Tarmaber woreda industry and investment group

Tarmaber woreda industry and investment group Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Tarmaber woreda industry and investment group, Advertising/Marketing, Debre Sina.

03/04/2026
የጣርማበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤትአምራች ኢንዱስትሪዎች ለዘመናዊ ግብርና  የዕውቀት ሽግግር ለማካሄድ ቁልፍ ሚና አላቸው-  የሰ/ሜሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢን...
05/01/2026

የጣርማበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት
አምራች ኢንዱስትሪዎች ለዘመናዊ ግብርና የዕውቀት ሽግግር ለማካሄድ ቁልፍ ሚና አላቸው
- የሰ/ሜሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡
- ታህሣስ 22/4/2018 ዓ.ም ደ/ሲና
- በመድረኩ የተሳተፉ የወረዳው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣የወረዳው ውስጥ ያሉ ባለሀብቶችና እጩ ባለሃብቶች ተገኝተዋል፡፡
- የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጣ/በር ወረዳ ምክትል አስተዳደሪና የውሃ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሽመልስ ማናዬ “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ መድረክ አምራች ኢንዱስትሪው ተኪ ምርት በማምረት ለገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን የእውቀት ሽግግር ለማካሄድ ወሳኝ ሚና አላቸው
- የግብርናው ዘርፍ በዘመናዊ መንገድ በማዘመን ምርትና ምርታማትን በመጨመር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች በቂ ግብዓት ሲቀርብ ኢንዱስትሪውና ግብርናው ተመጋጋቢ ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አምራች ኢንዱስትሪው ለዘመናዊ ግብርና /የገጠር ኢንዱስትሪያላዜሽን/ የእውቀት ሽግግር ለማከናወን ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡
- ለውይይቱም የሚሆን ሰነድ ተዘጋጅቶ በጣ/በር ወረዳ ኢንዱ/ኢንቨ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አድሴ ሰይፈ የቀረበ ሲሆን ሰነዱ በተለይም ወረዳው ውስጥ ያሉ የኢንቨስትመንት ፀጋዎችን በስፋት ያስተዋወቀ ሲሆን በግብርና ዘርፍ ብዙ ያልተሰራበት ለውጪ ገበያ የሚቀርብ ለምሳሌ፡- ማሾ ፣ሰሊጥ፣ጤፍ …..፣የአበባና የብዕር ዕህሎችን እንዲሁም ኦፓል፣ የድንጋይ ከሰል በተጨማሪም ሰፊ የቱሪዝም ሀብት…… ወዘተ በዚህ በተዘረዘሩት ፀጋዎች ላይ ባለሀብቶች ትኩረት ሰጥተው ኢንደሰሩ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡
- በማጠቃለያውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከግብርናው ጋር ተመገጋጋቢ በመሆን /የገጠር ኢንዱስትሪያላዜሽን/ በትኩረት አንዲሰራ ለባለሃብቶቹ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ወረዳውም የሚጠበቅበትን የድጋፍና ክትትል ምቹ ሁኔታ እንፈጠውራለን ተብሏል ።
-

Address

Debre Sina

Telephone

+251116800750

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tarmaber woreda industry and investment group posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share