09/10/2024
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤
አምላክህ ነኝና አትደንግጥ።
አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤
በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።
“እነሆ፤ የተቈጡህ ሁሉ፣
እጅግ ያፍራሉ፤ ይዋረዳሉም፤
የሚቋቋሙህ፣
እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ይጠፋሉም።
ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣
አታገኛቸውም፤
የሚዋጉህም፣
እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ‘አትፍራ፤
እረዳሃለሁ’
ብዬ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና።”
ኢሳይያስ 41፥10-13