16/09/2026
መሪዎችን አለመደገፍ ሕዝብን አለመደገፍ ነው !
~~~~//~~~~
በርካታ የክልልችን ወጣቶች ለዚህ ለውጥ ዋጋ ከፍለዋል። የተከፈለውን ዋጋ የተረዱ የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉና በህይወት ኖረው በጀግንንት እየመሩ ያሉ የአማራ ተወላጅ መሪዎች አሉን፡፡
ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ... እንዳንል ማንነት በሥራ እንጂ በስም ብቻ አይገለጽም ። መሪዎቻችን በማህበራዊ ሚዲያ ግንባር ቀርቶ በአውደ ውጊያው ግንባር ግንባራቸውን አላጠፉም።
ኢትዮጵያን ለግምሽ ምዕተ አመት ከተሰራባት ሴራ ለማውጣት እየሰራና እየተሳካለት ያለ የብልጽግና ፓርቲን መሪ መሆን ኩራት፣ አሁን ደግሞ ጀግንነት ነው።
ይህ በተደጋጋሚ የሚሞከር የአማራን ሕዝብ ያለ መሪ የማስቀረት የማይሳካ ሴራ ነው። እነዚህ እንደ ማንኛውም የአማራ ክልል አመራር እንደ ወርቅ በዕሳት የተፈተኑ ጀግኖች ሆነው ሳለ ነጥሎ የማጠልሸት የተለመደ ቅሌት እንጂ ሰሚ የለውምና አትድከሙ !