የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Silt'e
  • የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን
Warabe City Administration Youth's Federation

23/05/2026
22/05/2026
22/05/2026
21/05/2026
‎የክልሉ ወጣቶች ሰላምን በማረጋገጥ፣በምርጫው በመምረጥና በማስመረጥ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ‎‎ሆሳዕና፦ግንቦት 13/2018‎‎የክልሉ ወጣቶች የምትፈራ፣የምትከበር፤ተሰሚነት ያላ...
21/05/2026

‎የክልሉ ወጣቶች ሰላምን በማረጋገጥ፣በምርጫው በመምረጥና በማስመረጥ የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

‎ሆሳዕና፦ግንቦት 13/2018

‎የክልሉ ወጣቶች የምትፈራ፣የምትከበር፤ተሰሚነት ያላት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት በሁሉም ዘርፍ የተቀናጀ ርብርብ እንዲያደርጉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ።


‎የጋራ ምክር ቤቱ የወጣቶች ክንፍ በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የወጣቶች ሚና በሚል ርዕሰ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው።

‎በምክክር መድረኩ የተገኙት የክልሉ የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ደምስ ገብሬ ፣7ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ወጣቶች የአንበሳውን ድርሻ መውሰድ አለባቸው ብለዋል።

‎ሰላም ቁልፍ ጉዳይ ነው፣ስለሆነም ሰላምን በማረጋገጥ ጉዳይ ወጣቱ በማስተዋልና በቁርጠኝነት መንቀሳቀስ እንዳለበትም አሳስበው፤ወጣቱን ለግጭትና ለዕኩይ አላማ ማስፈጸሚያ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን መታገል እንደሚገባም አመላክተዋል።

‎ምርጫው ሀገራችንን አንድ ደረጃ ከፍ የሚያደርግና
‎ለዴሞክራሲ መሰረት የሚጥል እንዲሆን ወጣቱ መረባረብ እንዳለበት አቶ ደምስ አሳስበው፣ተፎካካሪዎች ለአንድ ሀገር እንደሚወዳደሩ አውቀው በሃላፊነትና በትብብር መንፈስ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።


‎የጋራ ምክር ቤቱ ወጣቶች ክንፍ ሃላፊ ወጣት መብራት ደገፈ፣ተሳስበንና እጅ ለእጅ ተያይዘን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት መረባረብ ተገቢ ስለመሆኑ ተናግሯል።

‎ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ ሀገርን ዛሬ የሚገነቡ ናቸው ያለው ወጣት መብራት፣የክንፉ ወጣቶች 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፉጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የድርሻውን እንደሚወጣም አስታውቋል።

‎ክልሉ በሰላም ጉዳይ ሞዴል ነው፣የጋራ ምክር ቤቱም እንደ ሀገር ተሞክሮ የሚወሰድበት ስለመሆኑም ያብራራው ወጣት መብራት ደገፈ፣ሁሉም የክልሉ ወጣቶች ልዩነትን ወደጎን በመተው ለጠንካራ ክልልና ለበለጸገ ሀገር ግንባታ በጋራ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርቧል።

‎በመድረኩ የመወያያ ሰነድ ያቀረበው የጋራ ምክር ቤቱ ወጣቶች ክንፍ ምክትልና የክልሉ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወጣት አብዱ ድንቁ፣
‎የሀገራችንም ሆነ የክልላችን ወጣቶች ለውጡን ለማምጣትና ለውጡን ለማጽናት እስከ ህይወት መስዋዕትነት የጠየቀ ዋጋ መክፈላቸውን ገልጿል።

‎የለውጡ መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በፖሊሲ የተደገፉ ጥረቶች እያደረገ እንደሚገኝም አስታውቆ፣ወጣቱ በስነ ምግባር ታንጾ ሀገሩን በመውደድ የዜግነት ግዴታውን መወጣት እንዳለበት አመላክቷል።

‎ምርጫና ወጣቶች የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደሆኑም ያስታወሰው ወጣት አብዱ፤በመመረጥና በመምረጥ፣ምርጫውን በመታዘብ ፣በበጎ ፈቃድ ስራዎች በመሳተፍና ራስን ለህዝብ ጥቅም በመስጠት የተጀመረው ሀገራዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ መረባረብ እንደሚገባ አስገንዝቧል።

‎መንግስት በአንድ እጁ የሰላምንና የልማት ስራዎችን በሌላ እጁ ደግሞ የምርጫ ስራዎችን ለማሳካት በጽናት እየሰራ ይገኛል ያለው ወጣት አብዱ፣እነዚህን ጥረቶች ከዳር ለማድረስ ወጣቱ ሚናውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባውም አሳውቋል።

‎በሀገር ጉዳይ የጋራ አረዳድ መፍጠር፣ቅሬታዎችና አለመግባባቶችን በጠረንጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መፍታት፣ህግና ስርዓትን አክብሮ መንቀሳቀስ፣የጥላቻ ንግግሮችን መታገልና የመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ የክልሉ ወጣቶች ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩም አሳስቧል።

‎ወጣቱ ፍትሀዊ አሰራሮችን ማጎልበት እንዳለበትሞ ወጣት አብዱ አመላክቶ፤አንድነትን የሚበትነውን፣
‎ቤተሰብንና ሀገርን የሚያፈርሰውን የሀሰት መረጃ ወጣቱ በጽናት መታገል እንዳለበትም ጥሪ አቅርቧል።

‎በውይይት መድረኩ የክንፉ አባላት፣የወጣት ፌዴሬሽን አመራሮች፣የዞንና የልዩ ወረዳ የሚመለከታቸወ የወጣት አደረጃጀቶች አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

21/05/2026
ከአዲስ አበባ ወደ ስልጤ ዞን የተለለያዩ አካባቢዎች የኢድ-አልዓድሃ አረፋ በዓል ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በአዲስ አበባ አማራጭ የባስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ...
21/05/2026

ከአዲስ አበባ ወደ ስልጤ ዞን የተለለያዩ አካባቢዎች የኢድ-አልዓድሃ አረፋ በዓል ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በአዲስ አበባ አማራጭ የባስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ገለጸ።

የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ/Siltie Zone Transport & Road Dev. Department
ግንቦት 13/2018 ዓ.ም ወራቤ

የስልጤ ዞን ትራንሰሰፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የማኔጅመንት አካላት ከፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ፣ ከአዲስ አበባ መናሀሪያዎች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ትራንሰሰፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ጋር በአማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ውይይት አካሄደዋል።

በውይይቱ የተገኙት የ ስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር አብደላ እንዳሉት በስልጤ ማህበረሰብ ዘንድ የአረፋ በአል በድምቀት የሚከበር በዓል ሲሆን ይህንንም በዓል ለማክበር በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች ወደ ስልጤ ዞን በብዛት እንደሚከትሙም አስረድተዋል።

ወደ ሀገር ቤት በዓሉን የሚያከብሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ የማድረግ ስራ አጽኖት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነ አስረድተዋል።

በአሉ ለማክበር ከከተማ ወደ ገጠር የሚገቡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሳይቸገሩ ገብተው በአሉን አክብረው ቶሎ በመመለስ ግንቦት 24 የሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጠት እንዳለባቸውም አመላክተዋል።

የዘንድሮ የአረፋ በዓል ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ዞኑ ለሚገቡ ታዳሚዎች በአየር ጤና ፣በሉካንዳ ፣በየሺ ደበሌ ፣በካራቆሬ፣በቄራ ፣በጀሞ ፣በቤተል ፣በአለም ባንክ ፣በዘነበወርቅ፣በሎሚ ሜዳ ፣ በላምበረት እንዲሁም በሁለቱም አውቶቢስ ተራ መናሀሪያዎች ከግንቦት 16 ጀምሮ በመደበኛነት ባሶች ተመድበው አገልግሎት እንደሚሰጡም አብራርተዋል።

ተጓዦች በተቀመጡ የትራንስፖርት አማራጮች ሄደው በመሳፈር ካላሰፈላጊ ወጪና እንግልት እራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስበዋል።

የፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ የአነስተኛና መለስተኛ ተርሚናል መናሀሪያ ዴስክ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ሳንካታ እንዳሉት በአሉን ለማክበር ወደ አገር ቤት የሚገቡ የእስልምና እምነት ተከታዮች ያለምንም እንግልት ወደ አገር ቤት እንዲደርሱ ለማድረግ ከስልጤ ዞንና ከ ጉራጌ ዞኖች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የአረፋ በአል ለማክበር ወደ ቄያቸው የሚሄዱ እንግዶች ያለምንም ስጋት የተሽከርካሪ እጥረት ሳይኖር እንዲጓዙ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየሰሩ እንደሆነም አመላክተዋል።

ከማህበራቶች ጋር ውይይት ያደረጉ እንደሆነና የደቡብ ምዕራብ ክልሎች እንዲሁም ከስልጤ ዞን ጋር ውይይት በማድረግ የመኪና ውስንነት እንዳይገጥም ወደ ሌላ ቦታ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች የአረፋ በአል ለማክበር በብዛት የሚጓዙባቸው ባሶች ወደ ስልጤ ዞንና ጉራጌ ዞን የሚንቀሳቀሱ ታዳሚዎች እንዲያመላልሱ ይደረጋል ብለዋል።

በፌዴራል ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ የአየር ጤና የህዝብ ትራንስፖርት መናሀሪያ ሀላፊ አቶ ካሌብ አንቺሎ በበኩላቸው ከአረፋ በአል ጋር ተያይዞ በየአመቱ የበአሉ ታዳሚዎች በበዛት ወደ ትውልድ አካባቢያቸው ይጓዛሉ ብለዋል።

ለዚህ በአል የሚጓዙ የእስልምና እመነት ተከታዮች ከዚህ በፊት በኮንትራት መልክ ይወጡ የነበረ ሲሆን ኮንትራት ይዘው ከሚሄዱ መናሀሪያና በመደበኛነት በሚመደቡ የታታ ባሶች ላይ ተሳፍረው ካለምንም ብዝበዛና እንግልት በሰላም ወደ አካባቢያቸው መግባት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የሚጓዙ እንግዶች በሚኒባስ ኮንትራት ይዘው መሄድ እንደሌለባቸውና በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 16 ጀምሮ በተመደቡ ባሶች መሳፈር ይችላሉ ብለዋል።

#በአዲስ አበባ ባሶች የሚገኙበት ቦታዎች

✒️ በአየር ጤና
✒️ በሉካንዳ
✒️ በየሺ ደበሌ
✒️ በካራቆሬ
✒️ በቄራ
✒️ በጀሞ
✒️ በቤተል
✒️ በአለም ባንክ
✒️ በዘነበወርቅ
✒️ በሎሚ ሜዳ
በላምበረትና በሁለቱ መናሀሪያዎች ከግንቦት 16/2018 ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጡ እንደሆነም ተናግረዋል ።

ከስር ያሉትን የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም መረጃዎችን ያግኙ👇

21/05/2026

ስፖርት ያርዳዶይ ስነ-አህላቅ ባጥቃቅሎ አዘር ያለይ አትዋጫት ጢሺት የሮሬን!!

Part 29

21/05/2026

ስፖርት ያርዳዶይ ስነ-አህላቅ ባጥቃቅሎ አዘር ያለይ አትዋጫት ጢሺት የሮሬን!!

Part 28

21/05/2026

ስፖርት ያርዳዶይ ስነ-አህላቅ ባጥቃቅሎ አዘር ያለይ አትዋጫት ጢሺት የሮሬን!!

Part 27

Address

Werabe
Silt'e

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to የወራቤ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ፌዴሬሽን:

Share