በሰቃ / Beseka Tube

በሰቃ / Beseka Tube ነገን በዛሬ ውስጥ እናያለን!

በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራችና ባለቤቶች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ክስ መመስረቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ...
28/03/2026

በዜጎች ላይ የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት ባደረሱት የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅት መስራችና ባለቤቶች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ክስ መመስረቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ

‎ፊንቴክ ኢንቬስትመንት የግል ድርጅት መስራችና ባለቤቶች የሆኑት ዳንኤል ዮሃንስ ኢየሱስ እና ግርማይ ገ/ሚካኤል ይህደጎ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በመጠቀም ከ1200 በላይ ዜጎችን በማጭበርበር የ1.7 ቢሊዮን ብር ጉዳት በማድረሳቸው በ19 ዓይነት የተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ አጣርቶባቸው ለዐቃቤ ሕግ በመላክ ዓቃቤ ሕግ ክስ መመስረቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።

መጀመሪያ ክሱ የቀረበው ለአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ቢሆንም ምርመራው ውስብስብና ከፍተኛ ልምድ የሚጠይቅ ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ በተደራጀ መልኩ መጣራት ስላለበት ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማምጣት ምርመራው በስፋት ሲጣራ መቆየቱን ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪ ዳንኤል ዮሃንስ ላይ ክስ ተመስርቶበት ማረሚያ ቤት ሆኖ ክሱን እንዲከታተል መደረጉንና ተጠርጣሪ ግርማይ ገ/ሚካኤልን ደግሞ በቁጥጥር ሥር ለማዋል ክትትል እያደረገ መሆኑን የገለፀው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ግርማይ ገ/ሚካኤል የተባለው ግለሰብ ከዚህ ቀደም እ.ኤ.አ አቆጣጠር በ2010 የደቡብ አፍሪካ የዓለም የእግር ኳስ ሻምፒዮና ወቅት አስካሉካን በተባለ ድርጅት ስም ወደ ደቡብ አፍሪካ ሄዳችሁ የዓለም ዋንጫ እንድትመለከቱ አደርጋለሁ በማለት ዜጎችን አጭበርብሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ካሰባሰበ በኋላ ተደብቆ ከሀገር በመውጣቱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል ጋር በመተባበር ባደረገው ጠንካራ ክትትል ከተደበቀበት ሀገር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ አድርጎ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን ማድረጉን የወንጀል ሪከርዱ እንደሚያመላክት አስረድቷል።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ተጎጂዎችን 50% ቅድመ ክፍያ 950 ሺህ ብር በማስከፈል በ90 ቀናት ውስጥ የመኪና ባለቤት እንደሚያደርጓቸውና ቀሪ 950 ሺህ ብር ደግሞ ያለወለድ በ5 ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ የባንክ ብድር እንደሚያመቻቹላቸው በመግለጽ ዜጎችን በማጭበርበር ክፍያውን እንዲፈጽሙ አድርገዋል ሲል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ ኅብረተሰቡን ለማሳመን 148 መኪኖች ከጅቡቲ በማስገባት 100 መኪኖች ለተወሰኑ ግለሰቦች እንዲከፋፈል በማድረግ እና ቀሪ 48 ዘመናዊ መኪኖችን መርጠው በድብቅ መሸጣቸውን እንዲሁም ወደ ሀገር ውስጥ ስለመግባታቸው ምንም አይነት መረጃና ማስረጃ ሳይኖር 350 መኪኖችን ከውጭ እንዳስገቡ በማስመሰል ኅብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ እንደነበር ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡

በተጨማሪም በጅቡቲ ወደብ ምንም ዓይነት መኪና ሳይኖር 400 መኪኖች ጅቡቲ ወደብ ላይ እንደቆሙና ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በሂደት ላይ እንዳሉ በማስመሰል ለተጎጂዎች ሐሰተኛ መረጃ መስጠታቸውን ፖሊስ ማረጋገጥ ችሏል።

በመስቀል አደባባይ ከተለያዩ ቦታዎች መኪኖችን በትውስት በማሰባሰብ ሕዝብን በሚያሳስት መልኩ ድርጅቱ ከውጭ ሀገር ያስገባቸው መኪኖች እንደሆኑ በማስመሰል እና የኤሌክትሪክ መኪና አምራች ከሆነው BYD ከተባለ የቻይና ካምፓኒ ጋር ምንም ዓይነት ውል ሳይኖራቸው ውል እንዳላቸው አድርገው የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽሙ መቆየታቸውን ፖሊስ በምርመራ ደርሼበታለሁ ብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ በጅቡቲ ውስጥ አልፋቲዞ በሚል ስም ድርጅት በማቋቋም BYD ከተባለ የቻይና ካምፓኒ ጋር አብሮ ከሚሰራ ሌላ ድርጅት ጋር በመነጋገር 10% ቅድመ ክፍያ በመክፈል የመጀመሪያዎቹን 148 መኪኖች ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው እንደነበርና ተጨማሪ 188 መኪኖችን በተመሳሳይ 10% ቅድመ ክፍያ ለድርጅቱ በመክፈል መኪኖቹን ተረክበው ወደ ሀገር ውስጥ ሳያስገቡ ጅቡቲ ላይ እንዲሸጡ ማድረጋቸውንና በአጠቃላይ 336 መኪኖችን 10% ጅቡቲ ለሚገኘው የቻይና ድርጀት በመክፈል ወስደው ቀሪ 90% ክፍያ አለመፈፀማቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ደርሶበታል።

ከ1200 በላይ ተጎጅዎችን በማጭበርበር መዝግበው 95 ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ፤ 285 ሺህ ብር የመንግስት ታክስ እንዲሁም 130 ሺህ ብር ለኤክትሪክ መኪና ቻርጀር ለማሰራትና ለባለሙያ በሚል ከእያንዳንዳቸው 1 ሚሊየን 365 ሺህ ብር መቀበላቸውን ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅትን ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ በህገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጋሪ በመሆን የተጠረጠሩ ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አብርሃም ግዛው፣ ይገረም ደጀኔ፣ መንሱር ጀማል እና ካሊድ ናስር የተባሉ ታዋቂ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎችንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ፍርድቤት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው ፍርድ ቤትም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም መፍቀዱ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማጭበርበርና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ (Money laundering) እና የድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ጨምሮ በ19 የወንጀል ጉዳዮች በተጠረጠሩ የፊንቴክ ኢንቬስትመንት ድርጅት መስራቾችና ባለቤቶች እንዲሁም በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸዉን ዕውቅናና ተቀባይነት በመጠቀም ሆነ ብለው የተጋነነ ማስታወቂያ በመንገር እና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ የሀሰት መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማሰራጨት ዜጎችን እንዲጭበረበሩ በማድረግ በሕገወጥ መንገድ ከተገኘዉ ገንዘብ እያንዳንዳቸዉ አሁን ባለዉ የገበያ ዋጋ ስምንት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ቢ.ዋይ.ዲ ሶንግ ፕላስ የመኪና ስጦታ በመቀበል፤ በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ (Money laundering) እና በዜጎች ላይ ከ1.7 ቢሊየን ብር በላይ ጉዳት በማድረስ በተጠረጠሩ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ይህ ውስብስብ የወንጀል ጉዳይ በተሳካ ሁኔታ ተጣርቶ ክስ እንዲመሠረት ከፖሊስ ጋር በትብብር ለሠራው የፍትህ ሚኒስቴር እና በጉዳዩ ላይ መረጃ ሲሰጥ ለነበረው ኅብረተሰብ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል።

የአሜሪካ የጦር ቤዞች ተወግደዋል-ኢራን‼️በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የአሜሪካ የጦር ቤዞች/ሰፈሮች) ተወግደዋል" - የኢራን ጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋጋሪ‼...
26/03/2026

የአሜሪካ የጦር ቤዞች ተወግደዋል-ኢራን‼️
በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ የሚገኙ ሁሉም የአሜሪካ የጦር ቤዞች/ሰፈሮች) ተወግደዋል" - የኢራን ጦር ኃይሎች ቃል አቀባይ ኢብራሂም ዞልፋጋሪ‼️
የአሜሪካ አዛዦች እና ወታደሮች ሸሽተው የት እንደገቡ አይታወቅም ብለዋል።
በቀጠናው ያሉ ሀገራት የአሜሪካ ወታደሮች የተደበቁባቸውን ቦታዎች እንዲጠቁሙን እንጠይቃለን" ብለዋል።
(አዩዘሀበሻ)

የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር የመዲናዋን የወንዝ ዳርቻ ልማት ጎበኙአዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብ...
26/03/2026

የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር የመዲናዋን የወንዝ ዳርቻ ልማት ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ በአዲስ አበባ ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአዲስ አበባ የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን ፣ የመሰረተ ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

ከፎረሙ ጎን ለጎን፣ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል።

ማሪያ ትሪፖዲ በበኩላቸው የአመራር ጥበብ የታየበት የአዲስ አበባ ወንዝ ዳርቻ ልማት የከተማዋን ደረጃ የሚያሳድግ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ሁሉ አስደንቀውኛል ያሉት ምክትል ሚኒስትሯ፤ የወንዝ ዳርቻ ልማቱ ነዋሪውን ታሳቢ አድርጎ መሰራቱ ለሌሎች አረዓያነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የሚመራበትን መንገድ እና አሰራር አድንቀው፤ በከተማ ማደስ ስራው ውስጥ ሀገራቸው በትብብር የመስራት ፍላጎት እንዳላት ጠቁመዋል።

23/11/2025

ህዳር 14/2018
አጫጭር ዜናዎች

22/11/2025

ህዳር 13/2018
አጫጭር ዜናዎች

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክትከቱርክዬ ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በኢኮኖሚ፣ የባሕል ወዳጅነት ግንኙነት፣ ዘላቂ ልማት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያካትቱ የ...
22/11/2025

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከቱርክዬ ፕሬዝደንት ጣይብ ኤርዶዋን ጋር በኢኮኖሚ፣ የባሕል ወዳጅነት ግንኙነት፣ ዘላቂ ልማት፣ በአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን በሚያካትቱ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል።

ህዳር 13/2018
22/11/2025

ህዳር 13/2018

🐪 አዲስ ፈተና በአዲስ አበባ፡ የሕገ-ወጥ የግመል ስጋ ሽያጭ! በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ-ወጥ የግመል እርድና ስጋ ሽያጭ መስፋፋቱ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አዲስ ፈተና ሆኖበታል።ቁልፍ መ...
22/11/2025

🐪 አዲስ ፈተና በአዲስ አበባ፡
የሕገ-ወጥ የግመል ስጋ ሽያጭ!

በአዲስ አበባ ከተማ ሕገ-ወጥ የግመል እርድና ስጋ ሽያጭ መስፋፋቱ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አዲስ ፈተና ሆኖበታል።

ቁልፍ መረጃዎች

* የችግሩ ስፋት: የቄራዎች ድርጅት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ ሕገ-ወጥ እርዱ ከወትሮው በተለየ መልኩ እየጨመረ መምጣቱን አምነዋል።

* የሽያጭ አካባቢ:
በተለይም ወደ ቦሌ ሚካኤል ባሉ አካባቢዎች የግመል ስጋ በድብቅ አስገብተው የሚሸጡ" ግለሰቦች መኖራቸውን ተገልጿል።

* የጤና ስጋት: ሕገ-ወጥ እርድ የሚከናወነው አስፈላጊው የጤና ምርመራ ባልተካሄደበት እና ባልተፈቀደ ቦታ ላይ ሲሆን፣ ይህም የህብረተሰቡን ጤንነት አደጋ ላይ ይጥላል።

የቄራዎች ድርጅት ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለማስተካከል እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ሥራ አስኪያጁ ሕብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ ስጋ እንደሚፈልግ በመግለጽ፣ ሕገ-ወጥ የግመል እርድን ወይም ሽያጭን ሲመለከት ወዲያውኑ ጥቆማ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

ሕጋዊውና የጤና ምርመራ የተደረገበት የግመል እርድ በስፋት የሚካሄደው በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ በሚገኘው የቄራዎች ድርጅት ውስጥ ነው።

ይህ አገልግሎት ስጋውን በስፋት ለሚጠቀሙት የሶማሌ እና የአፋር ህዝቦች ተደራሽ እንዲሆን ታስቧል።

ድርጅቱ በአማካኝ በቀን ከ7 እስከ 10 የሚደርሱ ግመሎችን ሕጋዊ በሆነ መንገድ ያርዳል።

ጤናዎ በእጅዎ ነው! ሕገ-ወጥ ስጋ ከመግዛት ይጠንቀቁ እና ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ይወጡ።

Via አሐዱሬዲዮ

22/11/2025

ህዳር 13/2018

ከዛሬ ኀዳር 13 ምሽት እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ በአዲስ አበባ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች:በነገው እለት ለ25ኛ ጊዜ  የሚከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተ...
22/11/2025

ከዛሬ ኀዳር 13 ምሽት እስከ ነገ እኩለ ቀን ድረስ በአዲስ አበባ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች:

በነገው እለት ለ25ኛ ጊዜ የሚከናወነው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች:-

👉ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ )
👉ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ) ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ
👉ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጥይት ቤት መስቀለኛ )
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ኮንሰን መታጠፊያ (ፓርላማ መብራት )
👉ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ገብርኤል (ኮንሰን መታጠፊያ )
ከጥይት ቤት ወደ ገብርኤል በጀርባው (ጥይት ቤት መታጠፊያ )
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ )
👉ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ )
👉ከ22 አደባባይ ወይም ዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ )
👉ከፒኮክ አዲሱ መንገድ ወደ ዑራኤል አደባባይ (ፒኮክ መብራት)
👉ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል (ጋዜቦ አደባባይ)
👉ከቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ ወደ ለገሃር መብራት (ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ነርክ ተራ )
👉ከላንድ ማርክ ሆስፒታል መታጠፊያ ገነት ሆቴል ወይም ወደ ገነት መብራት (ላንድ ማርክ ሆስፒታል መስቀለኛ )
👉ከጠማማ ፎቅ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ጠማማ ፎቅ መስቀለኛ )
👉ከአፍሪካ ህብረት መብራት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ሜክሲኮ ጥይት ፋብሪካ መስቀለኛ )
👉ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ (ፈረሰኛ መብራት )
👉ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር (ጌጃ ሰፈር መስቀለኛ )
👉ከከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ (ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ)
👉ከሠንጋ ተራ 40/60 ወደ ሠንጋ ተራ መብራት (ሠንጋ ተራ 40/60 መታጠፊያ)
👉ከጎማ ቁጠባ መብራት ወደ ብ/ቲያትር (ጎማ ቁጠባ መብራት)
👉ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ፖስታ ቤት መብራት (ሜትሮዎሎጂ መታጠፊያ )
👉ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን (ጥቁር አንበሳ ሼል)
👉ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን (ጎላ ሚካኤል መስቀለኛ)
👉ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አገር አስተዳደር መብራት (ቴዎድሮስ አደባባይ)
ከንጋቱ 11:30 - ሰዓት ጀምሮ ውድድሩ እስከሚጠናቀቅ የተጠቀሱት መንገዶች የሚዘጉ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ መኪና ለአጭርም ይሁን ለረጅም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት 011 1110111 ወይም ነጻ የስልክ መስመር 991 መጠቀም እንደሚቻል ፖሊስ አስታውቋል።
(አ/አ ፖሊስ)

ህዳር 12 2018 የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ። ማህበሩ በዛሬ ዕለትም በይፋ ስራ መጀ...
22/11/2025

ህዳር 12 2018

የተለያዩ እና ብዙም ያልተለመዱ የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቶችን ይዤ መጥቻለሁ ሲል ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ተናገረ።

ማህበሩ በዛሬ ዕለትም በይፋ ስራ መጀመሩን በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።

ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ለሚዲያ እና ኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተለይ የፋይናንስ ድጋፍ የሚያገኙበት አማራጭ መያዙንም አስረድቷል።

የህብረት ስራ ማህበሩ በሴት የቦርድ አባላት የሚመራና በዘርፉ የረጅም ዓመት ልምድ ባካበቱ ባለሞያዎች የተቋቋመ መሆኑም አስረድቷል።

በዘርፉ አሁን ላይ እየተተገበሩ ከሚገኙ የብድር አገልግሎቶች በተለየ መልኩ አዳዲስ አሰራሮችን ይዞ መምጣቱን በመጠቆም ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነትን ታሳቢ ያደረገ ስለመሆኑም ተጠቅሷል።

በቡድን የሚመጡ ብድር ፈላጊዎች ልዩ የወለድ ቅናሽ እንዲያገኙ የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ እንደሚያደርግ፣ወላጆች ተማሪ ልጆቻቸው የት/ቤት ክፍያ ብድር እንዲያገኙ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከትምህርታቸው ጋር በተገናኘ የሚያስፈልጋቸውን ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ጠቁሟል።

ለህክምና፣ የውጪ ጉዞዎች የሚሆን ብድር ማህበሩ በልዩነት ይዟቸው ከመጡ ብድሮች መካከል መሆናቸውም ተነግሯል።

ከወለድ ነፃ ብድር በማመቻቸት የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ተዘጋጅቻለሁም ብሏል።

የሚዲያ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከሚሰሯቸው ስራዎች ጋር በተገናኘ የፋይናንስ ችግር ለስራቸው እንቅፋት እንዳይሆን ልዩ የብድር አገልግሎት ለመስጠት መዘጋጀቱን ማህበሩ ጠቅሷል።

ይህንንም ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ስምምነት የኪነ ጥበብና የሚዲያ ባለሙያዎች ከኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ጋር በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።

ህዳር 12/2018
21/11/2025

ህዳር 12/2018

Address

ADDIS ABABA TO DEBREZEIT Road
Addis Ababa

Telephone

+251921741429

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሰቃ / Beseka Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to በሰቃ / Beseka Tube:

Share