𝐴𝑑𝑖𝑙 𝑀𝑒𝑑𝑖𝑎

𝐴𝑑𝑖𝑙 𝑀𝑒𝑑𝑖𝑎 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from 𝐴𝑑𝑖𝑙 𝑀𝑒𝑑𝑖𝑎, Social Media Agency, B51, Butajira.

10/02/2026

ቴሌ እና ንግድ ባንክ ምን ሆነው ይሆን?🥲🥲

በጦራ ከተማ ያለ ሄልሜት በሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ​ወራቤ፤ የካቲት 02 ቀን 2018 (የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ)​በስልጤ ዞን ጦራ ከተ...
09/02/2026

በጦራ ከተማ ያለ ሄልሜት በሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ

​ወራቤ፤ የካቲት 02 ቀን 2018 (የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ)

​በስልጤ ዞን ጦራ ከተማ አስተዳደር የራስ መከላከያ (ሄልሜት)ሳያደርጉ በህገ-ወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ የህግ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ።

​የከተማዋ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ከትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ባካሄደው ኦፕሬሽን፣ የደህንነት ደንብ ጥሰው የተገኙ አሽከርካሪዎችን ወደ ህጋዊ ስርዓት የማስገባት ስራ እየተሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረት ያለ ሄልሜት በመንዳት ራሳቸውንና ህብረተሰቡን ለትራፊክ አደጋ ተጋላጭ የሚያደርጉ አካላት ላይ ቁጥጥር ተደርጓል።

​በቁጥጥሩ ወቅት ህገ-ወጥ ድርጊት ላይ ተሰማርተው የተገኙ ሞተር ሳይክሎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአሽከርካሪዎቹ ላይም ተገቢው የህግ እርምት እየተወሰደባቸው መሆኑ ተብራርቷል። አሽከርካሪዎች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ሊደርስ የሚልን አደጋ አስቀድሞ የመከላከል ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ተላልፏል።

ለህዝባችን ሰላምና ደህንነት ያለመታከት እንሰራለን!

***
የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ትክክለኛ፣ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች ያሉ ሊንኮችን በመጫን follow በማድረግ ይከታተሉን ፦

📌 የፌስቡክ ገፅ 👇
https://www.facebook.com/abdisheycho.26

📌ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ደማቅ ድል አስመዘገበወራቤ፤ የካቲት 1/2018 ዓ.ም 📌በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው...
08/02/2026

📌ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ደማቅ ድል አስመዘገበ
ወራቤ፤ የካቲት 1/2018 ዓ.ም

📌በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ለተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው 10ኛው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል። በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ የተሳተፈው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ልዑክ በዝግጅቱ መዝጊያ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት የድሉ ተካፋይ ሆኗል።

📌በውድድሩ ወቅት የዩኒቨርሲቲው ስፖርተኞች ባሳዩት ከፍተኛ የፉክክር መንፈስ እና ብቃት ተከታዮቹን የሜዳሊያ ውጤቶች ማምጣት ችለዋል፦

📌የወርቅ ሜዳሊያ፡ 4

የብር ሜዳሊያ፡ 4

የነሃስ ሜዳሊያ፡ 11

📌ጠቅላላ ድምር፡ 19 ሜዳሊያዎችን ለዩኒቨርሲቲያችን አስመዝግበዋል።

📌ዩኒቨርሲቲው ለተሳታፊ ስፖርተኞች፣ ለአሰልጣኞች እና ለልዑኩ አባላት በሙሉ የተሰማውን ኩራት እየገለጸ፤ በቀጣይም ለስፖርቱ ዘርፍ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

📌ዕውቀት ለልህቀት! የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ይህን የስልክ ማፍጠኛ ዘዴ ታውቁታላችሁ ?📌 የስልካችን ፍጥነት መጨመሪያ ድብቁ   setting !​📌 ብዙዎቻችን ስልካችን ሲቆይ መዘግየት (Lag) ሲጀምር አዲስ ስልክ መግዛት ብቻ መፍትሄ ይ...
07/02/2026

ይህን የስልክ ማፍጠኛ ዘዴ ታውቁታላችሁ ?

📌 የስልካችን ፍጥነት መጨመሪያ ድብቁ setting !

📌 ብዙዎቻችን ስልካችን ሲቆይ መዘግየት (Lag) ሲጀምር አዲስ ስልክ መግዛት ብቻ መፍትሄ ይመስለናል። ነገር ግን በስልካችሁ "Settings" ውስጥ የተደበቀ አንድ ሚስጥር በመጠቀም ስልካችሁን እጥፍ ፈጣን ማድረግ ትችላላችሁ!

መፍትሄው ፦ "Developer Options" ነው !

ፍጥነቱን ለ መጨመር ፦

📌 ​Settings > Developer Options ውስጥ ይግቡ ።

​ወደ ታች ወረድ ብለው እነዚህን 3 ነገሮች ይፈልጉ ፦

🎯​Window animation scale

🎯​Transition animation scale

🎯​Animator duration scale

📌 ​ሶስቱንም ከ 1x ወደ 0.5x ይቀይሯቸው። (ጭራሽ ፍጥነት ለሚፈልግ ሰው ደግሞ Animation Off ማድረግ ይቻላል)።

ውጤቱ ምንድነው?

📌 አፕሊኬሽኖች የሚከፈቱበትና የሚዘጉበት ፍጥነት በአይን በሚታይ ሁኔታ ይጨምራል። ስልክዎ ልክ እንደ አዲስ ፈጣንና ቅልጥፍ ያለ ይሆናል!

ይህ ዘዴ በተለይ ለቆዩ ስልኮች ፍጹም መፍትሄ ነው ።

📌 የቴሌግራም ቻናላችን ፦ 👇
https://t.me/Andebet_digitals






06/02/2026

ቤተሰብ follw በማድረግ pageን እናሳድግ

04/02/2026
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተነሱ ጥያቄዎች ***********************************ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላ...
03/02/2026

ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተነሱ ጥያቄዎች
***********************************

ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ከምክር ቤት አባላት ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ይገኛል።

ከተነሱት ዋና ዋና ጥያቄዎች መካከል፦

ሰላምና ጸጥታ፦ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የጸጥታ ስጋቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ባለፉት 6 ወራት ምን ተሰራ?

ተፈናቃዮች፦ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተከናወኑ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ ይገኛሉ?

ተሃድሶ፦ የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመመለስ እና ግጭት የነበረባቸውን አካባቢዎች ወደ ልማት የማስገባት ሂደትስ?

ምርጫ 2018፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ ነጻ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ምን እየተሰራ ነው?

የትግራይ ክልል፦ በክልሉ ያለው አሁናዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?

ሀገራዊ ምክክር፦ ለምክክሩ ውጤታማነት ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ምን ይጠበቃል?

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ምላሽ እና ዝርዝር ማብራሪያ በኢቢሲ ዶትስትሪም የቀጥታ ስርጭት አሁኑኑ ይከታተሉ!

ፌስቡክ፦ https://web.facebook.com/share/v/17tXREhsnH/
ዩቲዩብ፦ https://youtu.be/5e3xq-LmMfk



የኢቢሲ ዶትስትሪም የዲጂታል አማራጭ አድራሻዎችን ከአስተያየት መስጫ ሳጥን ያግኙ፡-

Address

B51
Butajira
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when 𝐴𝑑𝑖𝑙 𝑀𝑒𝑑𝑖𝑎 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share