Dymans-Eth

Dymans-Eth አዳዲስ እና ትኩስ መረጃዎች የምታገኙበት page ነዉ። ቤተሰብ ይ?

 የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ 'በወንጀል የተጠረጠሩ' የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አሳወቀ።በዚህም መሰረት፦- ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካ...
12/11/2020



የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ስብሰባው ላይ 'በወንጀል የተጠረጠሩ' የምክር ቤት አባላትን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱን አሳወቀ።

በዚህም መሰረት፦

- ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል
- አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት
- አቶ አባይ ፀሃዬ
- ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ
- አቶ ጌታቸው ረዳ
- አቶ አፅበሃ አረጋዊ
- አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ ጨምሮ ሌሎችን ግለሰቦችን ያለመከሰስ መብታቸውን ምክር ቤቱ አንስቷል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋትና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል፦

የህ/ተ/ም/ቤት አቶ ፍቅሩ ገ/ሕይወትን የምርጫ ቦርድ አባል አድርጎ ሾሟል። (ኢቲቪ-HoPR)

DYMANS - ETH

 - በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1...
23/06/2020



- በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1 ሰው ከሸበዲኖ፣ 1 ሰው ከዳሌ፣ 1 ሰው ለዳራራ ፣ 1 ሰው ከአርቤጎና ነው።

- በኦሮሚያ ክልል 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ከሰበታ ፣ 1 ሰው ከሰንዳፋና 1 ሰው ከጉጂ ናቸው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ንክኪ ያላቸው ናቸው።

- በትግራይ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው።

- በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ከባህር ዳር ናቸው ፤ ሁለቱም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

- በአፋር ክልል 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 72 ደረሰዋል።

- በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- በሐረሪ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ግለሰቡ የሱማሌ ክልል ነዋሪ ሲሆን ለህክምና ሐረር መጥቶ ናሙና የተወሰደለት ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ባሉት ምስሎች ታገኛላችሁ!

ዱባይ!ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዝ እንደሚችሉ በመፍቀድ አንስተዋለች።ከዚህ በተጨማሪም በውጭ የ...
23/06/2020

ዱባይ!

ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዝ እንደሚችሉ በመፍቀድ አንስተዋለች።

ከዚህ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩና ወደ ዱባይ መግባት ለሚችሉ ሰዎች ከሐምሌ ሰባት ጀምሮ ወደ ዱባይ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዱባይን ለመጎብኘት የሚመጡ የውጭ ዜጎች በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዱባይ አየር መንገድ ውስጥ እንደገና ለመመርመር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

✅ያገገሙ ሰዎች 108 ደርሷል!በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ  ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፣ እስከ አሁን በአገሪቱ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል።ጤና ሚኒስተ...
13/05/2020

✅ያገገሙ ሰዎች 108 ደርሷል!

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 2 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከተማ ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፣ እስከ አሁን በአገሪቱ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 108 ደርሷል።

ጤና ሚኒስተር
𝐉𝐎𝐈𝐍➦

DYMANS-ETH ይህ ቻናል የተከፈተው በአለም ላይ እንዲሁም በሀገራችን ኢትዮጵያ አስጊ ደረጃ ላይ የደረሰውን ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የሚያስፈልጉንን እስካሁን ያልተሰሙ ቅድመ ሁኔታዎች ለማ.....

በአሜሪካ ኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬው በይፋ...
11/04/2020

በአሜሪካ ኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬው በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ይህን ብለዋል ፦

"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"

https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/

fb.me/dymansethiopia

 የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።ክልከላን ...
11/04/2020



የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይፋ አደረገ።

ክልከላን በሚመለከት፦

- ማንኛውም ሃይማኖታዊ ይሁን ፖለቲካዊ ስብሰባዎች፣ እድር፣ ደቦ፣ እቁብና ሌሎችም ከ4 ሰው በላይ ስብሰባዎች ክልክል ናቸው።

-አራት ሰዎችም ቢሆኑ ሁለት የአዋቂ ሰው እርምጃ የጠበቀ መሆን አለበት።

- ቀብርና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮች ሲኖሩ ግን እየታዩ ሊፈቀዱ የሚችሉበት አሰራር ይኖራል።

- ታራሚዎች ከጠበቆቻቸው ጋር አስፈላጊው ጥንቃቄ ተደርጎ እንዲገናኙ የሚፈቀድ ቢሆንም ጥየቃ ለሚሄዱ ሰዎች አይፈቀደም።

- በፖሊስ የተያዙ እስረኞችንም ስንቅ ከማቀበል በስተቀር መገናኘት የተከለከለ ነው።

- በድንበር አካባቢ ከካርጎ፣ የደረቅና ፈሳሽ ጭነት አገልግሎቶች በስተቀር ሌሎች እንቅስቃሴዎች ዝግ ተደርገዋል።

- የቤት ተከራዮች በራሳቸው ፍላጎት ካልወጡ በስተቀር ማስወጣትና ኪራይም መጨመር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተከልክሏል።

- ሰራተኞችን መቀነስና የስራ ቅጥር ውል ማቋረጥም ተከልክሏል።

- ተማሪዎችና መምህራን በኦን ላይን ካልሆነ በአካል እንዲገናኙ አይፈቀድም።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት (4) ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባ...
11/04/2020

በኢትዮጵያ ተጨማሪ አራት (4) ግለሰቦች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው!

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 345 ግለሰቦች መካከል አራቱ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ እስካሁን ባለው ሂደት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ለሶስት ሺህ 500 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተከናውኗል።

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው አራቱም ግለሰቦች ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውንም ነው የገለጹት።

ሁለቱ ወንድ ሁለቱ ደግሞ ሴቶች ሲሆኑ ሶስቱ የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።

ከእነዚህም መካከል አንድ የ30 ዓመት ሴትና አንድ የ29 ዓመት ወንድ ኢትዮጵያዊያን ከዱባይ መጥተው በለይቶ ማቆያ ክትትል ሲያደርጉ የነበሩ መሆኑን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

አንድ የ33 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ደግሞ የአሜሪካ አገር የጉዞ ታሪክ ያላት ናት።

ሌላኛው ግለሰብ የ42 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው ብለዋል። ግለሰቡ የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን፤ በህመሙ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ እንዳለውና እንደሌለው እየተጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dymans-Eth posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Dymans-Eth:

Share