14/08/2022
- ፍጹምነት ይሉት ነገር በየትኛውም የሕይወትህ ውስጥ ስለሌለ ፍጹምነት የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡ አዲስ ሥራ ለመጀመርም ይሁን የምትጠላውን ሥራህን ለመልቀቅ ወይም የእድሜ ልክ ምኞትህ የሆነውን ጉዞህን ለማድረግ የምትጠብቀው ፍጹም የሚባል ጊዜ የለም፡፡ ፍጹምነትን ትተህ አሁኑኑ ማድረግ መጀመር አለብህ፡፡ ውድቀትን ፍራቻ ስኬት ላይ ከመድረስ ወደ ኋላ እንዲያስቀርህ አትፍቀድለት፡፡
- በየትኛውም የሕይወት ክፍልህ ላይ ስኬትን መቀናጀት ከፈለክ ዕቅድ ልታወጣለት ይገባል፡፡ በራሱ ይሆናል በሚል ዝም ብለህ ተቀምጠህ ተስፋ በማድረግ የሚጨበጥ ነገር አታመጣም፡፡ የራስህ ሕይወት ፈጣሪው ራስህ ነህ፡፡ ይህ ማለት የየእለቱ ፣ የየሳምንቱ እና የየወሩ እቅድ ፈጣሪው አንተ ነህ፡፡
- በትንሹ መጫዎት ትተህ በትልቁ ማሰብ ጀምር፡፡ ትልልቅ ግቦች እና ሕልሞች ለብዙ ሰዎች እብደት ይመስላቸዋል፤ በርግጥ ሰዎች ሕልሞችህን ሊያጣጥሉብህ እና ሊጠራጠሩህ ይችላሉ ታዲያ አንተ ምን አግብቶህ! በራስህ ላይ የተሰላ ኪሳራን ለመውሰድ ካልደፈርክ ሕልምህ አብሮህ ይሞታል፡፡ ከሀሳብህ አልፈው በፍጹም ወደ ገሃድ አይመጡም፡፡ ዓለምም ካንተ ልትጠቀም የምትችለውን ያህል አትጠቀምም፡፡ ሌሎችን ለመማረክ የምታደርገውን ሙከራ ትተህ ትልቅ ስኬትን ለመቀናጀት ወስን!
- ስኬትን መቀዳጀት ከፈለግክ ሰበቦችን መተው አለብህ፡፡ በሕይወትህ ላይ ለሚገጥሙህ መልካምም ሆነ መጥፎም አጋጣሚዎች ሁሉ ራስህን ተጠያቂ ማድረግ ጀምር፡፡
- በአንድ ለሊት የሚመጣ ሥኬት አልተፈጠረም ፤ አባባል ነው፡፡ የአንድ ለሊት ስኬት የሚመጣው ከዓመታት ያለመታከት ሕልምን ከመከተል ጥረት በኋላ ነው፡፡ ሎተሪ ለማሸነፍ ሳይሆን ግብህ ላይ ለመድረስ በየቀኑ የምታደርገውን መሻሻል ፈጽሞ አታቋርጥ፡፡
አስታውስ ስኬት ማለት ሁልጊዜ በሕይወትህ ላይ አንድ ነገር እየጨመሩ መሄድ ማለት ብቻ ሳይሆን፣ አንዳንድ ነገሮችን መተውም እንዳለብህ፣ ራስን ማስገንዘብ እና ስርዓት ማስያዝ መሆኑንም ማወቅም ነው፡፡ ስኬታማ ልማዶችን ገንባ እና ዙሪያህንም በአሸናፊዎች ክበብ!!!
መጽሐፍ በገበያ ላይ ውሏል።