Fana Ethiopia

Fana Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fana Ethiopia, Advertising/Marketing, Addis Ababa.

03/06/2026

"ክህሎት የሌለው ህዝብ በዓለም ላይ በየጊዜው የሚከሰቱ ተጽዕኖዎችን መቋቋም አይችልም"

ዶ/ር አብዱላዚዝ ዳውድ

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ ለ7ኛ ዙር በአሰላ ከተማ በአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ "በሙያና በክህሎት የዳበረ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ የለማ፣ አስተማማኝ የስራ ዕድልና ለጋራ ብልጽግና የተዘጋጀ ትውልድ!" በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የነበረው የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የቢዝነስ ሃሳብና የተግባር ምርምር ውድድር በስኬት ተጠናቋል።

የውድድሩን አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ነስረዲን ቃዲ፤ ቢሮው የማህበረሰቡን የክህሎት ፍላጎት በማሳደግ የሰልጣኞችን ቅበላ እቅድ ለማሳካት በሁሉም የክልሉ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የክህሎት ፌስቲቫል ተግባራዊ ማድረጉን ገልጸዋል።

በተወዳዳሪዎች መካከል የፉክክር መንፈስ ከመፍጠር ባለፈ፣ ልምድ እንዲለዋወጡና የመነሳሳት ስሜት እንዲያድግ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል።

በውድድሩ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶ/ር አብዱላዚዝ ዳውድ፤ መንግስት የሙያና ቴክኖሎጂ አቅምን በማጠናከር የብልጽግና ጉዞውን ለማሳካት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

"ክህሎት የልማትና የብልጽግና መሰረት ነው" ያሉት ዶ/ር አብዱላዚዝ፣ ክህሎት የሌለው ህዝብ በዓለም ላይ በየጊዜው የሚከሰቱ ተጽዕኖዎችን መቋቋም ስለማይችል የክልሉ ማህበረሰብ ቢያንስ አንድና ከዚያ በላይ ሙያ ሊኖረው እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአሰልጣኞች፣ በሰልጣኞች፣ በኢንተርፕራይዞችና በፈጣሪዎች የሚሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በስፋት ተመርተው ወደ ኢኮኖሚው እንዲቀየሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

በውድድሩ ማጠቃለያም ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ለወጡ አሸናፊዎች የሽልማትና የዕውቅና አሰጣጥ የተከናወነ ሲሆን፤ በርካታ አሸናፊዎችን በማስመዝገብ የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር፣ የሰበታ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር እና የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ክላስተር እንደ ቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ በመውጣት የዋንጫና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ለፕሮግራሙ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ለኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ፣ ለኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት እና ለአርሲ ዩኒቨርሲቲ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።

ወደ ካናዳ ሰራተኛ መላክ ተጀምሯል ?" ገንዘብ አስከፍለዋቸው ተበልተው የመጡ ሰዎች አሉ " - ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴርኢትዮጵያውያንን ለሥራ እድል ተጠቃሚነት ወደ ካናዳ ለመላክ "ፊውቸር ፊ...
03/06/2026

ወደ ካናዳ ሰራተኛ መላክ ተጀምሯል ?

" ገንዘብ አስከፍለዋቸው ተበልተው የመጡ ሰዎች አሉ " - ሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር

ኢትዮጵያውያንን ለሥራ እድል ተጠቃሚነት ወደ ካናዳ ለመላክ "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" ከተሰኘው ድርጅት ጋር የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ ዜጎችን መላክ እንደተጀመረ በማስመሰል በሚያጭረብሩ አካላት ገንዘብ የተጭበረበሩ ሰዎች መኖራቸውን ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ፣ ከካናዳ "ቀረበልኝ" ባለው ጥያቄ መሰረት ወጣት ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ ለሥራ ለመላክ ከድርጅቱ ጋር በቅርቡ ስምምነት መፈራረሙ ይታወቃል።

ባለሙያዎቹን ወደ ካናዳ ለማሰማራት በመንግስት ፈቃድ የተሰጠው ብቸኛው ድርጅት "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል" መሆኑንና ከካናዳ ኤምባሲ ውጭ የቪዛ ወኪል እንደሌለ ሚኒስቴሩ በስምምነቱ ወቅት መግለጹ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ ስምምነቱ ከተፈጸመ በኋላ በርካቶች " ወደ ካናዳ እንልካችኋለን " በሚሉ አካላት የማይገባቸውን ገንዘብ እየከፈሉ እየተጭበረበሩ ናቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ መላክ ጀምራለች ? " እንልካችኋለን " በሚል ገንዘብ ስለሚያስከፍሉ አካላት ጥቆማ ደርሷችኋል ? ሲል በሚኒስቴሩ የውጪ ሀገር ሥራ ስምሪት የውል ምርመራ እና ማጽደቅ ዴስክ ኃላፊ አቶ በዛወርቅ ከተማን ጠይቋል።

አቶ በዛወርቅ " ወደ ካናዳ መላክ አልተጀመረም። ክፍያም የለም " ብለዋል።

" ስምምነት ተፈረመ እንጅ ወደ ካናዳ የሚልክ መንግስት የሚያውቀው እውቅና የሰጠው ኤጀንሲ የለም " ያሉት ኃላፊው፣ " ገና የመላክ ስራው አልተጀመረም፤ ሲጀመር መንግስት እከሌ የሚባል ኤጀንሲ ካናዳ ላይ ፈቃድ ወስዷል ብሎ ያሳውቃል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በዚህ ወቅት መላክ ስላልተጀመረ የሚልከው ህገወጥ ነው፤ ህገወጥ ላይ የሚሳተፍ ማህበረሰብ መኖር የለበትም። ክፍያም የለውም። ግን አብዛኛዎቹ አስከፍለው 'እንልካችኋለን' ብለው ነው ማስታወቂያ የሚያሰሩት። ይሄ ስህተት ነው " ብለዋል።

እያጭበረበሩ ያሉ ድርጅቶች፣ የተጭበረበሩ ዜጎች እንዳሉ ፈትሸው እንደሆነ ማብራሪያ የጠየቅናቸው ኃላፊው፣ " ገንዘብ አስከፍለዋቸው ተበልተው ወደዚህ (ወደ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር) የመጡ ሰዎች አሉ። ከፌደራል ፖሊስ ጋር ሆነን ገንዘብ የተቀበሉ ሰዎች ላይ ክትትል እየተደረገበት ነው። ጥቆማዎችም ይመጣሉ " ብለዋል።

" ተጭበረበርን " ብለው ያመለከቱት ዜጎች ብዛት ስንት እንደሆኑ ስንጠይቃቸው ግን ቁጥራቸውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

አቶ በዛወርቅ ከተማ ፥ ስምምነት ተፈረመ ማለት ባለሙያዎችን ወደ ካናዳ መላክ ተጀምሯል ማለት እንዳልሆነና ክፍያም እንደሌለው ገልጸው፣ ማህበረሰቡ ይህን እንዲገነዘብ አሳስበዋል።

ከካናዳ መንግሥት " 'ይሄን ስራ እንድትሰሩልኝ ባለሙያ ትልኩልኛላችሁ ወይ?' " የሚል ጥያቄ እንደቀረበላቸው ገልጸው፣ "መንግስትም 'አዎ፤ ባለሙያ አለን፤ እንልካለን የሚል ስምምነት ተፈራርሟል። ያ ማለት ግን መላክ ተጀምሯል ማለት አይደለም " ነው ያሉት።

አዲስ አበባ
👇👇👇👇👇
https://digital-skills-ethiopia.carrd.co/

" የተፈጠረውና የደረሰው ጉዳት በዝርዝር የሚጣራ ነው የሚሆነው " - ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በ143 ምርጫ ጣቢያዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት የምርጫ ሂደቱ መቋ...
02/06/2026

" የተፈጠረውና የደረሰው ጉዳት በዝርዝር የሚጣራ ነው የሚሆነው " - ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ በ143 ምርጫ ጣቢያዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት የምርጫ ሂደቱ መቋረጡን አሳውቆ ነበር።

የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ለሊት በሰጡት መግለጫ፤ በኦሮሚያ ክልል ባሉ ቢሎኖጳ ፤ መኮሳቺ ፤ ቀርሳ ምርጫ ክልሎች የጸጥታው ሁኔታ መሻሻል ባለማሳየቱ ምርጫው አለመካሄዱን ተናግረዋል።

" ቢሎኖጳ ችግሩ እንዳለ ስለሆነ መፈጸም ስላልቻለ በሚቀጥለው ቀን (ዛሬ) የድምጽ መስጠት ሂደቱ እንዲከናወን ነው ቦርዱ የወሰነው። መኮሳቺን በተመለከተ ችግሩ እንደቀጠለ ስላለ የድምጽ መስጠት ሂደቱ አልተከናወነም " ሲሉ ገልጸዋል።

በአማራ ክልል በጸጥታ ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የኩታበር ምርጫ ክልል፥ ከነበሩት 19 ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ 4ቱ አሁንም ምርጫ ሳይካሄድባቸው ሲቀር በ15ቱ ድምጽ መስጠት የሚያስችል ሁኔታ ስለተፈጠረ ምርጫ ማድረግ መቻሉን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

ሰብሳዊዋ የጸጥታ ችግር በተፈጠረባቸው አከባቢዎች ምን አይነት ጉዳት እንደደረሰ ተጠይቀው " የተፈጠረውና የደረሰው ጉዳት በዝርዝር የሚጣራ ነው የሚሆነው። ተቃጥሏል ፤ ወድሟል የሚለውን ዝርዝር የማጣራት ሥራ መሰራት አለበት ፤ የደረሰው ጉዳት ምን ያህል ነው ? ፤ ምንድን ነው ? የሆነው ምንድን ነው የተፈጠረው ? የሚለውን ማጣራት ስላለብን ባልተጣራ ነገር ላይ በዚህ ደረጃ መናገር ስለማይቻል እሱን ሙሉ ለሙሉ አጣርተን ምላሽ እንሰጣለን " ብለዋ።

አዲስ አበባ,Ethiopia

01/06/2026
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (ህብረት ለምርጫ) በዛሬው ዕለት የተካሄደውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ የነበረውን የትዝብት ሪፖርቱን ይ...
01/06/2026

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ (ህብረት ለምርጫ) በዛሬው ዕለት የተካሄደውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ የነበረውን የትዝብት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል።

ህብረቱ ከ3 ሺህ በላይ ታዛቢዎችን በመላ ሀገሪቱ ባሉ 2,258 ጣቢያዎች በማሰማራት ሂደቱን ሲከታተል መቆየቱን ገልጿል።

በሪፖርቱ መሰረት፣ በብዙዎቹ ጣቢያዎች የምርጫ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን፣ 99 በመቶ የሚሆኑት ታዛቢዎች ያለ ምንም ገደብ ወደ ጣቢያዎች ገብተው ስራቸውን ማከናወን ችለዋል ብሏል።

ሂደቱን ከሚያስፈፅሙ አካላት መካከል የሴቶች እና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎ የሚበረታታ መሆኑም አመልክቷል።

በተለይም በ61 በመቶ ጣቢያዎች ከአንድ በላይ ሴት አስፈፃሚዎች የተመደቡ ሲሆን፣ በ26 በመቶ ጣቢያዎች ደግሞ ሴቶች በኃላፊነት እየመሩ መሆናቸው በሪፖርቱ ተካቷል።

ሆኖም ህብረቱ በሂደቱ ላይ የታዩ በርካታ አሳሳቢ ግድፈቶችንና የፀጥታ ችግሮችን ይፋ አድርጓል።

በሪፖሩቱ መሰረት በአማራ ክልል ፦
- ማዕከላዊ ጎንደር (አምባ ጊዮርጊስ)፣
- ሰሜን ወሎ (መቄት)
- በደቡብ ጎንደር (ፋርጣ እና ደብረ ታቦር) አካባቢዎች በተሰማ የተኩስ ድምፅ ምክንያት የምርጫ ሂደቱ ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።

በአንዳንድ ቦታዎች አስፈፃሚዎች ጣቢያዎችን ዘግተው ለመውጣት መገደዳቸው ህብረቱ ታዝቧል።

በአዲስ አበባ እና በሀዋሳ አንዳንድ ጣቢያዎች የብልፅግና ፓርቲ ወኪሎች የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ መታዘባቸውን ህብረቱ ገልጿል።

በተጨማሪም በሀዋሳ ቱላ ወረዳ የቀበሌ አመራሮች ወደ ድምፅ መስጫ ሳጥን ድረስ በመሄድ መራጮችን ሲያስገድዱ እንደነበር በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

ማህተም ያልተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች መታደል፣ የድምፅ መስጫ ሳጥኖች ባዶ መሆናቸው ሳይረጋገጥ መታሸግ እና ታዛቢዎችን ወደ ጣቢያ እንዳይገቡ የመከልከል ሁኔታዎች በተወሰኑ ጣቢያዎች ታይተዋል ብሏል።

የምርጫ ጣቢያዎች በጤና ተቋማት እና በሆስፒታሎች ግቢ ውስጥ (ለምሳሌ ሳቢያን ሆስፒታል) መቋቋማቸው በምርጫ ህጉ መሰረት የተከለከለ ቢሆንም፣ በተግባር ግን ታይቷል ብሏል ህብረቱ።

ህብረት ለምርጫ እስከ እኩለ ቀን 203 አሳሳቢ ሁኔታዎችን የተቀበለ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 40ዎቹ መረጋገጣቸውንና ቀሪዎቹ 163 ጉዳዮች በማጣራት ሂደት ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

ዝርዝር መረጃዎችን የያዘው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በሚቀጥሉት ሁለት እና ሶስት ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም ህብረቱ በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ/ም
https://digital-skills-ethiopia.carrd.co/

ፊትን እና የመኪና ሰሌዳን መለየት የሚችሉ የደህንነት ካሜራዎች የሚሰበስቡት መረጃ ደህንነት ጉዳይ ? የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በ...
24/04/2026

ፊትን እና የመኪና ሰሌዳን መለየት የሚችሉ የደህንነት ካሜራዎች የሚሰበስቡት መረጃ ደህንነት ጉዳይ ?

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለህግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርቦ ነበር።

ኢንስቲትዩቱ " የከተሞችንና የተቋማትን ደህንነት መጠበቅ የሚያስችሉ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በማልማት ለከተሞች እና ለተቋማት የደህንነት ካሜራዎችን በመዘርጋት ላይ መሆኑን " በሪፖርቱ ጠቅሷል።

የቴክኖሎጂው ተደራሽነት የሚበረታታ መሆኑን የጠቀሰው ቋሚ ኮሚቴው ከእነዚህ ካሜራዎች የሚሰበሰቡ መረጃዎች ደህንነት ጉዳይ እንዴት ይጠበቃል የሚለው ጉዳይ ላይ ጥያቄ አንስቷል።

ካሜራዎቹ የሚሰበስቡት የሰዎች የፊት ገጽታ እና ሌሎች የግል መረጃዎች ለሌላ ዓላማ እንዳይውሉ እና ከሳይበር ጥቃት የተጠበቁ እንዲሆኑ ምን አይነት ቴክኒካል እና ህጋዊ የዲጂታል ስነ-ምግባር (AI-Ethics) ማዕቀፍ ተዘርግቷል ? የሚል ጥያቄ ተነስቷል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና(ዶ/ር) ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተዘረጉ ያሉ የደህንነት ካሜራዎችና የመረጃ አሰባሰብ ስራዎች የዜጎችን የግል ነጻነት በማይነካና በቴክኖሎጂ በታገዘ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ስር እንዲከናወኑ እየተደረገ መሆኑን ገለጸዋል።

በከተሞችና በተለያዩ የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚዘረጉ የፊት ገጽታንና የተሽከርካሪ ሰሌዳን መለየት የሚችሉ ዘመናዊ ካሜራዎች ተልዕኮ ፤ በሀገሪቱ የጸደቁትን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲና የግል መረጃ ጥበቃ ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

በካሜራዎቹ አማካኝነት የሚሰበሰቡ መረጃዎች ለታለመላቸው ልዩ ዓላማዎች ብቻ እንዲውሉ የሚደረግ ሲሆን፣ መረጃዎቹን የማግኘትና የመጠቀም መብት (Access) ለፌዴራል ፖሊስና ለተመሳሳይ ህጋዊ ሃላፊነት ለተሰጣቸው ተቋማት ብቻ የተገደበ ነው።

ይህም መረጃዎች በግለሰቦች እጅ እንዳይገቡና ለተሳሳተ ዓላማ እንዳይውሉ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው አመላክተዋል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fana Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share