የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication

  • Home
  • Ethiopia
  • Butajira
  • የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication This is The official Butajira City Gov't COMM.fb page-ይህ ትክክለኛው የቡታጅራ ከተማ የመንግስት ኮሙኒኬሽን (fb)ፔጅ ነው፦
(1)

የኢትዮጵያውያን የሥነ ልቦና ትሥሥር የሚገለጥበት የመስቀል በዓል ********************** የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ በዓላት መካከል በተ...
27/09/2026

የኢትዮጵያውያን የሥነ ልቦና ትሥሥር የሚገለጥበት የመስቀል በዓል
**********************

የመስቀል በዓል በኢትዮጵያ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊ፣ ታሪካዊ እና ባህላዊ በዓላት መካከል በተለየ መልኩ የኢትዮጵያውያን የሥነ ልቦና ትሥሥር የሚገለጥበት በዓል ነው።

በዓሉ ወቅታዊውን የክረምት ማብቃት እና የመጸው መባቻን ተከትሎ የሚከበር በመሆኑ፣ የተፈጥሮን መታደስ ከሃይማኖታዊ እና ማኅበራዊ እሴቶች ጋር አዋህዶ የያዘ ልዩ መገለጫ አለው።

በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ መልክዓ-ምድር ውስጥ ሲቃኝም፣ እያንዳንዱ ብሔር እና ማኅበረሰብ የራሱን ሀገር በቀል ባህል፣ ዜማ እና ሥነ-ሥርዓት አዋህዶ የሚያከብርበት የሕብረ ቀለም መድረክ ነው።

በሰሜኑ በማዕከሉ የኢትዮጵያ ክፍል በዓሉ በዋናነት በሊቃውንት ያሬዳዊ ወረብ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ያዕቆባዊ ዜማ፣ በካህናት ያጌጠ አልባሳት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት በደመራ ማበራት ይጀመራል። የደመራው መውደቂያ አቅጣጫ ለወደፊቱ ዘመን ሰላም፣ ምርት እና በረከት ትንቢታዊ ምልክት ተደርጎ ይጠናቀቃል።

በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍል ደግሞ የራሱ የሆነ መገለጫ አለው፤ ለምሳሌ በጉራጌ ሕዝብ ዘንድ መስቀል የዓመቱ ታላቅ ማኅበራዊ እና ባህላዊ በዓል ሲሆን በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖሩ የማኅበረሰቡ አባላት ወደ ትውልድ ቀያቸው የሚመለሱበት፣ የጋራ ማዕድ የሚቀርብበት፣ ባህላዊው ክትፎ እና የቡልጉ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወንበት ነው።

ከሁሉም በሀገር ሽማግሌዎች አማካኝነት ባለፉት ዓመታት የተፈጠሩ ቂሞች እና አለመግባባቶች የሚታረቁበት የሰላም መድረክ ሆኖ ያገለግላል።

በወላይታ እና ጋሞ መስቀል የዘመን መለወጫ፣ የምርት መሰብሰቢያ እና የአዲስ ተስፋ መባቻ ነው። በበዓሉ የከብት እርድ፣ ባህላዊ ጨዋታዎች እና የትውልድ መስተጋብር በሰፊው ይከናወንበታል።

በምሥራቅ እና ምዕራብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች ደመራ ማብራት ከተፈጥሮ መታደስ፣ ከአካባቢ ጥበቃ እና ከማኅበራዊ ደስታ ጋር ተያይዞ ይከበራል። በየአካባቢው ያሉ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች በጋራ በመሆን የደመራ እንጨት ይሰበስባሉ፤ በደስታ እና በባህላዊ እልልታ በዓሉን ያደምቁታል።

ይህ የሚያሳየው በዓሉ በብዝኃነት ውስጥ ያለ አንድነትን በግልጽ የሚያንጸባርቅ ማኅበራዊ ተቋም መሆኑን ነው።

የመስቀል በዓል የየማኅበረሰቡ ልብስ፣ ባህላዊ ምግብ፣ ዜማ እና ውዝዋዜ ጎን ለጎን የሚታዩበት በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን የሌላውን ባህል እንዲያውቁ፣ እንዲያከብሩ እና እንዲወዱ ያደርጋል።

ምንም እንኳን ሃይማኖታዊ መሠረት ያለው ቢሆንም፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ እሴቱ ግን የተለያየ እምነት ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በጋራ ማዕድ፣ በደስታ እና በወዳጅነት ያስተሣሥራል።

ከሁሉም የሀገራችን ማዕዘናት የሚሰበሰቡ ማኅበራዊ እሴቶች ኢትዮጵያዊነት በጋራ በተገነቡ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ሃብቶች ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያረጋግጣሉ።

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊ ይዘቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የኢትዮጵያውያን ማኅበራዊ ካፒታል፣ የሰላም ግንባታ መሣሪያ እና የኅብረ-ብሔራዊ አንድነት ማተም ነው።

በዓሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ሀገር በቀል እሴቶች ተስፋን፣ ዕርቅን እና ወንድማማችነትን እንዴት ማደስ እንደሚችሉ የሚያሳይ ሕያው የመደመር ምስክር ነው።

EBC

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር በወራቤ ከተማ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት አስረከበ ((መስከረም 17/2019)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽህፈት ቤት በክ...
27/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር በወራቤ ከተማ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት አስረከበ

((መስከረም 17/2019)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሴቶች ማህበር ጽህፈት ቤት በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት ሙሉ የቤት እቃ አሟልቶ አስመርቆ አስረክቧል።

የክልሉ የሴቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ፎዚያ መሀመድ እንደገለጹት፤ ማህበሩ ልዩ ልዩ አካላትን በማስተባበር የተቸገሩ ወገኖችን ችግር የሚያቀልሉ በርካታ የበጎ ተግባር ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

የስልጤ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አማን ከድር በበኩላቸው፤ በክረምቱ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በዞኑ ከ605 በላይ ቤቶች ለአቅመ ደካሞች እየተገነቡ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ማህበሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቤቱን ገንብቶ ሙሉ እቃ በማሟላት ላስረከበበት በጎ ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

አዲስ ቤት ከተረከቡት መካከል ወ/ሮ ሀቢባ ነስሬ፤ ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረው ጎጆ በማርጀቱ ለዝናብና ለፀሐይ ተጋልጠው ይኖሩ እንደነበር አስታውሰው፣ የተደረገላቸው ድጋፍ ከነበሩበት ዘመናት የተሻገረ ችግር በመገላገሉ ትልቅ ደስታ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
(የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

በበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ድርብ ድል ተቀዳጁ *************************** በ2026 የበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለ...
27/09/2026

በበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ፆታዎች ድርብ ድል ተቀዳጁ
***************************

በ2026 የበርሊን ማራቶን የሴቶች ውድድር አትሌት ትዕግስት አሰፋ ለሦስተኛ ጊዜ ባለድል ሆናለች። በርቀቱ የዓለም የክብረ ወሰን ባለቤቷ አትሌት ትዕግሥት፣ ውድድሩን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ04 ሴኮንድ ወስዶባታል።

በተመሳሳይ ከደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የ2026 በርሊን ማራቶን የወንዶች ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ጉዬ አዶላ ባለድል ሆኗል። በ2021 የውድድሩ አሸናፊ የነበረው አትሌት ጉዬ ዛሬ በድጋሚ ባለድል ሲሆን፣ ርቀቱን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ51 ሴኮንድ ወስዶበታል።

በወንዶች ማራቶን ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ገመቹ ዲዳ 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ፣ ታንዛኒያዊው ጋብርኤል ጌራልድ ጊዬ 3ኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን አጠናቅቋል።

EBC

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃትየኢትዮጵያ አዲስ አመት መባቻ አብሳሪው ወር መስከረምና ቱሪዝም ልዩ ቁርኝት አላቸው። በየአመቱ መስከረም 17 ላይ በልዩ ልዩ ሁነቶች በአለም...
26/09/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት

የኢትዮጵያ አዲስ አመት መባቻ አብሳሪው ወር መስከረምና ቱሪዝም ልዩ ቁርኝት አላቸው። በየአመቱ መስከረም 17 ላይ በልዩ ልዩ ሁነቶች በአለም ዙሪያ ታስቦ የሚውለው የአለም ቱሪዝም ቀን ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በአዲስ መልክ ከተደራጀበት ጊዜ ጀምሮ በቱሪዝሙ ዘርፍ መሰረታዊ ለውጥ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

ከጢያ አለም አቀፍ መካነ ቅርስ ጀምሮ ሁሉንም አይነት አስደናቂ የቱሪዝም አማራጮች አካቶ የያዘው ክልሉ ይህን ዘርፍ በማጎልበት ሁነኛ የኢኮኖሚ አቅም፣ የስራ እድል ምንጭና ለአካባቢው ገጽታ ግንባታ ቁልፍ መሳሪያ አድርጎ ባደረገው የተቀናጀ ጥረት አመርቂ ውጤት አስመዝግቧል ።

የዘርፉን እምቅ አማራጮች በተለያዩ ዘዴዎች ለአለም ማህበረሰብ ከማስተዋወቅ ባለፈ እነዚህን አማራጮች በማልማት የገቢ ምንጭ በማድረግ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ይገኛል ።

ዘርፉ ለበርካታ ወገኖች በተለይም ለወጣቱ የስራ እድል እንዲፈጥርም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ቁልፍ ተብለው በተለዩ የቱሪስት መስህቦች ላይ ወሳኝ መሰረተ ልማቶች እየተሟሉ ነው።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በእነዚህ የቱሪዝም ዘርፍ ልማት ጥረቶች ከኢፌዴሪ የቱሪዝም ሚኒስቴር እውቅና ተሰጥቶታል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቱሪዝም ዘርፍ የተሻለ አፈጻፀም ላሰመዘገቡ የክልል የዘርፉ ቢሮዎች እውቅና በሰጠበት መድረክ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በቱሪዝም ዘርፍ ባስመዘገበው አመርቂ ውጤት ሶስተኛ በመውጣት እውቅና አግኝቷል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር በያዝነው በጀት አመት ለሪፎርም ሥራዎችና ለአዲሱ የቱሪዝም ፖሊሲ ትግበራ የሚያግዙ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በተለይም ለፖሊሲው ትግበራ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በማጠናከር፣ ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በዘርፉ ማስፋፋት እንዲሁም የቱሪስቶችን ደህንነት በማጠናከር እና የአደጋ ጊዜ የቱሪዝም መረጃ ሥርዓትን ማቋቋም ላይ እንደሚሰራ አስታውቋል ።

ይህም ብቻ ሳይሆን እንደ ሀገር “አንድ ወረዳ አንድ መዳረሻ” በማልማት ዘርፉን ይበልጥ ለማጎልበትና የቱሪስት መዳረሻዎችንና አማራጮችን ለማስፋት በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከሀገራዊ አቅጣጫ መነሻ ዘርፉ በስኬት ታጅቦ የህዝብን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ በልዩ ትኩረት የሚሰራ ይሆናል።
(የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

26/09/2026

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ ፦
መስከረም 16/2019

የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያን የብሩህ ተስፋ፣የይቅርታ፣የመገናኛ፣አዲስ ተስፋ እና ልምላሜ የሚስተዋልበት ወቅት ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)(መስከረም 16/2019 )በማዕ...
26/09/2026

የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያን የብሩህ ተስፋ፣የይቅርታ፣የመገናኛ፣አዲስ ተስፋ እና ልምላሜ የሚስተዋልበት ወቅት ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(መስከረም 16/2019 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን በደቡብ ሶዶ ወረዳ የመስቀል ደመራ ስነ ስርዓት በድምቀት ተከብሯል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በደመራ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያን የብሩህ ተስፋ፣የይቅርታ፣የመገናኛ፣አዲስ ተስፋ እና ልምላሜ የሚስተዋልበት ወቅት ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል ከሀይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ በህብረተሰቡ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር በማጠናከር ረገድ የጎላ አበርክቶ አለው በማለት አብራርተዋል።

የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሀይማኖታዊ እና በባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በድምቀት መከበሩ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው እንዲነቃቃ ምክንያት መሆኑን አመላክተዋል።

ወርሀ መስከረም በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከዘመን መለወጫ ጀምሮ የተለየ ግምት የሚሰጠው እና ህብረተሰቡ እርስ በርስ የመረዳዳት እሴቶቹን የሚያጎለብትበት ነው ብለዋል።

መስቀል ማህበራዊ መስተጋብሮቻችን እንዲጎለብቱ እድል ከመፍጠር ባለፈ ህብረተሰቡ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ወቅት ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በዓለ መስቀሉን ስናከብር የበጎነት፣ የመደጋገፍ፣ የአብሮነት እና የፍቅር እሴቶችን በማጠናከር ፤ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በማበረታታት መሆን ይኖርበታል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ጠቁመዋል።

ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች ብርሃነ መስቀሉ፣ የበረከት፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
(የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተከበረ።የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣ዘማሪያን እና ዲያቆናት ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የክርትና እምነት ተከታ...
26/09/2026

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ በድምቀት ተከበረ።

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ የሀይማኖት አባቶች፣ዘማሪያን እና ዲያቆናት ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የክርትና እምነት ተከታይ ምዕመን በተገኙበት በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎችና ስርዓቶችን በመፈፀም በድምቀት ተከብራል።

የምስራቅ ጉራጌና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ ኢጵፋኒዮስ በዓሉ የሰላም የበረከት እና የመጠያየቅ በዓል ይሁን ብለዋል።

በዓሉን ሀይማኖቱ በሚፈቅደው ስርዓት ማክበር ሌሎችን በመደገፍና ያለን በማካፈል ማክበር ይገባልም ብለዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ እንኳን ለዚህ ታላቅ፣ ውብና በሀገራችን በልዩ ክብር ለሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመስቀል በዓል የፍቅርን እና አብሮነትን እንዲያጠናክርልን፣ በቤተሰቦቻችን ደስታን፣ በሥራችን ስኬትን፣በሀገራችን ሰላምንና ብልጽግናን እንዲያመጣልን ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።

ዛሬ በዚህ ስፍራ የተሰባሰብነው አንድ ታላቅ በዓልን ለማክበር ብቻ ሳይሆን፣ ትውፊታችንን፣ባህላችንን፣እሴቶቻችንንና አብሮነታችንን ለማጠናከርና ለማስቀጠልም ነው።

መስቀል በሀገራችን ከሃይማኖታዊ ትርጉሙ ባሻገር የብዙ ትውልዶች ታሪክ፣ ባህልና የጋራ እሴት መገለጫ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ በዓል የእርስ በርስ መደጋገፍን፣መተሳሰብን፣ ይቅርባይነትንና አብሮ መኖርን የሚያጠናክሩ እሴቶችን የምናድስበት ወቅት ነው።

በተለይም ዛሬ ከምንጊዜውም በላይ ሰላምና አንድነ የሚያስፈልገን በመሆኑ የበዓሉን መልእክት በተግባር ልንኖረው ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።

በዓሉን ስናከብር የአካባቢያችንን ሰላም እንጠብቅ፣ ለእንግዶቻችንን ክብር እንስጥ፣ የሀገራችንን እሴቶች እናክብር በማለትም ጥሪ አቅርበዋል።

የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የአብሮነት በዓል ይሁን በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በዓሉን በመረዳዳት በደግነትና በአብሮነት የተቸገሩትን በመርዳት በመጠየቅና ደስታን በማጋራት በጋራ ማክበር ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የመስቀል በዓል በሀገራችን ከሚከበሩ ትላልቅ ሀይማኖታዊ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን ትልቅ ትርጉም ያለው የሰላም ፣የደስታ ፣የአብሮነት፣ የእርቅና የፍቅር በዓል ነው።

ከንቲባ አቶ አብዱ አያይዘውም በከተማዋ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ኢንቨስት የተደረገባቸው የተለያዩ ካፒታል ፕሮጀክቶችን በማስገንባት ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ነገን ታሳቢ ያደረጉ የሁላችንንም ጥረትና ተሳትፎ የሚጠይቁ ተጨማሪ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለመስራት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።

የተሰሩ ውጤታማ ስራዎች የህዝባችን ጥረትና ተሳትፎ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የከተማዋ ትልቁ ሀብት "ሰላም " መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ አቶ አብዱ ሰላምን አብሮነትን አጠናክሮ በማስቀጠል ዘላቂ ልማትና እድገትን ማረጋገጥ አለብን ሲሉም ገልፀዋል።

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ በምስል፦
26/09/2026

የመስቀል ደመራ በዓል በቡታጅራ ከተማ በምስል፦

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር ቆይቷል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) (መስከረም 16/2...
26/09/2026

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር ቆይቷል:-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

(መስከረም 16/2019 )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስቀል በጉራጌ ልዩ የበአል ዝግጅት በደቡብ ሶዶ ወረዳ ተከብሯል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት መስቀል ለጉራጌ ማህበረሰብ ልዩ በዓል ነው ብለዋል።

ጉራጌም ለመስቀል ልዩ መሆኑን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ያስታወቁት።

የጉራጌ ማህበረሰብ የመስቀል በዓልን ሀይማኖታዊ ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ሳይለቅ ለረጅም ዘመናት በድምቀት ሲያከብር መቆየቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰዋል።

ለበዓሉ የ11 ወራት ዝግጅት በማድረግ መከበሩ በህብረተሰቡ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ መስተጋብር በማጠናከር ረገድ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው አስታውቀዋል።

መስቀል መላው የጉራጌ ልጆች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ተሰባስበው ቤተሰቦቻቸውን የሚጠይቁበት እና እርስ በእርስ የሚደጋገፉበትን እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል።

የመስከረም ወር በጉራጌ ማህበረሰብ ዘንድ ከዘመን መለወጫ ጀምሮ ወደየ አካባቢው በመምጣት ቤተሰቡን የሚያገለግልበት፣እርሻውን የሚያቃናበት፣ቤቶቹን የሚያድስበት፣ልጆቹን ለትዳር የሚያዘጋጅበት እንዲሁም ፈጣሪን የሚያመሰግንበት ወቅት ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ በአብነት ጠቅሰዋል።

በዚህ ጊዜ ተሰባስበን ፈጣሪን እንድናመሰግን ለረዳን አምላክ ምስጋና ማቅረብ ተገቢ ነው ብለዋል።

የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሀይማኖታዊ እና በባህላዊ ይዘቱን ሳይለቅ በድምቀት የሚከበር በዓል ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

የመስከረም ወር ለኢትዮጵያውያኖች የብሩህ ተስፋ፣የይቅርታ፣የመገናኛ፣አዲስ ተስፋ እና ልምላሜ የሚስተዋልበት መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ወርሀ መስከረም ተማሪዎች ወደ አዲስ የመማሪያ ክፍል የሚገቡበት፣ነጋዴዎች በአዲስ እቅድ ትርፋቸውን የሚያሰሉበት፣አርሶ አደሩ የላቡን ውጤት የሚያገኝበት፣በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ዜጎች አዳዱስ እቅድ አዘጋጅተዉ የህይወታቸውን ምዕራፍ የሚጀምሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

በሁለቱም የጉራጌ ዞኖች አልፎ አልፎ የሚያጋጥሙ የጸጥታ ችግሮች መኖራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ድንበር ተሻጋሪ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ከኦሮሚያ ክልል እና ከፌደራል የጸጥታ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

አሁን በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮች ከጥቂት ጊዜ በኋላ መልክ መልክ ይይዛሉ ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።

2019 ዓ/ም የኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን የሚረጋገጥበት ዓመት እንደሚሆን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ለቀጣዩ የስራ ጊዜ ዝግጁ መሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው በጋራ እና በትብብር እየሰራን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ እናሻግራለን ብለዋል።

በክልሉ ከተለያዩ አካባቢዎች ሉኡካን ቡድኖቻቸውን ይዘው በዓሉን ለማድመቅ ለተገኙ አካላት ርዕሰ መስተዳድሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት እና የወዳጅነት በዓል እንዲሆን ርዕሰ መስተዳድሩ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደሱ አበጋዝ በበኩላቸው የመስቀል በአል በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኒስኮ) ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር ኢኮኖሚ የላቀ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል።

መስቀል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የላቀ ትርጉም ያለው በዓል ስለመሆኑም አቶ ደሱ ጠቁመዋል።

አመቱን ሙሉ ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚገናኙበት፣ማህበራዊ ችግሮቻቸውን የሚፈቱበት፣ወጣቶች ወደ ጋብቻ የሚያመሩበት፣በዳይና ተበዳይ ይቅር የሚባባሉበት እና ሌሎች አያሌ እሴቶቻችን በጉልህ የሚንጸባረቁበት በዓል ስለመሆኑም ምክትል አስተዳዳሪው አስታውቀዋል።
(የየክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ(መስከረም 16/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር...
26/09/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

(መስከረም 16/2019) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል

እንኳን ለመስቀል በዓል በሠላም አደረሳችሁ!አደረሰን!

ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣
እንኳን ለዘንድሮዉ የመስቀል በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! በማለት መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።

የመስቀል በዓል በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ ነዉ።

የመስቀል በዓል አከባበር በዩኔስኮ የማይዳሰስ የባህል ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወቅ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን ገፅታ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድም የበኩሉን እያበረከተ ይገኛል።
በዓለ መስቀሉ፣ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮቶች እና ትዉፊቶች ባሻገር፣ ባህላዊና ማህበራዊ ፋይዳዉ ከፍተኛ ነዉ ።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የመስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮቶች እና ትዉፊቶች ባሻገር፣ ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ በተለያዩ የሥራና የሕይወት ዘርፎች ተሠማርተዉ የሚገኙ ወገኖች ወደ ቤተሰቦቻቸዉ ቀዬ በመመለስ ወላጆቻቸዉን፣ ቤተ_ዘመዶቻቸዉን በበዓል ስጦታዎች የሚያስደስቱበት፣ እና የሚደሰቱበት ደማቅ መነቃቃት የሚፈጠርበት የበረከትና የደስታ ወቅት ነዉ፤

በዓለ መስቀሉን ስናከብር የበጎነት፣ የመደጋገፍ፣ የአብሮነት እና የፍቅር እሴቶችን በማጠናከር ፤ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳትና በማበረታታት መሆን ይኖርበታል።

ብርሃነ መስቀሉ፣ የበረከት፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንልን እመኛለሁ !

Address

Butajira

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የቡታጅራ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን Butajira City Gov't Communication:

Shortcuts

Share