Day To Day Tube

Day To Day Tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Day To Day Tube, Advertising/Marketing, 1313 13 Avenue sw, Nairobi.

06/05/2022

ይህ በምስሉ የምትመለከቱት ልጅ አብዱልዋሲዕ መሀመድኑር ይባላል። ልጁ የ14 አመት ታዳጊና በስልጤ ዞን አለም ገበያ ከተማ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነው።
ባለፈው ማክሰኞ ሚያዚያ 25/2014 ኢድአልፈጥር በተከበረ ማግስት ከቤተሰብ ጋር ሆኖ ኢዱን ካከበረበትና ዲላ ከሚገኘው የአክስቱ ቤት ጧት ለ1 ሰዓት 20 ጉዳይ አከባቢ ነጭ አፓቼ ሞተር እየነዳ የወጣ ሲሆን ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ቤተሰቦቹ በሞባይል ስልኩ ከመደወል ጀምሮ አለ ባሉት አማራጭ ሁሉ እየፈለጉ ቢሆንም ስልኩም አይሰራም ልጁንም ማግኘት አልተቻለም።
ስለሆነም ታዳጊ አብዱልዋሲዕ መሀመድኑርን ያገኛችሁ፣ ያያችሁ ወይም ያለበትን የምታውቁ ከታች በተዘረዘሩት ቁጥሮች ደውላችሁ ብታሳውቁን ወሮታውን ከፋይ ነን ይላሉ እጅግ በጣም የተጨነቁ ፈላጊ ቤተሰቦቹ።
የጥቆማ ስልኮች፣
09 11 55 95 24
09 16 17 42 38
09 16 26 85 11
በማናቸውም መልኩ ትብብር ለምታደርጉልን ሁሉ ከወዲሁ አላህ ኸይር ጀዛችሁን ይክፈላችሁ፣ እጅግ በጣም እናመሰግናለን!!!!

#ሼር

06/05/2022

በዳዮች ወዮላቸው

05/05/2022

ከወላጆቻቸው ጋር ተጠፍፍተው ከነበሩት ህፃናት መካከል ከአንድ ህፃን በስተቀር ሁሉም ህፃናት ከቤተሰባቸው. ጋር ተገናኝተው ቤተሰብ ወስዷቸዋል ::

አሁን የቀረችው በምስሉ ላይ የምትመለከቷት ታዳጊ ብቻ ናት:: ሜክሲኮ ተባረክ ጀርመን መስጂድ ነው ያለችው:: ልጅቷ ከሲዳምኛ ቋንቋ ውጪ መናገር አትችልም ። ቤተሰቦቿ ጀርመን መስጂድ ቢመጡ ያገኟታል ።

05/05/2022

ከለውጥ ወዲህ ብቻ በነበሩት ባለፉት 4 ዓመታት በአማራ ክልል ስልጣን ላይ በነበሩ አምስት የክልሉ ፕሬዝዳንቶች ዘመን በክልሉ ሙስሊሞች ላይ ከሞጣ እስከ እስቴ፥ከጃራ ገዱ እስከ ቢቸና፥ ከጭልጋ እስከ ጎንደር በተደጋጋሚ ጊዜ ሃይማኖትን መሠረት ባደረገ መልኩ ከሠላሣ በላይ መስጊዶች ሲቃጠሉና ሲጠቁ፥የሙስሊሞች ሱቆችና ቤቶች ተለይተው ሲዘረፉና በርካቶች በተገደሉበት በንጹሃን ሙስሊሞች ላይ የሽብር ጥቃቶች ሲፈጸሙ «ለእውነት፥ ለፍትህ፥ ለዲሞክራሲና ለሕግ የበላይነት ቆመናል» የሚሉት የደሴቷ ናፋቂ ሚዲያዎች ፥አክቲቪስቶች፥ጋዜጠኞች፥ የክልሉ ባለስልጣናት፥ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ሌሎች አካላት ጭምር አንዳቸውም ቢሆኑ የለበጣ «ድርጊቱ አስነዋሪ ነው።»፥ «እኛም አውግዘነዋል።»፥«የድርጊቱ ፈጻሚዎች ሕዝቡን አይወክሉም።» ፣«ከተማችን ወደ ቀድሞ ሰላሟ ተመልሳለች።» ወዘተ በማለት ለማድበስበስ ይሠራሉ።ዋናው ጥያቄና ጭብጥ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ማንን ይወክላሉ! የሚለው ሳይሆን ለፈጸሙት የሽብር ወንጀል ተጠያቂ ተደረጉ ወይ የሚለው ነበር።

ሆኖም ከጅምሩ ዓላማቸው የችግሩን መጠን ማቃለል ፣ለወንጀለኞቹ ሽፋንና ከለላ መስጠት፣ ለእውነትና ፍትህ ከመወገን የራስን የጠለሸ ስም ማደስ በመሆኑ የተፈጸሙት ወንጀሎች በተደጋጋሚ ጊዜ ሆነ ተብለው ተድበስብሰው ቀሩ።

ከዚያ ሁሉ ባለሚዲያ፣አክቲቪስት፣የመብት ተሟጋች፣ ጋዜጠኛ፣ታዋቂ ሰዎችና ሰባኪያን መካከል «የሽብር ጥቃቶቹ ጉዳዩ ሳይድበሰበስ በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ወንጀል ፈጻሚዎቹ ላይ አስተማሪ የሆነ ፍርድ ሊያገኙ ይገባል» ብሎ ለተግባራዊነቱ እስከመጨረሻው የሞገተና ለእውነት የቆመ አንድም አካል አላየንም። እንዲያውም ከፊሎቹ የሐሰት ዉንጀላዎቹን በመደገፍ ላይ ተጠምደው ተገኙ። በአንዱም የሽብር ጥቃት ላይ እንኳን የተሳተፉ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር ዉለው ፍርድ አግኝተው አለማወቃቸው በራሱ ችግሩ የተቀናጀና መዋቅራዊ መሆኑን ያስገነዝበናል። ለዚህም ነው በአሁኑ የጎንደር የሽብር ጥቃት ፈጻሚዎችም በተለመደው መንገድ «በቁጥጥር ስር ዋሉ» የሚለው ዘገባም የሽብር ፈጻሚዎቹ ጉዳይም እንደከዚህ ቀደሞቹ በዚያው በአማራ ክልል የሚታይ ከሆነ ዜናው ማስተኛ ኪኒን ከመሆን አይዘልም።

ለነዚህ ጥቃቶቹ ሁሉ ሽፋን ሲሰጡ፥ ጉዳዩቹን ለማቃለል ሲተጉ፥ ችግሮቹን ዉጫዊና የጠላት ሴራ አድርገው በማቅረብ ራሳቸውን ንጹህ ሲያደርጉ ለተበዳዮቹ ድምጽ በመሆኔ «አጋለጠን»፥«ልናፍነው የፈለግነውን ድምጽ እንዲስተጋባ አድረገ» በሚል ቁጭት የገዛ ወገኖቻቸው እስኪታዘቧቸው ድረስ እኔኑና መስሊሞችን መልሰው ለመወንጀል ተፍጨረጨሩ። እንደለመዱት የኔን ስምና ገጽታ ለማጠልሸት የፈጠራ ዜናዎችን በየጓዳዎቻቸው እየፈበረኩ በሚዲያዎቻቸው ተቀባበሉ።አሰራጩ።

በተቆጣጠሩዋቸው ሚዲያዎቻቸው በኩል በለመዱት የሀሰት ክስ ጋጋታ ላይ ተንተርሰው ጠልፎ የመጣል ዘመቻቸውን ጀመሩ።የማታውም ዶኪዩመንተሪ ተበዳይን የመክሰስ፣የጎንደሩን ጥቃት የማቃለልና የችግሩን ሥረ መሠረትን ከዋናው ሥፍራ ለማራቅ ዓላማን ያነገበና ከዚሁ የሚዲያ ጦርነት ጎራ የሚመደብ ነው።

ሚዲያውን የተቆጣጠሩት አካላት በዘገባዎቻቸውም ሆነ ዘጋቢ ፊልሞቻቸው፣ ስለጉዳዩ መግለጫ የሚሰጠው የመንግስት አካልም ለጎንደሩና መሰል የሙስሊሞች ጥቃቶችን ስላነሳሱት የሽብር ቅስቀሳዎች ከስር ባለው የቴሌግራሜ ቻናል( https://t.me/ahmedin99/4273 ) ላይ ስለተያያዙት ቪዲዮዎች እያወቁ እንዳላዩ ማለፍን መርጠዋል።ተሳክቶላቸው ጥቂት ወደነዚህ የሽብር ቅስቀሳዎች ቀረብ የሚል የጥቂት ሰከንዶች የኔን ቪዲዮ ወይም ድምጽን ቢያገኙ የዘወትር ጸሎት ያክል ደጋግመው ለሕዝባቸው ባሰሙም ነበር።

የቴሌግራም ቻናሌ ላይ የተያያዘውን ቪዲዮ ሊንኩን በመጫን ይመልከቱ። 👇

https://t.me/ahmedin99/4273

05/05/2022

Mashaa Allah

Address

1313 13 Avenue Sw
Nairobi
00517

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Day To Day Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Day To Day Tube:

Share