Adabay Media አዳባይ ሚዲያ

Adabay Media አዳባይ ሚዲያ All Entertainment

23/02/2023
22/02/2023

ተዋወቋቸው...

በጂጂ “ናፈቀኝ” የተሰኘው ሙዚቃ ላይ ያሉት ‘አያ ታዴ’ ማለት እኝህ ምስሉ ላይ ያሉት አዛውንት ናቸው። አያ ታዴ በዘመኑ የነጂጂ ቤት ከብቶች ጠባቂ (እረኛ) ነበሩ።

ምንጭ፦ አበባየሁ የዓባይልጅ

 #ደብረብርሃንDebre Brehan international investment trade & finance
17/01/2023

#ደብረብርሃን

Debre Brehan international investment trade & finance

በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገጣጠሙበት ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ ይጀምራል።******************በደብረ ብርሃን ከተማ በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን...
13/01/2023

በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚገጣጠሙበት ፋብሪካ ከ3 ወራት በኋላ ሥራ ይጀምራል።
******************
በደብረ ብርሃን ከተማ በዓመት 1 ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መገጣጠም የሚያስችል የተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ከሦስት ወራት በኋላ ሥራ ይጀምራል፡፡

በደብረ ብርሃን ከተማ ለተገነባው የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካ 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል፡፡

የፋሪካው ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፣ ፋብሪካው ከሦስት ወር በኋላ ወደማምረት ሥራ ይገባል፡፡

ፋብሪካው በዓመት 1ሺህ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ገልጸው÷ ከሦስት ወራት በኋላ ወደ ሥራ ሲገባ በዚህ ዓመት ከ250 በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንደሚገጣጠሙ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው ለ500 ሰዎች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርም ተመላክቷል፡፡

ዝም_በል!አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራአዲስ መኪና ገዛ? አትናገር ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለትለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በልንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አ...
09/01/2023

ዝም_በል!
አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ

አዲስ መኪና ገዛ? አትናገር

ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት

ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል

ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ

ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ

አብዛኛውን ጊዜ
ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት ዋነኛው ምክንያት ከመከናወናቸው በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው -ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ ሸለምጥማጦችን እንጠራለን::

ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች "ሰዋዊ ቅናት" እና "የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ" በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው:: ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ::

አብዛኛው ሰው
ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይለዋል ሆኖም ግን ጥለኸው እንድትሄድ እና አንጋጦ ሊያይህ ይተናነቀዋል::

ዘመላዕክ እንድሪያስ ነው ይህን ግሩም መልዕክት ያደረሰን!!

17/11/2022

#አዳባይ
ወደ #ጅሁር እና #መርሀቤቴ አቅጣጫ

Photo Credit

ስለ ዳማከሴ ይህን ያውቁ ኑሯል?በሀገራችን ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ እጽዋት ለሕክምና አገልግሎት ይውላሉ። ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ደማ ከሴ አንዱ ነው። • ደማ ከሴ አገር በቀል ተክል ሲሆን በሳይን...
07/11/2022

ስለ ዳማከሴ ይህን ያውቁ ኑሯል?

በሀገራችን ወደ 85 ሺህ የሚጠጉ እጽዋት ለሕክምና አገልግሎት ይውላሉ።
ከነዚህ ውስጥ ደግሞ ደማ ከሴ አንዱ ነው።

• ደማ ከሴ አገር በቀል ተክል ሲሆን በሳይንሳዊ ስሙ ኦሲመም ላሚፎለም(Ocimum lamiifolium) እየተባለ ይጠራል።

• ተክሉ ሁለገብ የሆነ የመድኃኒትነት ባህሪ አለው። በሀገራችን በአብዛኛው ቦታዎች የምች መድሀኒት በመባል ይታወቃል።

• በባህላዊ ሕክምና ከተክሉ የሚገኝ ጭማቂ ለተለያዩ የዐይን በሽታዎች፣ ለራስ ምታት፣ በተለይ ትኩሳት ሲያጋጥም በባሕላዊው አጠራር ‹‹ምች›› እየተባለ ለሚጠራው ሕመም ማስታገሻነት ይውላል።

• በተጨማሪም ለምለም ቅጠሉ ተጨምቆ ሲጠጣ ለተቅማጥ፣ ለአሜባ (ደም ያለው ተቅማጥ)፣ ለሳልና ለሌሎችም ሕመሞች ለማስታገሻነት ይውላል።

• በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ለቆዳ፣ ለአንጀት፣ ጨጓራና ተያያዥነት ላላቸው ሕመሞች ይወሰዳል።

• ተክሉ ለተለያዩ የጤና ችግሮች አስተማማኝ የሚባል የፈውስ ባህሪ አለው።

• የፀረ-ወባ ገቢርነት እንዳለውም ይታወቃል።

• ቅጠሉን በማጨስ የወባ ትንኞችን ከአካባቢ እንዲርቁ ማድረግ ይቻላል።

• በተጨማሪም ፀረ ፈንገስና ፀረ ነፍሳት ባህሪ አለው። እንዲሁም ትኩሳትን ያበርዳል።

• ደማ ከሴ በኢትዮጵያ የሚበቅል ዕፅ ሲሆን ለዕቃ ማጠኛ አገልግሎት ይውላል።

• አብዛኛውን ጊዜ ለመድኃኒትነት ጥቅም የሚውለው ቅጠሉን በመጭመቅና በማሽተት፣ ወይም ቅጠሉን በውሀ አፍልቶ በመታጠን ወይም በመጠጣት ነው።

• ለጉንፋን፣ ለራስ ምታት ጥቅም ላይ ይውላል።

• የቅጠሉ ጭማቂ በውሃ ወይም ከቡና ጋር ለትኩሳት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

• የአንጎል ጥቃት (ስትሮክ)፣ የጀርባ አጥንት መጨፍለቅ፣ የጅማት መጨማደድን ለማከም ከፍተኛ ጥቅም አለው።

• በጥቅሉ ከነርቭና ከጡንቻ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለማከም ማለትም የጡንቻ መዛል፣ ከቀዶ ሕክምና በኋላ የሚደረጉ የአካል እንክብካቤዎች፣ ከስፖርት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን፣ ከእጅና እግር መቆረጥና ከአጥንት መሰንጠቅ ጋር ያሉ ችግሮችን በቀላሉ ለማከም አገልግሎት ላይ ይውላል።

• የቅጠሉ ወይም የልጡ አካል በቁስል ላይ በመለጠፍ ቁሰሎችን በቀላሉ ለማዳን አገልግሎት ይሰጣል።

Source ፥ Trust Media

Address

Debre Birhan

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adabay Media አዳባይ ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share