04/08/2026
ሉቺያኖ ቫሳሎ
🎁የጨዋታ ስፍራው ፤ አማካይ
🎁አለም አቀፍ ጨዋታዎች ብዛት፡ ብዙ
🎁የተጫወተባቸው ክለቦች ፡ ቅ/ጊዮርጊስ ፤ በገጀረት፣ በጂዲ አስመራ፣ በጥጥ ማህበር
🎁የክለብ ስኬት ፡ ዋንጫ
🎁ብሔራዊ ቡድን ስኬት ፡የአፍሪካ ዋንጫ ሻምፒዮን
የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አምበል ሉቺያኖ ቫሳሎ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው እና ትልቁ ድል የአፍሪካ ዋንጫ ሲገኝ የቡድኑ አምበል የነበረ ተጫዋች ነው።
በኤርትራ የተወለዱት፣ ቅይጥ ዜግነት ያላቸው እና በጣሊያንኛ ስም የሚጠራው የወቅቱ ታላቁ ተጫዋች ሉቺያኖ ቫሳሎ
በገጀረት፣ በጂዲ አስመራ፣ በጥጥ ማህበር እና በቅዱስ ጊዮርጊስ በክለብ ደረጃ እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በአምበልነት በመምራት ስኬታማ የተጫዋችነት ጊዜን አሳልፏል።
በኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ታሪክ ጉልህ ስም ያለው ሉቺያኖ በመድረኩ የብሔራዊ ቡድናችን የመጀመርያ ጎል አስቆጣሪ በመሆን ባለ ታሪክ ሲሆን በ3ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ጎል ማስቆጠር እና በአምበልነት ዋንጫውን ማንሳትም ችሏል።
በአስመራ የተወለደው ሉቺያኖ ከተጫዋችነት ባለፈ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ብሔራዊ ቡድን አጭር የአሰልጣኝነት ጊዜያት ያሳለፈ ሲሆን ረጅም ዓመታት በጣልያን ኑሮውን አድርጎ ቆይቶ በዚያው ህልፈቱ ሆኗል ።
ሉቺያኖ የአፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ "በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ 50 የምንግዜም ምርጥ አማካዮች" ውስጥ ተካቷል
(ለምስሉ ጥራት ይቅርታ 🙏)
🎁ኮከቦቻችን በዘመናት እርዝማኔ ተሸፍነው እንዳይረሱ እናስታውሳቸው 🎁
የኢትዮጵያን ቀደምት ከዋክብት እያነገስን አዲሶቹን እያሳደግን ታሪካቸውን ለመጪዎቹ እናሻግራለን ✅
🎁🎁🎁አፍሮ ሶከር ኢትዮጵያ🎁🎁🎁
🎁🎁🎁 የኢትዮጵያ ሌጀንዶች ቤት 🎁🎁🎁