Mulugeta Anberber Gebeyaw

Mulugeta Anberber Gebeyaw አንበርብር

ዘመቻ አንሻ ሰይድ በይፋ ተጀምሯል!በግራራይ እና አቡነ ዮሴፍ ግንባሮች በተደረገ መጠነ-ሰፊ ፍልሚያ የአገዛዙ ጦር ክፉኛ ተመታ፤ እንጃፋት ከተማ ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ ሆነች!የብልፅግና አገዛ...
28/05/2026

ዘመቻ አንሻ ሰይድ በይፋ ተጀምሯል!

በግራራይ እና አቡነ ዮሴፍ ግንባሮች በተደረገ መጠነ-ሰፊ ፍልሚያ የአገዛዙ ጦር ክፉኛ ተመታ፤ እንጃፋት ከተማ ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ ሆነች!

የብልፅግና አገዛዝ ወታደራዊ መዋቅርና የምርጫ ማስፈጸሚያ ስልት በየቀጠናው በፋኖ ብርቱ ክንድ እየፈረሰ ባለበት በዚህ ወቅት፣ በሰሜን ወሎ ዞን በተቀጣጠሉ ሁለት አውደ ውጊያዎች ለአገዛዙ ሰራዊት መርዶ የሆነ ታላቅ ወታደራዊ ስብራት መገናኘቱ ታወቀ።

በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ ስር የሚንቀሳቀሰው 303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር፣ ዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም በግራራይ ግንባር እና አቡነ ዮሴፍ ሎጅ ግንባር በመግባት በወሰደው የተቀናጀና መብረቃዊ ጥቃት፣ በአካባቢው ሰፍሮ የነበረውን የአገዛዙን ጦር እንደ በረዶ አቅልጦታል።

ከዕዙ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ የተገኘው የፊት መስመር መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ውጊያው ከንጋቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ አመሻሹ 11:00 ሰዓት ድረስ ለሙሉ ቀን የቆየ ጽኑ ፍልሚያ ነበር።

የአገዛዙ ሰራዊት በመድፍ፣ በ107 ሮኬት፣ በዙ-23 ፀረ-አውሮፕላን መሣሪያ፣ በሞርተር 120 እና ሞርተር 82 የከበደ ሜካናይዝድ ታግዞ ምሽግ በመያዝ ብርቱ መከላከል ለማድረግ ቢሞክርም፣ የኮሩ አናብስቶች የጠላትን ስድስት ስልታዊ ምሽጎች አንድ በአንድ በመደርመስ የጠላትን ወታደራዊ ቅስም ሰብረዋል። በዚህ አንጸባራቂ ድል በተመዘገበበት አውደ ውጊያ ላይ የኮሩ 14ኛ፣ 16ኛ, 19ኛ፣ 21ኛ እና 30ኛ ክፍለ ጦሮች በግንባር ቀደምትነት ተሳትፈውበታል።

በዚህ መጠነ-ሰፊ ፍልሚያ የአገዛዙ ጦር እንጃፋት፣ ድልገን እና አቡነ ዮሴፍ ከተባሉ ይዞታዎቹ ሙሉ በሙሉ የተጠረገ ሲሆን፣ ስልታዊዋ እንጃፋት ከተማም ከአገዛዙ ሰራዊት ነፃ መውጣቷ ተረጋግጧል።

በዕለቱ የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ያስመዘገባቸው የድምሰሳ፣ የምርኮና የትጥቅ ስኬቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል፦

♦️የሰው ኃይል ኪሳራ፦ 3 ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች እና 236 የሰራዊቱ አባላት (በድምሩ 239) ሙሉ በሙሉ ተሸኝተዋል፤ 46 የአገዛዙ ወታደሮች ደግሞ በምርኮኛነት ተማርከዋል።

♦️የተማረኩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎች፦ 02 ድሽቃ፣ 03 ብሬን፣ 01 ስናይፐር እና 118 ዘመናዊ ጥቁር ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች በፋኖ እጅ ገብተዋል።

♦️የተማረኩ ተተኳሾችና የጦር ቁሳቁሶች፦ 3500 የብሬን ጥይት፣ 5400 የክላሽ ጥይት፣ 160 የድሽቃ ተተኳሽ፣ 26 የእጅ ቦምብ፣ 03 መገናኛ ሬዲዮ (ዎኪቶኪ) እና 74 የደረትና የወገብ ወታደራዊ ትጥቆች ተወርሰዋል።

የ303ኛ ግዙፉ አሳምነው ኮር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ መዳረሻው ሙሉ ነፃነትና ድል የሆነው የአማራ ሕዝብ የህልውና ተጋድሎ በአስተማማኝ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾ፣ በሌሎች ግንባሮች የተመዘገቡ ታላላቅ ድሎችንም በቀጣይ ቀናት ከቪዲዮና ከፎቶ ማስረጃዎች ጋር አያይዞ ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይቀጥላል!

28/05/2026

የዛሬውን ጨምሮ ቀጣይ ዘመቻዎቻችን "ዘመቻ አንሻ ሰይድ" በሚል ታውጇል።

28/05/2026

ሰበር ዜና አለ፣ ይጠብቁ!

ሸር እያደረጋችሁ!

28/05/2026

ሰበር ዜና!

በርካታ ክላሽ፣ 3 ዲሽቃ ተማርኳል፣ ይቀጥላል።

28/05/2026

ጀብደኛው ምኒልክ ዕዝ ተነስቷበታል፣ ድል ለጀብደኞች!

27/05/2026

📜 የማይዳስ ንክኪ፡ የመዋቅራዊ ውድቀት ፖለቲካዊ ስነ-ልቦና

(ሙሉጌታ አንበርብር)

በቀደመው የትዝታ ማኅደራችን ውስጥ፣ በየአካባቢያችን አንድ ክስተት ማስታወስ እንችላለን። በራስ የመተማመን ስሜታቸው ከሰማይ የደረሰ፣ ነገር ግን የሚነኩት ማናቸውም የንግድም ሆነ የማኅበራዊ መስተጋብር መስመር በአጭር የተቀጨ ባለሀብት ሰፈራችን ውስጥ ነበሩ። እኚህ ሰው አዲስ የምርት መስመር በዘረጉ ቁጥር፣ ወይም አዲስ የጋራ መጋዘን በከፈቱ ማግስት፣ ንብረቱ መውደሙ ወይም በኪሳራ መዘጋቱ አይቀሬ ነበር። የሰፈሩ ማኅበረሰብ ሁኔታውን በአንክሮ በመታዘብ "እኚህ ሰው የተፈጥሮ ምርቃት ሳይሆን የእርግማን እጅ ነው ያላቸው፤ እባካቸው ምንም ሳይነኩ በዝምታ ቢቀመጡ ይሻላል" እስከማለት ደርሶ ነበር። ችግሩ ግን እዚህ ላይ አይደለም፤ ግለሰቡ የደረሰውን መዋቅራዊ ኪሳራና ውድቀት ከመቀበል ይልቅ፣ በየቀኑ አዳዲስና ግዙፍ "የስትራቴጂክ ዕቅዶችን" በወረቀት ላይ እያሳዩ፣ ማኅበረሰቡን ወደ ከፋ የዕዳ መረብ ውስጥ ይስቡት ነበር። ይህ በግል ደረጃ የሚታይ አውዳሚ ባህሪ፣ ዛሬ በሀገራዊ የፖለቲካ መድረክ ላይ ወደሚታይ ሥር የሰደደ መዋቅራዊ ቀውስ ሲሸጋገር የምንመለከተው እውነታ ሆኗል።

በክላሲካል የግሪክ ስነ-አፈታሪክ ውስጥ የሚገኘው የንጉስ የማይዳስ ታሪክ፣ ተራ ተረት ሳይሆን በስልጣንና በሀብት ስግብግብነት የሚለከፉ አገዛዞችን ስነ-ልቦናዊ ውድቀት የሚያሳይ ፍልስፍናዊ መስተዋት ነው። የማይዳስ የነካው ነገር ሁሉ ወደ ወርቅ እንዲቀየርለት ከአማልክት ዘንድ ያገኘው ስጦታ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ፍፁም እርግማን ተቀየረ። ምግቡን፣ ውኃውን፣ አልፎ ተርፎም የገዛ ልጁን ሲነካ ወደ ግዑዝ ወርቅነት መቀየራቸው፣ ሕይወትንና ህልውናን መሠረት ባደረገ ተፈጥሯዊ ሥርዓት ላይ የተፈጸመ ትልቅ መዋቅራዊ ጥሰት ነበር። ይህ ዘይቤ በዘመናዊው የፖለቲካ ሳይንስ ውስጥ "የማይዳስ ንክኪ" ተብሎ ሲተነተን፣ አንድ ሥርዓት ሁሉንም ተቋማዊ መዋቅሮች በራሱ ፍፁም ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚያደርገው የገዥነት አባዜ፣ የነካቸውን ነፃና ሕያው የሆኑ ተቋማትን በሙሉ ወደ ግዑዝና ጥቅም አልባነት የመቀየር ሂደትን ያመለክታል። ሥርዓቱ "የእኔ ንክኪ ሁሉንም ወደ ወርቅ ይለውጣል" በሚል የፕሮፓጋንዳ ስካር ውስጥ ሲገባ፣ ትክክለኛው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሕይወት ግን እየሞተ ይሄዳል።

የአራት ኪሎ የፖለቲካ መዋቅርና አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ስንመረምር፣ ይህንኑ የማይዳሳዊ ውድቀት በግልጽ እንመለከታለን። አገዛዙ የነካቸውንና የተረከባቸውን ሀገራዊ ምሶሶዎች በሙሉ ወደ ቀውስ ማዕከልነት ቀይሯቸዋል። የገንዘብና የገበያ ሥርዓቱን "እናስተካክላለን" በሚል ፖሊሲ በማክሮ-ኢኮኖሚው ላይ በነኩት ቁጥር፣ ውጤቱ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ የዋጋ ግሽበት፣ የኑሮ ውድነትና የዜጎች የመግዛት አቅም ፍፁም መውደቅ ሆኗል።

በቀጠናዊና ሀገራዊ መረጋጋት ረገድ ደግሞ ዲፕሎማሲውንና የደህንነት መስመሩን በድርድር ስም ለመፍታት የተደረጉ ንክኪዎች በሙሉ፣ ይበልጥ ውስብስብ ወደሆኑ የድንበር፣ የሉዓላዊነትና የውስጥ ጦርነት አዙሪቶች ተቀይረዋል። በተመሳሳይ መልኩ የፍትህ፣ የሕግና የአስተዳደር መዋቅሮች በካድሬ ስልጠናና በፖለቲካ ታማኝነት ብቻ እንዲመሩ መደረጋቸው፣ ተቋማቱ ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ሕያው አካላት መሆናቸው ቀርቶ፣ የሥልጣን ማራዘሚያ ግዑዝ መሣሪያዎች ብቻ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። አገዛዙ በየእለቱ በሚዲያ መስኮቶች የሚያሳየን "የሜጋ ፕሮጀክቶች" እና የስብስብ ስታቲስቲክስ፣ ልክ እንደ የማይዳስ ወርቅ ከውጭ የሚያብረቀርቅ ነገር ግን እውነተኛውን ማኅበረሰባዊ ረሃብና መፈናቀል የማይፈታ የትዕይንት ፖለቲካ ነው።

በታሪኩ ማጠቃለያ ላይ፣ ንጉስ የማይዳስ ከዚህ አውዳሚ እርግማን ለመውጣት የቻለው በራሱ ስሌት ሳይሆን፣ ወደ ዲዮኒሰስ ወንዝ በመሄድ የገዛ እጁን ታጥቦ ያንን የወርቅ የመቀየር ኃይል ወደ ወንዙ ውስጥ ሲያፈስስ ብቻ ነበር። ወንዙ የተፈጥሮ፣ የንፅህና እና የሕይወት መገኛ ምልክት ነው። ዛሬ በአማራ ሕዝብ ዘንድ እየተካሄደ ያለው የህልውና ትግል፣ ከዚህ ከተቋማዊና ከመዋቅራዊ መርዝ ማክሸፊያ ወንዝ ጋር ይመሳሰላል።

ይህ ትግል የካድሬውን የውሸት ወርቅ ፕሮፓጋንዳ ሰብሮ፣ ሀገሪቱን ወደ ቀደመው ተፈጥሯዊ፣ ፍትሃዊና ታሪካዊ ሚዛኗ ለመመለስ የሚደረግ የህልውና እንቅስቃሴ ነው። ሕዝቡ የአስተዳደር፣ የፍትህና የማኅበራዊ ዋስትና መዋቅሮችን ከአገዛዙ አውዳሚ ንክኪ ነጥቆ፣ በራሱ እውነተኛና ሕያው በሆነ የሕዝብ ተሳትፎ መልሶ ለመገንባት ቆርጦ ተነስቷል።

ታሪክ እንደሚያስተምረን፣ በስግብግብነትና በትዕቢት ላይ የተመሰረተ የወርቅ ቅዠት በሒደት የገዛ ራሱን መዋቅር መበላቱ አይቀሬ ነው፤ በተፈጥሯዊና በእውነተኛ የሕዝብ ማዕበል ፊት ደግሞ የውሸት ስኬቶች በሙሉ ቀልጠው መሬቱ ላይ ያለው እውነት ብቻ መቅረቱ ታሪካዊ እውነታ ነው።

📜 የጎርዲያን ቋጠሮ፡ የካድሬው ውዥንብር እና የሰይፍ መፍትሄ(ሙሉጌታ አንበርብር)በግሪክ ታሪክ ውስጥ "የጎርዲያን ቋጠሮ" (Gordian Knot) የሚባል እጅግ የተወሳሰበ የገመድ ቋጠሮ ነበር...
26/05/2026

📜 የጎርዲያን ቋጠሮ፡ የካድሬው ውዥንብር እና የሰይፍ መፍትሄ

(ሙሉጌታ አንበርብር)

በግሪክ ታሪክ ውስጥ "የጎርዲያን ቋጠሮ" (Gordian Knot) የሚባል እጅግ የተወሳሰበ የገመድ ቋጠሮ ነበር። የፍሪጊያ ንጉስ ጎርዲያስ የሰራት ይህች ቋጠሮ፣ ማንም ሊፈታት ያልቻለች፣ ጫፍና መነሻ የሌላት እጅግ የተጠላለፈች ነበረች። የኦራክል ትንቢት "ይህችን ቋጠሮ የፈታ የእስያ ንጉስ ይሆናል" አለ። ብዙ ምሁራን፣ ፈላስፎች እና መሪዎች ሊፈቷት ሞከሩ፣ ነገር ግን በየቀኑ ይበልጥ እያጠነከሩት ሄዱ። በመጨረሻ የሜሶዶኒያው ንጉስ አሌክሳንደር ዘ-ግሬት (ታላቁ እስክንድር) ወደዚያ መጣ። ቋጠሮውን ሲያየው ማንም ሊፈታው እንደማይችል ተረዳ፤ ምን አደረገ? ሰይፉን መዘዘና በሰይፉ ቋጠሮውን በአንድ ምት ቆረጠው። ይህ ዘይቤ ዛሬ በፖለቲካ ውስጥ፣ በአስተዳደር ውዥንብር የታሰረን እጅግ የተወሳሰበ ቀውስ፣ በቆራጥ እና በፈጣን እርምጃ መፍታት ማለት ነው።

የብልጽግና ሰዎች የአራት ኪሎውን ወንበር የምኒልክ ቤተመንግስት ከተቆጣጠሩ በኋላ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምስቅልቅሉን በማውጣት ልክ እንደ ጎርዲያን ቋጠሮ ነው ያደረጉት። በየቀኑ አዲስ መመሪያ፣ አዲስ ኮሚቴ፣ አዲስ ህግ፣ አዲስ የካድሬ መግለጫ ይወጣል። ችግሩን ለመፍታት ሲሞክሩ፣ ይበልጥ እያጠነከሩት ነው። በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በኢኮኖሚ፣ እና በህልውና ጥያቄዎች የተጠላለፈው የኢትዮጵያ ፖለቲካ፣ አገዛዙ በየቀኑ በሚያወጣቸው የውሸት ደንቦች ተጨምረው ፓለቲካችን እንደ ጎርዲያን ቋጠሮ ተጠላልፏል። አገዛዙ በዚህ መረብ ውስጥ ተጠምዷል፤ ቋጠሮው እራሱ የሱ ገመድ ሆኖ እያነቀው ነው።

ነገር ግን የአማራው የህልውና ትግል፣ የዛሬው የታላቁ እስክንድር ሰይፍ የጨበጠ ነው። ህዝቡ አገዛዙ የጠለፈውን የፖለቲካ መረብ፣ በሰይፉ (በትግሉና በቆራጥነት) እየቆረጠው ነው። የካድሬው "ውይይት" ወይም "የድጋፍ ሰልፍ" የሚባለው የውሸት ቋጠሮ፣ ትግሉን ሊያቆመው አይችልም። ህዝቡ የያዘው የነፃነት ጥያቄ፣ ቋጠሮውን በአንድ ጊዜ የሚፈታ እጅግ ሹል የሆነ ሰይፍ ነው።

አገዛዙ የቱን ያህል በውሸት ደንብና በፕሮፓጋንዳ ቋጠሮው ቢጠመጥም፣ የህዝቡ የትግል ሰይፍ ግን መፍትሄው አለው። የፖለቲካ ቋጠሮ ሲጠላለፍ፣ መፍትሄው መፍታቱ ሳይሆን መቁረጡ ነው። አማራው የጠለፈውን መረብ እየቆረጠ፣ ወደ ነፃነት ጉዞው እየተመመ ነው።

የጎርዲያን ቋጠሮ ለተቆራረጠው የካድሬ አገዛዝ፣ መጨረሻው የታወቀ ነው፤ ትግሉ ሰይፉን መዞ ቋጠሮውን መፍታት ሳይሆን መቁረጥ ነው!

ድል ለአማራ ሕዝብ!

📜 የአማራው 'ኦዲሲ' እና የሳይረን ዜማዎች!(ሙሉጌታ አንበርብር)አንድ ሩቅ አገር እየነገደ የሚተዳደር ጠንካራ ሰው ነበር። ይህ ሰው ለንግድ ቤቱን ዘግቶ በወጣ ቁጥር፣ የሰፈሩ ምቀኛ እና ወሬ...
26/05/2026

📜 የአማራው 'ኦዲሲ' እና የሳይረን ዜማዎች!

(ሙሉጌታ አንበርብር)

አንድ ሩቅ አገር እየነገደ የሚተዳደር ጠንካራ ሰው ነበር። ይህ ሰው ለንግድ ቤቱን ዘግቶ በወጣ ቁጥር፣ የሰፈሩ ምቀኛ እና ወሬኛ ሁሉ በየቡናው እየተሰበሰበ "ሰማችሁ አይደል? አምና ሄዶ የውሃ ሙላት ወስዶት ሞቷል፤ እከሌ የሚባል ጫካ ውስጥ አውሬ በልቶታል" እያለ የውሸት መርዶውን ያረደዋል። አንዳንዱ ደግሞ የሰውየውን ንብረት ለመቀራመት ሟርት ይጀምራል። ይህ ጠንካራ ሰው ግን ከወራት በኋላ፣ ዝናብና ፀሀይ ተፈራርቆበት፣ ተራራ ወጥቶ ወርዶ፣ የገጠመውን ሌባ እና አውሬ ሁሉ ጥሶ፣ በበቅሎው ላይ ሀብት ጭኖ በሰፈሩ መሃል ብቅ ይላል። ወሬኛው ሁሉ አፉን ከፍቶ፣ በገዛ ውሸቱ አፍሮ ወደ ቤቱ ይገባል። ለዚህ ነጋዴ፣ ጉዞው የአንድ ጀንበር ሽርሽር ሳይሆን፣ የፅናት ፈተና ነበር።

በግሪክ ስነ-ፅሁፍ አባት በሆነው ሆመር (Homer) ከተፃፉት ታላላቅ ስራዎች ውስጥ "ኦዲሲ" (Odyssey) የሚለው ይገኝበታል። የኢታካው ንጉስ ኦዲሰስ (Odysseus) ከትሮይ ጦርነት በኋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ እና ቤተሰቡ ለመመለስ ያደረገው የ10 ዓመታት እጅግ አድካሚ እና ፈታኝ ጉዞ ነው። ዛሬ በፖለቲካውም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ ዓለም፣ "ኦዲሲ" ማለት በብዙ ፈተናዎች፣ ማዕበሎች፣ እና አሳሳች ወጥመዶች የታጀበ፣ ነገር ግን በመጨረሻ ወደ እውነተኛው መዳረሻ እና ነፃነት የሚያደርስ ረጅም የትግል ጉዞ ማለት ነው።

የዘንድሮዎቹ የብልጽግና ፖለቲከኛ ነን ባዮችም፣ የአማራውን ህዝብ የህልውና ትግል ገና ከመነሻው ሲያዩት ልክ እንደ አጭር ርቀት ሩጫ (Sprint) አሊያም እንደ አንድ ጀንበር የሰፈር ፀብ አስበውት ነበር። ካድሬው እና ጄኔራሉ በየቴሌቪዥኑ መስኮት ወጥተው "በሁለት ሳምንት እናጠናቅቀዋለን፤ በሶስት ቀን እናስረክባለን" ብለው ሲደነፉ የነበረው፣ ትግሉ ጥልቅ የታሪክ፣ የስነ-ልቦና እና የማንነት 'ኦዲሲ' መሆኑን ካለማወቅ የመነጨ የፖለቲካ ድንቁርና ነው።

በኦዲሰስ ጉዞ ውስጥ ከተገጠሙት ታላላቅ ፈተናዎች አንዱ "ሳይረን" (Sirens) የሚባሉት ፍጥረታት ነበሩ። እነዚህ ፍጥረታት የባህር ዳርቻ ላይ ሆነው እጅግ አሳሳች እና ጣፋጭ ዜማ ይዘፍናሉ፤ መርከበኞችም ዜማውን ሰምተው ሲፈዝዙ እና ሲጠጉ፣ መርከባቸውን ከቋጥኝ ጋር አጋጭተው ይከሰከሳሉ። ኦዲሰስ ይህንን ወጥመድ ለማለፍ የመርከበኞቹን ጆሮ በሰም ደፍኖ፣ የራሱን እጅና እግር ደግሞ ከመርከቡ ምሰሶ ጋር አስሮ ነበር ይህንን የውሸት ዜማ ያለፈው።

የዛሬዎቹ ገዢዎቻችን ፕሮፓጋንዳም ከ"ሳይረኖቹ" ዜማ በምንም አይለይም። ጦር አዝምተው፣ ድሮን አሰማርተው ህዝብ እየገደሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ "የሰላም ኮንፈረንስ፣ የሽግግር ፍትህ፣ ብልፅግና እና ሪባን ቆረጣ" የሚል እጅግ አሳሳች የካድሬ ዜማ ይዘፍናሉ። አንዳንድ የፖለቲካ የዋሃን ይህንን ዜማ ሰምተው፣ በመንግስት ሚዲያ የተባለውን አምነው ህልውናቸውን ከገደል ሲያጋጩ አይተናል። የተራራው አርበኛ እና የአማራ ህዝብ ግን ልክ እንደ ኦዲሰስ መዳረሻ አላማውን እና የህልውና ስጋቱን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ፣ ለካድሬው የውሸት የሰላም ዜማ ጆሮውን ጥጥ አድርጎ የራሱን ፅኑ የትግል መንገድ እየተጓዘ ይገኛል።

አገዛዙ ሌላም የገጠመው ችግር አለ፤ እሱም እንደ "ሳይክሎፕስ" (Cyclops - አንድ አይን ብቻ ያለው ግዙፍ ጭራቅ) መሆኑ ነው። የመንግስት ሚዲያዎች እና የካድሬው ስብስብ የሚያዩት በዚያች በአንዲት አይናቸው (በገዛ ፕሮፓጋንዳቸው) ብቻ ነው። የሚያዩት የራሳቸውን ውሸት፣ የሚሰሙት የራሳቸውን ማስተጋባት (Echo-chamber) ብቻ ነው። መሬት ላይ ያለውን ግዙፍ የህዝብ ማዕበል እና የትግሉን ስፋት በሁለት አይናቸው ሚዛናዊ አድርገው ማየት ተስኗቸዋል።

የአማራው የህልውና ትግል "ኦዲሲ" ነው። ጉዞው ውጣ ውረድ አለው፣ ማዕበል እና ቋጥኝ ይበዛዋል፣ ሟርተኛ እና የውሸት ዜማ አዚመኛ በመንገዱ ላይ ይቆማል። ነገር ግን ይህ ረጅም ጉዞ ህዝቡን ይበልጥ ያጠነክረዋል እንጂ አያቆመውም። የቱንም ያህል የመከራ ማዕበል ቢመታው፣ መርከቡ ወደ እውነተኛው መዳረሻው፣ ወደ ነፃነት እና ወደ ማህበራዊ ፍትህ መድረሱ አይቀሬ ነው!

ድል ለአማራ ሕዝብ!

25/05/2026

📌 መርከቧ እና የአኪሊስ ተረከዝ ምስጢር!

(ክፍል ፪)

የባለመሪዋ መርከብ ጉዞ አሁንም በአስፈሪው ማዕበል ውስጥ ቀጥሏል። መርከበኞቹ የሳይረንን አሳሳች ድምፅ ተቋቁመው፣ መርከባቸውን አፅንተው ይዘው ወደፊት ለመጓዝ ቢሞክሩም፣ አሁን ደግሞ ከበፊቱ የከፋ ሌላ የውስጥ ወጀብ ተደቅኖባቸዋል። ይህ አዲስ ፈተና በጥንታዊው የግሪክ ጦርነት ታሪክ ውስጥ የሚነገሩትን ሁለት ታላላቅ ምስጢሮች ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።

የመጀመሪያው የአኪሊስ ተረከዝ (Achilles' Heel) በመባል የሚታወቀው ጥንታዊ ታሪክ ነው። አኪሊስ የተባለው ታላቅ ጀግና መላ አካሉ በጦርም ሆነ በሰይፍ የማይበገር፣ ፍፁም ጠንካራ የነበረ ቢሆንም፣ በአንዲት ትንሽ ድክመቱ (በተረከዙ) ላይ በተሰነዘረችበት መርዛማ ቀስት ምክንያት ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል።

ዛሬ መርከበኞቻችን በብዙ መከራና ዋጋ የገነቡት ይሄ ግዙፍ መዋቅር፣ ልክ እንደ አኪሊስ ጠንካራና የማይበገር የብረት ጋሻ ሆኗል። የውቅያኖሱ ሞገድና ከውጭ የሚመጣው ጠላት በሃይልና በግልፅ ጦርነት ሊሰብረው፣ ጉዞውን ሊያስቆመው አልቻለም። ነገር ግን የዚህ ግዙፍ መርከብ የአኪሊስ ተረከዝ (ብቸኛ ደካማ ጎኑ) በየክፍሉ ያሉ ኃላፊዎች እርስበርስ ለመተማመን መቸገራቸውና በረንዳው ላይ የጀመሩት እልሃዊ ክርክር ነው። ከውጭ ያለው ጠላት ይሄንን ደካማ ተረከዝ በትኩረት አይቷል።

ሁለተኛው ደግሞ የትሮይ ፈረስ (Trojan Horse) ምስጢር ነው። በጥንት ዘመን ጠላቶች የትሮይን ግንብ በሃይል ሰብረው መግባት ሲያቅታቸው፣ አንድ ትልቅ የእንጨት ፈረስ ሰርተው በደጃፋቸው ጥለው የተመለሱ መሰሉ። የትሮይ ሰዎችም "ፈረሱ የስጦታ ነው" ብለው በገዛ እጃቸው ወደ ውስጠኛው ግንባቸው አስገቡት። ለካስ በፈረሱ ሆድ ውስጥ ጨካኝ ተዋጊዎች ተደብቀው ነበር፤ ማታ ሁሉም መከላከያቸውን ጥለው በተኛበት ሰዓት ከፈረሱ ሆድ ወጥተው የትሮይን ከተማ ከውስጥ አፈራረሷት።

ዛሬም በመርከበኞቻችን መሃል የሚነፍሰው የሃሜት ወሬ፣ የእርስበርስ ጥርጣሬና የበረንዳው ላይ ሽኩቻ፣ ልክ እንደ ትሮይ ፈረስ ነው። ጠላት የመርከቧን ግንብ በሃይል ማፍረስ ሲያቅተው፣ በመርከበኞቹ የጓዳ ወሬና የጥርጣሬ ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ ውስጠኛው መዋቅር ዘልቆ ገብቷል።

ነገር ግን አሁን ነገሩ ከሹመት አልፏል፤ እርስበርስ ከመጠራጠር የተነሳ እያንዳንዱ ኃላፊ የራሱን ታንኳ ነጥሎ ለመውሰድ የመርከቧን ጣውላዎችና ብሎኖች ማላላት ጀምሯል። ይህ እልህ ግንባር ቀደሞቹን የብረት ጋሻዎች ነቃቅሎ ዋናዋን መርከብ ራሷን ሊያፈርሳትና ሊበታትናት ደርሷል።

አንጋፋውና እድሜ ጠገቡ መርከበኛ አሁንም በረንዳው ላይ ቆመው፣ የመርከቧን ጣውላዎችና ገመዶች ሲነቃቅሉ ያዩዋቸውን ኃላፊዎች እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድንጋጤና ቁጭት ገሰጿቸው፦ "ልጆቼ! ቆሙ እንጂ! ምን እያደረጋችሁ እንደሆነስ ታስተውላላችሁ? እናንተ 'የእኔ ክፍል ይበልጣል፣ እኔ የዚህኛው ወለል አዛዥ ልሁን' ስትሉ፣ ውጭ ያለው ጠላት ሊወጋችሁ የሚፈልገው በግንባር ሳይሆን፣ በዚህ በኩል ባለው የአኪሊስ ተረከዛችሁ (በመካከላችሁ ባለው ክፍፍል) ነው።

"የምታስተናግዱት የእርስበርስ መጠራጠር ደግሞ፣ ጠላት ወደ መርከቧ የላከው የትሮይ ፈረስ ነው። አሁንማ እልሃችሁ በዝቶ የጋራ መጠለያችን የሆነችውን፣ በሺዎች ደም የቆመችውን ዋናዋን መርከብ ራሷን ልታፈርሷት እጅ አነሳችሁባት! ከውጭ የሚመጣውን ማዕበል መቋቋም አያቅተንም፤ ነገር ግን በገዛ እጃችን መርከቧን ካፈረስናት፣ ሁላችንም በአንዴ ውቅያኖስ ስር መስጠማችን እኮ አይቀሬ ነው። የህልውና አደጋ የገጠመው ኃይል፣ ለአንዳችም ሰዓት ቢሆን ተረከዙን ለጠላት ቀስት ማሳየት፣ የቆመባትን መርከብ መሰንጠቅ የለበትም! መርከባችሁን ይዛችሁ በአንድ ልብ ቁሙ!" ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጩ!

24/05/2026

ጣሊያን ሮም!

በዛሬው ዕለት ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ጣሊያን ሮም ላይ የአብይ አህመድ አገዛዝን አውግዘዋል!

ይቀጥላል!

Address

Kampala

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mulugeta Anberber Gebeyaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category