Ethioድሬ

Ethioድሬ የማህበረሰብ ገንቢ ግንዛቤ መፍጠር

የኢትዮጵያን ሰላም ለማናጋት የሚጥሩ አካላት ተላላኪ መሆንህን የድሬዳዋ ህዝብ ቀድሞ አውቆታል። በሰላም ስም የትርምስ አጀንዳ አትሸምት።
13/04/2026

የኢትዮጵያን ሰላም ለማናጋት የሚጥሩ አካላት ተላላኪ መሆንህን የድሬዳዋ ህዝብ ቀድሞ አውቆታል። በሰላም ስም የትርምስ አጀንዳ አትሸምት።

09/04/2026
ከነዳጅ አምራች ሀገራት ውጭ ዝቅተኛ የነዳጅ ዋጋ ያላት ቀዳሚዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ዓለም አቀፉ ጫና በዜጎች ላይ እንዳይበረታ የተዘረጋው ኢኮኖሚያዊ ከለላ ውጤት እያመጣ ነው።
03/04/2026

ከነዳጅ አምራች ሀገራት ውጭ ዝቅተኛ የነዳጅ ዋጋ ያላት ቀዳሚዋ ሀገር ኢትዮጵያ ናት። ዓለም አቀፉ ጫና በዜጎች ላይ እንዳይበረታ የተዘረጋው ኢኮኖሚያዊ ከለላ ውጤት እያመጣ ነው።

31/03/2026

መጋቢት 22 2018

ድሬዳዋ፡ የሰላም፣ የአብሮነት እና የሚዛናዊ ውክልና ተምሳሌት! 🕊️✨
ሰሞኑን በድሬዳዋ የሕዝብ ውክልና እና የምክር ቤት ወንበር ድልድል ላይ የሚነሱ "የአሃዝ ጨዋታዎች" እውነታውን ያላገናዘቡና በከተማውና በገጠሩ ነዋሪ መካከል ጥርጣሬን ለመዝራት ያለሙ ናቸው። "ፍትሃዊነት የለም" የሚለው የተዛባ አመለካከት ከጀርባው የገጠሩን ወገናችንን የመዘንጋት እና ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ከለውጥ ወዲህ የመጣውን ሰላም ለማናጋት የመፈለግ ዝንባሌ ይታይበታል።
እውነታው ግን ይህ ነው፦
1. አካታችነት እንጂ መገለል አይጠቅመንም! ⚖️
ድሬዳዋ የኢትዮጵያ ትንሿ ተምሳሌት ናት። የምክር ቤት ወንበሮች ድልድል የተከናወነው እያንዳንዱ ማህበረሰብ በነዋሪነቱ በሚኖርበት አካባቢ ወይም ቀበሌ (በከተማም ሆነ በገጠር ) ተገቢው ድምፅ እንዲኖረው ታስቦ ነው።
• የገጠሩ ውክልና፦ የድሬዳዋ ገጠር በ38 ሰፋፊ ቀበሌዎች የተዋቀረ ነው። ለእነዚህ ቀበሌዎች 114 ወንበር መሰጠቱ የእያንዳንዱን አካባቢ ልዩ ፍላጎትና ድምፅ ለማረጋገጥ የተደረገ ጥንቃቄ የተሞላበት አሰራር ነው።
• የከተማው ውክልና፦ ቀደም ሲል የነበሩት 25 የከተማ ቀበሌዎች ወደ 9 ዘመናዊ ወረዳዎች የተቀየሩት ለአስተዳደር ቅልጥፍና ነው። ለከተማው የተመደቡት 75 ወንበሮች ከወረዳዎቹ ነባራዊ ሁኔታና መዋቅር ጋር የተመጣጠኑ ናቸው።
• ማሳሰቢያ፦ የገጠሩን ወገናችንን የመዘንጋት ለፖለቲካ ትርፍ፣ የድሬዳዋን ሰላም እና አብሮነት የሚጎዳ አደገኛ አካሄድ ነው።
2. የፓርላማ (HoPR) ውክልና፡ የአንድነታችን ማሳያ! 🇪🇹
በድሬዳዋ ያሉት 2 የፓርላማ ወንበሮች በሁለት የምርጫ ክልሎች (Region 1 and Region 2) የተከፈሉት እጅግ በበሰለና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ነው።
• በእያንዳንዱ የምርጫ ክልል ውስጥ የከተማ ወረዳዎችና የገጠር ቀበሌዎች ተቀላቅለው ይገኛሉ። ይህ ማለት የድሬዳዋ ተወካይ በፓርላማ ሲቆም የከተማውንም ሆነ የገጠሩን ችግር እኩል ተረድቶ እንዲሟገት ያደርገዋል።
• ይህ ስርአት ከተማውና ገጠሩ ተነጣጥለው ሳይሆን ተሳስረውና ተደጋግፈው እንዲያድጉ የሚያደርግ እንጂ "የወንበር ቁጥር ሽሚያ" አይደለም።
3. ከፖለቲካ ትርፍ ይልቅ እውነታው ይቀድማል! ⚠️
"የገጠሩ ውክልና ይበዛል" የሚለው አስተሳሰብ ገጠሩን ወገናችንን እንደ ሁለተኛ ዜጋ የመቁጠር አዝማሚያ አለበት። ድሬዳዋ የሁላችንም ናት! አንዱን አሳንሶ ሌላውን ከፍ ለማድረግ መሞከር ለሰላማችንም ሆነ ለብልጽግናችን አይበጅም ።
ዛሬ ድሬዳዋ ላይ የምናየው ተጨባጭ ለውጥ፣ የኮሪደር ልማትና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴዎች የመጡት በሽኩቻ ሳይሆን፣ መንግስት ከተማውንና ገጠሩን እኩል በሚያይ አካታች መርህ በመመራቱ ነው።
ማጠቃለያ፦
የድሬዳዋ አስተዳደርና የብልጽግና ፓርቲ የሚከተሉት መርህ "ፍትሃዊነትን እና አብሮነትን" ነው። ዛሬ ላይ የሚያስፈልገን በቁጥር መሰባበር ሳይሆን፣ በልማት ተባብረን ድሬዳዋን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከልነቷን ማረጋገጥ ነው!
ድሬዳዋ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለች!
ለድሬዳዋ ሰላምና ልማት የምትቆሙ ወገኖች ሁሉ ይህን እውነታ ሼር በማድረግ ሕዝባችንን ህብረ ብሄራዊ አንድነት እንጠብቅ!

23/03/2026

ድምፅዎ የወደፊት እጣ ፈንታዎ ነው! ዛሬውኑ በመመዝገብ የምርጫ ካርድዎን ይያዙ። ለውጥ የሚጀምረው በእርስዎ ምርጫ ነው!

03/07/2025

የትግራይ ህዝብ 100 % ጦርነት አይፈልግም፤ አይቶታል ፤ ትርፍ የለውም ፡፡
ጦርነት አያስፈልግም ፤ በሰላምና በውይይት ጉዳያችንን መፍታት ይቻላል ፡፡

ድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

03/07/2025

ኢትዮጵያ የማዕድን ክምችት ያላት ሀገር ነች!!
ድሬዳዋ አስተዳደር ወረዳ 6 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

Address

Dire Dawa
3000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethioድሬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share