Fiath photography

Fiath photography Keep a moment

ለመከላከያ ሠራዊት አባላት መኖሪያ ቤት ለማስገንባት የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ!!የግንባታ ውሉን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሜጀር ጄኔራል ኩምሳ ሻንቆ እና የኦቪድ ኮን...
23/08/2022

ለመከላከያ ሠራዊት አባላት መኖሪያ ቤት ለማስገንባት የሚያስችል ስምምነት ተካሄደ!!

የግንባታ ውሉን የመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሜጀር ጄኔራል ኩምሳ ሻንቆ እና የኦቪድ ኮንስትራክሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዮናስ ታደሰ ተፈራርመዋል።

የሚገነቡት ቤቶች ባለ ሦስት እና አራት መኝታ ሲሆኑ በ14 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁም በሥነ ሥርዓቱ ወቅት ተጠቁሟል። ቤቶቹም ባለ ሰባት ወለል 128 ቤቶች እና ባለ ዘጠኝ ወለሉ ደግሞ 120 ቤቶች መሆናቸው ተገልጾ ኩምካንግ አሉሚኒየም ፎርምወርክ በተባለ ቴክኖሎጂ እንደሚገነቡ ተነግሯል።

በአጠቃላይ 248 ቤቶች የሚገነቡ ሲሆን ከ1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግባቸውም ተገልጿል።የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ዛሬ ከተፈጸመው ውሉ በተጨማሪ በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ እና ባሕርዳር ከተሞች ከ2100 ቤቶች በላይ በመገንባት ላይ መሆኑም ተገልጿል።

 #እረኛዬ✌😜
22/08/2022

#እረኛዬ
✌😜

ቡራዩ :  #ጥንቃቄ በጅብ ተበልቶ ሁለት  እግሮቹን ያጣው ወጣት  | ብርሃኑ ዳባ ቤተሰቦቹ የሚኖሩት ቡራዩ ለኩ ከታ መንደር ነው።ባላፈው ሳምት ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. ረቡዕ ዕለት ከሚኖር...
22/08/2022

ቡራዩ : #ጥንቃቄ
በጅብ ተበልቶ ሁለት እግሮቹን ያጣው ወጣት

| ብርሃኑ ዳባ ቤተሰቦቹ የሚኖሩት ቡራዩ ለኩ ከታ መንደር ነው።

ባላፈው ሳምት ነሐሴ 04/2014 ዓ.ም. ረቡዕ ዕለት ከሚኖርበት ሞጆ ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ የሄደው ጉዳይ ለማስፈፀም ነበር።

ነገር ግን አልተሳካለትም፤ በማግስቱ ሞጆ ተመልሶ የሥራ ገበታው ላይ መገኘት ያሰበው ብርሃኑ ወደ ጓደኛው ዘንድ ደወለ።

“ሌሊቱን ወደ ሞጆ የሚሄዱ መኪኖች አሉ። ስለዚህ ወደ ዊንጌት ሄጄ እነርሱን ለመያዝ ነበር ያሰብኩት” ሲል ያክላል።

“የዚያን ዕለት ቡራዩ ቤተሰቦቼ ጋር ሄጄ ነበር። ያሰብኩት ጉዳይ አልተሳካልኝም። የሥራዬ ቦታ ደግሞ ሞጆ ስለሆነ አንድ የማውቀው ሰው ጋር ደወልኩኝ። እና ዛሬ ማታ ስለምወጣ አብረን ተጉዘን ነገ ሥራ መግባት ትችላለህ አለኝ” ይላል አደጋው ከመድረሱ በፊት የተፈጠረውን ሲያስታውስ።

ብርሃኑ የደወለለት ወዳጁ ‘ዊንጌት እጠብቅሃለሁ’ ስላለው ከቡራዩ ከታ ወደ አስኮ እየተጓዘ እያለ በተለምዶ በግ ተራ ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ጅብ ማየቱን ያስታውሳል።

ነገር ግን ብርሃኑ ያሰበበት ቦታ ከመድረሱ በፊት መንገድ ላይ ጅቦች ተተናኮሉት። በዚያም የተነሳ ሁለት እግሮቹን አጣ።

“በግ ተራ አካባቢ ቁልቁለቱን እየወረድኩ፣ አንድ ጅብ ሲመጣ አይቻለሁ። ከዚያ በኋላ የሆንኩትን ነገር አላስታውስም። በማግስቱ አምስት ሰዓት ላይ ራሴን ሆስፒታል ውስጥ አገኘሁት፝።”

ብርሃኑ የተለያዩ የአካል ክፍሎቹ በጅብ ተነክሷል።

ጀርባው እጁ እንዲሁም እግሮቹ ላይ ከንክሻው የተነሳ ጉዳት ደርሶበታል።

ከሁሉም ግን እግሮቹ ላይ የደረሰው ጉዳት የከፋ ነበር።

“ስነቃ ሆስፒታል ውስጥ ተኝቻለሁ። ከጉልበቴ በታች ያለው አካሌ የለም። ቤተሰቦቼ የተኛሁበትን አልጋ ከብበው ቆመዋል።”

ከገባበት ሰመመን ሲነቃ ራሱን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ያገኘው ብርሃኑ ስለገጠመው ነገር በቅጡ የሚያስታውሰው የለም።
“ወደ ሆስፒታል ያመጣህ የፖሊስ አምቡላንስ ነው ይሉኛል እንጂ በትክክል ማን እንዳመጣኝ አላውቅም። ስነቃ ራሴን ሆስፒታል ውስጥ ተኝቼ ነው ያገኘሁት” ይላል ብርሃኑ።

“ከጉልበቴ በታች ተጎድቷል። አንደኛው እግሬ ከቁርጭምጭሚቴ በታች የለም። የቀኝ እግሬ ደግሞ ተንጠልጥሎ ነበር። ከዚህ በላይ ደም ከፈሰሰህ ትሞታለህ ስላሉኝ ተቆረጠ” ሲል ያክላል።

ብርሃኑ በአሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው አቤት ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ ይገኛል።

ወደ ሆስፒታል ሊጠይቁት የመጡ ሰዎች በቅድሚያ ቡራዩ ጤና ጣቢያ የመጀመርያ እርዳታ ከተሰጠው በኋላ፣ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ አቤት ሆስፒታል መምጣቱን እንደነገሩት ለቢቢሲ ገልጿል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የፖሊስ ባልደረቦች ብርሃኑን ጉዳት ከደረሰበት ስፍራ አንስተው ወደ ሕክምና ተቋም የወሰዱት የአካባቢው የፀጥታ አባላት መሆናቸውን ይናገራሉ።

ኢንስፔክተር መልካሙ አሰፋ፣ በቡራዩ ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ናቸው።

በዕለቱ እኩለ ሌሊት ላይ የፀጥታ አካላት ብርሃኑ የወደቀበት ስፍራ እንዳገኙት ለቢቢሲ ገልፀዋል።

“ስንደርስ አንድ እግሩ ሙሉ በሙሉ ተበልቷል። ሁለተኛው እግሩ ደግሞ ከቁርጭምጭሚቱ በታች ተበልቷል። ግራ ጎኑ ደግሞ ተቦጭቋል።”

የፀጥታ አባላቱ በስፍራው ሲደርሱ የጅብ ጩኽት ይሰማ እንደነበር የሚናገሩት ኢንስፔክተሩ፣ ብርሃኑን አንስተው በፖሊሰ መኪና በቅርብ ወደ ሚገኘው የቡራዩ ጤና ጣቢያ መውሰዳቸውን እና ከዚያ በኋላ ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ድጋፍ ማድረጋቸውን ይናገራሉ።

ወደ ቡራዩ ፖሊስ ከተመደቡ ቅርብ ጊዜያቸው መሆኑን የሚናገሩት ኢንስፔክተር መልካሙ በከተማው እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች አልፎ አልፎ ሲከሰቱ እንደ

አሸንዳን በወሎ❤ #ኢትዮጵያ  #ወሎ  #አሸንዳ
22/08/2022

አሸንዳን በወሎ❤
#ኢትዮጵያ
#ወሎ
#አሸንዳ

እረኛዬ ተከታታይ ድራማ ሳይንዛዛ እጥር ምጥን ብሎ ማለቁ መልካም ሁኖ ሳለ፣ ነገር ግን የአፀድዬን ጉዳይ መጨረሻ ሳያሳዩ ድራማው መፈፀሙ ብዙዎቹን አሳዝኗል😕 #እረኛዬ  #ኢትዮጵያ  #ድራማ
22/08/2022

እረኛዬ ተከታታይ ድራማ ሳይንዛዛ እጥር ምጥን ብሎ ማለቁ መልካም ሁኖ ሳለ፣ ነገር ግን የአፀድዬን ጉዳይ መጨረሻ ሳያሳዩ ድራማው መፈፀሙ ብዙዎቹን አሳዝኗል😕 #እረኛዬ #ኢትዮጵያ #ድራማ

እውነተኛ አርቲስት ማለት ተመስጦ ሚቃርም  ሳይሆን ሌሎችን የሚያነሳሳ ነው።አርቲስት መሆን በጣም እፈልግ ነበር ግን በቃ አልሳካ አለኝ ብዙ ተስፋ ሁላ ቆረጥኩ የኮሮና ግዜ የዘጋሁትን  ፌስቡክ...
22/08/2022

እውነተኛ አርቲስት ማለት ተመስጦ ሚቃርም ሳይሆን ሌሎችን የሚያነሳሳ ነው።
አርቲስት መሆን በጣም እፈልግ ነበር ግን በቃ አልሳካ አለኝ ብዙ ተስፋ ሁላ ቆረጥኩ የኮሮና ግዜ የዘጋሁትን ፌስቡክ ድጋሚ ከፍቼ ሚያሰራኝን ስፈልግ ነው ይህን ድንቅ ስራ ያገኘሁት ፣ ቤተሰቦቼ ጸሎተኛ ናቸው ይህ ስራ የመጀመርያዬ ነው የነሱ ጸሎት መሰል በተአምር እዚህ ደርሻለው ገና ብዙም ሰራለው አደይን በጣም ምወደው ስራ ነው ፣
ፓርቲ ምሽት ምናምን ወጥቼም አላቅም እንደውም አንድ ግዜ እረዘም ያለ ቀሚስ ደብቄ ወጣሁና ተመለስኩ ቤተሰቤን መሸወድ እናቴን መዋሸት ከበደኝ ተመለስኩ ፣
ፍቅረኛ አለኝ ፣
በእምነት ሙሉጌታ ( አደይ )

ኮርፖሽሬኑ በመርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ በተከሰተ የሕንጻ መደርመስ አደጋ በሰዎችና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ከፍተኛ ሐዘን ይገልጻል*****የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን  መርካ...
22/08/2022

ኮርፖሽሬኑ በመርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ በተከሰተ የሕንጻ መደርመስ አደጋ በሰዎችና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ከፍተኛ ሐዘን ይገልጻል
*****

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን መርካቶ አካባቢ ለሱቅ እና ለመጋዘን አገልግሎት በመስጠት ላይ በሚገኘውና የኮርፖሬሽኑ ንብረት የሆነው የንግድ ቤት የፈትለፊት የግንባታ አካል ፈርሶ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ባስከተለው ጉዳት ኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ ሐዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጸ፣ ለተጎጂ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ልባዊ መጽናትን ይመኛል፡፡

ኮርፖሬሽኑ አደጋው ከደረሰ ሰዓት አንስቶ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያቀፈ አስቸኳይ ግብረ ሀይል አቋቁሞ ወደ ሥራ የገባ ሲሆን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካለት ጋርም በቅርበት እየሰራ ይገኛል፡፡

በቀጣይም መከናወን ያለባቸውን ተግባራት በሚመለከት ፣ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት አስፈላጊውን ሁሉ የሚያከናውን ይሆናል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በድጋሜ ለተጎጂ ወገኖቻችን ቤተሰቦች ልባዊ መጽናትን ይመኛል፡፡
**********

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
ነሐሴ 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በመዲናዋ መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈበአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ የኪራይ ቤቶች መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታ...
22/08/2022

በመዲናዋ መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ የኪራይ ቤቶች መጋዘን ተደርምሶ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የመሳለሚያና አካባቢው የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ይበቃል ጠመረ ለኢዜአ እንደገለጹት÷ ዛሬ ከሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው መርካቶ መሀል አዳራሽ አካባቢ ባጋጠመ የሕንጻ መደርመስ አደጋ የሥድስት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም ሰባት ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመው÷ ህብረተሰቡ ከተገነቡ ረጅም ጊዜ ያስቆጠሩ ቤቶችን ሁኔታ በማየት ለሚመለከተው አካል እንዲጠቁም አሳስበዋል።
FBC

  .m@2022
10/08/2022


.m
@2022

3Obsa  👍👍👍👏👏
15/09/2021

3Obsa


👍👍👍
👏👏

28/06/2021



 #ሰናይ #ቅዳሜ
27/02/2021

#ሰናይ
#ቅዳሜ

Address

HaileGarment
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fiath photography posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share