Ephrem Mekete

Ephrem Mekete Graphics Designer and Social Media Marketer
i help businesses to build a strong brand

ሰበር ዜና‼️አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ የ150 ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።ወደ ህዳሴ ግድብ መገንጠያ እንጅባራ ከተማ ለተገኘችው ...
26/08/2026

ሰበር ዜና‼️
አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገበችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ የ150 ሺህ ብር የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።

ወደ ህዳሴ ግድብ መገንጠያ እንጅባራ ከተማ ለተገኘችው ለጀግናዋ ታሪክ ሰሪ ህዳሴ ዘመኑ አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል የ150 ሽህ ብር የገንዘብ የማበረታቻ ሽልማት አበርክቶላታል።

በአማራ ክልል፣ በአዊ ብሄ/አስ እንጅባራ ከተማ የተገኘችው የአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ከቀረቡበት 600 ጥያቄዎች ውስጥ 583 ያህሉን በትክክል በመመለስ አስደናቂ ውጤት አስመዝግባለች።

ነገሩ እንዲህ ነው የአገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤት አያና ስማቸው(ዶ.ር) በ2017 ዓ.ም በአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሀገራዊ የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ባበረታቱበት ወቅት አንድ ቃል ገብተው ነበረ።

ሕዳሴ ዘመኑን ጨምሮ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች በተገኙበት "በ2018 የውጤት ሪከርድ ለሚሰብር የ50ሽህ ብር የገንዘብ ሽልማት እሰጣለሁ " በማለት ቃል ገብተው ነበር ።

ዶር አያና ስማቸው ቃላቸውን ጠብቀው ለዚች የሀገር ኩራት ለሆነችው የከፍተኛ ውጤት ሪከርዷ ባለቤት ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ ቤተሰቦቿ በተገኙበት፤ ባለቤታቸውና የሆስፒታሉ ምክትል ሥራ አስኪያጅ በሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ገነቱ በኩል የ150 ሺህ ብር ሽልማት አበርክተውላታል።

​ይህ የተመዘገበው የላቀ ውጤት፤ በዘመኑ የፈተና ታሪክ ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሴቶች አንደኛው እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ በጠባብ ውጤት ልዩነት ሦስተኛው ከፍተኛ ውጤት ሆኖ የተመዘገበ ነው። ይህም በመንግሥት ትምህርት ቤት በመማር በተማሪዋ ጠንካራ የጥናት ባህልና በትምህርት ላይ ባላት ከፍተኛ ትጋት የተገኘ ውጤት መሆኑን የሚያሳይ ነው።

ተማሪዋ ከሷ በፊት ከፍተኛ ውጤት እንዳስመዘገቡት ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤት ብትማር ኖሮ ከዚህ የበለጠ ውጤት ታስመዘግብ እንደነበር የታመነ ነው።

የተማሪ ህዳሴ ዘመኑ ስኬት ለተማረችበት አገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ለብሄረሰብ አስተዳደሩ እንዲሁም ለመላው የአማራ ክልል ትልቅ ኩራትና ለቀጣይ ተፈታኞችም አርአያ በመሆን አዎንታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ ተጠቅሷል።

ህዳሴ ዘመኑ በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሳይንስ (Natural Science) ዘርፍ 583. (97.17% አቨሬጅ) በሴቶች አንደኛ በማስመዝገብ አስደማሚ ውጤት አምጥታለች!

የአገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤት ትግስት አገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እንደዚህ አይነት የጥራት እና የስኬት ማሳያ የሆነች ጀግና ተማሪ በማፍራቱ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል ለህዳሴ ዘመኑ እና ለቤተሰቦቿ ታላቅ ኩራቱን እየገለጸ፣ ለቀጣይ የዩኒቨርሲቲ ህይወቷ የላቀ ስኬትን ተመኝተዋል።

ተቋሙ ወደፊትም በሚያስፈልጋት ቦታና ጊዜ ሁሉ እንደማይለያት ቃል ገብቷል።
//ከሆስፒታሉ ፌስቡክ ፔጅ የተወሰደ//

18/08/2026

መርካቶ በአጇኳሚዎች ወይም በአክሲዮን ሸቀጣቸውን የሚሸጡ አሉ:: Say ጫማ እና ልብስ የሚሸጡ አስር ሰዎች ካሉ ይ70ሰቡና አንዱ ሻጭ ዘጠኙ ደግሞ ገዢ መስለው ይተውናሉ:: ትልቅዬ ሴትዮ, ሽማግሌ, ዘናጭ ወዘተ ሆነው ሳያስፎግሩ ይተራመሳሉ:: ሰው ደግሞ ግርግርና ቫይራል ነገር ስለሚወድ የእውነት እየመሰለው ተሻምቶ ይገዛል:: ዋጋ እየተከራከርክ አንዱ አጇኳሚ ቀድሞህ ይከፍላል:: ተናደህ ሌላ ተቀራራቢ እቃ አንስተህ ሳትከራከር ትከፍላለህ:: መወጋ^ትህን የምታውቀው ቆይተህ ከሳምንት በሗላ ነው:: ብዙ አክሲዮኖች እንደዚህ ናቸው:: ለአክሲዮኑ ስትከፍል ነገውኑ ትርፍ የምታገኝበት የሚያስመስል ማስታወቂያና የትርፍ ግርግር ታያለህ:: ከሦስት ዓመት በሗላ መግዛትህን ለመርሳት ነው የምትታገለው:: ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ግማሽ ሊትር ውኃና ኩኪስ በልተህ ትበተናለህ:: ከጠቅላላ ጉባዔው መድረክ ችግሮች ለምን እንደተፈጠሩ, ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈሉና እንዴት ያለ ምርጥ መጻዒ ዕድል እንዳላቸው ይደሰኮርልሃል:: እያለ እያለ ይቀጥላል::
Abdulkadir Hajj Nureddin

የኛ ሀገር ላይ እውቀትና አቅም ያላቸው ሰዎች አይበረክቱልንም፡፡አቶ ተወልደ የህንድ አየር መንገድን እንዲመሩ ተመርጠዋል አሉ፡፡ወርቅህን ለሰው አሳልፈህ መስጠት ማለት ይህ ነው፡፡
06/08/2026

የኛ ሀገር ላይ እውቀትና አቅም ያላቸው ሰዎች አይበረክቱልንም፡፡አቶ ተወልደ የህንድ አየር መንገድን እንዲመሩ ተመርጠዋል አሉ፡፡
ወርቅህን ለሰው አሳልፈህ መስጠት ማለት ይህ ነው፡፡

06/08/2026

ንብረት መያዝ ቪትዝ ሊያስተምረን አይገባም ነበር:: አምና አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር የነበረ ቪትዝ ዘንድሮ ሁለት ነጥብ ስድስት ብር ሲደርስ ምን ያህል ያበደ ገበያ እንዳለን ያሳያል:: ይህ የሚያሳየው አንድ ተፈጥሯዊ ጉዳይ አለ:: ሕዝባችን ብዙ በመሆኑ ከአቅርቦት ውጭ ሕግ አይገድበውም:: ንብረት ላይ ማተኮር ሁሌም አዋጭ ነው::

ከዚሁ ጋር በማያያዝ ባንኮች ለደሃ አያበድሩም:: ከባንክ ውጭ ብድር ጣጣው ብዙ ነው:: ለመበደር ደግሞ ትርፋማ ቢዝነስ እና ማስያዣ ሳይነጣጠሉ ባንድነት መገኘት አለባቸው:: ሚስት ስታገቡ ይህንን ሲስተም ያልገባት ከሆነች in near future ድህነት ያፋታችሗል:: ሲስተሙ double edged sword 🗡️ ነው:: ባንክ ስታስቀምጥ 20% ግሽበት, ስታወጣው 15% ቫት ይበላዋል:: አንጡራ ብርህን ንብረት ላይ አድርገህ በሞኝ ብር ስትሠራ ሰይፉን አንተ ነህ የምትይዘው::
Abdulkadir Hajj Nureddin

05/08/2026
02/08/2026

እጅግም መወደድ እጅግም መጠላት ሁለቱም ያስፈራል
በመወደድና በመጠላት መሀል መረሳት ይሻላል
/ዳዊት ፀጋዬ/

02/08/2026

ምን ተረዳችሁ?

Address

Bahir Dar
Bahir Dar
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ephrem Mekete posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share