ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡

ያኔ የአለም የሰብዓዊ መብት ማለት የግብረሰዶማዉያን መብት ማለት ነዉ እያሉ ሲያዜሙለት የነበረዉ አጀንዳ፤ ዛሬ ላይ የአሜሪካ መንግስት እንደዚህ አይነት ልምምድ ዉስጥ ያለ ግለሰብ የአእምሮ ጤና መታወክ ያለበት ነዉ ህክምና ያስፈልገዋል ወደሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡

ታዲያ ሰሞነኞቹ የኛ ጉዶች የአለምን አቅጣጫ አልተረዱም ወይንስ አርፍደዉ የነቁ ሆነዉ ይሆን?
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም ብሏል እና መኃሪዉ አምላክ፤ ምህረቱን ይስደድልን!

27/08/2025

ከዕለታት በአንዱ ቀን የዱር አራዊት ንጉስ የሆነው አንበሳ በማለዳ ተነስቶ "የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ" በማለት ወደ ፈጣሪው ፀለየ።
በሌላኛው አቅጣጫ ደግሞ ሚዳቋ ከእንቅልፏ ነቅታ "ቀኑን በሰላም አውለኝ" ብላ ፀልያ ስትወጣ: ምግቤን ስጠኝ ብሎ ከጸለየው አንበሳ ጋር ፊት ለፊት ተገናኙ።
የአዳኝ ታዳኝ ሩጫ ተጀመረ። በመሃሉ አንበሳው እንቅልፋን ለጥ ብሎ የተኛ ድኩላ ያገኝና ቅርጥፍጥፍ አድርጎ ይበላዋል።
"የእለት ጉርሴን ስጠኝ ያለውም ምግቡን አገኘ"
"በሰላም አውለኝ ያለውም ከክፋ ተጠበቀ"
የተኛ ግን ተበላ....
ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና... ተግታችሁ ፀልዩ።

የኢንግሊዝ  ፕሪሚየር  ሊግ ላለፉት ስምንት አመታት ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 5 ድረስ በግድ የሚያስደርገዉን የግብረሰዶማዉያን ቀስተ ደመና ምስል ያለበትን የአንበሎች አርም ባንድ እና የታኬ...
18/08/2025

የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላለፉት ስምንት አመታት ከህዳር 29 እስከ ታህሳስ 5 ድረስ በግድ የሚያስደርገዉን የግብረሰዶማዉያን ቀስተ ደመና ምስል ያለበትን የአንበሎች አርም ባንድ እና የታኬታ ማሰሪያ ክር ከዚህ በኋላ እንዳስቆመ አስታወቀ፡፡

English Premier Leauge/EPL/: Premier League ends partnership with Stonewall
The Premier League will no longer take part in the Rainbow Laces campaign after ending its partnership with LGBTQ+ charity Stonewall.

English Premier Leauge/EPL/: Premier League ends partnership with StonewallThe Premier League will no longer take part in the Rainbow Laces campaign after en...

Address

Ethiopia
Addis Ababa
04620

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Glance of Jan posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share