AmharicTube

AmharicTube እንኳን ወደ ፔጃትን በሰላም መጣቹ : ኣብራቹን ስላላቹ እናመሰግናለን ።
(1)

✨ካሙዙ ካሳ ✨ ሀገራዊው ምርጫ ላይ ይወዳደራል!ዝነኛው አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ የካ ክፍለ ከተማ ላይ ምርጫውን ይወዳደራል። ብልፅግና ፓርቲ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እጩ አድርጎ ካቀረባቸው ግለሰ...
03/24/2026

✨ካሙዙ ካሳ ✨ ሀገራዊው ምርጫ ላይ ይወዳደራል!

ዝነኛው አቀናባሪ ካሙዙ ካሳ የካ ክፍለ ከተማ ላይ ምርጫውን ይወዳደራል። ብልፅግና ፓርቲ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እጩ አድርጎ ካቀረባቸው ግለሰቦች መሀከል አንዱ አርቲስት ካሙዙ መሆኑ ታውቋል።

✨እስራኤል በሳውዝ ፓርስ (South Pars) የጋዝ መስክ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን ወደ ቱርክ (Türkiye) የምታደርገውን የጋዝ ኤክስፖርት አቋረጠች።✨ቱርክ ለፍጆታዋ የሚውለው...
03/24/2026

✨እስራኤል በሳውዝ ፓርስ (South Pars) የጋዝ መስክ ላይ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ፣ ኢራን ወደ ቱርክ (Türkiye) የምታደርገውን የጋዝ ኤክስፖርት አቋረጠች።✨

ቱርክ ለፍጆታዋ የሚውለውን 14 በመቶ (14%) ያህል ጋዝ ከኢራን የምታገኝ ቢሆንም፣ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ እጥረትን ከሩሲያ፣ ከአዘርባጃን እና ካከማቸችው ክምችት (Stored reserves) በመጠቀም ልታካክስ ትችላለች።

ይህ የአቅርቦት መቋረጥ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እስካሁን ግልጽ አይደለም። ምንጭ፦ ብሉምበርግ (Bloomberg)

ትንሹ ዮኒ ማኛ እያሉት ነው 😂
03/23/2026

ትንሹ ዮኒ ማኛ እያሉት ነው 😂

03/21/2026

Eዒድ ሙባረክ ለመላው የምስልና ሃይማኖት ተከታዮች 🙏

Big shout out to my new rising fans! Fetene Hassene
03/21/2026

Big shout out to my new rising fans! Fetene Hassene

🔺ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዓለም ትልቁን የኢራን የጋዝ ማምረቻ እንደሚያወድሙ አስጠነቀቁ🔺የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በኳታር ላይ ድጋሚ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ በዓለም ትልቁን የቴህ...
03/19/2026

🔺ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዓለም ትልቁን የኢራን የጋዝ ማምረቻ እንደሚያወድሙ አስጠነቀቁ🔺

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን በኳታር ላይ ድጋሚ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ በዓለም ትልቁን የቴህራን የጋዝ ማምረቻ ማዕከል በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጋዩ አስጠንቅቀዋል፡፡

ከሁለት ሳምንታት በላይ ያስቆጠረው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ንብረትን እያወደመ፤ የሰው ሕይወትንም እየቀጠፈ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

ኢራን በኳታር፣ ሳዑዲ ዓረቢያ እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የነዳጅ ማውጫ ማዕከላት ላይ ያነጣጠረ የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን አስታውቃለች፡፡

ቴህራን ጥቃቱን የፈጸመችው እስራኤል በደቡብ ፓርስ ውስጥ የሚገኘው የኢራን የተፈጥሮ ጋዝ ማዕከል ላይ የሚሳዔል ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ነው፡፡

ኢራን በአጸፋዊ ርምጃዋ በተለይም ራስ ላፋን በተሰኘው ግዙፍ የኳታር የተጣራ የተፈጥሮ ነዳጅ ማቀነባበሪያ ማዕከል ላይ የፈጸመችው ጥቃት ዋሽንግተን እና ዶሃን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡

በተፈጸመው ጥቃት ራስ ላፋን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ማዕከል ላይ እሳት ተነስቶ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ኢራን ለቀጣናው ቀውስና አለመረጋጋት ከፍተኛ ስጋት ናት ያለው ሚኒስቴሩ ÷ በዶሃ የሚገኙ የኢራን ዲፕሎማቶችና ወታደራዊ አታሼዎች ከሀገሪቱ መባረራቸውን ጠቅሷል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ ÷ አሜሪካ እና ኳታር እስራኤል በኢራን የጋዝ ማምረቻ ማዕከል ላይ ስለፈጸመችው ጥቃት ምንም አይነት መረጃም ሆነ ተሳትፎ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም ኢራን በኳታሩ ራስ ላፋን የነዳጅ ማቀነባበሪያ ማዕከል ላይ የፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉ መኮነናቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢራን በድጋሚ ኳታር ላይ ጥቃት የምትፈጽም ከሆነ አሜሪካ በደቡብ ፓርስ የሚገኘውንና በዓለም ትልቁን የቴህራን የጋዝ ማምረቻ ማዕከል ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እንደምታወድመው አስጠንቅቀዋል፡፡

Via fana tv

🔺ይሸጣል🙏🔺 ይሀንን 64500 ፈለወርስ እና በ2 ሳምንት ብቻ ከ5.4ሚልዮን ቪውስ በ ያለው ፔጅ መግዛት የምትፈልጉ ኣናግሩን ። በተለይም ከኢትዮጵያ ውጭ የምትኖሩ ሰዎች በደምብ ገንዘብ ልትሰ...
03/19/2026

🔺ይሸጣል🙏🔺 ይሀንን 64500 ፈለወርስ እና በ2 ሳምንት ብቻ ከ5.4ሚልዮን ቪውስ በ ያለው ፔጅ መግዛት የምትፈልጉ ኣናግሩን ። በተለይም ከኢትዮጵያ ውጭ የምትኖሩ ሰዎች በደምብ ገንዘብ ልትሰሩበት ትችላላቹ 🙏

🔺ሰበር 🔺ኢራን በዓለም ግዙፉ የጋዝ ማከፋፈያ "ራስ ላፋን" (Ras Laffan) ላይ ሚሳኤል ተኮሰች ምሽት ከኢራን የተተኮሰ የባሊስቲክ ሚሳኤል በኳታር የሚገኘውንና የዓለምን 25 በመቶ የፈሳ...
03/18/2026

🔺ሰበር 🔺
ኢራን በዓለም ግዙፉ የጋዝ ማከፋፈያ "ራስ ላፋን" (Ras Laffan) ላይ ሚሳኤል ተኮሰች ምሽት ከኢራን የተተኮሰ የባሊስቲክ ሚሳኤል በኳታር የሚገኘውንና የዓለምን 25 በመቶ የፈሳሽ ተፈጥሮአዊ ጋዝ (LNG) የሚያቀርበውን ግዙፍ የኢንዱስትሪ ማዕከል መምታቱ ተረጋገጠ።

🚀 ከ5 ሚሳኤሎች አንዱ ኢላማውን መትቷል
የኳታር መከላከያ ኃይል እንደገለጸው፣ ከኢራን ከተተኮሱ አምስት የባሊስቲክ ሚሳኤሎች ውስጥ አራቱ በአየር ላይ ተመትተው የወደቁ ሲሆን፣ አምስተኛው ግን በዓለም ግዙፉ የጋዝ ኤክስፖርት ተርሚናል በሆነው "ራስ ላፋን" (Ras Laffan Industrial City) ላይ አርፏል።

ኳታር ኢነርጂ (QatarEnergy) በደረሰው ጥቃት በቁልፍ ተቋማት ላይ "ከፍተኛ ጉዳት" መድረሱንና የእሳት አደጋ መነሳቱን አረጋግጧል።
የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እያደረጉ ሲሆን፣ እስካሁን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ሪፖርት አልተደረገም።

🔥"የኢነርጂ ጦርነት" አደገኛ ምዕራፍ
ይህ ጥቃት ኢራን በእራሷ የ"ሳውዝ ፓርስ" (South Pars) የጋዝ መስክ ላይ ለደረሰባት ጥቃት የሰጠችው ግልጽ የአጸፋ እርምጃ መሆኑ ተነግሯል።

ቴህራን ቀደም ሲል በባህረ ሰላጤው ሀገራት የኢነርጂ ማዕከላት ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ማስፈራሪያዋን ወደ ተግባር ቀይራዋለች።

🌍 የዓለም ኢኮኖሚ ስጋት
የራስ ላፋን ማዕከል ለዓለም ገበያ የሚያቀርበው የጋዝ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ፣ የዚህ ተቋም ስራ መስተጓጎል በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ እና የጋዝ ዋጋን በእጅጉ ሊያ ንረው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በተለይም አሜሪካንና አውሮፓውያን አጋሮቿን ለከፍተኛ የኢነርጂ ቀውስ ሊዳርግ እንደሚችል ታዛቢዎች ይጠቁማሉ።
🇶🇦 የዶሃ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ
ኳታር ጥቃቱን "ቀጥተኛ የጸጥታ ስጋት" ስትል የኮነነች ሲሆን፣ በዶሃ የሚገኙ የኢራን ወታደራዊ አታሼዎች (Military Attaches) ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዛለች።

ፈጣሪ ሰላማችን ያምጣው

ሰበር ዜና   5.5 ሚልዮን ፈለወር ደርሷል ። congra ልጃችን
03/18/2026

ሰበር ዜና 5.5 ሚልዮን ፈለወር ደርሷል ። congra ልጃችን

🔺በጣም ያሳፍራል ደግሞም ያስፈራል🔺በዩቱብ ላይ ከተሰጠው ርእስ ይጀምራል በጣም አሳፋሪው እና አስፈሪው ነገር። እንዲህ ይላል "የነፃነት ወርቅነህ ቤተሰቦች ስለሚስቱ ያጋለጡት አስደንጋጭ ሚስጥ...
03/18/2026

🔺በጣም ያሳፍራል ደግሞም ያስፈራል🔺
በዩቱብ ላይ ከተሰጠው ርእስ ይጀምራል በጣም አሳፋሪው እና አስፈሪው ነገር። እንዲህ ይላል
"የነፃነት ወርቅነህ ቤተሰቦች ስለሚስቱ ያጋለጡት አስደንጋጭ ሚስጥር"****
ልብ በሉ ይሄን እረስ የሰጠው ይቱትብ ቻናል አንዲት አክስት ስለ ወንድሟ ሚስት ስለ ተዋለዱ ትልቅ ቤተሰብ ቁጭ ብላ በምታወራበት ቻናል ላይ ነው።"ያጋለጡት አስደንጋጭ ሚስጥር" ተብሎ ልብ ማንጠልጠል የተጀመረው።****
የአጎት ማእረግ ያለውም የዚሁ ቤተሰብ አባል ቁጭ ብሎ የመገላለጡ እና የማጋለጡ አንዱ አካል ነው። ዝም ብላችሁ አስቡት። ውንድም እና እህት "አጎት እና አክስት" ሲያጋልጡ! የገዛ የወንድማቸውን የሚያድጉ ልጆች ስሜት ምን ሊሆን ይችላል? ብለው ሳያስቡ።****
አልገባቸውም እንጂ የሟች ነፃነት እህት እና ወንድም ቢገባቸው ለወንድማቸው ልጆች እንደ አባት እና እናት መሆን ነበረባቸው። በተለይ በኢትዮጵያ ባህል አጎት እንደ አባት ነው አክስት እንደ ሁለተኛ እናት ነች። አንዳንዴም ከዛም በላይ!****
ነፃነትን የሚያክል ወንድም አጥተው በዚህ ደረጃ ወርደው ችግር ቢኖር እንኳን የፈለገ ቢበደሉ የፈለገ ደረጃ ቢደርሱ ስለ ነፃንት ልጆች ሲሉ ህመማቸውን ቻል አድርገው ፍርድን ከ እውነተኛ አምላክ ይፈልጉ ነበር።****
በየትኛውም ቤተሰብ መካከል ብዙ ድብቅ እና ድብልቅልቅ ታሪኮች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ አይነት ታሪክ ያለ የሚኖርም ነው። ምንም አዲስ ነገር የለም። ሁሉም በየቤቱ ብዙ የሚያልፍበት ችግር ሊገጥመው ይችላል።****
በዚህ ደረጃ ግን ወርዶ እና ተዋርዶ ልክ እንዳልተዋለደ በደም ገመድ እንዳልተሳሰረ ሰው ከንቱ በሆነ ቃላት አደባባይ ላይ ወርዶ መዋረዱ እና ማዋረዱ ምን ትርፍ ሊገኝበት? ማን ሊከብርስ? ማንስ ሊጠቀም?****
እኔ ግን እንዲህ እላለው!
ባልና ሚስት በአንድ ቤት ሲኖሩ ግጭትም ሊኖር ይችላል፣ ችግርም ሊያጋጥማቸው ይችላል። ነገር ግን ከእነርሱ አንዱ በሞት ሲለይ፣ ያኔ የቀረው ነገር ክርክር ሳይሆን ሐዘን ነው፤ የልብም ስብራት ነው። ለመላው ቤተሰብ።*****
ነገር ግን ጊዜ ጠብቆ ያልተስተካከሉ ነገሮችን አንስቶ በአደባባይ ቃል መለዋወጥ የሞተውን አያከብርም፣ የቀሩትንም አያፅናናም። ሞት የጥላቻ መድረክ አይደለም፤ የሰውነት፣ የክብር እና የዝምታ ጊዜ ነው። ****
በዝምታ ውስጥ ብዙ መልሶች አሉ። በመቻቻል ውስጥ ጥልቅ መናበብ ፤ መግባባት ፤ስምምነት አለ። በተለይ ልጆች ሲኖሩ እንደ ድልድይ ናቸው። እነሱን አልፎ የሚደረግ የትኛውም ፀብ ጊዜ ጠብቆ ይጎዳቸዋል። ከዚህ ይልቅ በዝምታ ማለፍ ብልህነት አስተዋይነትም ነው።

ፀሓፊው TST APP ነው

Address

Kenya
Arvada, CO
00200

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AmharicTube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share