Doitamie Productions

Doitamie Productions Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Doitamie Productions, Advertising/Marketing, Hossana.

🇪🇹 አዲሱ ትውልድ ቋንቋውንና ባህሉን አውቆ እንዲያድግ እንሰራለን።
🎯ለተለያዩ ኩነቶች (Events)፣ ለምርቃት፤ ለባህለዊ ፕሮግራሞች፤ ለሰርግ፤ ለሽምግልና እና ወዘተ.... በ 0935156114 ይደውሉልን!!
የተለየ ተሰጥኦ እና ታለንት ያላቸውን ወጣቶች በማሳተፍ አቅማቸውን እናወጣለን።
✨ ባህልና ቋንቋን ለትውልድ ማሻገሪያ የሚዲያ መድረክ!

20/09/2026

አርቲስት ካሳውን ለማ

በወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል ያደረግነው ቆይታ በፎቶከዚሁ ጋር በተያያዘም የደመራ መቃጠል ሥነ-ሥርዓት የበዓሉን ድባብ ውብ አድርጎታል።🔥የዚህን ውብ ቆይታና የደመራ ሥነ-ሥርዓት ትዝታዎች ...
20/09/2026

በወጣቶች ስብዕና ግንባታ ማዕከል ያደረግነው ቆይታ በፎቶ

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የደመራ መቃጠል ሥነ-ሥርዓት የበዓሉን ድባብ ውብ አድርጎታል።🔥
የዚህን ውብ ቆይታና የደመራ ሥነ-ሥርዓት ትዝታዎች በፎቶ። 📷✨

በተጨማሪም የአታከና ግብዣ ተደርጎልን፣ የተለያዩ ባህላዊ ምግቦችን በመመገብ የአካባቢውን ባህልና የእንግዳ ተቀባይነትን በተግባር ተመልክተናል። 🍽️✨

Doitamie Productions@followers
#ዶይታሜሚድያ #ያሆዴ2019 #ያሆዴ

እነሆ በታላቅ ድምቀት እንደ ሆሳዕና ከተማ ስከበር የነበረው የያሆዴ በአል ፍጻሜውን አገኝ። በአሉ እጅግ በርከታ ሰዎች በተገኙበት በሽማግሌዎች ገራዶች እና ዳኞች ምርቃት ተጀምሮ በገመራ ተጠና...
19/09/2026

እነሆ በታላቅ ድምቀት እንደ ሆሳዕና ከተማ ስከበር የነበረው የያሆዴ በአል ፍጻሜውን አገኝ።
በአሉ እጅግ በርከታ ሰዎች በተገኙበት በሽማግሌዎች ገራዶች እና ዳኞች ምርቃት ተጀምሮ በገመራ ተጠናቋል።

የሆሳዕና ከተማ ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ትንሳኤ ታደሰ ፕሮግራሙን በንግግር ከፍተዋል። አያይዘውም በያሆዴ በአል የእያንዳንዱ ሰው ድርሻ ምን እንደሆነ በማብራራት ሁሉም ሰው ይህንን የሀድያን ብሔር ዘመን መለወጫ ያሆዴን መጠበቅ እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተዋል ።

በእለቱ የተገኙት የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ ሆሳእና ከተማ በ2018አ.ም ላይ ከ20ኛው የብሔር ብሔረሰብ በአል አንስቶ እጅግ በርካታ ሀገራዊ እና ክልላዊ ፕሮግራሞችን ተቀብላ በሚደንቅ ብቃት ተወጥታለች። ይህም የከተማዋን እና የማህበረሰቡን ፈጣን እድገትን ያሳያል ነው ያሉት።

አያይዘውም "የያሆዴ " በአልን በዩኔስኮ(UNESCO ) ለማስመዝገብ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።

የያሆዴ በአል መስከረም 12/01/19 ላይ በተንጣለለው ሀድይ ነፈራ ላይ በታላቅ ድምቀት እንደምከበርም ተወስተዋል።
#ዶይታሜሚድያ #ያሆዴ

የመጨረሻው ቀን 3 እነሆ በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው የያሆዴ...
19/09/2026

የመጨረሻው ቀን 3 እነሆ በጀግናው ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ያዘጋጀው የያሆዴ በአል ነው። ከገራዶች እስከ ዳኞች እንዲሁም ከወጣቶች እስከ አዛውንት እንዲህ ደምቀው ተገኝተዋል።

ዶይታሜ ሚድያ የፕሮግራሙን ድባብ እየተከታተለ ለተከበራችሁ እና ለተወደዳችሁ ተመልካቾቻችን የምናደርስ ይሆናል።

አብራችሁን ቆዩ።

19/09/2026

Part #1
Ella Hotel and Resorts

የ2019 ያሆዴ በዓል | የኤላ ሆቴል የቀን 2 መርሃ ግብር በድምቀት ተጠናቀቀ! 🎊የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ያሆዴን አስመልክቶ በኤላ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የበዓሉ የቀን 2 መርሃ ...
19/09/2026

የ2019 ያሆዴ በዓል | የኤላ ሆቴል የቀን 2 መርሃ ግብር በድምቀት ተጠናቀቀ! 🎊

የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ያሆዴን አስመልክቶ በኤላ ሆቴል ሲካሄድ የቆየው የበዓሉ የቀን 2 መርሃ ግብር በተለያዩ ባህላዊ ዝግጅቶች፣ በፋሽን ሾው እና በልዩ ልዩ ትዕይንቶች ታጅቦ በድምቀት ተጠናቋል።

🌿 በሽማግሌዎች ምርቃት ተጀመረ

መርሃ ግብሩ በሀዲያ ሽማግሌዎች ምርቃትና መልካም ምኞት በይፋ ተጀምሯል። በዕለቱም የሀዲያን ባህልና ማንነት የሚያንፀባርቁ በርካታ ዝግጅቶች ቀርበዋል።

👗 ያሆዴ ፋሽን ሾው

የሆሳዕና ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከሄቨን ኢቨንትስ ዲኮር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ያሆዴ ፋሽን ሾው የዕለቱ ዋነኛ መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ ነበር።
የውድድሩ ዓላማ ከውበትና ከውድድር ባሻገር፣ የሀዲያ ብሔርን ባህል፣ ባህላዊ አልባሳትና ማንነት ለማስተዋወቅና ለማሳወቅ መሆኑ ተገልጿል።

👥 ከፍተኛ ባለሥልጣናትና እንግዶች ተገኝተዋል

በመርሃ ግብሩ ላይ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የሀዲያ ሽማግሌዎች፣ ባህል አፍቃሪዎች፣ ተጋባዥ እንግዶችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

🗣️ የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ትንሳኤ ታደሰ እንደገለጹት፣ የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ የሀዲያን ማንነት የሚገልጹ የተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎችን በማዘጋጀት የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓልን ለሌሎች ማስተዋወቅ ነው።

🏛️ ያሆዴን ወደ ሀዲይ ነፈራ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ ለ2019 ያሆዴ በዓል መልካም ምኞታቸውን ካቀረቡ በኋላ፣ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓልን ከአዳራሽ ወጥቶ “ሀዲይ ነፈራ” በሚል ስያሜ ህዝባዊ በዓል ለማድረግና በዩኒስኮ ለማስመዝገብ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

🏅 የእውቅናና የምስጋና ሰርተፍኬት

በመጨረሻም ከመርሃ ግብሩ አዘጋጆች ለፋሽን ሸው አቅራቢዎች እና ሞዴሎች እንዲሁም ለመድረክ አጋፋሪዎች የእውቅናና ምስጋና ሰርተፍኬት በመስጠት የቀን 2 መርሃ ግብር ተጠናቋል።
🌿 ያሆዴ — የሀዲያ ማንነት፣ ባህልና ትውፊት! 🌿
የሀዲያን ታሪክ፣ ባህልና ማንነት ወደ ዓለም! 🇪🇹

#ዶይታሜሚድያ@followersDoitamie Productions

🌟 የ2019 ያሆዴ አስገራሚ ክንውኖች ቀጥለዋል! 🎉 ቀን 2 — መስከረም 8/01/2019📍 ኤላ ሆቴል እና ሪዞርት — ሆሳዕናየሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ያሆዴ 2019 አስደሳችና አስገ...
18/09/2026

🌟 የ2019 ያሆዴ አስገራሚ ክንውኖች ቀጥለዋል!

🎉 ቀን 2 — መስከረም 8/01/2019
📍 ኤላ ሆቴል እና ሪዞርት — ሆሳዕና

የሀድያ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል ያሆዴ 2019 አስደሳችና አስገራሚ በሆኑ የተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
👗✨ ዛሬ በኤላ ሆቴል እና ሪዞርት ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ አስደናቂ የፋሽን ሾው (Fashion Show) መርሃ ግብር ተጀምሯል።
በዚህ የፋሽን ሾው ላይ የተለያዩ ዲዛይነሮች ያዘጋጇቸውን ውብና ፈጠራን የተላበሱ የፋሽን ሥራዎች በመድረኩ ላይ እያቀረቡ ይገኛሉ። የባህልና የዘመናዊ ፋሽን ጥምረትም የዝግጅቱን ድምቀት አሳድጎታል። 👗🌿
በዝግጅቱም የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ጨምሮ በርካታ ታዋቂ እንግዶችና የተጋበዙ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
🤝 ይህ ድንቅ መርሃ ግብር የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ከተለያዩ አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።

💚💛❤️ ያሆዴ — ባህልን የምናከብርበት፣ ትውፊትን የምናስቀጥልበት፣ ፈጠራን የምናበረታታበት!
📸 ከዝግጅቱ ተጨማሪ የፎቶና የቪዲዮ ዘገባዎችን በዶይታሜ ሚድያ ይጠብቁ!
#ያሆዴ2019
#ያሆዴ



#ዶይታሜሚድያ

17/09/2026

Fashion Exhibition!!

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ከ ሄቨን ኢቨንትስ & ዲዛይን ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን የሆሳዕና የፋሽን ኤግዚቢሽን (Fashion Exhibition).
Doitamie Productions

🎉✨ ባህልን፣ ፋሽንንና አንድነታችንን በአንድ ላይ የምናከብርበት ልዩ መርሃ ግብር! ✨🎉የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ከ ሄቨን ኢቨንትስ & ዲዛይን ጋር በመተባበር የ...
17/09/2026

🎉✨ ባህልን፣ ፋሽንንና አንድነታችንን በአንድ ላይ የምናከብርበት ልዩ መርሃ ግብር! ✨🎉

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ጽሕፈት ቤት ከ ሄቨን ኢቨንትስ & ዲዛይን ጋር በመተባበር የተዘጋጀውን የሆሳዕና የፋሽን ኤግዚቢሽን (Fashion Exhibition) በታላቅ ደስታ አቅርቦላችኋል! 👗🧵✨

ይህ ልዩ ኤግዚቢሽን የ2017 ዓ.ም የሀድያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓልን (Yaahode hadiyyi giichch dooll dabassanch uguda) ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የብሔሩን ሀገር በቀል የፋሽን ጥበቦች፣ ባህላዊ አልባሳትና የፈጠራ ሥራዎችን በደመቀ ሁኔታ የሚያስተዋውቅ ነው። በተጨማሪም እነዚህ የባህል አልባሳት ከወትሮው በታላቅ ቅናሽ ለሽያጭ ቀርበዋል።

📍 አድራሻ/ቦታ፦ ሆሳዕና — በሀድያ ባህል አዳራሽ ፊት ለፊት በሚገኘው ኮብልስቶን መንገድ ላይ

ይምጡ! የባህል አልባሳቱን ውበት ይጎብኙ፤ የሀገር ውስጥ ባለሙያዎችን ያበረታቱ፤ በዓሉንም አብረን በደስታ እናክብር! 🇪🇹💫

Productions #ዶይታሜሚድያ #ያሆዴ2019

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doitamie Productions posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share