25/09/2026
በንቡር ካኘ የታዳጊዎች የክረምት ስፖርታዊ ውድድር የመጀመሪያው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በይመር ዋጮ 2ኛA 4ለ2 አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መሰከረም 15/2019 ዓ/ም {የምስራቅ መስቃን ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት}
በታዳጊዎቹ መካከል በተደረገው በዚህ ብርቱ ፉክክር የታየበት የመጀመሪያ ጨዋታ ይመርዋጮ 2ኛA ተጋጣሚውን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ድል ቀንቶታል።
ይህንን ጨዋታ ተከትሎም፣ ሁለተኛው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በሀሙስ ገበያ A እና በባሞ A መካከል በአሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ፉክክር በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የዕለቱ የጨዋታው የተጠቃለለ መረጃ የምናደርስ ይሆናል።
ዜናው:-የምስራቅ መስቃን ወረዳ መንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።