02/08/2026
እንኳን ደስ አላችሁ !
በኦሮሚያ ክልል ባሌ ሮቤ ከተማ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የ2018 በጀት ዓመት የግምገማ መድረክ፤ የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ የላቀ አፈፃፀም በማስመዝገብ 1ኛ በመውጣቱ የተሰማንን ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት እንገልጻለን! ይህ ስኬት የእያያንዳንዳችን የጋራ ጥረት፣ ቁርጠኝነት እና የጠንካራ አመራር ውጤት ነው። ለዚህ ኩራት ያበቁንን የጽሕፈት ቤታችንን አመራሮች፣ አባላት እና ባለሙያዎች በሙሉ እያመሰገንን፤ ወደፊትም ለበለጠ ስኬት በአንድነት እንሰራለን!
ድሬዳዋ – የላቀ አፈፃፀም እና የአሸናፊነት ምሳሌ!