21/09/2026
በወላይታ ውሃ ሥራዎችና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እየተገነባ ያለው የደቡብ ኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ባለ6 ወለል ሕንፃ ግንባታ የደረሰበት ደረጃ ተጎበኘ ።
መስከረም 11/2019 ዓ.ም | ወላይታ ሶዶ
የደቡብ ኢትዮጵያ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ከፍተኛ አመራሮች፣ አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ፣ በወላይታ ሶዶ የሚገነባውን ባለ6 ወለል የቢሮ ሕንፃ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።
ሕንፃው በወላይታ ውሃ ሥራዎችና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ እየተገነባ ሲሆን፣ በጉብኝቱ ወቅት የግንባታው ወቅታዊ አፈጻጸም፣ የሥራ ጥራት፣ የግንባታ ሂደት፣ የሥራ ፍጥነት እና ቀጣይ የሥራ እቅድ በዝርዝር ተገምግሟል።
በአሁኑ ወቅት የግንባታው አፈጻጸም 53 በመቶ የደረሰ ሲሆን፣ ሥራው በተያዘለት የሥራ መርሃ ግብር መሠረት በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። ተቋራጩም የግንባታ ጥራትን በማስጠበቅ፣ የሥራ ፍጥነትን በማሳደግና የተያዘውን የሥራ መርሃ ግብር በመከተል ግንባታውን ከውል ጊዜ ገደብ በፊት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
የቢሮ ሕንፃው ዘመናዊና ተግባራዊ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ ጂምናዚየም፣ የሕፃናት ማቆያ፣ ካፍቴሪያ፣ የመኪና ማቆሚያ እና ሌሎች አስፈላጊ የአገልግሎት ክፍሎችን ያካትታል።
በጉብኝቱ መጨረሻ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲጠናቀቅ፣ የግንባታ ጥራትና ደረጃ እንዲጠበቅ እና የሥራ አፈጻጸሙ በተጠናከረ ክትትል እንዲቀጥል አስፈላጊው ትብብርና ክትትል እንደሚደረግ ተገልጿል።
ወላይታ ውሃ ሥራዎችና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ —