LIGHT MEDIA 30

LIGHT MEDIA 30 WELL CAME TO LIGHT MEDIA 30!

''የተሻለ ትውልድ ለመፍጠር ዛሬን እንተጋለን''
#ማስታወቂያ ለማሰራት ከፈለጉ በ ያውሩን
The sun will rise again and I will try again.
(10)

Yana Tafesse (Engineer) Contact:-

አርሰናል የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናገደ ! የወቅቱ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል ከብራይተን ያደረገውን የሊግ ጨዋታ 3ለ0 ተሸንፏል። ፓስካል ግሮስ ፣ ኮስቱላስ እና ቼማ አንድሬስ የብራይ...
19/09/2026

አርሰናል የመጀመሪያ ሽንፈቱን አስተናገደ !

የወቅቱ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ አርሰናል ከብራይተን ያደረገውን የሊግ ጨዋታ 3ለ0 ተሸንፏል።

ፓስካል ግሮስ ፣ ኮስቱላስ እና ቼማ አንድሬስ የብራይተንን የድል ጎል አስቆጥረዋል።

መድፈኞቹ በውድድር ዘመኑ የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ብራይተን በሊጉ ከየትኛውም ክለብ በላይ በተጋጣሚዎቹ ላይ 16 ጎሎች አስቆጥሯል።

የሊግ ደረጃቸው ?

2️⃣ አርሰናል :- 12 ነጥብ
3️⃣ ብራይተን :- 10 ነጥብ

ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት መልስ :-

- አርሰናል ከ ሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም
- ብራይተን ከ ሰንደርላንድ ጋር ይጫወታል።

  !! በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው   የሚያገናኝ ደንቅ የወዳጅነት ጨዋታ በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም ።ይህ በዱራሜ ከተማ የሚካሄድ የአርሴናል እና የዩናይትድ ደጋፊዎች የወዳጅነት ጨዋታ እጅግ ...
18/09/2026

!! በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው የሚያገናኝ ደንቅ የወዳጅነት ጨዋታ በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም ።

ይህ በዱራሜ ከተማ የሚካሄድ የአርሴናል እና የዩናይትድ ደጋፊዎች የወዳጅነት ጨዋታ እጅግ የሚደነቅና መልካም በጎ አድራጎታዊ እንቅስቃሴ ነው ።

የጨዋታው ዋነኛ አላማ ለተማሪዎች ደብተርና የትምህርት ቁሳቁስ መግዣ የሚሆን ገቢ ማሰባሰብ በመሆኑ አቅም የሌላቸውን ተማሪዎች በመደገፍ ትምርህታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ ይረዳል ።
በወጣቶችና ህፃናት ዘንድ ለትምህርት ያላቸውን ተነሳሽነት ይጨምራል ።

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች (የአርሴናል እና የዩናይትድ ) ደጋፊዎች ስፖርታዊ ፉክክርን ወደ በጎ አድራጎትና ማህበራዊ አገልግሎት መቀየራቸው ለሌሎች ከተሞችና ደጋፊዎች መልካም አርአያ ይሆናል ።

በዱራሜ ከተማ የሚገኙ ስፖርት ወዳዶች ደረጃውን የጠበቀ የወዳጅነት ጨዋታ በመመልከት እራሶን መዝናናት ይችላሉ ።

ይህ ታላቅ የደርቢ ጨዋታ የመስቀል በዓል ሁለተኛ ቀን በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም በድምቀት ይደረጋል ።
መጫወት የምትፈልጉ ድንቅ የሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በውስጥ መስመር አውሩን !!!!
Conta Man

18/09/2026

ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የፉላ ግድብን ለመገንባት በዝግጅት ላይ መሆኗን ገለጸች

ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የሚገነባውን የፉላ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ፕሮጀክት ለማስጀመር ዝግጅት እያደረገች መሆኗን የሀገሪቱ የኃይል እና ግድቦች ሚኒስቴር አስታወቀ።

በጁባ በተካሄደው 7ኛው ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን (GLC 2026) ይፋዊ የሚዲያ ማስጀመርያ ስነ-ስርዓት ላይ የተናገሩት የኃይል እና ግድቦች ሚኒስትር አጎክ ማኩር፣ ሀገራቸው የግድቡን ግንባታ ለማካሄድ ከግብፅ በኩል የሚመጣ ምንም ዓይነት ፍራቻ እንደሌላት ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም ደቡብ ሱዳን በአሁኑ ወቅት እየተጠቀመች ያለችው ከአጠቃላይ የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅሟ አንድ በመቶ ያህሉን ብቻ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ማቆየቱን አስረድተዋል።

በዕቅድ ላይ ያለውና በኒሙሌ አካባቢ የሚገነባው የፉላ ግድብ 1,800 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ሲሆን፣ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የደቡብ ሱዳንን የሀገር ውስጥ ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ማሟላት ከማስቻሉም በላይ ለጎረቤት ሀገራት የሚተርፍ ትርፍ ኃይል እንደሚያመነጭ ተገልጻል።

አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለኢንዱስትሪ፣ ለኢንቨስትመንት፣ ለሎጂስቲክስ እና ለጠቅላላ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፣ ሀገሪቱ በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም (August 2026) በጁባ በሚገኘው ፒራሚድ ኮንቲኔንታል ሆቴል የምታስተናግደው የሎጂስቲክስ ኮንቬንሽን የዘርፉን ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮችን እና ፖሊሲ አውጪዎችን እንደሚያገናኝ ተናግረዋል።

LIGHT MEDIA 30

 #መሳላ፡- የከምባታዎች የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የማንነት መገለጫ‎‎‎የከምባታ ብሔር ዘመን መለወጫ የሆነው “መሳላ” በብሔሩ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ፣ በታላቅ ድምቀት የሚከበር እና አዲሱ ዓ...
18/09/2026

#መሳላ፡- የከምባታዎች የፍቅር፣ የመተሳሰብ እና የማንነት መገለጫ


‎የከምባታ ብሔር ዘመን መለወጫ የሆነው “መሳላ” በብሔሩ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ፣ በታላቅ ድምቀት የሚከበር እና አዲሱ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀምርበት ነው። ‎መሳላ የክረምቱ ወቅት አልፎ ጨለማው በብርሃን ሲተካ የሚከበር በዓል ሲሆን፣ በክረምት ወራት በብርቱ ሥራ ተጠምዶ የቆየ ሰውነት ከሥራውም ከድካሙም አረፍ የሚለው በአዲስ ዓመት መጀመሪያ በመሳላ ቀን ነው።

ከምባታ ከሰኔ ወር ማለቂያ አንስቶ ከመሳላ ዕለት በፊት ያሉትን ሳምንታት በራሱ የቀመር ስሌት ከፋፍሎና ለይቶ ከአሥረኛ ሳምንት (ቶርዱሜ ሰነ) ወደ ታች በመቁጠር አንደኛው ሳምንት (መቴ ሰነ) ሲጠናቀቅ መሳላን ያከብራል።

‎የከምባታ ሕዝብ የኑሮ መሠረት የሆነውን የእርሻ ሥራ በውጤታማነት የሚሠራበት የራሱ የሆነና ዘመናትን የተሻገረ የአሠራር ጥበብና የጊዜ ቀመር አለው፡፡ ‎ሕዝቡ እርሻውን በተለያዩ ወቅቶች የሚከውን ሲሆን፣ የመኸሩ የዘር ወቅት ግን በተለየ ሁኔታ ትኩረትን የሚስብ ነው፡፡

የመኸር እርሻ የዘር ወቅትን ሐምሌ 1 ቀን በመጀምር መስከረም 16 ቀን ላይ ያበቃል። ‎ይህም ወቅት የተለያየ ስያሜ ባላቸው 11 ሣምንታት ይከፈላል፡፡ እነዚህ አስራ አንዶቹ ሣምንታት የዘር መዝሪያ ሣምንታት ይባሉ እንጂ በዋናነት ቀጣዩን አዲስ ዓመት “መሳላ” ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግባቸው ናቸው፡፡

መሳላን ለመቀበል ልጅ፣ አዋቂ፣ ወንድ፣ ሴት ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ዝግጅቱን የሚያጧጡፈው ከዚህ ወቅት ጀምሮ ነው፡፡ ‎ሐምሌ 1 ቀን በከምባታ ባህል “ሐምሌታ ሐበራትታ” ተብሎ ይታወቃል፡፡ ሐምሌታ ሐበራትታ ብዙ ትርጉም ያለው ሀረግ ሲሆን፣ ከመሳላ አንፃር ግን ሐምሌ የወር ስም ሆኖ “ሐበራትታ” ማለት ደግሞ አሃዱ ማለት ነው፡፡

የአዲሱ ዓመት የበጀት ዕቅድ አሃዱ ብሎ መጀመሩን ማሳያ ቃል ነው፡፡ “ሐምሌታ ሐበራትታ” የሚባለው ጊዜ አንድ ሳምንት ቆይቶ ያበቃል። በርከት ላሉ የመሳላ በዓል ዝግጅት ተግባራትም መንደርደሪያ ይሆናል፡፡

‎ሐምሌ 1 ቀን የመሳላ ዝግጅት አሃዱ ብሎ ሲጀምር ለሰው ከሚደረገው ዝግጅት ጎን ለጎን ለእንስሳት የመሳላ ሳር የመከለል (መሳል ህጥተ ከሉ) ተግባር ይከናወናል፡፡ ይህ የሚሆነው መሳላ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም የደስታና የጥጋብ በዓል ስለሆነ ነው፡፡

‎የማህበራዊ ይዞታ በሆነ ቦታ በአግባቡ ተከልሎ የቆየ ሳር በመሳላ ወቅት ብዙም ሆነ ውስን እንስሳት ያሉት የእገሌ በዝቷል፤ የእገሌ አንሷል ወይንም ለእገሌ ምንም የለውም የሚል ክርክር ሳይኖር ያለአንዳች ተቃውሞ በሰፈሩ ያሉት እንስሳት ሁሉ መሳላ በሚል ከተከለለው ሳር እንዲግጡ ይደረጋል፡፡

‎በከምባታ የመሳላ ሳር የሚባል ከመሳላ ከሎ የተለየ ሌካ ሳርም አለ፡፡ የመሳላ ሳር ከማንኛውም ቆሻሻ በፀዳ ሁኔታ በእያንዳንዱ ግለሰብ ይዞታ የሚያድግ የሳር ዓይነት ነው፡፡ በቂ ይዞታ የሌለው ጎረቤት ያለውን ሲጠይቅ የዕለቱ ዕለት ሁለት ውይም ሦስት ሸክም ሣር አጭዶ ለከብቶቹ እንዲወስድ በነፃ ይሰጣል፡፡ ይህ ሳር ከእርድ በኋላ የሚሰጥ ሲሆን፣ ትርጉሙም ከብቶቹ ከእርድ ስለመትረፋቸው ማረጋገጫ ነው፡፡

‎በመሳላ በዓል ወቅት ለእንስሳት መኖ የሚሆን ሳርን ከመከለል ጎን ለጎን ሌላኛው የአባቶች ተግባር ለማገዶነት የሚያገለግል እንጨት ማዘጋጀት ነው። የእንጨት ዝግጅቱ የሚጀመረው ሐምሌ 1 ቀን ሆኖ መሳላ በሚታረድበት በር በጌዝማ (በቡድን) በመፍለጥ ይጀመራል፡፡

የተፈለጠው እንጨትም በቡድን ወደበራፍ ተግዞ በተለየ ስልት (መሳሊ ናረተ) በሚል ስያሜ ይከመራል፡፡ የመሳላ እንጨት ክምር በአሠራሩ ለየት ያለ በመሆኑ ለተመልካች ሁሉ የመሳላን ድባብ ያመጣል፡፡

በቤተሰብ ደረጃ ያሉ ሴቶች ለሚከበረው በዓል ስጋ መብያ የሚሆንና ለበዓሉ ማድመቂያ፤ የበዓሉም አካል ለሆነው አተካኖ ዝግጅት የሚውል ቆጮ የመሳላ እርድ በሚፈጸምበት ቤት ሐምሌ 1 ቀን አሃዱ ብለው ማከማቸት ይጀምራሉ፡፡

‎ቀጣዩ ሣምንት አሥረኛ ሣምንት “ቶርዱሜ ሰነ” በመባል ይታወቃል፡፡ ቶርዱሜ ሰነ ማለት ለአዲሱ መሳላ አሥር ሣምንታት (ሰናከት) እንደቀሩ ማብሰሪያ ቃል ሲሆን፣ ከወዲህ ደግሞ የመኸር ወቅት እህል ለመዝራትና የማሳ ዝግጅት ለማድረግ ተጨባጭ ሰዓቱን ማረጋገጫ ስሌትም ነው፡፡

‎ከዚህ አቆጣጠር ለሰዓታት ዝንፍ ያለ አዝመራ ውጤቱ እያሽቆለቆለ እንደሚሄድ አርሶ አደሮች ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ቀጥሎ የሚመጡት ዘጠነኛ ሳምንት (ሆንሴ ሰነ) እና ስምንተኛ ሳምንት (ሄዜቴ ሰነ) ሲሆኑ፣ በእነዚህ ሳምንታት የዘርና የመሳላ በዓል ዝግጅት ሥራዎች በከፍተኛ ውጥረትና ጥድፍያ ይሠራሉ፡፡

‎ቀጥሎም የነሐሴ ወር አራት ሣምንታትን (ሰናከተ) ይዞ ይገባል፡፡ ሣምንታቱም ሰባተኛ ሣምንት (ለመሌ ሰነ)፣ ስድስተኛ ሣምንት (ሌሄ ሰነ)፣ አምስተኛ ሣምንት (ኦንቴ ሰነ) እና አራተኛ ሣምንት (ሾሌ ሰነ) ሲሆኑ በእነዚህ ሣምንታትም ዘር የመዝራትና የመጪው አዲስ ዓመት በዓል መሳላ ዝግጅት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

‎ሦስተኛ ሳምንት (ሰሴ ሰነ) ጳጉሜን ላይ የሚውል ሲሆን፣ ሁለተኛ ሳምንት (ለሜ ሰነ) ለመሳላ በዓል ሁለት ሣምንት ስለመቅረቱ ማሳያ ሆኖ ይህ ሣምንት እንግጫ የሚለቀምበት፤ ከለጋ ስንደዶ ኮንዴና ወከሌ የሚሠሩበት እንዲሁም ለመሳላ በዓል የሚሆኑ ግብዓቶች የሚቀራረቡበት ጊዜ ነው፡፡

‎አንደኛ ሣምንት (መቴ ሰነ) ከሁለተኛው ሣምንት ማብቂያ ጀምሮ መስከረም 16 ቀን የሚደመደም የአሮጌው ዓመት የመጨረሻው ሣምንት ነው፡፡ ይህ ሣምንት መሳላን የሚመለከቱ በርካታ ጉዳዮች የሚፈጸሙበት በመሆኑ ልጆች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና ወንዶች በተለያዩ ሥራዎች የሚጠመዱበት ነው፡፡

መሳላ የሚከበርበት ቀን በከምባታ ምድር የአዲስ ዓመት ጅማሮ፣ የአዲስ ዕቅዶች መሠረት፣ የአዳዲስ ትልሞች መግቢያ በር እና መተሳሰብ፣ መረዳዳት፣ ተሃድሶ፣ እርቅ፣ ሠላም፣ ደስታ እና መልካም ምኞት ሲቀዱበት የኖረ የዘመናት ምንጭ ነው፡፡

‎መሳላ አሮጌው ዓመት አልፎ አዲሱ አሃዱ ብሎ የሚጀምርበት ከ11 ሣምንታት ልፋትና ድካም የሚታረፍበት፣ ሀሴትም የሚደረግበት ልዩ ቀን ነው። መሳላ የእረፍትም የሀሴትም ምልክት መሆኑን የከምባታ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

“አንድ ሀገር አባል ባልሆነበት ስምምነት ሊገደድ አይችልም” — ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ**********************የ1929 እና የ1959 የዓባይ ውኃ ስምምነቶች የላይኛውን የናይል ተፋ...
17/09/2026

“አንድ ሀገር አባል ባልሆነበት ስምምነት ሊገደድ አይችልም” — ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ
**********************

የ1929 እና የ1959 የዓባይ ውኃ ስምምነቶች የላይኛውን የናይል ተፋሰስ ሀገራት ያላካተቱ በመሆናቸው በእነዚህ ሀገራት ላይ አስገዳጅ የሕግ መሠረት ሊሆኑ እንደማይችሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ ገልጸዋል።

የ1929 ስምምነት በግብጽ እና በብሪታንያ፣ እንዲሁም የ1959 ስምምነት በግብጽ እና በሱዳን መካከል የተደረጉ ሲሆን፣ የናይል ተፋሰስን የሚጋሩ ሌሎች ሀገራት የስምምነቶቹ ተዋዋይ ወገኖች አልነበሩም።

በመሆኑም ስምምነቶቹ ሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት ያካተተ አጠቃላይ የውኃ አስተዳደር ሥርዓት እንዳልዘረጉ ከኢቲቪ እንግሊዝኛ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል።

“አንድ ሀገር ተዋዋይ ወገን ባልሆነበት ስምምነት ሊገደድ አይችልም” የሚለው መርሕ በዚህ ጉዳይ ላይ ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ፕሮፌሰሩ፤ የዓባይ ውኃ በአንድ ወይም በሁለት ሀገራት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን በበርካታ ሀገራት የሚጋራ የጋራ የተፈጥሮ ሀብት መሆኑን ፕሮፌሰር ያቆብ አስረድተዋል።

በተፋሰሱ የላይኛው ክፍል የሚገኙ ሀገራት ለዓባይ ውኃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ቢያደርጉም በውኃው ላይ "ብቸኛ መብት አለን" የሚል ጥያቄ እንደማያነሱ ጠቅሰው፣ የውኃ ሀብቱ በሁሉም ተፋሰስ ሀገራት ትብብር መልማት እንዳለበት አመልክተዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ለዓባይ ውኃ ከፍተኛውን ድርሻ የምታበረክት በመሆኗ፣ የተፋሰሱ ሀገራት የውኃ ሀብታቸውን በጋራ ለማልማት እና ለሁሉም በሚጠቅም መልኩ ለመጠቀም የትብብር መንገድ መከተል እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብም የዚህ የውኃ ሀብት ልማት እና የተፋሰሱ ሀገራት ግንኙነት ዋነኛ ማሳያ ነው።

በአሁኑ ወቅት በሙሉ አቅሙ ኃይል በማመንጨት ላይ የሚገኘው ይህ ግድብ በራሷ ግዛት ውስጥ የተገነባ በመሆኑ፣ የውኃ ሀብቷን ማልማት ከሉዓላዊነቷ ጋር የተያያዘ ተፈጥሯዊ መብት መሆኑ ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በግድቡ አሞላል እና አሠራር ላይ ለዓመታት ድርድር ማድረጋቸውን ያወሱት ፕሮፌሰር ያቆብ፤ ኢትዮጵያ የሀገራቱን ሉዓላዊነት የሚያከብር የጋራ ተጠቀሚነት መርሕን እንደምትከተል አስገንዝበዋል።

የግድቡ አሞላል በዝናብ ወቅት በሚገኘው የውኃ ትርፍ ላይ የተመሠረተ እንደነበረ እና በአሁኑ ወቅትም ውኃው በተርባይኖች በኩል አልፎ ኃይል እያመነጨ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል፡፡

በውኃ ፍሰት ላይ የሚነሱ ክርክሮች በተጨባጭ መረጃ እና በሳይንሳዊ ጥናት መመራት እንዳለባቸውም አብራርተዋል።

የዓባይ ጉዳይ በታሪካዊ ስምምነቶች ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ሁሉንም የተፋሰሱን ሀገራት ባሳተፈ የጋራ ውይይት፣ ትብብር እና በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆች ላይ በተመሠረተ አቀራረብ መመራት እንዳለበት ፕሮፌሰር ያቆብ አርሳኖ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በኢንቲሃድ አብራር

17/09/2026


#አፍሪካ !!

የተግባር መምህር የህዝብ ልጅ እና የጽናት ተምሳሌት ወንድምአለም ደሳለኝ (ወንድዬ)​በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ እውነተኛ ለውጥ የሚያመጡ አበጋዞች በንግግር ሳይሆን በተግባር፣ በስልጣን ጥማት ሳ...
17/09/2026

የተግባር መምህር የህዝብ ልጅ እና የጽናት ተምሳሌት ወንድምአለም ደሳለኝ (ወንድዬ)

​በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ እውነተኛ ለውጥ የሚያመጡ አበጋዞች በንግግር ሳይሆን በተግባር፣ በስልጣን ጥማት ሳይሆን በህዝብ ፍቅር፣ በራስ ወዳድነት ሳይሆን በራሳቸው መስዋዕትነት የሚለኩ ናቸው። ወንድምአለም ደሳለኝ (ወንድዬ) ደግሞ የዚህ እውነተኛ ህዝባዊ አገልጋይነት ፍጹም ማሳያና የዘመናችን ህያው ምሳሌ ናቸው።

​ወንድዬ ራሳቸውን ካወቁበት ጊዜ አንስቶ ሀሳባቸውም ሆነ ተግባራቸው ሙሉ በሙሉ ከአካባቢው ዕድገትና ከህዝብ ብልጽግና ጋር የተሳሰረ ነው። በአሁኑ ወቅት በKTZ OVC እና በHolit International ድርጅቶች የቃጫቢራ አካባቢ አስተባባሪ (ኮርዲኔተር) በመሆን በጤናው ዘርፍ፣ በልዩ ሁኔታ በትምህርቱ ዘርፍ ትውልድ የመቅረጽና ተስፋ የማስጨበጥ አመርቂና ስኬታማ ተግባር እያከናወኑ ይገኛሉ።

ወንድዬ በትምህርቱ ዘርፍ በድርጅታቸው በኩል እያከናወኗቸው ያሉ ዘመንን ተሻጋሪና አርአያነት ያላቸው ተግባራት የማህበረሰባችንን ተስፋ ከማለምለም አልፈው ሀገራዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ ናቸው። በጥራት፣ በውጤታማነትና በፈጠራ የታጀበው ይህ ታላቅ ስራቸው ከአካባቢው አልፎ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችን፣ የክልል እንዲሁም የዞን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ቀልብና ትኩረት እንደ ማግኔት የመሳብ ተአምር ሰርቷል።

​የወንድዬ የትምህርት ዘርፍ አሻራ በቀላሉ የሚታለፍ ሳይሆን፣ በከፍተኛ አመራሮች ዘንድ «እንደ ሀገር ልምድና ተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባው የላቀ የትውልድ ግንባታ ሞዴል» ተብሎ በወርቃማ ቀለም የተጻፈ ህያው ተግባር ነው። ይህም የእርሳቸውን አርቆ አስተዋይነት፣ የላቀ ህዝባዊ ፍቅርና የዓላማ ጽናት በግልጽ የሚያሳይ አሸናፊ ስብዕናቸው ነው።

ወንድዬ አገልጋይነታቸው የዛሬ ብቻ ሳይሆን የትላንት ጠንካራ መሠረት ያለው ነው። ከብዙ በጥቂቱ ለማውሳት ያህል በ2007 ዓ.ም በሺንሽቾ ከተማ የተከናወኑትን እጅ በአፍ የሚያስጭኑ የህብረተሰብ ተሳትፎ የልማት ሥራዎች በማንቀሳቀስ ረገድ የልማቱ ዋና ሞተርና መሪ ነበሩ።

​ወንድዬ ላመኑበት በጎ ዓላማ እስከመጨረሻው የሚቆሙ፣ ሀቀኛና ቆራጥ ናቸው። በእርሳቸው ዘንድ መስራትና ማሳየት እንጂ ከንቱ ድካም የለም፤ በሥራቸው ሁሌም ለሌሎች መምህር ናቸው።

ወንድዬ እውቀታቸው፣ ልምዳቸውና አመለካከታቸው በእግዚአብሔር ከተሰጣቸው አንደበተ ርቱዕነት ጋር ተጣጥሞ ከአፋቸው የሚወጣው እያንዳንዱ ቃል መሬት ሳይወድቅ የሰውን ልብ የሚያንቀሳቅስ፣ ለልማትና ለበጎ ነገር የሚያነሳሳ ተፅዕኖ አለው።

​ወንድዬ የስልጣን ጥማትና «እኔ ብቻ ልጠቀም» የሚል የልጅነት ልክፍት ፈጽሞ የሌለባቸው፣ ይልቁንም ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠትና ጎድተው እንኳን ለሌላው የሚኖሩ የእውነተኛ ህዝባዊነት ተምሳሌት ናቸው።

​ወንድዬ በአላማ የታሰሩ፣ የሀገራቸውንና የአካባቢያቸውን ትውልድ በላቀ ደረጃ ለማየት የተራቡና የተጠሙ የፅናት ሰው ናቸው።

​ወንድምአለም ደሳለኝ (ወንድዬ) ላበረከቱት ታላቅ አገልግሎት፣ ላሳዩት መተኪያ የሌለው ፍቅርና መስዋዕትነት በየትኛውም ደረጃ የሚሰጥ የክብር ሽልማትና እውቅና ሙሉ በሙሉ የሚገባቸው፣ የትውልድ አርአያና የማህበረሰባችን የቁርጥ ቀን ልጅ ናቸው!

🙏❤🙏

LIGHT MEDIA 30

የጨዋታ አሰላለፍ ! 7:00 ኢትዮጵያ ከ ሩዋንዳ ⏩ ከ 20ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣርያ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታ።
17/09/2026

የጨዋታ አሰላለፍ !

7:00 ኢትዮጵያ ከ ሩዋንዳ

⏩ ከ 20ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣርያ ውድድር የመጀመሪያ ጨዋታ።

17/09/2026

እመኑኝ ማይክል ካሪክ ማንችስተር ቤት ውስጥ ይነግሳል !

ዛሬ በደቡብአፍሪካ ምን ምን ተሰማ!!────────────────────────────────────1.በደቡብ አፍሪካ ጋውተንግ ግዛት የሴቶች ግድያ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ደረሰ─────────────...
16/09/2026

ዛሬ በደቡብአፍሪካ ምን ምን ተሰማ!!
────────────────────────────────────

1.በደቡብ አፍሪካ ጋውተንግ ግዛት የሴቶች ግድያ አስደንጋጭ ደረጃ ላይ ደረሰ
────────────────────────────────────
በደቡብ አፍሪካ ጋውተንግ ግዛት ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ስድስት ሴቶች በተከታታይ መገደላቸው በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
የቅርብ ጊዜው አስከሬን በዛሬው ዕለት መገኘቱን ተከትሎ፣ጉዳዩ በደቡብ አፍሪካ መገናኛ ብዙሃን ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል።

2.የጆሃንስበርግ ከተማ አስተዳደር መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች ህጋዊ ፈቃድ እንዲኖራቸው እና አካባቢን እንዲጠብቁ አሳሰበ
────────────────────────────────────
የጆሃንስበርግ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ የሚንቀሳቀሱ መደበኛ ያልሆኑ ነጋዴዎች (Informal Traders) የከተማዋን ህግና ደንብ በማክበር ንግዳቸውን እንዲያከናውኑ ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሰጠ ተሰምቷል።

እንደ ከተማ አስተዳደሩ መግለጫ ፣ ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው ወይም በተፈቀደላቸው ቦታዎች ውጪ የሚነግዱ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ተገልጿል።

ነጋዴዎች ንግዳቸውን በህጋዊ መንገድ ለመጀመር በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የአካባቢ ማዘጋጃ ቤት አስፈላጊውን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባቸው ተጠቁሟል።

3.በጆሃንስበርግ የፖሊስ መኮንኖች በከፍተኛ የገንዘብ ዝርፊያ ወንጀል ከስራ ታገዱ
────────────────────────────────────
በእ.ኤ.አ በ2021 ተፈጽሟል በተባለ የጠለፋ እና የ5 ሚሊዮን ራንድ የዝርፊያ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት የጆሃንስበርግ ሜትሮ ፖሊስ (JMPD) መኮንኖች ዛሬ ከስራ እንደታገዱ ተገልጿል።

4.በሌናሲያ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን በመቃወም ነዋሪዎች አደባባይ ወጡ
────────────────────────────────────
ዛሬ በጆሃንስበርግ ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው ሌናሲያ፣ ሜሪቲንግ ዋርድ ነዋሪዎች ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በመቃወም ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ መንገዶችን በድንጋይ እና ጎማዎችን በመቀጠል እና በመዝጋት፣ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግሩ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንደጠየቁ ተዘግቧል።

ETHIO777
LIGHT MEDIA 30

Address

Gimbi
PAPY_17

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when LIGHT MEDIA 30 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share