Gifata Tube

Gifata Tube Wolaita worqa mayzana

16/08/2025

➽ግፍ የበዛበት እና መላ ያጣው የወላይታ ሀገረ ስብከት ጋንደባ በዓታ ለማርያም ጉዳይ
➽በቅድሚያ የበዓታ ጉዳይ ሲነሳ፤ እነዛ ከጅምር ጀምሮ ምንም ከሌለበት አንስቶ እንዲኖር ያደረጉ ካህናት ፥ሰበካ ጉባኤ አባላት እና ካላቸዉ ይዞታ ቆርሰዉ ለቤተ ክርስቲያን የሰጡ ምዕመናን ክብር ይገባችኋል። ሕይወታቸውን ፥ልጆቻቸውን፥ ሥራቸውን እግዚአብሔር ይባርክልን ።ከክፉ ነገር ሁሉ ፈጣሪ አምላካችን ይጠብቃቸው።
➽እነዚህ ሕዝቡን ሰብስቦ ቦታ አግኝቶ መቃኞ ሲሰሩ፥ለፊት ለፊቱ ቦታ ሲታሰሩ ፥ሲያንገላቱዋቸው፥ሲሰደዱ አልነበሩምን? እነሱ የሆኑትን የትኛዉ የቤተክህነቱ ባለ ስልጣን ሆኖ ተገኘ?
➽ከቤተክህነት የታሰረ ማነው?ገሚሶች ለምን ኋላ ሰራችሁ እያሉ የለፉትን ሲያሸማቅቁ የነበረው ሀገረ ስብከት አልነበረምን?
➽በ2014 ዓ.ም በቦታው ጥምቀተ ባህር እንዳናከብር ከባለስልጣን ጋር በመመሳጠር ወደ ኋላ ሄዳችሁ አክብሩ ያለን የሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ አመራር /ኃላፊ አልበረምን?➽ለጊዜው ስሙ ይቆይና፤ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም ያለ የመምሪያ ኃላፊ አልነበረም? ቦታውን በጀመሪያ እየተከሰስን ነው ብለን ችግር የለውም ክሱን እንዲቋረጥ አደርጋለሁ ብሎ ቤተክርስቲያን ተሸንፋ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንድትገባ ያደረገ የሀገረ ስብከቱ ኃላፊ አይደለምን? ስንቱ ይዘረዘራል???
➽ይህ ሳያንስ አሳፋሪ ድርጊት :
🇫🇷ይህንን ሁሉ ስራ ሸፍኖ ያለሕዝብ ፍላጎት እንደፈለጉት ማቡካት እና ለመጋገር መሞከር እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነው!!!
➽ብፁዕነታቸውም ቢሆኑም ሰድቦ ከማባረር ሰብስቦ መምከር አይሻልም። የለፉትን ማንም ሳይነግራቸው ያውቁ የለምን? ምን አጠፉ ቤተክርስቲያን ስለተከሉ ይሰደዳሉ? ምዕመናንን ሰብስቦ እንዳይጠፉ ስላደረጉ ? ሰፋ ያለ ቦታ ይዞ የወደፊት ራዕይውን ስላሰፉ ይሰደዳሉ?
➽ይህ ቦታ እንዴት ሆኖ እንደመጣ የምታውቁት ነገር የለም??? ካላወቃችሁ ከሚያውቁት መጠየቅ አይሻልም?
➽የትኛው የሀገረ ስብከት ሠራተኛ ነው በዚህ ቤተክርስቲያን እንስራ ብሎ ወርደው ሕዝብን ያስተባበረ ማነው?መልሱ አያሻማም -ማንም!
ታዲያ ትላንት የሌላችሁ ዛሬ ከየት መጣችሁ?ትላንት ያልተዘራ ዛሬ ከየት ይታጨዳል? በእንግልቱ ሰዓት ያልነበራችሁ ጣጣው ካለቀ በኋላ ለምን ክንዳችሁን አበረታችሁ! ለምን የዛሬ ዓመት/ ሳይት ፕላን ሳያልቅ ቀድማችው ሰበካውንና አስተዳዳሪውን አላነሳችኋቸውም? ለምን ጠበቃችሁ? ምን አደረጉ አብሯችሁ ስለማይጠጡ ? ስለማያበሏችሁ?ሙስና እጅ መንሻ ስለማይሰጡ?ስለማያቃጥሩ?
➽እነሱማ ለሰማይ ጽድቅ እንጂ በዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ የሉበትም! እስቲ ከእናንተ ውስጥ እንደ እነሱ የሰራችሁ ካላችሁ ንገሩን!
➽ብፁዕነታቸው እነዚህ አገልጋዮች እንዲህ ብለዋል ካሉ ፤ወሬውን ያደረሰውን አካል እና አገልጋዮችን ቁጭ አድርጎ መዳኘት፥መውቀስ አይቻልም?
➽ይህን ድርጊት የፈጸሙት የወላይታ ሀገረ ስብከት እና ሀገረ ስብከቱ የቀጠሯቸው አካላት ናቸው!!! እኛ ምዕመናን እኛን በዓታን እንደበተናችሁ እግዚአብሔር ይበትናችኋዋል። ይህ ሩቅ አይደለም! ከወላይታ ምዕመናን ጫንቃ እስከምትወገዱ ድረስ ትግላችንን አሁን እንጀምራለን!!!
➽ ከኪሳችን እና ከመቀነታችን በሰበሰብነው ገንዘብ ውስኪ ስትራጩ በገጠር ካልሲ መቀየር ያልቻሉ ካህናት ግፍ በሰማይ እግዚአብሔር ይመለከታል።ዝምም አይልም!!!
➽ብዙ ታግሰናል ባሪያ እና ጌታ/ከበርቴ እና ጢሰኛ ሆነን የኖርንበት ጊዜ ያከትማል!!!ለሁሉም ልክ አለው!
➽የሰላም ቀጠና የሆነዉን ጋንደባ በዓታ እንደበተናችሁ አትቀሩም!
➽መላው ኦርቶዶክሳዊያን!! የወላይታ ሀገረ ስብከት ችግር ተዘርዝሮ አያልቅም፤
እባካችሁ ከእውነት ጎን እንድትቆሙ በበዓታ ለማርያ

12/08/2025
01/08/2025

እነሆ ዛሬ (ቀን 25/11/2017ዓ/ም) አምስተኛ ቀን ያስቆጠረዉ በወላይታ ሀገረ ስብከት የጋንዳባ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ሮሮና ጩኸት እንደቀጠለ ነዉ፤ ይኸዉም የእኛ ጥያቄአችን🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
🍎ያለ ምዕመናን ፍላጎት በሀገረ ስብከቱ ጫና የተዋቀሩ ሰበካ ጉባኤ አይወክለንም አንሱልን፤
🍎እኛ መመራት የምንፈልገዉ በቋንቋችን ማስተማር በሚችል አስተዳዳሪ ነዉ፤ ያለ ሕዝቡ ፍላጎት በጫና የተመደበዉን አስተዳዳሪ አንሱልን፤ አንቀበልም፤
🍎በደብሩ ላይ ሀገረ ስብከቱ ያደረሰዉን በደል በተመለከተ ሽማግሌዎች ባሉበት በብፁዕነታቸዉ መሪነት ሀ/ስብከቱና ሰ/ጉባዔ አባላትን ቁጭ አድርገዉ በማወያየት በአስቸኳይ እንዲፈታልን፤
🍎ይኽ ሳይሆን ቀርቶ በእኛ በምዕመናን ቀጣይ አገልግሎት ላይ ለሚደርሰዉ የትኛዉም በደል በእንዝላልነት የቆየዉ ሀገረ ስብከቱ ተጠያቂ እንደሆነና፤ ወደ ቀጣይ መፍትሄ ሰጭ አካል ሄደን የደረሰብንን በደል የምናሳዉቅ መሆኑን
በአፅንዖት እንገልፃለን።

Viva!
12/11/2024

Viva!

939 likes, 45 comments. “ ❤️💛🇧🇪🇪🇹 ❤️💛🇧🇪🇪🇹 ❤️💛🇧🇪🇪🇹 ❤️💛🇧🇪🇪🇹 ”

Address

Infront Of Luturan Church
S**o

Telephone

+251916471616

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gifata Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Gifata Tube:

Share