Doch HD

Doch HD DOCH [Digital Outlet for Creative Hits]
Positive Vibes Only
________________________
❚█Your Hate Comments Are REMOVED█❚
(18)

Doch HD ገና በጅምር ላይ ያለ የመረጃና የመዝናኛ ሚዲያ ነው። በዚህም መረጃ ሰጪ ቪዲዮ እና ምስል እንዲሁም ፅሁፍ በየቀኑ በየሰዓቱ ከእኛ ይመልከቱ። ዶች

ዴላን አደረገው፤ ኢትዮጵያዊው ተስፈኛ የእግርኳስ ተጫዋቹ አማን በእንግሊዝ አካዳሚ ዕድል አገኘበዛሬው እለት በተሰማው ዜና መሠረት የአንድ ኢትዮጵያዊ ተስፈኛ እግርኳስ ተጫዋች ህልም እውን ሊሆ...
12/06/2026

ዴላን አደረገው፤ ኢትዮጵያዊው ተስፈኛ የእግርኳስ ተጫዋቹ አማን በእንግሊዝ አካዳሚ ዕድል አገኘ

በዛሬው እለት በተሰማው ዜና መሠረት የአንድ ኢትዮጵያዊ ተስፈኛ እግርኳስ ተጫዋች ህልም እውን ሊሆን የዳር ለመድረሱ ማረጋገጫ ተሰምቷል።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረው ታዋቂው የዜና አንባቢ ዴላን ፔጅ ቃል በገባው መሠረት አማንን ከህልሙ ማገናኘቱን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል።

ዛሬ አሜን በዚህ ክረምት ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (UK) በማቅናትበቦልተን ዎንደረርስ አካዳሚ (Bolton Wanderers Academy) በሚካሄድ ውድድር ላይ የመሳተፍ ዕድል እንደተሰጠው ተነስተው ተናግሯል።

ዛሬ ህልሙ እውን ሆኗል።ለአሜን ይህንን ዕድል ስለሰጠው ከ SMS Pro Soccer ለሆነው ለማርክ ሄይስ (Mark Hayes) ትልቅ ምስጋና ይግባውም ብሏል ዴላን።

ውሎ አድሮ፣ አንዳንድ ጊዜ ለአንድ ሰው የሚያስፈልገው አንድ አጋጣሚ ብቻ ነው።በአንተ እንተማመናለን አሜን ሲል በኢትዮጵያዊው ወጣት ያለውን ተስፋ በመግለፅ እንደምታኮራንም እናውቃለን፤ በቅርቡ እንገናኛለን ሲልም አረጋግጧል።

ዴላን ዕድሉ ይገኝ እንጂ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎችን እሸፍናለሁ ማለቱን ዶች ኤችዲ መዘገቡ ይታወሳል።

ዶች ኤችዲ

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአቶ ሀብታሙ አለሙ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ተፈፀመየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ የ...
12/06/2026

የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአቶ ሀብታሙ አለሙ ሥርዓተ ቀብር በዛሬው እለት ተፈፀመ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት የአቶ ሀብታሙ ዓለሙ ሥርዓተ ቀብር፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሥራ ባልደረቦቻቸው፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በቦንጋ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።

በሥራ ዘመናቸው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ሕዝብና መንግሥትን ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ሀብታሙ፣ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በጅማ ሆስፒታል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ44 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከታሪካቸው መረዳት እንደተቻለው፣ አቶ ሀብታሙ ዓለሙ በ1974 ዓ.ም በካፋ ዞን ሳይለም ወረዳ ልዩ ስሙ አጋሮ ኦጊቲ በተባለ ሥፍራ የተወለዱ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአጋሮ ሹንጋ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በማሻ አጠናቀዋል።

በ1994 ዓ.ም ከቦንጋ መምህራን ማሠልጠኛ ተቋም በማስተማር ሙያ ከተመረቁ በኋላ፣ ከ1994 እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ በቅንነትና በትጋት በመምህርነት አገልግለዋል።

በተጓዳኝም ራሳቸውን በትምህርት ለማበልጸግ ባደረጉት ጥረት በ1999 ዓ.ም በሕግ ዲፕሎማ፣ በ2003 ዓ.ም በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪ (LL.B) እንዲሁም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የሁለተኛ ዲግሪ እውቀታቸውን አሳድገዋል።

ይህንን የሕግና የማኔጅመንት ዕውቀታቸውን ይዘው ወደ መሪነት የመጡት አቶ ሀብታሙ፣ በሥራ ዘመናቸው በርካታ መንግሥታዊ ኃላፊነቶችን በብቃት ተወጥተዋል።

በዚህም የሳይለም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣ የካፋ ዞን ንግድና ኢንዱስትሪ፣ ከተማና አደረጃጀት ዘርፍ፣ ፍትሕ እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በተለያዩ የአመራር እርከኖች ላይ ደማቅ አሻራ አሳርፈዋል።

እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስም የክልሉን ሰላምና ጸጥታ በማስከበር ረገድ በምክትል ቢሮ ኃላፊነት ግንባር ቀደም ሚናቸውን ሲወጡ የቆዩት አቶ ሀብታሙ ዓለሙ፣ በትዳር ሕይወታቸው የ4 ሴት ልጆች አባት ነበሩ።

የክልሉ መንግሥት በአቶ ሀብታሙ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በድጋሚ እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።

ዶች ኤችዲ

የቀጠለው ቀልድ፤  "ደቡብ አፍሪካዊ ያልሆነ መማታት አያስጠይቅም ቀይ አያሰጥ። አይቻልም እዚህ?""አንድ ደቡብ አፍሪካ ያልሆነ ተማቶ ቀይ ካርድ የተሰጠው ተጫዋች እንዲህ የደነገጠው፤ በሀገሩ ...
12/06/2026

የቀጠለው ቀልድ፤ "ደቡብ አፍሪካዊ ያልሆነ መማታት አያስጠይቅም ቀይ አያሰጥ። አይቻልም እዚህ?"

"አንድ ደቡብ አፍሪካ ያልሆነ ተማቶ ቀይ ካርድ የተሰጠው ተጫዋች እንዲህ የደነገጠው፤ በሀገሩ ጎዳናዎች ደቡብ አፍሪካዊ ያልሆነ መማታት ተጠያቂ ስለማያደርግ ነው" ይላል።

መራራ እውነት በቀልድ ቀርቧል

ይሞታል፤ አበቃለት ተብሎ ነበር፤ እሱ ግን ፀና ትናንት ለሃገሩ ግብ አስቆጥሮ አነባ 🔥እግር ኳስ አንዳንድ ጊዜ ከሜዳው አድማስ የዘለለ፣ የህይወት ትርጉምን የሚያስተምረን ታላቅ መድረክ ነው። ...
12/06/2026

ይሞታል፤ አበቃለት ተብሎ ነበር፤ እሱ ግን ፀና ትናንት ለሃገሩ ግብ አስቆጥሮ አነባ 🔥

እግር ኳስ አንዳንድ ጊዜ ከሜዳው አድማስ የዘለለ፣ የህይወት ትርጉምን የሚያስተምረን ታላቅ መድረክ ነው።

ትናንት ምሽት በዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን 2ለ0 በረታችበት ጨዋታ ሁለተኛዋን የማሸነፊያ ጎል ያስቆጠረው ራውል ሂሜኔዝ በሀገሩ ደጋፊዎች ታጅቦ ግብ ሲያስቆጥር አይኖች በእንባ የተሞሉት ለዚያ ነው።

ያ እንባ የድል ብቻ አልነበረም፤ የረዥም ጊዜ የህመም፣ የጥርጣሬ እና የአልበገር ባይነት ታሪክ ማጠቃለያ እንጂ።

ከስድስት ዓመታት በፊት፣ በፕሪሚየር ሊጉ ሜዳ ላይ የተፈጠረው ግጭት የአጥቂውን የራስ ቅል ሲሰብር፣ ሁሉም ሰው የራውል ሂሜኔዝ የስፖርት ህይወት ማለቁን ብቻ ሳይሆን፣ ህይወቱ በራሱ አደጋ ላይ መውደቁን ሰግቶ ነበር።

"እዚህ በህይወት መኖሬ ራሱ ትልቅ ተአምር ነው" ብሎ የነበረው ሂሜኔዝ፣ ወደ ሜዳ ለመመለስ ያደረገው ጉዞ ቀላል አልነበረም።

ብዙዎች ተስፋ በቆረጡበት ወቅት፣ እርሱ ግን በጽናት ተመለሰ። ሆኖም የስቃዩ ጉዞ በዚህ አላበቃም። እንደገና ተጎዳ፣ እንደገና ተሰበረ።

በዘንድሮው ዓለም ዋንጫ ዋዜማ፣ የሂሜኔዝ ዝና በሜክሲኮ ህዝብ ዘንድ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ ነበር።

አዲሱ ትውልድ እና ሌሎች አጥቂዎች ከርሱ እንደሚበልጡ ይነገር ነበር። ነገር ግን አሰልጣኝ ሀቪየር አጊሬ አንድ ነገር ጠንቅቀው ያውቁ ነበር፤ ሂሜኔዝ በቴክኒክ ብቻ ሳይሆን በሜክሲኮ እግር ኳስ አቅም እና ጽናት ምልክት መሆኑን።

አሰልጣኙ የቡድኑን የመሪነት በትረ ስልጣናቸውን የሰጡት ለርሱ ነው።

ሂሜኔዝ ምናልባት ከቡድኑ እጅግ ጎበዝ ተጫዋች ላይሆን ይችላል፤ ነገር ግን አሁን ላይ እርሱ የቡድኑ "ልብ" ነው።

ሜክሲኮ ስትታገል፣ ሂሜኔዝ የመንፈሷ መገለጫ ነው።

ትናንት ምሽት በስምንት አስር ሺህ ተመልካቾች ፊት ግብ ሲያስቆጥር፣ ያ ግብ ለሜክሲኮ ብቻ ሳይሆን፣ በስቃይ ውስጥ ላለፉ እና ተስፋ ለቆረጡ ሁሉ መልእክት ነበር።

ኳሷ ወደ መረቡ ስታርፍ፣ የራውል ሂሜኔዝ ታሪክ በድጋሚ ተጻፈ።

ይህ ታሪክ ስለ ግብ አቆጣጠር አይደለም፤ ይህ ታሪክ ስለ ሰው ልጅ የውስጥ ጥንካሬ ነው።

ራውል ሂሜኔዝ ከጨለማው ጉድጓድ ወጥቶ፣ የራሱን የህይወት ውብ ታሪክ በዓለም ዋንጫ መድረክ ላይ በወርቃማ ቀለም ጽፎታል።

ዶች ኤችዲ

አፍሪካዊያን በጠሏት ደቡብ አፍሪካ ላይ ተሳለቁደቡብ አፍሪካ በ2026 የፊፋ አለም ዋንጫ ትናንት የመክፈቻ ጨዋታዋን ከአዘጋጆቹ አንዷ ከሆነችው መክሲኮ ተጫውታ  2ለ0 ተሸንፋለች።አፍሪካዊያን ...
12/06/2026

አፍሪካዊያን በጠሏት ደቡብ አፍሪካ ላይ ተሳለቁ

ደቡብ አፍሪካ በ2026 የፊፋ አለም ዋንጫ ትናንት የመክፈቻ ጨዋታዋን ከአዘጋጆቹ አንዷ ከሆነችው መክሲኮ ተጫውታ 2ለ0 ተሸንፋለች።

አፍሪካዊያን 'ድል ለሜክሲኮ' ሲሉ ከጨዋታው በፊት የከዷት ደቡብ አፍሪካ ከሽንፈቷ በተጨማሪ የተሸነፈችው ከ2 ቀይ ካርድ ጋር መሆኑ 'እርግማን' አስብሎታል።

በዛሬው እለት የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች የአስተያየት መስጫ ሳጥን ያጨናነቀው ይህ የተያያዘው ምስል 'ደቡብ አፍሪካ ልታሸንፍ የምትችልበት ብቸኛው መንገድ" ተብሎ ተጋርቷል።

ከቀልዶቹ ብዙሃን የተቀባበሉት አንድ የደቡብ አፍሪካ ደጋፊ "እኛ ለቫይቡ ብለን እንጂ እናሸንፋለን ብለን አልጠበቅንም" ማለቷ አስቂኝ ተደርጎ ተወስዷል።

በሌላ በኩል 'የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን አባላት የሜክሲኮ አቻቸው ልምምድ ሲሰራ ስደተኞችን እያሳደደ ስለነበር ትሬኒንግ አልሰራም" የሚለው ቀልድም ተጠቃሽ ነው።

ይህ ስደተኞችን የማሳደዱ ሥራቸው ጋር ለመመለስና ሥራቸውን እንዲሁም እንስቶቻቸውን ለመጠበቅ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመመለስ ስለቸኮሉ ነው ተዋቸው የሚለውም በብዙን የሚነገር ጥላቻ አዘል ቀልድ ሆኗል።

ዶች ኤችዲ

አፍሪካዊያንን አሳዳጇ አፍሪካዊት ሀገር ከ2 ቀይ ካርድ ጋር በ2 ጎል ተረመረመች 🔥ሜክሲኮ 2-0 ደቡብ አፍሪካ
11/06/2026

አፍሪካዊያንን አሳዳጇ አፍሪካዊት ሀገር ከ2 ቀይ ካርድ ጋር በ2 ጎል ተረመረመች 🔥

ሜክሲኮ 2-0 ደቡብ አፍሪካ

ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ በአቶ ሀብታሙ አለሙ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕዕ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልሉ ሠላምና ፀጥ...
11/06/2026

ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ በአቶ ሀብታሙ አለሙ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕዕ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሃዘን መግለጫ በወንድማችንና የሥራ ባልደረባችን አቶ ህብታሙ ዓለሙ ድንገተኛ ህልፈት የተሰማኝ ሐዘን ጥልቅ ነው ብለው አቶ ሀብታሙ ባጋጠማቸው የጤና ችግር በጅማ ሆስፒታል በህክምና እየተረዱ በድንገት ህይወታቸው ማለፉን ተናግረዋል።

አቶ ሀብታሙ ዓለሙ ከክልላችን ምሥረታ ማግስት ጀምሮ የክልላችን የሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ምክትል ቢሮ ኃላፊ በመሆን በፍፁም ታማኝነትና ቅንነት ሲያገለግሉ ነበሩ ያሉት ዶክተር ነጋሽ የተጣለባቸውን የህዝብና መንግሥት አደራ ለመወጣት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ አስተዋጽኦ ሲያበርክቱ ነበር ሲሉ መስክረዋል።

አቶ ሀብታሙ ትሑትና ሰው አክባሪ፣ በጣም ወሳኝ በሆኑ የሠላምና ፀጥታ ማስከበር ጊዜያትም ከመንግሥትና ህዝብ ጎን ያልተለዩ ጠንካራ አመራርም ነበሩ ሲሉም ተናግረዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ በመልእክታቸው ማሳረጊያም ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና ለሥራ ባልደረቦቹ መፅናናትን እየተመኘው ፈጣሪ ነፍሱን በአፀደ ገነት እንዲያሳርፍ ፀሎቴ ነው ብለዋል።

ዶች ኤችዲ

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩየደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ከዚህ አለም በሞት መለ...
11/06/2026

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰምቷል። የተወዳጁ አመራር ህልፈት በቅርበት ለሚያውቋቸው ሁሉ ልብ ሰባሪ ዜና ሆኗል። አቶ ሀብታሙ መካሪና በሥራቸው ታታሪ እንዲሁም ሰው አክባሪ ነበሩ። ፈጣሪ ለቤተሰቦቻቸውና የሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ወዳጆቻቸው መፅናናትን ይስጥ።

ዶች ኤችዲ

11/06/2026

ጆኒና ንቃተ የደነቃቸው ስዕልና ሰዓሊ 🔥

ሚኒስቴሩ በክልሉ ለሚገኘው የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ባህላዊ ፍርድቤት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገየፍትህ ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር በክ...
11/06/2026

ሚኒስቴሩ በክልሉ ለሚገኘው የሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ባህላዊ ፍርድቤት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

የፍትህ ሚኒስቴር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግሥት ፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር በክልሉ ለሚገኙ የባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች የተዘጋጀ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

ሚንስቴሩ የባህላዊ ፍርድ ቤቶችን ተግባር ሊያሳልጥ የሚያስችል የተለያዩ የቢሮ ቁሳቁሶችን ከደስቲን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለሺሺንዳ ከተማ አስተዳደር ባህላዊ ፍርድ ቤት ድጋፍ አድርጓል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጰያ ህዞቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል የፍትህ ሚኒስተሩ በክልሉ ከ700 በላይ በሚሆኑ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ከ30 በላይ ለሚሆኑ ባህል ምክር ቤቶች እየሰጠ ላለው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስተር ዴታ ኤርሚያስ የማነ ብርሃን ( ዶ/ር) ለበዙ ዘመናት በባህላዊ የግጭት አፈታት ውስጥ ባህላዊ ዳኝነት ምናው የጎላ ነው ብለዋል።

ይህ ባህል ሳይበረዝ መቀጠል እንዳለበት ታስቦና በመንግስት በኩል ለ3 ዓመታት መሠራቱን ጠቁመዋል።

ይህም በ 9 ክልሎች ተግባራዊ እየሆነ መሆኑን የገለጹት ኤርሚያስ የማነ ብርሃን ( ዶ/ር ) ከእዚህም ውስጥ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል አንዱ መሆኑንም አስረድተዋል።

የባህላዊ ፍርድ ቤት ዳኞች የክህሎት ውስንነትን የሚቀርፍ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸው የፍትህ ሚኒስትሩ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እያደረገ መሆኑ አስረድተዋል።

መንግሥት የህብረተሰቡን የፍትህ ጥያቄ ለመመለስ በሚያደረገው ጥረት ውስጥ የባህላዊ ዳኝነት ሥርዓት ፋይዳው የጎላ መሆኑንም ገልጸዋል።

Bonga FM

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Doch HD posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share