ዜና-ቪው

ዜና-ቪው "ትኩስ መረጃን እና ምርጥ የገበያ አማራጮችን በአንድ እይታ የሚያገኙበት የታመነ የዲጂታል መስኮት።"

 ።
19/08/2026

 #ቡሄ
19/08/2026

#ቡሄ

 #ከመቀሌ በቅርብ የምትገኘው በእንደረታ ወረዳ ልዮ ስሙ ቀዳማዊ ወያ'ነ አካባቢ ላይ በዛሬው ቀን ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ የሎጀስቲክ ማዕከሉን ከጥ-ቅም ው-ጭ አድር-ጋዋለች❗❗👉🙌 ያ ሰላም በላይነ...
18/08/2026

#ከመቀሌ በቅርብ የምትገኘው በእንደረታ ወረዳ ልዮ ስሙ ቀዳማዊ ወያ'ነ አካባቢ ላይ በዛሬው ቀን ብቻ ለሁለተኛ ጊዜ የሎጀስቲክ ማዕከሉን ከጥ-ቅም ው-ጭ አድር-ጋዋለች❗❗
👉🙌 ያ ሰላም በላይነሽ ✈✈✈✈😘

የታፈነውን የሀገር እስትንፋስ ማስለቀቅና የተገፈፈውን ሀገራዊ ገመና የመሸፈን የትውልድ አደራ*****************የባህር በር ማጣት የሀገርን የደህንነት ምስጢር፣ የህዝብን ኪስ እና የሀ...
17/08/2026

የታፈነውን የሀገር እስትንፋስ ማስለቀቅና የተገፈፈውን ሀገራዊ ገመና የመሸፈን የትውልድ አደራ
*****************

የባህር በር ማጣት የሀገርን የደህንነት ምስጢር፣ የህዝብን ኪስ እና የሀገራችን ኢኮኖሚ እስትንፋስ በሌሎች እጅ አሳልፎ የሚሰጥ እጅግ አንገብጋቢ የህልውና ጉዳይ ነው።

እኛ ኢትዮጵያውያን በችግርም ሆነ በደስታ ጊዜ ገመናችንን ሸፍነን በክብር መኖር ከፍተኛ ማህበራዊ እሴታችን ያደረግን ህዝቦች ብንሆንም፣ የባህር በር አልባነታችን ግን ይህንን ክብራችንን ገፎ ገመና አልባ አድርጎናል።

ዛሬ ሀገር የምታስገባው እያንዳንዱ ስትራቴጂካዊ የደህንነት ቁሳቁስም ሆነ ወደ ውጭ የምትልከው አንጡራ ሀብት በሌሎች ሀገራት እጅና እይታ ስር ማለፉ፣ ሀገራዊ ምስጢራችንን ለአደባባይ ያጋለጠው ሲሆን፤ አንድ ግለሰብ በቤቱ ውስጥ የሚበላውን፣ የሚጠጣውን፣ የሚገዛውንና የሚሸጠውን ጎረቤቱ እንዲያውቅበት እንደማይፈልገው ሁሉ፣ የኢትዮጵያም የዲጂታል እና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በሌሎች መዳፍ ላይ መውደቁ ሀገራችን በቀላሉ ሊጠለፍ ለሚችል የጂኦ-ፖለቲካ ሴራ አጋልጧታል።

ታሪካዊ ጠላቶቻችን ማናቸውንም ሀገራዊ እንቅስቃሴዎቻችንን ለማጨናገፍ እድል የሚያገኙትም ይኸው ሉዓላዊ ገመናችን በወደብ አልባነታችን ሳቢያ በመገፈፉ ነው።

በሌላ በኩል፣ ዛሬ በገበያዎቻችን ላይ የምናየው የዋጋ ንረት ዋነኛ ምንጭ የወደብ አልባነታችን የፈጠረው የሎጂስቲክስ ስብራት ጠባሳ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉዳዩን ሲገልጹት አንድ ምርት ከቻይና ተነስቶ ጎረቤት ሀገር ናይሮቢ ከሚሸጥበት ዋጋ ይልቅ፣ ወደ እኛ ሀገር ሲገባ የባህር በር ባለመኖሩ ምክንያት ብቻ ቢያንስ የ30 በመቶ የዋጋ ጭማሪ እንዲኖረው ያስገድዳል።

ከባህር በር ባለቤት ሀገራት አንጻር ሲታይ ከ50 እስከ 100 በመቶ የሚደርስ ተጨማሪ የሎጂስቲክስ ወጪ በቀጥታ የሚጫነው በሸማች ትከሻ ላይ ሲሆን፣ ምርቶች በረዥም የየብስ ጉዞ ሲጓተቱ ጥራታቸው ይበላሻል፣ ወሳኝ የንግድ ኮንትራቶች ይሰረዛሉ፤ በዚህም የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ እግሩ ተጠፍንጎ ይያዛል።

ከፖለቲካዊ ተጋላጭነትና ከኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ባሻገር የባህር በር ጥያቄን እጅግ ስሜት ሰጪ እና ቀጥተኛ የሞትና የሽረት ጉዳይ የሚያደርገው በጤናው ዘርፍ ላይ የሚያደርሰዉ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ነው።

ኢትዮጵያ የህይወት አድን መድሃኒትና የህክምና መሳሪያ ፍላጎቷን የምታሟላው ከውጭ በማስገባት ሲሆን፣ እጅግ ጥብቅ የሆነ የሙቀት ቁጥጥር የሚፈልጉ ክትባቶችና መድሃኒቶች፣ በሌሎች ሀገራት ወደብ ላይ በሚፈጠር ቢሮክራሲያዊ መጓተትና በረዥም ጉዞ ለከፍተኛ ፀሐይ ሲጋለጡ ፈዋሽነታቸው ይቀንሳል።

የራሳችን ወደብ ቢኖረን ኖሮ፣ የመድሃኒት የሎጂስቲክስ ጊዜን በግማሽ እንዲሁም የትራንስፖርትና የችርቻሮ ዋጋን እስከ 25 በመቶ በመቀነስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ እናቶችና ህጻናትን ህይወት መታደግ ይቻላል።

በዓለም አስረኛ የሆነውን ግዙፍ የህዝብ ቁጥር የያዘችና ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የምታስተዳድር ሀገር ከምጽዋ ጫፍ እስከ ሞቃዲሾ ጥግ በተዘረጋው አምስት ሺህ ኪሎሜትር ርዝመት ባለው ሀብት በሞላው የውሀ ዳርቻ ላይ ተከባና ታፍና እስከ ወዲያኛው ትኖራለች ብሎ ማሰብ የዋህነት ብቻ ሳይሆን ትልቅ የጂኦ-ፖለቲካ ሴራ ነው።

ይህ አንገብጋቢ የህልውና ጥያቄ በክፋት በሮችን ዘግቶ ኢትዮጵያን ማፈን ለማንም ሀገር ዘላቂ አዋጭነት የለውም። ስለዚህ የባህር በር ባለቤትነት የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን የተገፈፈውን ሀገራዊ ገመና የመሸፈን፣ የዜጎችን ኪስ የማዳን እና የሀገርን ደህንነትና ኢኮኖሚ የመታደግ ሀገራዊ አጀንዳችን በመሆኑ፣ ይህን አደራ በአሸናፊነትና በዲፕሎማሲያዊ

17/08/2026

ለእናታችን ማሜ በርሴሳ ፊታ የታሰበው ድጋፍ ተጀመረ፤ 95 ሺህ ብር ገቢ ተደርጓልለእናታችን ማሜ በርሴሳ ፊታ (Mame Bersessa Fita) ያለንን ጥልቅ ፍቅር፣ ክብር እና የማይናወጥ አጋ...
17/08/2026

ለእናታችን ማሜ በርሴሳ ፊታ የታሰበው ድጋፍ ተጀመረ፤ 95 ሺህ ብር ገቢ ተደርጓል

ለእናታችን ማሜ በርሴሳ ፊታ (Mame Bersessa Fita) ያለንን ጥልቅ ፍቅር፣ ክብር እና የማይናወጥ አጋርነት በተግባር ለማሳየት የተጀመረው የበጎ አድራጎት እንቅስቃሴ በይፋ ተከፍቷል!

የቃል ድጋፍ ብቻ ሳይሆን ከጎናቸው መቆማችንን ለማረጋገጥ የተሰበሰበው የመጀመሪያው 95,000 (ዘጠና አምስት ሺህ) ብር ቀጥታ ወደ ባንክ አካውንታቸው ገቢ ተደርጓል።

ለዚህ መልካም ስራ አርአያ በመሆን የመጀመሪያውን የፍቅር ስጦታ ላበረከቱት ቀዳሚ ባለውለታዎቻችን ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረስ፦

1. የMMA አዘጋጅ ጌታቸው መለሰ (50,000 ብር)፦ ለእናታችን ላሳዩት ትልቅ አጋርነት እና ግዙፍ ልግስና።

2. ጉርሻ ፔጅ 30,000 ብር፦ ለዚህ መልካም እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም በመሆን እና ድምፅ በመሆን ላደረገው ድጋፍ።

3. ሰለሞን ጌታቸው - ሶል ውሃ ጠጡ (15,000 ብር)፦ ሁልጊዜም ለወገን ደራሽ በመሆን ላሳየው ቅንነት እና መልካም ልብ።

አሁን ደግሞ ተራው የእናንተ ነው! (Challenge Started)

እናታችንን በችግሯ ጊዜ የማንተው፣ ደስታዋ ደስታችን የሆነው መላው አድማጭ እና ተከታታያችን ከአቅሙ በላይ እንደሚያደርግ ሙሉ እምነት አለን።

የምታበረክቱት አነስተኛዋም ስጦታ ለእናታችን ትልቅ ተስፋ እና ብርሃን ናት!

የባንክ ሂሳብ መረጃ፦

* የአካውንት ስም፦ Mame Bersessa Fita
* የአካውንት ቁጥር፦ 1000373399039

ወገን ለወገኑ ደራሽ ነው! እጃችሁን ዘረጉ፣ መልእክቱን ለሌሎች በፍጥነት SHARE በማድረግ የዚህ መልካም ነገር አካል ሁኑ!

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው!"

ሰበርአቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ! ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን ...
17/08/2026

ሰበር

አቶ ክርስቲያን ታደለ የመንግሥትን የምሕረት ቅድመ ሁኔታ ተቀበሉ!

ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ተከስሰው በእስር ላይ የሚገኙ በርከት ያሉ ታሳሪዎች መንግሥት ያቀረበላቸውን በቅድመ ሁኔታ የታሠረ የምኅረት መጠየቂያ ሠነድ መፈረማቸውን ዋዜማ ራድዮ ዘግቧል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርሰቲያን ታደለን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ማዕረጉ ቢያበይንን ጨምሮ በርካታ እስረኞች የምኅረት መጠየቂያውን በመሙላት ስምምነታቸውን እንደገለጡ ምንጮች እንደነገሩት ዘገባው ጠቅሷል። አምስት ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን ጨምሮ 30 ያህል እስረኞች ግን ሠነዱን 'አንፈርምም' ማለታቸው ታውቋል።

ሠነዱን አንፈርምም ካሉት መካከል፤ የአማራ ክልል ምክር አባሉ ዮሐንስ ቧያለው፤ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ዶ/ር ወንደወሠን አሠፋ፣ መስከረም አበራ እና ጎበዜ ሲሳይ ይገኙበታል ተብሏል። የምኅረት ሠነዱን እንዲፈርሙ የቀረበላቸው እስረኞች 300 ገደማ እንደሚጠጉ ታውቋል፡፡

#በላይነሽአመዴ
-ቪውBBC News

በጥቃቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ!በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሲሰራጭ በነበረው አሳዛኝ የጥቃት ቪዲዮ ውስጥ ተሳትፋለች የተባለችው “ፈርደውስ” እና አባሪዎቿ፣ በ...
17/08/2026

በጥቃቱ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ!

በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ሲሰራጭ በነበረው አሳዛኝ የጥቃት ቪዲዮ ውስጥ ተሳትፋለች የተባለችው “ፈርደውስ” እና አባሪዎቿ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣንና የተቀናጀ ኦፕሬሽን በህግ ጥላ ስር እንዲውሉ ተደርገዋል።

ህብረተሰቡ መረጃዎችን ለህግ አካላት ብቻ እንዲያደርስ ቀደም ሲል የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ፣ የህግ አስከባሪዎቻችን የተጣለባቸውን ኃላፊነት በከፍተኛ ሙያዊ ብቃት በመወጣት እውነታውን አጣርተው ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

የህዝብን ሰላምና ደህንነት ለማስከበር፣ ጥፋተኞችን ለፍትህ ለማቅረብ እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ላሳየው ፈጣን፣ ቁርጠኛ እና አርዓያነት ያለው ተግባር ከፍተኛ ምስጋና ይገባዋል!

ቀንና ሌሊት ሳይሉ ለሰላማችን እና ለደህንነታችን ለሚደክሙት መላው የፖሊስ አባሎቻችን ያለንን ጥልቅ አክብሮትና ምስጋና እናቀርባለን።

ክበሩልን!

📷Fuad Hussein

🙏🙏🙏

Ethio mereja

-ቪው

""ማን ቀረ ከጫካ " ሁሉም እየመጡ ነው"" እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏🙏
17/08/2026

""ማን ቀረ ከጫካ " ሁሉም እየመጡ ነው"" እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏🙏

አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆን ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው ? ብዙ ሰዎች አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይሁን ማለት ምን ማለት ነው ? ተጠሪነ...
16/08/2026

አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆን ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው ?

ብዙ ሰዎች አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ይሁን ማለት ምን ማለት ነው ? ተጠሪነት ማለትስ ምንን ያካትታል ? ብለው ይጠይቃሉ

ተጠሪነት ሲባል የከተማዋ የበላይ የፖለቲካ፣ የሕግ፣ የፋይናንስ እና የአስተዳደር ባለቤትነትና ተጠያቂነት ሙሉ በሙሉ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ይዛወራል ማለት ነው።

ይህ ሃሳብ በተግባር ሲተረጎም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ያካትታል፡

የፖለቲካ እና የሕግ የበላይነት

አሁን ባለው የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 49 መሠረት አዲስ አበባ የራሷ አስተዳደር ያላት እና ተጠሪነቷ ለፌዴራል መንግሥት የሆነች "ራስ ገዝ" የፌዴራሉ መዲና ናት።

ተጠሪነቷ ለኦሮሚያ ክልል ሆነ ማለት ግን ከተማዋ የክልሉ አንዷ አካል (ከተማ) ትሆናለች፤ የፌዴራል መንግሥት በከተማዋ ላይ ያለው የቀጥታ የበላይነት ያበቃል።

የሕግ አውጪነት እና አስፈጻሚነት ሥልጣን

የከተማዋ ምክር ቤት የሚያወጣቸው ደንቦችና መመሪያዎች ከኦሮሚያ ክልል ሕገ-መንግሥትና ሕጎች ጋር የተጣጣሙ መሆን አለባቸው። የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮችም (ለምሳሌ ከንቲባው) ተጠሪነታቸው ለኦሮሚያ ክልል ጨፌ (ምክር ቤት) እና ለክልሉ ፕሬዚዳንት ይሆናል።

የበጀትና የታክስ አስተዳደር ጉዳይ

አዲስ አበባ የምትሰበስበው ገቢ፣ የቦታ አጠቃቀምና የመሬት ካዳስተር ሥርዓት፣ እንዲሁም የበጀት ክፍጣኔ በኦሮሚያ ክልል የፋይናንስና የመሬት ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ ይወድቃል።

የወሰንና የቋንቋ ጉዳይ

አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል የወሰን ክልል ውስጥ ሙሉ በሙሉ የምትጠቃለል ሲሆን፣ የክልሉ ሥራ ቋንቋ (አፋን ኦሮሞ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ሥራ ቋንቋ እንዲሆን ያደርገዋል ማለት

ተጠሪነት ሲባል ይህንን እና መሰል ጉዳዬችን ያካትታል

Adresse

Democratic Republic Of The

Site Web

Notifications

Soyez le premier à savoir et laissez-nous vous envoyer un courriel lorsque ዜና-ቪው publie des nouvelles et des promotions. Votre adresse e-mail ne sera pas utilisée à d'autres fins, et vous pouvez vous désabonner à tout moment.

Raccourcis

Partager