Red fox advertising and printing

Red fox advertising and printing Real estate

31/03/2021
28/06/2020

Ha ha

11/06/2020

በሳቅ

Sky
07/06/2020

Sky

28/05/2020

ሰውና ኮሮና

25/05/2020
13/05/2020

አፋር አዋሽ ወንዝ

ሰሞኑን በተከሰተው የጥቂት ወታደሮች ወደቤተመንግስት ከነመሳሪያቸው መሄድ በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ህሳብ ቢሰጥበትም በእኔ እይታ ግን ቀደም ብሎ በሰራዊቱ ቤት ከነበረኝም ቆይታ አንፀር ስመለከ...
12/10/2018

ሰሞኑን በተከሰተው የጥቂት ወታደሮች ወደቤተመንግስት ከነመሳሪያቸው መሄድ በተለያዩ ሰዎች የተለያየ ህሳብ ቢሰጥበትም በእኔ እይታ ግን ቀደም ብሎ በሰራዊቱ ቤት ከነበረኝም ቆይታ አንፀር ስመለከተው ድርጊቱ ከወታደራዊ ሦነምግባር ውጪና በወታደራዊ ኮርት ተጠያቂ የሚያደርግ ለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር አይደለም። ለምን ቢባል በመሰረቱ ማንኛውም የመከላከያ አባል ከጉዋድ መሪ እስከመቶ መሪ ከመቶ መሪ እስከሻምበል አዛዥና ከዛም ካለፈ የእዝ ጠገጋቸው በርቀት ያለ ቢሆንም የብርጌድ አዛዥና የክፍለጦር አዛዥን ጥሶ ሁለት ሻምበል የሆነ ሰራዊት የሀገሪቱን ጦር ጠቅላይ አዛዥ በግል ለማነጋገር የጦር መሳሪያ እንደያዘ ቤተመንግስት ድረስ መሄድ ፍፁም በስነምግባር ከታነፀ መለዮ ለባሽ አይጠበቅም። ይሁንና ሰራዊቱን ለዚህ ብሶት የዳረገውን ጉዳይ ማጣራት ለጠቅላይ ምኒስትሩም ቢሆን ተገቢና ጠቃሚ ይመስለኛል። ምክነያቱም እኔ ካለኝ መረጃ ከታች ያለው ሰራዊት ጥቂት ከሚባሉ በስተቀር የጠቅላይ ምኒስትሩ ደጋፊ መሆናቸውን አውቃለሁኝ። ነገርግን ሰራዊቱ የአስተዳደር በደል ሲፈፀምበት እና በአለቆቹ ተሰሚነት ሲያጣ እሳቸውን አግኝተን ችግራችንን ብንናገር ይሻላል ከሚል በወጣትነት ስሜት በመገፋፋት የእዝ ሰንስለቱን መጣስ የታየ ይመስለኛል። ይህን ስል ስቪሎች መብታቸውን ጠየቁ እንጂ ምን አጠፋ እንደምትሉኝ እርግጠኛ ነኝ። ይሁንና እናንተ የምታቁት የስቪል ህግና ወታደራዊ ህግ በጣም የተራራቀ በመሆኑ ነው። በመሆኑም ማንኛውም ሰው ወደሰራዊት ሲቀላቀል የመጀመሪያው ስልጠና ወታደራዊ ባህልና ጨዋነት ወታደራዊ ህግና ወታደራዊ ሰልፍ ሳይሰለጥን ወደ ሌላው ስልጠና እንደማይገባም ግንዛቤው ቢኖራችሁና የሚዳኘውም በዚሁ መሰረት መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ከዚህም ህግ አንፃር ወታደሮቹ የፈፀሙት ከፍተኛ ስህተት ነው። ይሁንና አንዳንድ ወገኖች በተለይም የኢሳት ቴሌቪዥን ጣቢያ ተንታኞች በምትሰጡት ትንተና ላይ ትንሽ ቅሬታ አለኝ። በሙያችሁ የማከብራችሁ ቢሆንም በተለይ ስለሰራዊቱ ሁኔታ ትንተና ለመስጠት የህጉ ግንዛቤ ከሌለን አንዳንሳሳት መጠንቀቅ አስፈላጊ በመሆኑ ነው። በመሆኑም መሪያችን የወሰዱትን ጥበብ የተሞላው እርምጃ ከሲቪሉ ህግ ነባራዊ ሁኔታ ተነስቶ ማብጠልጠል ስለማይቻል ነው። ስትገልፁትም ድርጊቱን የመሸፋፈን ወይም የልምምጥ አድርጋችሁ የሳላችሁት ትልቅ ስህተት ያለው አገላለጽ መሆኑን ልገልፅላችሁ እወዳለሁኝ። ለዚህም ስህተት የተዳረጋችሁት ያለምንም ምክነያት አይደለም። እስከዛሬ በታሪክ የምናቃቸው መሪዎቻችን-አቶ ኃይለማሪያምን አይመለከትም- እንኳንስ ጠመንጃ ይዞ ቤተ-መንግስት የመጣ ወታደር አይደለም በስብሰባ ላይ የተለየ ሀሳብ ያነሳ ሰራዊትም ሆነ ሌላ ግለሰብ ከንጉሱ ጊዜ ጀምሮ ሲታፈን፣ሲገደልና ታስሮ ደብዛው ሲጠፋ ስለነበር የአሁኑ መሪ ጥበባዊ አካሄድ ለሁላችንም አዲስ ቢሆንብን ምንም እይገርምም። ይሁንና እንደአንዳንድ ወገኖች ስጋትና እንደ እናንተም ስጋት የወታደሮቹ አመጣጥ ለመፈንቅለ መንግስት ቢሆን ኖሮ ይሳካል የሚል ግምት የለኝ። ምክነያቱም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህዝብ የሚደገፉና የሚወደዱ በመሆናቸው ህዝቡ ያከሽፈዋል። ለእዚህ ማስረጃ ባቀርብላችሁ በህዝብ የሚወደድ መሪ በ250 ወታደር አይደለም በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች የተሳተፋበት የቱርክ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት መሪያችንን መንካት አትችሉም በሚል የህዝብ አመፅ ከሽፎ ወታደሮቹን ወህኒ አውርደዋል። ይህን ስል ግን መሪያችን በወታደሩም ሆነ በሌላው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል የለውጥ ተከታዮቻቸውን በማብዛት በኩርፊያ ህዝብ ላይ በደል የሚያደርሱትን አመራሮች እስካላነሱና ፍትሀዊ አሰራር እስካልሰፈነ ድረስ የወደፊቱ ሁኔታ ጥሩ ይሆናል ማለት አይደለም። በመሆኑም እነኝህ ወታደሮች ክፋ አላማ ቢኖራቸው ኖሮ እንደደረሱ ከቤተመንግስቱ ጠባቂ ሀይሎች ጋር ተኩስ ይገጥሙ ነበር እንጂ መሳሪያ አስረክበው ስብሰባ አይገቡም ነበር። ለማንኛውም በእኔ እድሜ የማውቀው የተጠራጠሩትን ሳይቀር የሚገሉና የሚያስሩ መሪዎችን ስለነበረ ጠመንጃ ይዞ ቤተ-መንግስት የመጣን ወታደር አስተምሮ፣ አወያይቶ፣ ምሳ ጋብዞ የሚመልስ መሪ በማየቴ ፈጣሪ ሆይ እንዲህ አይነት መሪ ስለሰጠኸን ምስጋና ይግባህ ብዬ አምላኬን አመስግኛለሁኝ። እናንተስ?

ምንጭ፦ አቶ ለገሠ ደምሴ
የአቤ ዘብሄረ ድሬዳዋ ፋይል

Address

Dire Dawa
Dire Dawa

Telephone

911060755

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Red fox advertising and printing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share