Multi Ethnic Shoa

Multi Ethnic Shoa ሸዋ የትልቋ ኢትዮጲያ ማዕከልነቱን እንዳስጠበቀ ኅብረ ብሄራዊ ክልላዊ አስተዳደር ይዋቀራል፡፡

አፋብን ሸዋ ጠ/ግዛት ዕዝ - ማህበረሰቡን ያማረሩ አጋቾችን ፣ ዘራፊና ወንበዴዎችን የመመንጠሩን ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል!በሁሉም ቀጠና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነው!.  ፋኖ የሌባ እና...
23/03/2026

አፋብን ሸዋ ጠ/ግዛት ዕዝ - ማህበረሰቡን ያማረሩ አጋቾችን ፣ ዘራፊና ወንበዴዎችን የመመንጠሩን ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል!

በሁሉም ቀጠና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ተግባር ነው!. ፋኖ የሌባ እና የባንዳ ጥርቅም ነው የምንላችሁ በምክንያት ነው።

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት መስራች እና ምክትል አዛዥ ኮረኔል ማነገረው መለሰ ከእነ ኮረኔል ፋንታሁን ሙሐቤ ጋር 👇
22/03/2026

የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት መስራች እና ምክትል አዛዥ ኮረኔል ማነገረው መለሰ ከእነ ኮረኔል ፋንታሁን ሙሐቤ ጋር 👇

   የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል አዛዥ፣ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ወታደራዊ አዛዥ ኮ/ል ማነገረዉ መለስ መዘዞ ከተማ  እጁን ለመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች ሰጥቷል።ግለሰቡ በቡድኑ ዉስጥ ...
17/03/2026



የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል አዛዥ፣ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ወታደራዊ አዛዥ ኮ/ል ማነገረዉ መለስ መዘዞ ከተማ እጁን ለመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች ሰጥቷል።

ግለሰቡ በቡድኑ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበረ ቡድኑንም ከመሰረቱ ዋነኛዉ ሰዉ ነበር። በአሁኑ ሰዓት በጣርማ በር ወረዳ ጣርማ በር ዋሻዉ ላይ በሰራዊቱ እጅ ይገኛል።

 #‎አንኮበር‎‎ኢትዮጵያ ሀገሬ ሀገረ እግዚአብሔር ፣‎የማርያም አስራት የነገስታት ሀገር ፣‎ታሪክሽ ቢወሳ ዝናሽም ቢነገር፣‎አያልቅም ተጠቅሶ በሰው ልጅ ከናፍር።‎አባይን በጭልፍ ቢሆንም ታሪክ...
08/03/2026

#‎አንኮበር

‎ኢትዮጵያ ሀገሬ ሀገረ እግዚአብሔር ፣
‎የማርያም አስራት የነገስታት ሀገር ፣
‎ታሪክሽ ቢወሳ ዝናሽም ቢነገር፣
‎አያልቅም ተጠቅሶ በሰው ልጅ ከናፍር።
‎አባይን በጭልፍ ቢሆንም ታሪክሽ፣
‎ከብዙ አካላትሽ ከብዙ ታሪክሽ፣
‎የነገስታቱን ምድር አንኮበርን ላንሳልሽ።
‎በአብርሃ እና አፅብሃ የተመሰረተች ፣
‎በአፄ ይኩኖአምላክ የተመሰረተች፣
‎የነገስታት ቦታ የታሪክ ጮራ ነች ።
‎እነ መርድ አዝማች እነ አምሀኢየሱስ፣
‎አፅማቸው ያረፈው አንኮበር ጊዮርጊስ ፣
‎ሣህለ ሥላሴ ኢትዮጵያን የገዛው ፣
‎አንኮበር ሚካኤልን በክብር የሳነፀው፣
‎የወለሉን አፈር ከእስራኤል ያስመጣው፣
‎አፅመም በዚያው ቦታ በክብር የሚገኘው ፣
‎ያየጥቁር ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ፣
‎የጥቁር ነፃነት የስልጣኔ ልክ፣
‎ጎንደር ውስጥ ያደገው የኢትዮጵያው መሪ ፣
‎ስሙ እንኳን ሲጠራ የሚያሰኘው እሪ፣
‎ያሰው ምኒልክ ነው አንኮበር መስክሪ ።
‎ምን ብዬ ልግለፃት እምዬ አንኮበርን፣
‎ለአንቺማ ፈጣሪ አላዳላም ይሆን?
‎እውነት አምላክ ለአንቺ አላደላም ይሆን ?
‎እንቁ መስህቦችን በብብትሽ የያዝሽ፣
‎ጥቂቱን ልመስክር ጥቂቱን ላንሳልሽ።
‎አንኮበር ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣
‎ሣህለ ሥላሴ ያሳነፀውን፣
‎ገብስ እህል ከሰማይ ያወረደውን፣
‎ምሰሶው እስከ አሁን ደዌ ፈዋሹን፣
‎ሀዋርያዊ መስቀል ምስል የጻድቃን፣
‎ታሪክ የታየበት ጷግሜ ሶስት ቀን።
‎እጅግ ያስደንቃል አንኮበር ውበትሽ፣
‎ብርኩሚት ማርያምን በብብትሽ ይዘሽ፣
‎ተዓምርሽ ብዙ ነው ብርኩሚት ማርያም፣
‎ከጎንሽ አለና መዳኛ ለአለም፣
‎በእቅፍሽ አለና መድሀኔ አለም።
‎አስቲት ላይ ያለችው ኪዳነ ምህረት፣
‎በክብር የሞላት ሰባት መቶ አመት።
‎ቸነፈር ሲበዛ ረሀብ ሲከሰት፣
‎በአምሀ ኢየሱስ ዘመነ መንግስት፣
‎ስንዴ ከሰማይ ላይ የወረደባት፣
‎የመስጫ ማርያምን ምን ብዬ ልርሳት።
‎የዋሻው ገብርኤል ጎርጎ የሚገኘው፣
‎በአምሀ ኢየሱስ የተቦረቦረው።
‎ህዝቅኤል የሰራው ቦታው የሰላም፣
‎ሚጣቅ ተክለ ሀይማኖት አንድነት ገዳም፣
‎የአበዉ ቅዱሳን የጠበል መገኛ፣
‎እውራንን አብሪ የድውይ መዳኛ።
‎የመነኩሴ ዋሻ እመ ምህረት ያለው፣
‎መናኝ ጸሎተኛን አቅፎ የሚይዘው፣
‎ስንቱን ልዘርዝረው ታሪክሽ ብዙ ነወ።
‎እነ ሊቅ ማረፊያ መሀል ወንዝ ያለው፣
‎የተማሩ ሰዎች መቀመጫቸው፣
‎እምዬ ምኒልክ የመሰረተው፣
‎ሀኪሙ ዶክተሩ ጂኦግራፈሩ፣
‎ዋና መቀመጫው እዚያ ነው ሰፈሩ።
‎የጋጀሎ ቦታ ያ የመሀል ወንዙ፣
‎የባሩድ ማንጠሪያ ጥይት ለአፈሙዙ።
‎እምዬ አልዬ አምባ የጉምሩክ ከተማ፣
‎አማራን ከአርጎባ በአንድ የምታስማማ፣
‎ደምቃ የምትታይ በታሪኳ ማማ።
‎የአልዬ መኖሪያ ነጋዴው ሲራራ፣
‎ጥንታዊ መስጊዱ ከሩቅ የሚያበራ።
‎ወፍ ዋሻ ጥቅጥቁ የተፈጥሮው ደን፣
‎በእቅፉ የያዘው እንቁ ሶረኔን።
‎በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለሽ፣
‎እጅግ ያስደንቃል አንኮበር ውበትሽ።
‎በዙሪያሽ የያዝሽ እንቁ መስህቦችን፣
‎እውነት አምላክ ለአንቺ አላደላም ይሆን?
‎የታሪክ ባለቤት የነገሥታት ምድር፣
‎ሰዓታት አይበቁም ታሪክሽ ቢነገር፣
‎ከኢትዮጵያ እንብርት ከሸዋዎች መንደር፣
‎አንኮበር አንኮበር አንኮበር አንኮበር ።

‎ገጣሚ፦ ዜና ሸዋበረ (ዜሾ)
‎ ቀን፦ 27/05/2014 ዓ.ም አንኮበር; ኢትዮጵያ

የበልበሊት እየሱስ ገዳም....!ይህ ገዳም በእንሳሮና መረሐቤቴ መሀል፣ በጀማ ሸለቆ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ በ152 ኪ.ሜ ከደብረብርሀን 105 ኪ.ሜ እንዲሁም ከለሚ ከተማ በ2...
07/03/2026

የበልበሊት እየሱስ ገዳም....!

ይህ ገዳም በእንሳሮና መረሐቤቴ መሀል፣ በጀማ ሸለቆ አቅራቢያ የሚገኝ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ በ152 ኪ.ሜ ከደብረብርሀን 105 ኪ.ሜ እንዲሁም ከለሚ ከተማ በ22 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል።ገዳሙ ልዩ ጸጋዎችና ቅርሶች፡ሲኖሩት

የግብፅ ስደት መታሰቢያ፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስደት ዘመን ከእናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ካረፈባቸው 5 ገዳማት አንዱ እንደሆነ ይነገራል።

የተፈጥሮ ሀብት፡ አካባቢው ምንም እንኳን ደረቅ ቢመስልም፣ በገዳሙ ውስጥ ግን ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ሙዝና ሸንኮራ ከአመት አመት ይመረታል።

ሚስጥራዊ ዋሻዎች፡ አቡነ ዜናማርቆስ እና አቡነ ተክለኃይማኖት የጸለዩበት፣ እስከ እየሩሳሌም የሚያስኬድ መንገድ እንዳለው የሚታመንበት እና በ"ተርቦች" የሚጠበቅ አስደናቂ ዋሻ ይገኝበታል።

ፈዋሽ ጸበል፡ ከተለያዩ ህመሞች የሚፈውስ ጸበል እና በአቡነ ተክለኃይማኖት ዘንግ ፈልቆ ለመዋኛነት የሚያገለግል ገንዳ አለው።

በአድዋ ተራሮች ለኢትዮጵያ ክብርና ለጥቁር ሕዝብ ነፃነት ሲሉ የተዋደቁትን ጀግኖች አባቶቻችንንና እናቶቻችንን ሁሌም በታላቅ ኩራት እናስባቸዋለን።መልካም የአድዋ ድል በዓል!
02/03/2026

በአድዋ ተራሮች ለኢትዮጵያ ክብርና ለጥቁር ሕዝብ ነፃነት ሲሉ የተዋደቁትን ጀግኖች አባቶቻችንንና እናቶቻችንን ሁሌም በታላቅ ኩራት እናስባቸዋለን።

መልካም የአድዋ ድል በዓል!

አለምን ያንቀጠቀጡ ብቸኛ የምድሪቱ ክስተት አፄ ሚኒሊክ ናቸው 💪✅
01/03/2026

አለምን ያንቀጠቀጡ ብቸኛ የምድሪቱ ክስተት አፄ ሚኒሊክ ናቸው 💪✅

ልጅ ኃይለማርያም_ማሞ!!ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ በትውልድ ሃገራቸው ደብረብርሃን ሲሆን ከጣሊያን ፋሽስት ጋር በአንድ ቀን ውስጥ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ጦርነት 4 የጠላት መኪናዎችን በማ...
28/02/2026

ልጅ ኃይለማርያም_ማሞ!!

ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ በትውልድ ሃገራቸው ደብረብርሃን ሲሆን ከጣሊያን ፋሽስት ጋር በአንድ ቀን ውስጥ በአደረጉት እልህ አስጨራሽ ጦርነት 4 የጠላት መኪናዎችን በማቃጠል፣ 40 የፋሽስት ወታደሮችን በመግደል ትልቅ ታሪክ የሰሩ ዘመን የማይሽራቸው ጀግና ነበሩ፡፡

ሃገር አማን ብሎ ወደ መሀል ሃገር በሚተመው የፋሽስት ወራሪ ኃይል ላይ በደፈጣ ውጊያ ከፍተኛ ኪሳራ አደርሷል፡፡ በዚህም የተነሳ መጪው ዘመን ከጀግኖኞች አርበኞች ጋር ለፋሽስት ኢጣሊያ ጨለማ መሆኑን የተግባር መልዕክት እሰተላለፉ፡፡

ደጃዝማች ኃይለማሪያም ማሞ በአሥር ሰዓት ገደማ ላይ ከቤቱ ተነሥቶ ጫጫ ሱኬ ሴራቤ ከምትባለው ቀበሌ ምቹ ቦታ ይዘው ጠበቁት ፤ ጠላትም ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ አልፋለሁ ሲል አደጋ ጥለው አምስት ካሚኒዮኖች ሰብረው በውስጡ የነበሩትን አንድ መቶ አርባ የሚሆኑ የጠላት ወታደሮች ገድለው ሰባት ማረኩ፤ ከእነዚሁ ሁለት ሸሽተን እናመልጣለን ብለው ሲሞክሩ በጥይት ተመትተው ተያዙ፡፡

ይህ የደጃዝማች ኃይለማሪያም ማሞ ገድል የመንፈስ ጥንካሬ የዘራባቸው የሸዋ ጎበዛዝት ቀፎው እንደተነካበት ንብ በነቂስ ለምተመም አልዘገየም ነበር፡፡ ያላቸው ጥይትም ሆነ ስንቅ የሚያወላዳ ስላልነበረ ምሽግ ይዞ ከመዋጋት ይልቅ የደፈጣ ወጊያን ምርጫቸው አደረጉ፡፡

ጥሬ በቆሎ ቀርቀጭ እያደረጉ፣ ከወንዝ ውሃ እየተጎነጩ፣ በአንድ ቦታ ሳይረጉ ጣሊያንን በደፈጣ ውጊያ መግቢያ መውጪያ አሳጡት፡፡ ደጃዝማች ኃይለማርያም በጠላት ጦር ላይ ባደረሱት ተደጋጋሚ ጉዳት የፋሺስት ጦር ደጃዝማች ኃይለማርያምን ከዋነኛ ጠላቶቹ መካከል አንዱ አደርጎ እንዲፈርጃቸው ተገዷል፡፡

በደብረ ብርሃንና አካባቢው የነበረው የፋሺስት ጦር ደጃዝማች ኃይለማርያምን መደምሰስ ስላልቻለ በርካታ ወታደርና ትጥቅ ከሌሎች አካባቢዎች ለመውደስ ተገዶ ነበር፡፡ ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች ኃይለማርያም ማሞ ግንቦት 28 ቀን 1930 ዓ.ም ቡልጋ ውስጥ በተደረገ ከባድ ጦርነት ላይ ህይወታቸው አለፈ።

👉የፋሺስት ጦር ከኢትዮጵያ ከተባረረ በኋላም ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ በስማቸው ት/ቤት ተገንብቶላቸዋል፡፡

👉በአዳማ (ናዝሬት) ከተማ የሚገኝ ሆስፒታልም በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥም በስማቸው የተሰየመ መንገድ ይገኛል፡፡

👉ከዚህ በተጨማሪም፣ 75ኛው የአርበኞች ድል መታሰቢያ ሲከበርም ከሌሎች 25 ታላላቅ አርበኞች ጋር በስማቸው የመታሰቢያ ቴምብር ታትሞላቸዋል፡፡

ለደጃዝማች ኃ/ማርያም ማሞ ጀብድና ጀግንነት ከተገጠሙ ግጥሞች መካከል…

ኃይለማርያም ማሞ የጦሩ ገበሬ፣
ይኸንን ሶላቶ ነዳው እንደበሬ።

መተኮሱንማ ማንም ይተሳል፣
ኃይለማርያም ማሞ አንጀት ይበጥሳል።

ሀይለማሪያም ማሞ የጦሩ ገበሬ፣
ፈረሱን እንደሰዉ አስታጠቀዉ ሱሬ፡፡

ኃይለማርያም ማሞ የጦሩ ገበሬ፣
እያላጋው መጣ ነጬን ከነጭ በሬ፡፡

ተብሎ ተገጥሞላቸዋል ።

ለስራ ፈላጊወች የቅጥር ማስታወቂያዎች 👇
26/02/2026

ለስራ ፈላጊወች

የቅጥር ማስታወቂያዎች 👇

ሸዋ የደራሲያን፣ የአርበኞች፣ የነገሥታት መፍለቂያ!ሸዋ ውስጥ በመሳፍንትነትና፣ በመኮንነት እያገለገሉ፣ በድርሰቱም የኢትዮጵያ ስነ- ጽሑፍ ከፍ አርገው እና ሀገርን  በማቋቋም ትልቅ ሚና ያላቸ...
25/02/2026

ሸዋ የደራሲያን፣ የአርበኞች፣ የነገሥታት መፍለቂያ!

ሸዋ ውስጥ በመሳፍንትነትና፣ በመኮንነት እያገለገሉ፣ በድርሰቱም የኢትዮጵያ ስነ- ጽሑፍ ከፍ አርገው እና ሀገርን በማቋቋም ትልቅ ሚና ያላቸው የሸዋ መሳፍንት እና መኳንት !

👉ጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ ወልድ
👉ጸሐፌ ትዕዛዝ ገብረ ሥላሴ
👉ተከለ ጻድቅ መኩሪያ
👉ከበደ ሚካኤል
👉አምባሳደር ከተማ ይፍሩ
👉መርስኤ ኃዝን ወለደ ቂርቆስ
👉ራስ መኮንን
👉አለቃ ኪዳን ወልድ ክፍሌ
👉አለቃ ዘነበ
👉መኮንን ሀብተ ወልድ
👉ዶ/ር ተፈራ ደግፌ
👉 ደስታ ተክለ ወልድ
👉ራስ ተሰማ ናደው
👉ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም
👉ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ
👉ጸሐፌ ትዕዛዝ ወልደጊዮርጊስ ወልደ ዮሐንስ
👉ራስ አበበ አረጋይ
👉ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደ መድኅን
👉ራስ አባተ ቧ ያለው
👉ብላቴን ጌታ ማሕተመሥላሴ ወልደመስቀል
👉ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ
👉ቀኝአዝማች ተስፋ ገብረሥላሴ
👉አርበኞ ሸንቁጥ
👉ደጃዝማች ተሾመ ሸንቁጥ
👉ልጅ ኃይሌ ሸንቁጥ
👉ደጃዝማች አበበ ሸንቁጥ
👉ልጅ ይነሱ ሸንቁጥ
👉ልጅ ጥላሁን ሸንቁጥ
👉ደጃዝማች ሐብተሥላሴ በላይነህ
👉የዓለም ሎሬት መላኩ ወረደ
👉የዓለም ሎሬት ዶክተር አርቲስት አፈውርቅ ተክሌ
👉ልጅ ኃይለ ማርያም ማሞ
👉ራስ ደስታ ዳምጠው
👉ፊታውራሪ ገበየሁ
👉አርበኛ ሽዋረገድ ገድሌ
👉ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ
👉አርበኛ አስማረ ዳኜ

እነዚህ እና ሌላም በጀግንነታቸውና በድርሰታቸው ከፍተኛ የስነ ጽሑፍ ሚና ያላቸው እነ "ዳኛቸው ወርቁ" አሉ "አደፍርስ" በሚል ርእስ እስከ ዛሬ ድረስ ሕዝብን ያስደነቀ ነው።

በተለይ የኢትዮጵያን ታሪክ ለሕዝቡ በማሳወቅ ደረጃ "ተክለ ጻድቅና ብላቴን ጌታ ኅሩይ" ሁሌ በልባችን አሉ።

ሽዋ የሙህራንና የጀግኖች የነገሥታት መፍለቂያ።

✍️ Abreham Demeke

እናንተም ጨምሩበት🙏

ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ካፈራቸው አንዱ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ!   (ከ1906_1992 ዓ. ም)ታላቅነት አይወረስም፣ ይቀዳጁታል እንጂ። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ከጐተራ ጸሐፊነትና የመዝገብ አለቃነት እስ...
25/02/2026

ሽዋ ጠቅላይ ግዛት ካፈራቸው አንዱ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ!
(ከ1906_1992 ዓ. ም)

ታላቅነት አይወረስም፣ ይቀዳጁታል እንጂ። ተክለ ጻድቅ መኩሪያ ከጐተራ ጸሐፊነትና የመዝገብ አለቃነት እስከ ሚኒስተርነት ፣ ከዚያም ዕውቅ ደራሲ እስከ መሆን የበቁት በመንፈስ ፅናትና ብርታት፣ በግል ጥረትና ቁርጠኝነት በመሆኑ ነው።

ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ በምትገኘው አሳግርት ወረዳ አቆዳዳ ወይም ሣር አምባ መንደር መስከረም ፩(1) ቀን ፲፱፻፮(1906) ዓ.ም ተወልደው፣ ሐምሌ ፲፮(16) ቀን ፲፱፻፺፪ (1992) ዓ.ም ይችን ዓለም ሲለይዋት፣ ኢትዮጵያ ከብርቅየ ልጆቿ አንዱን አጣች። ተክለ ጻድቅን የመሰለ ታላቅ ዜጋ አረፈ እንጂ ሞተ አይባልም። ድርሳኖቻቸው ለዘለዓለም ሕያውነታቸውን ሲያወሱላቸው ሲያስመሰግኑአቸው ይኖራሉና።

‎ይህንን ውለታቸውን በመገንዘብ ነው ላዕከ ተክለማርያም ሐምሌ 20 ቀን 1992 ዓ.ም ለተክለፃዲቅ መኩሪያ
‎የሚከተለውን ቅኔ ያቀረቡት።

‎ተክለፃድቅ መኩሪያ
‎ያንድ ቤት ያስር ቤት የመቶ ቤት እያልን፣
‎የታሪኩን ሂሳብ ገና እያሰላሰልን፣
‎በሺ ቤት መቁጠሩን ሳንማርልዎ፣
‎አቶ ተክለፃድቅ ምነው መሔድዎ ?
‎እንግሊዝ ፈረንሳይ ጣሊያኖች እረፉ፤ ሃሳብ አይግባችሁ፣
‎አይመጣም እንግዲህ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚጠይቃችሁ።

‎ያፄ ልብነ ድንግል የቦካን ተራራ፣
‎ያፄ ፋሲል ጎንደር የመቅደላ ጎራ፣
‎እንደ ተክለፃዲቅ ከሌለህ ወዳጅ፣
‎ማን ይፅፍልሃል ተረስተህ ቅር እንጂ።
‎ተክለፃዲቅ መኩሪያ የበቀለብሺ፣
‎ኩሪ አገሬ ቡልጋ ደብረ ፅላልሺ።
‎የተፈለፈለ የተሰራ ከአለት፣
‎እንደ ላሊበላ እንደ አክሱም ሐውልት፣
‎የታሪክ አምድ ነው ተክለፃዲቅ መኩሪያ፣
‎መናኸሪያ እሚሆን መነሻ መድረሻ።

‎ታሪክ ይመላለስ እንደ ለመደው፣
‎የማይመለሰው ተክለፃዲቅ ነው።
‎ከዚያ ከትልቁ ከሰማይ ቤት፣
‎የምትፅፈውን ታሪክ ለመስማት፣
‎ልሂድ ካንተ ጋራ አብሬ ልሙት፣
‎ተክለፃዲቅ መኩሪያ የታሪክ አባት።

‎የተክለፃዲቅ ነፍስ ምን ቸግሯት ቦታ፣
‎ቢሻት ከአብርሃም ጎን ከነ ይስሃቅ ተርታ፣ ቢሻት ከቴዎድሮስ ከዮሐንስ ጋራ፣
‎ቢሻት ከምንልክ ከተፈሪ ጋራ፣
‎ትኖራለች የትም እንደ ልቧ ሆና፣
‎እየፃፈች ታሪክ በጽድቅ ብራና።

‎ታሪክ አልማርም ባፍንጫዬ ይውጣ፣
‎ተክለፃድቅ መኩሪያ መምሕሬ ከታጣ።
‎ጥያቄ አትጠይቁኝ አታስቸግሩኝ፣
‎ተክለፃድቅ መኩሪያ ማነው አትበሉኝ፣
‎ጣይ ሞቆት ጣይ ሞቆት አገር ያወቀው፣
‎ተረት ተረት ሳይሆን ታሪክ ፃፊ ነው።

ተክለ ጻድቅ መኩሪያ በአማርኛ ጽፈው ለኢትዮጵያ ያበረከቷቸው 13 መፃህፍት!

፩: የኢትዮጵያ ታሪክ ኑብያ(ናፓታ-መርዊ)
፪:የኢትዮጵያ ታሪክ አክሱም-ዛጉዬ
፫:የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ይኲኖ አምላክ- ዐፄ ልብነ ድንግል
፬ :የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ልብነ ድንግል- ዐፄ ቴዎድሮስ
፭:የኢትዮጵያ ታሪክ ከዐፄ ቴዎድሮስ-ዐፄ ኃይለ ሥላሴ
፮: ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና
፯: የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ
፰: ጥንታዊት ኢትዮጵያና ግብፅ
፱ : የግብፅ፣ የሳባና የኢትዮጵያ ፊደሎች (ማስታወሻ)
፲ : የግራኝ አህመድ ወረራ
፲፩: ዐፄ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት
፲፪: ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት
፲፫: ዐፄ ምኒልክና የኢትዮጵያ አንድነት
እንዲሁም የሕይወት ታሪካቸውንና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ፭(5) መጻሕፍትን ጽፈዋል።

ሽዋ ጠቅላይ ግዛትን እጅ እንነሳለን🙏

ይገርምሃል ሸዋ !   ዳግም አልወለደችም አንድ ነው ለእናቱ። ሣህለ ማሪያም ፡ ኃይለ መለኮት ፡ ሣህለስላሴ ብርቱ ሠው ነው። ራሱን ሲጠራ  አጤ ምኒልክ ንጉሠ ሸዋ (አጤ ምኒልክ  ንጉሠ ነገሥ...
25/02/2026

ይገርምሃል ሸዋ !

ዳግም አልወለደችም አንድ ነው ለእናቱ።

ሣህለ ማሪያም ፡ ኃይለ መለኮት ፡ ሣህለስላሴ ብርቱ ሠው ነው። ራሱን ሲጠራ አጤ ምኒልክ ንጉሠ ሸዋ (አጤ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ) ብሎ ነው።

በማንም ዘመን ፣ በየትኛውም ግዜ በቆዳ ቀለሙ ፣ በሚናገረው ቋንቋ ፣ በሚስቱ ዘመዶች ፣ በሌላም ሌላም የሠው ፍጡር በሆነ ሠይሞ አያውቅም ። ምናበ ሠፊ ፣ አርቆ ተመልካች ፣ ትኩስ ደግሞ ገር ነው ።

እኔ በእግዝሐር አምሳል የተፈጠርኩ ፣ የእግዝሃር ባሪያ ነኝ ማለት ወጉ ነው ።

ለፈረንጆች አዲስ አይደለም ። አብሯቸው ከታሠረበት ከመቅደላ ጀምሮ ያውቃቸዋል ። ከፈረንጅ በመዋል ስለቆዳ ቀለማቸው ፣ ስለሚናገሩት ቋንቋ ስለሌላም ሌላም ጠይቋቸው፣ ግድ ሠጥቶትም አያውቅም ። በእለት በእለት በደጃፉ ለሚረግጡ አውሮፓውያን የነበረው አንድ ጥያቄ ብቻ ነው ።

" ምን ሙያ አለህ ?" የምትል ብቻ ።

የመሠልጠን ጥም ፣ የዘመናዊነት ህልም ፣ የከፍታ ራእይ ብቻ ነው ያለው ።

በምኒልክ ቤት ሐፍረት አለመቻል ነው ። አለመስራት ። "ወስላታ" - ታሉ በቃ ነው ።

ከፊት ቀድመው ፣ ሀገርን ማስቀደም ፣ ህዝብን መምራት ፣ ያኮረፈውን አባብሎ ፣ የጠገበውን አስተንፍሶ ፣ አቻችሎ መኖር ያውቅበታል ። እሱ የሠተራት ትልቋ ኢትዮጵያ ፣ አይኗን ሳትገልጥ ከፊቷ የተደቀነውን ፈተና ፣ አደዋ ላይ የረታው በዚሁ ጥበቡ ነው ።

አጤ ምኒልክ በአደዋ ድል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን በደም አሻራ አተመ ። ይህ ዘልዓለማዊ ማህተም መቼም ላይፋቅ ፣ በሠማየ ሠማያት ፣ ከግሪክ አማልክት ከነዜውስ ፣ አንድሮሜዳ ጋር ፣ ምልክት ተቀምጦለታል ።

የአደዋ ድል - ጥቁር ነን በሚል ውዳቂ ተረት ነጮችን ለመመከት አልወጣም ፣ ከእከሌ ዘር ነኝ በሚል ሌላ ዘር ለመውጋት አልተሠለፈም ፣ በመከፋፈል የሚኖርን ሠው ወለድ ስርዓት ፣ በአንድ በሚያስር መለኮታዊ ዓላማ ስር አስተባብሮ ተዋጋ እንጂ።

ለኢትዮጵያዊ ማንነትህ
ለኢትዮጵያዊት ሚስትህ
ለኢትዮጵያ ምድር
ለኢትዮጵያዊቷ እናትህ
ኢትዮጵያዊ መንግስትህን ሊወጋ የመጣ ጠላት አለና ፣ የመኖርህን አስትናፋስ ፣ ልእለ ህላዌ ከፊት ቀድመህ አስመስክር አለ እንጂ።

መከፋፈልን በአንድነት ፣ ዘረኝነትን በሠብዓዊነት ፣ እብሪትን በጀግንነት ማሸነፍን ላስተማረን ሚኒልክ አባታችን ክብሩ ይስፋ ። ስሙ ዳግም ደግም በትውልዶች ሁሉ ይነሳ ። ከእሱ ጎን የቆሙ ፣ ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ ናቸውና ዳግም ይባረኩ ።

ኢትዮጵያዊነትን አፀና!
የእግዚአብሔር አምሳለ ፍጡርነትን አፀና!

***

#ዓድዋ130





Address

Addis Ababa
WWW.MULTIETHNICSHOA.COM

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Multi Ethnic Shoa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share