04/09/2022
ብራቮ ቭላድሚር ቡቲን የድሀ አገሮች አለኝታ
እንደ ሩሲያ አውሮፓዊያንን እየተጫወተባቸው ያለ ሀገር የለም !
በጣም በሚገርም ሁኔታ የአውሮፓ የኢኮኖሚ ህልውና በሩሲያ መዳፍ ውስጥ ገብቶ ሩሲያ እንደፈለገች እያወዛወዘቺው ነው ቢባል ማን ያምናል ?
ጀርመንን የመሰለች የአውሮፓ የኢኮኖሚ ቁንጮ በአለምም አራተኛዋ ባለ ግዙፍ ኢኮኖሚ የመፀዳጃ ሶፍት ለማምረት ጭምር ጭንቅ ውስጥ እንደሆነችስ ማን ያምናል ?
እንግዲያውስ ነገሩ በእውኑ ተከስቷል ።
ቁማርተኛው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን አውሮፖችን ቀላል ቆመረባቸው እንዴ !!??
ሩሲያ ዩክሬይንን ስትወር አውሮፖች እንደ አደገኛ ነገር አጫወታቸውና በሩሲያ ላይ የማእቀብ ናዳ ማውረድ ጀመሩ ። በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች ቢሉ አሳጠረች እንዲሉ ለካስ አውሮፖች በሩሲያ ላይ ማእቀቡን ሲጥሉ በሩሲያ ላይ ሳይሆን በሪሳቸው ላይ ነበሩ እየጣሉ የነበሩት ። ራሳቸው ላይ ተኮሱ !
አሁን ሩሲያ በቀል ላይ ነች በቀል - አልኢንቲቃም አለ ሰአደዲን ኮቢክ 😁
እናም ሩሲያ አሁን ወደ አውሮፓ የምትልከውን ጋዝ ሙሉ በሙሉ ጥርቅም አድርጋ ዘግታዋለች - ሙሉ ለሙሉ ! የአውሮፓ ኢኮኖሚያ ማእበል እንደሚያናውጣት ጀልባ ከዚያ እዚህ እየተንገጫገጨ ነው ። የጋዝ ዋጋ በ በፊት ከነበረው በ 10 እጥፍ ጨምሮ አንዱ በርሜል 500 ዶላር ደርሶ ነበር አሁን ጨርሶ ሲዘጋ የት እንደሚደርስ መገመት አያዳግትም ።
ጀርመን አሁን ያላት ጋዝ ለማለቅ የሚፈጅበት ከ 3 ወር ያነሰ ብቻ ነው ። አውሮፓን ቀጣዩ እጅግ ብርዳማው የበጋ ወቅት አይኑን አፍጥጦ እየመጣላቸው ነው ። ካለ ጋዝ ያንን ወቅት ማለፍ አይቻልም ። ጀርመን ወይ ኢንዱስትሪዎቿን መዝጋት አለበት አሊያ ህዝቦቿን መስዋእት ማድረግ አለባት ።
ልብ በሉ !
የአውሮፓ መገበያያ ገንዘብ ዩሮ የቁልቁለት ጉዞውን ተያይዞታል ! የአውሮፓ የዋጋ ግሽበት የማይቀመስ ሆኗል ። ኢንዱስትሪዎቻቼው ለመዘጋት እየተዘጋጁ ነው ። አለምን የሚጠመዝዙባቸው የኢኮኖሚ ተቋሞቻቼው ሺባ ለመሆን እየተወላሸሹ ነው ። በማን የተባለ እንደሆነ በሩሲያ !
ማእቀብ ጣዮቹ በማእቀብ ሲቀጡ ማየት እንደት ደስ ይላል !
ብራቮ ሩሲያ ! ብራቮ ፑቲን !
ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial