16/09/2026
?
የቴፕ ማጫወቻው ምርጫ የለውም፤ የጫኑበትን ዘፈን ያንጎራጉራል፣ የከተቱበትን መዝሙር ያዜማል። የሰዉም ልጅ አእምሮ እንዲሁ ነው። የሰነቅነውን ነው የሚተፋው፣ የሞላነውን ነው የሚያፈሰው።በቀን ውሎአችን ውስጥ ወደ አእምሯችን የምናስገባቸው ነገሮች ሁሉ በውስጣችን ተቀርጸው ይቀራሉ። በኋላ ላይ በንግግራችን፣ በባህሪያችንና በህይወት ምርጫችን ላይ ተጽዕኖ ማድረጋቸው አይቀሬ ነው።
ስለዚህ፦አእምሮህን በንጹህ ሃሳብ አስውበው።ጆሮህን ከማይጠቅም ወሬ ጠብቅ።አይንህን መልካም ነገር ላይ አሳርፍ።ምክንያቱም አንተ ማለት አእምሮህ ውስጥ የጫንከው ሃሳብ ውጤት ነህ!