Akotet Graphics Design and Digital Marketing

Akotet Graphics Design and Digital Marketing Akotet Digital Marketing

21/06/2023
Social media post design.
22/03/2022

Social media post design.

Daily social media design. You wanna growth your business? We can design your social media post and your social media go...
26/01/2022

Daily social media design.
You wanna growth your business? We can design your social media post and your social media gonna be clear and attractive.

Just contact us on: 09011305018.

💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂ ➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን...
05/03/2020

💻የኮምፒውተር ኪቦርዳችን ላይ ከላይ የሚገኙትን (F1-F12) በተኖች ጥቅማቸውን ያውቁ ኖሯል?
▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂▂

➢ካላወቃችሁ አትጨነቁ!! ዛሬ የተወሰነ ጥቅማቸውን እናሳያችኋለን፡፡ እነዚህን የኪይቦርድ በተኖች ከዚህ በፊት ድምፅ ለመጨመር እንዲሁም የብርሃን መጠን ለማስተካከል ተጥቀምውባቸው ይሆናል፡፡

➢ነገር ግን ጥቅማቸው ከዚህ ከፍ ያለ ነው ሁሉም ኮምፒውተር በሚያስብል ሁኔታ እነዚህን በተኖች ይዞ ነው የሚመጣው፡፡ እና ምንም ማስተካከል ሳያስፈልግ መጠቀም እንችላለን። ይሁን እንጂ አንዳንድ ኮምፒውተሮች ላይ እነዚህን በተኖች ለመጠቀም FN (https://t.me/Computer_Android_tricks) የሚለውን በተን በቅድሚያ መንካት አለብን::

❖ከF1 እስከ F12 ያሉትን በተኖች ጥቅም አንድ በአንድ ከስር ዘርዝረናል ....

☛ሼር በማድረግ ከራስዎ አልፈው ለሌሎችም ይትረፉ፡፡

❒የ F1 ጥቅሞች
► ከ”Windows ቁልፍ (button) ጋር በጋራ ስንነካው help menuን ያመጣልናል፡፡
► Excel እና Word በምንጠቀምበት ወቅት ከ Control ጋር በጋራ ስንነካው Hides or displays ribbon menu ያደርግልናል፡፡

❒የ F2 ጥቅሞች
◕ Alt + Ctrl + F2 - opens Document Library in Microsoft Office
◕ Allows you to edit the selected folder or file name in Windows Explorer

❒የ F3 ጥቅሞች
► Opens search feature in Windows Explorer
► Shift + F3 - lets you change from lowercase to uppercase to all caps in Word
► Opens find feature in Firefox and Chrome

❒የ F4 ጥቅሞች
◕ Alt + F4 closes window
◕ Places the cursor in the address bar in Explorer

❒የ F5 ጥቅሞች
► Starts slideshow in Power Point
► Refreshes Internet browser pages
► Opens Find and Replace in Microsoft Office

❒የ F6 ጥቅሞች
◕ Goes to the next page in a split screen in Microsoft Word
◕ Ctrl + F6 lets you easily switch between Word documents

❒የ F7 ጥቅሞች
► Alt + F7 does a spelling and grammar check in Microsoft Word
► Shift + F7 open Thesaurus in Microsoft Word

❒የ F8 ጥቅሞች
◕ In Excel, enables extend mode for arrow keys
◕ Enables safe mode in Windows

❒የ F9 ጥቅሞች
► Ctrl + F9 inserts empty fields into Word
► Updates fields in Word

❒የ F10 ጥቅሞች
◕ Opens menu bar
◕ Ctrl + F10 maximizes window in Word
◕ Shift + F10 does the same thing as a right click

❒የ F11 ጥቅሞች
► Exits and enter full screen mode in browsers
► Shift + F11 adds a new spreadsheet in Excel

❒የ F12 ጥቅሞች
◕ Opens Save As in Word
◕ Shift + F12 saves Word document
◕ Ctrl + F12 opens Word document

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና ወሲብ***************************የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በብዛት ከወሲብ ጋር ተከትሎ የሚመጣ ነገር ነው። ሆኖም የሚገባውን ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረ...
28/02/2020

የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን እና ወሲብ
***************************
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን በብዛት ከወሲብ ጋር ተከትሎ የሚመጣ ነገር ነው። ሆኖም የሚገባውን ቅድመ ጥንቃቄ ከተደረገ በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል።
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ምልክቶች፦
1. ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት
2. በሚሸኑበት ጊዜ የማቃጠል ስሜት
3. የደፈረሰ ወይም ቀላ ያለ ሽንት
4. ትኩሳት፣ ማንቀጥቀጥ፣ ብርድ ብርድ ማለት የመሳሰሉት ይገኙበታል
እንዴት የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ከወሲብ በሃላ በቀላሉ ይይዛቸዋል?
 አዲስ የወሲብ ጏደኛ
 የቤተሰብ ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን
 የስኳር በሽታ
እንዴት ከወሲብ ጋር የተያያዘ የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን መከላከል እንችላለን?
 ከወሲብ በፊት እና በሃላ መሽናት
 ከወሲብ በፊት እና በሃላ ብልት አካባቢን ማጽዳት
 ውሃ በብዛት መጠጣት
 ብልት አካባቢ ሽቶ እንዲሁም የተለያዩ ቅባቶችን አለመጠቀም

ምህረት አላባ የሆነው የኩላሊት በሽታ ምንድነው?ዛሬ ስለ ኩላሊት ቀለል ያለ በቤታችን ተጠቅመን ከ ኩላሊት ኢንፌክሽን ፥ከኩላሊት ጠጠር በሽታ እንዴት መዳን እንደምንችል አባራላችኃለሁ።ኩላሊት ...
14/02/2020

ምህረት አላባ የሆነው የኩላሊት በሽታ ምንድነው?

ዛሬ ስለ ኩላሊት ቀለል ያለ በቤታችን ተጠቅመን ከ ኩላሊት ኢንፌክሽን ፥ከኩላሊት ጠጠር በሽታ እንዴት መዳን እንደምንችል አባራላችኃለሁ።

ኩላሊት መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ከሰውነት ለማስወገድ ትርፍ ውሃን ከደም ውስጥ ለመቀነስና የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳሉ፡፡ ሰዎች ሁለት ኩላሊቶች ያሏቸው ሲሆን በግ ራና በቀኝ ከጎድን አጥንት መጨረሻ አከባቢ የሚገኙ ሲሆን በተለያየ መንገድ ጉዳት በደረሰባቸው ግዜ የኩላሊት በሽታ ይከሰትና የዘወትር ተግባራቸውን ስለሚያውክባቸው የበሽታው መገለጫ የሆኑ ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡

ይህም እንደ ጉዳቱ መጠንና ምክንያት ቀላልና በፍጥነት የሚያገግሙ ወይም የኩላሊቱን ተግባር በፍጥነት የሚያሰናክሉ አልያም በግዜ ሂደት እያዳከሙት ከጥቅም ውጭ ሊያደርጉ( ኪድኒ ፌይለር ሚያመጡ) ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የኩላሊት ተግባራት ምንድናቸው?

የውሀና ንጥረ ነገሮችን ሚዛና( እንደ ጨው፣ፖታሽየምና ፎስፈረስ ያሉትን) ይጠብቃልከምግብ መፈጨት፣ከአካል እንቅስቃሴ ወይም ለኬሚካሎች ከተጋለጡ በኋላ ሚኖሩትን ቆሻሻዎች ከደም ውስጥ ያስወግዳልየደም ግፊትን ለመቆጣጠር የሚያገለግለውን ሬኒን የተባለ ንጥረ ነገር ያመርታልሰውነት የቀይ ደም ሴልን እንዲያመርት የሚያደርገውን ኢሪትሮፓኤቲን የተባለ ኬሚካል ያመርታልሰውነት ሊጠቀመው የሚችለውን የቫይታሚን ዲ ( vit. D) አይነት ያመርታል።

የኩላሊት በሽታዎች ድንገተኛ እና የቆየ(ከራሚ) በሚል በሁለት ልንከፍላቸው እንችላለን፡፡

#ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት

ድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ( መድከም) የሚያጋጥመው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲኖሩ ነው፡

ወደ ኩላሊት የሚደርሰው ደም መጠን ከበቂ በላይ እና ከበቂ በታች ሲሆን ኩላሊት በቀጥታ ጉዳት ሲያገጥመው እና ሽንት ወደ ኩላሊት በሚመላለስበት ግዜ ሲሆን እነኝህ የሚከሰቱት ደግሞ በሚከተሉት ሁኔታዎች ነው፡፡

ደም መፍሰስ የሚያስከትል አካለዊ ጉዳት ሲገጥም ከፍተኛ የፈሳሽ እጥረት ሲኖር ወይም የበዛ የጡንቻ ስብርባሪ በመኖሩ ምክንያት ከፍተኛ ፕሮቲን ወደ ደም ውስጥ በሚገባ ግዜ በከፍተኛ ኢንፌክሽን ወይም የደም መመረዝ ምክንያት ከፍተኛ የግፊት መቀነስና እራስን በሚስቱ ግዜ ፕሮቴስት የሚባለው እጢ( በወንዶች) በማበጡ ምክንያት የሽንት ፍሰት ሲዘጋ አንዳንድ ለኩላሊት መርዛማ የሆኑ መድሃኒቶችን ሲወስዱ ወይም ለኬሚካል ሲጋለጡ እንዲሁም ከእርግዝና ጋር የተያያዙ ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የደም ግፊት የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ነው፡፡

#የቆየ የኩላሊት ጉዳት

ኩላሊትዎ ከ3 ወር ለረዘመ ግዜ ተግባሩን በትክክል መወጣት በማይችልበት ግዜ ከራሚ የኩላሊት ጉዳት ( መዳከም) አጋጥሞታል ይባላል፡፡ ምንም እንኳን ለህክምና ወይም ለማከም የሚቀለው በግዜ ሲደረስበት ቢሆንም ምልክቶቹ ግን በአብዛኛው በግዜ አይታዩም ከራሚ የኩላሊት ጉዳትን ከሚያስከትሉት ውስጥ የስኳር በሽታና የደም ግፊት ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡

የስኳር በሽታ በቁጥጥር ስር ካልዋለ ከፍተኛው የስኳር መጠንና አላስፈላጊ የሆኑ ቆሻሻዎች በኩላሊት ላይ ጫና በመፍጠር ጉዳት ያደርሳሉ፡፡የደም ግፊት በበኩሉ በትንንሾቹ የኩላሊት የደም ስሮች ላይ የሚያሳድረው ውጥረትና መሸርሸር ኩላሊቱን ስራወን በአግባቡ እንዳይሰራ ያደርገዋልወይም ይጎዳዋል ከነዚህ በተጨማሪ ሌሎች እንደ ምክንያት ከሚቀመጡት ውስጥ ከሰውነት መከላከያ ህዋሳት በኩላሊት ላይ ጉዳት እንዲደርስ የሚያደርጉ የተለያዩ በሽታዎችለረጅም ግዜ የቆዩ የቫይረስ ኢንፌክሽኖች(አንደ ኤች አይ ቪ/ ኤድስ)የተለያዩ የኩላሊት ውስጥ ትቦ ኢንፌክሽኖችና በኩላሊቱ አካላዊ ይዘት ላይ የሚከሰቱ የተፈጥሮ መዛባቶችና የመሳሰሉት ከራሚ የኩላሊት ጉዳት ወይም መድከምን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡

#የድንገተኛ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች

የሽንት ፍሰት መዘጋት ወይም በጣም መቀነስ የአይንና የእግር እብጠት ትኩሳትና ጠቅላላ የአካል ህመም ስሜቶች ይጠቀሳሉ፡፡

#የቆየ የኩላሊት ጉዳት ምልክቶች

ይህ ጉዳት መጀመሪያ አከባቢ ምልክቶች ሊያሳይ ባለመቻሉ አስቸጋሪ የሚያደርገው ሲሆን ጉዳቱ እየቆየ ሲሄድ የሚታዩት ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ፡፡

የማቅለሽለሽና ተደጋጋሚ ትውከት ሽንት የመሽናት ድግግሞሽ በከፍተኛ መጨመር እና አረፋማ ሽንትየአይን እና የእግር እብጠትከፍተኛ የድካም ስሜትምክንያት የሌለው ከፍተኛ የክብደት መቀነስየተለየ የቆዳ መድረቅ እና መሳሳትየምግብ ፍላጎት መቀነስየምግብ ጣዕም ማጣት የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

እነኚህን ምልክቶች ባዩ ግዜ ( ምንም እንኳን በሌላ ምክንያትም ሊከሰቱ ቢችሉም) ሃኪምዎትን በፍጥነት ማማከር ተገቢ ነው፡፡ በተለይ የስኳር እና የደም ግፊት በሽታዎች ካለብዎ እንዲሁም የኩላሊት በሽታ በቤተሰብ ያለ ከሆነ ፈጣን የህክምና እርዳታ ያስፈልግዎታል፡፡

ፈጣሪ በክህሎቱ እጅግ በረቀቀ እና በማይዛነፍ ፈጣሪነቱ የፈጠራት ኩላሊትን ስለ ኩላሊት፦

ሊቃውንት ሳይንሳዊ እውቀታቸውን በመንተራስ ከፈጣሪ በተሰጣቸው ፀጋ ከላይ እንዳስቀመጥኩት በሚገባን ቋንቋ እንዲህ ብለው ከርትሰው ተገኝተዋል።

እኔም እንደዚህ እላለሁ አንድ የዕጽ ኃይል እጅግ የተለያዩ እንዲሁም የተወሳሰቡ ችግሮችን ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጣት ፀጋ የማዳን ብቃት አላት ብየ አምናለሁ። እውነትም ነው።

#የተወሳሰበ የኩላሊት በሽታ መፍትሔ፦

#ዕሬት ፈሳሽ(ጄል) # Aloe vera

#ዕሬት በዓለማችን ውስጥ ከ 400 በላይ የዝርያ ዓይነት እንዳለው ይታወቃል።

#ዕሬት ለሰውነታችን ጠቃሚ በሆኑ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ተክል ነው።
ዕሬት ከ200 በላይ አክቲቭ ኮምፓዎንዶች እንዳሉት በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ብዙ ቫይታሚኖች፣ ሚኒራሎች፣ አሚኖ አሲዶችና ሌሎችንም ይዟል፡፡ ቫይታሚን A B C K የተባሉት አሉት፡፡ ካልሲየምና ዚንክም እሬት ውስጥ ይገኛሉ፡

#ዕሬት በብዙ ዓለማት የተለያዩ ከባህላዊ ህክምና ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ህክምና ድረስ በሰፊው አገልግሎት ሲውል ይታያል።

እውነተኛው ዕሬት ለቆዳ ችግር፣ለጸጉር መበጣጠስ ፣ለካንሰር፤ለድክመተ ወሲብ ፣ለካንሰር፣ለሆድ እቃ ችግር፤ለኩላሊት ችግር፣ ለኪንታሮት ችግር፣ለላብ ችግር፣ለፈንገስ፤ትኩሳትንም ያቀዝቅዛል፣ የጣፊያና የጉበት ችግሮች፣ የጉልበት ችግሮች....ወዘተ ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል።

ሁሉንም የዕሬት ዓይነቶችን ወደ ሆድ ውስጥ መግባት የለባቸውም ምክንያቱም መርዛማ የሆነ የዕሬት ዝርያም ስላሉ።

በተለይ ከኢትዮጵያ ውጭ ያላችሁ ቤተሰቦቻችን የተገኘውን የዕሬት ዓይነት መጠቀም እንደሌላችሁ አሳስባለሁኝ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ዕሬት ከስር በምስሉ እንደምታዩት ወፍራም ክንፍ ወይም ግንድ ያለው አረንጓዴ ቀለም ቢጫ እና ቀይ አበባ ያለው ዕሬት ለመጠቀም ሞክሩ።
#አጠቃቀም፦

#የእውነተኛው ዕሬት የውስጡ ፈሳሽ ወይም ጄል 4 የሾርባ ማንኪያ
#ግማሽ ሌትር የላም ወተት
#አንድ የሾርባ ማንኪያ ንፁህ ቀይ ወይም ነጭ ማር

እነዚህን በአንድ በማቀላቀል ማታ ማታ አንድ አንድ ቀን በመዝለል ማታ ማታ በመኝታ ሰዓት አፍልተው አጥልለው ቀዝቀዝ አድርገው መጠጣት።
የመምረር ጣዕም አይኖረውም.
ይህንን ድርጊት በተከታታይ ለ 3 ሳምንታት ያክል ይጠቀሙ እና ውጤቱን ለማየት ይሞክሩ።

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

Lasta Digital Ads Inc.

ኪንታሮት!!!-----ኪንታሮት የምንለው የቆዳ ችግር ሂዩማን ፓፒሎማ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን ተላላፊና የትኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ኪንታሮ...
12/02/2020

ኪንታሮት!!!
-----

ኪንታሮት የምንለው የቆዳ ችግር ሂዩማን ፓፒሎማ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት ሲሆን ተላላፊና የትኛውም የሰውነት ክፍል ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ኪንታሮት በብዛት እጅ፣ እግር እንዲሁም መገጣጠሚያ ቦታ ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

መተላለፊያ መንገዶች
-------
• ኪንታሮቱን ማከክ
• ጣት መጥባት
• ጥፍር መብላት (ኪንታሮት የወጣበት ካለ)

መፍትሄ
-----
• ነጭ ሽንኩርት መጠቀም
• አንቲባዮቲኮችን መጠቀም ኢንፌክሽን
• የተለያዩ የኪንታሮት ክሬሞች

መከላከያ መንገዶች
------
• ኪንታሮት የተያዘን ሰው አለመንካት
• ፎጣ እና ልብሶችን በጋራ አለመጠቀም
• ኪንታሮትን አለማከክ
• መዋኛ ገንዳዎች አካባቢ በባዶ እግር አለመሆን
• እጅን በተቻለ አቅም በደረቁ ለመያዝ መሞከር ይጠቀሳሉ፡፡

Lasta Digital Ads Inc.

ከሞት የታደገው ጎሽ ከቤት አልወጣም ብሎት የተቸገረው ኢትዮጵያዊ--------------------------------------------------------------------ወጣት ጋሻው ደመላሽ...
12/02/2020

ከሞት የታደገው ጎሽ ከቤት አልወጣም ብሎት የተቸገረው ኢትዮጵያዊ

--------------------------------------------------------------------

ወጣት ጋሻው ደመላሽ ነዋሪነቱ ኢሉ አባቦራ ዞን፤ ዳሪሙ ወረዳ አቡነ ጋሊ በምትሰኝ ቀበሌ ውስጥ ነው።

በግብርና ሥራ የሚተዳደረው ጋሻው፤ ከአራት ዓመታት በፊት በሚኖርበት አካባቢ በጭቃ ተይዞ መንቀሳቀስ ያቃተው የጎሽ ግልገል ባጋጣሚ ይመለከታል።

ጥሎት ቢያልፍ የግልገሉ እጣ ፈንታ ሞት መሆኑን በመረዳቱ፤ የጎሹን ግልገል ጥሎ ማለፍ አልቻለም፤ ጎሹን ከጭቃ ለማስለቀቅ ግብግብ ያዘ።

ከዚያም ጎሹን ከጭቃ አስለቅቆ ወደ መኖሪያው ይዞት ይሄዳል።

"ወደ ቤት ይዤው ሄድኩ። አባቴን አስፈቅጄ አንገቱ ላይ ገመድ አስሬ የላም ወተት እያጠጣሁት ማሳደግ ጀምርኩ" ይላል ጋሻው።

የጎሹን ግልገል በአካባቢው የሚያገኛቸውን የተለያዩ ነገሮች እየመገበ እንዳሳደገ ጋሻው ይናገራል። "... እንጀራ፣ አሞሌ ጨው፣ የአረቄ አተላ፣ ማር ሁሉ አበላው ነበር። ከዛ በፍጥነት አደገ ከዛ ተላመደ" ይላል።

በአጋጣሚ ህይወቱን አትርፎ ያሳደገው የጎሸ ግልገል ግን በትላልቅ ቀንዶቹ የሰፈሩን ሰው እና የቤት እንስሳት ለማሸበር የወሰደበት ጊዜ አጭር ነበር።

"አሁን ስላስቸገረ ታስሮ ነው የሚውለው። ሰው እና ከብቶችን መውጋት ሲጀምር ነው ማሰር የጀመርኩት። ከዛ በፊት ከከብቶች ጋር ነበር ተሰማርቶ የሚውለው። ከእኔ ውጪ ሁሉንም ሰው እና ከብቶች እየወጋ ሲያስቸግር ለመጣል ወሰንኩ። እርቆ ወደሚገኝ ጫካ ወስጄ ብተወውም ተመልሶ መጣ። እንደገና ብወስደውም ስለተላመደ ተመልሶ መጣ" በማለት ጋሻው ጎሹን ወደ ጫካ ወስዶ ለመጣል ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካ ያስረዳል።

አመጸኛውን ጎሸ ጠምጄ ለማረስ ሞክሬ ነበር የሚለው ጋሻው፤ የአከባቢው ኃላፊዎች የዱር እንስሳ በመጠቀም ማረስ እንደማይችል በመግለጽ ክልክላ እንዳደረጉበት ይናገራል።

"በጣም ነው የሚያርሰው፤ የትኛውም በሬ እንደ ጎሹ አያርስም። ከቀበሌ እየመጡ የዱር እንስሳ አጥምደህ ማረስ አትችልም ሲሉኝ ነው የተውኩት።"

ጎሹን መጠቀምም ሆነ ከቤቱ ማስወጣት ያልቻለው ጋሻው፤ ለዱር እንስሳው ቀለብ መስፈር ቢበዛበት፤ ከገባበት ጣጣ መንግሥት እንዲገላግለው በአካባቢ ይመለከታቸዋል ላላቸው የመንግሥት መስሪያ ቤት ኃላፊዎች አቤት ቢልም መፍትሄ አለማግኘቱን ይናገራል።

"በዞን እና በወረዳ ላሉት አሳውቂያለሁ። ከብት እርባታ ለሚባሉትም ነግሬያቸዋለሁ። ይሄው ስንት ግዜ ደብዳቤ ይዤ፣ ስንት ቦታ ተመላለስኩ፤ መፍትሄ የሚሰጠኝ ግን ላገኝ አልቻልኩም። እየመጡ ፎቶ አንስተው ይሄዳሉ እንጂ ምንም የረዱኝ ነገር የለም" ይላል።

የኦሮሚያ ክልል የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ጨመረ ዘውዴ፤ የዱር እንስሳትን ማልመድም ሆነ በመኖሪያ ቤት ውስጥ አስሮ ማስቀመጥ በህግ የተከለከለ ተግባር ነው ይላሉ።

አቶ ጨመረ እንደ ጎሽ ያሉ የምግብ ፍጆታቸው ከፍተኛ እና አደገኛ የዱር እንስሳትን የማላመድ ተግባር ከዚህ ቀደም ገጥሟቸው እንደማያውቅ ይናገራሉ።

"በቅድሚያ እንዲህ አይነት ነገር ገጥሞን አያውቀውም። ይሄን ጎሽ እንዴት ማላመድ እንደጀመረ አላወቅንም። ግን ይዘው ካቆዩት በኋላ አድጎ የዱር እንስሳነት ባህሪው ሲመጣ ነው ለእኛ ያሳወቁን። ይህን መሰል ተግባርም የተከለከለ ስለመሆኑ በሃገሪቱ ህግ ላይ ሰፍሯል"

አቶ ጨመረ ለዚህ ጉዳይ መፍትሄ ያሉትን ሁለት ሃሳብ ያስቀምጣሉ፤ ጎሹን ወደ ጫካ ለመመለስ ጥናት ማካሄድ አልያም ደግሞ ጎሹ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነ ከሆነ እርምጃ መውሰድ።

"እንዲህ አይነት የዱር እንስሳ ወደ ጊዜያዊ ማቆያ መውሰድ አይችልም። ከሰዎች ጋር የተላመደን የዱር እንስሳ ወደ ጫካ ይመለስ ከተባለ በጫካ የመኖር ባህሪውን አጥቷል። ስለዚህ ጎሹ ስለሚገኝበት ሁኔታ ማጥናት ግድ ነው። አለበለዚያ ግን ጎሹ በሰዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት የደቀነ ከሆነ እርምጃ መውሰድ የመጨረሻው አማራጭ ይሆናል" ይላሉ።

- BBCAmharic



ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ካርድ በፍጥነት እየጨረሰብዎ ተቸግረዋል ?--------------------------------------------------------- ኢንተርኔት አጠቃቀም ዝርዝር ምክሮች እ...
12/02/2020

ኢንተርኔት ሲጠቀሙ ካርድ በፍጥነት እየጨረሰብዎ ተቸግረዋል ?

---------------------------------------------------------

ኢንተርኔት አጠቃቀም ዝርዝር ምክሮች እነሆ፡፡

1. የዳታ አጠቃቀምዎን ይገድቡ / ይወስኑ፡፡

Data usage limit-- ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት ሪስትሪክት ዳታን ይክፈቱት

2. አዉቶማቲክ አፕዴትን ይዝጉ

Turn off automatic Updater

አንዳንድ አፕሊኬሽኖች ወይም ቀፎዎች ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ ራሳቸዉን አፕዴት ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ስለዚህ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት automatic Updater Turn off ያድርጉት፡፡

3. Turn off mobile data when using Wi-Fi

በዋይ ፋይ እየተጠቀማችሁ ከሆነ የሞባይል ዳታችሁን ኦፍ አድርጉት

4. ዳታሮሚንግንይዝጉት

Turn off data roaming when overseas

5. የማትጠቀሙባቸዉንአፕሊኬሽኖችአስወግዱ ፡፡ Remove unused apps from your phone

6.Turn off push notifications & background data for apps

አንዳንድ አፕሊኬሽኖች ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ ስለራሳቸዉ መረጃ የሚሰጡ

ኖቲፊኬሽኖችን ይልካሉ፡፡ ስለዚህ እነዚህን አፕሊኬሽኖች (የሚመጡ ኖቲፊኬሽኖችን ጫን ብሎ በመያዝ Turn off ያድርጉት፡፡

7. Delete unsent emails; they can be a data drain ለመላክ የተዘጋጁ (ድራፍት) የኢሜይል መረጃዎቻችሁን አስወግዱ፡፡ ወይም ላኩ፡፡ ያለበለዚያ ኢንተርኔት ኮኔክሽን በተከፈተ ቁጥር እንቅስቃሴ ስሚያደርጉ ሳንቲም ይጨርሳሉ፡፡

8. Video, music or game streaming can use data fast ---ኢንተርኔት ኮኔክሽን ላይ ሆናችሁ ሙዚቃ፣ ቪዲዮችን ጌሞችን ኦንላየን የምትከታተሉ ከሆነ ወይም ዳወንሎድ ማድረግ ሳንቲም ይጨርሳሉ፡፡

9.Turn off location services

የጂፒኤስ እና መሰል አገልግሎቶችን ይዝጉ፡፡ ያላችሁበትን አካባቢ መረጃ ፣የአየር ንብረት እና ሌሎች ሁኔታዎችን ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሲከፈትላቸዉ ወዲያዉ መረጃ መስጠት ይጀምራሉ፡፡ስለዚህ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት Turn off ያድርጉት፡፡

10. Email settings

የኢሜይል ሴቲንግ ማስተካከል፤ አዳዲስ የሚመጡ ኤሜሎችን በየስንት ደቂቃ ኢንተርቫል እንደሚያሳውቃችሁ አስተካክሉለት ፡፡ ሲንክሮናይዝ የሚደረግበት የጊዜ ምጣኔ ማለት ነዉ፡፡ ኤሜይል ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት synchronaizing schedule interval በየስንት ደቂቃ ኢንተርቫል እንደሚያሳውቃችሁ አስተካክሉለት ፡፡

11. Hotspots and tethering

እናንተ ለራሳችሁ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ከፍታችሁ በምትጠቀሙ ሰአት ከአቅራቢችሁ ያለሰዉ በእናንተ ኢንተርኔት ኮኔክሽን ሊጠቀም ይችላል፡፡ ወይም በኬብል ከላፕቶፕ ጋር ተተገናኝቶ ከሆነ ላፕቶፑ ራሱን አፕዴ ትማድረግ ይጀምራል፡ ስለዚህ ሴቲንግ ዉስጥ በመግባት Turn off ያድርጉት፡፡

12. Switch mobile data off

ምናልባት ሳናዉቀዉ የሞባይል ኢንተርኔት ኮኔክሽናችንን ኦን አድርገነዉ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ተች ስክሪኖችን በኪሳችን ስንይዝ ተነካክተዉ ሊከፈቱ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ማየት እና መዝጋት ያስፈልጋል፡፡

Lasta Digital Ads Inc.

ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…?በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?✴️ የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያ...
11/02/2020

ስማርት ስልኮቻችን ሀይል እንዴት መሙላት አለብን…?

በርካታ ተግባራትን የሚያከናውኑበት ስማርት ስልክዎ ባትሪ በፍጥነት እያለቀ ተችገረዋል?

✴️ የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅመው የስልክዎን ባትሪ ቢያንስ ሙሉ ቀን እንዲያስጠቅምዎትስ ጥረት አድርገዋል?

✴️በቴክኖሎጂው መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች የስልካችን ባትሪ በፍጥነት እያለቀ የምንቸገረው በሶስት ምክንያቶች መሆኑን ይገልፃሉ።

✴️የመጀመሪያው በስማርት ስልኮቻችን የጫንናቸው መተግበሪያዎች መብዛት እና እያወቅንም ይሁን ሳናውቅ ተከፍተው ባትሪ መብላታቸው
ነው።
✴️የስማርት ስልካችን ላይ ሙጭጭ ብለን አልላቀቅ ማለትም ሌላኛው የባትሪ እድሜን የሚያሳጥር ልማድ ነው።

✴️ሶስተኛው እና ዋነኛው የባትሪ ህይወትን የሚያሳጥረው ተብሎ በባለሙያዎች የተጠቀሰው ደግሞ የሀይል አሞላላችን (ቻርጅ አደራረጋችን መሆኑ ተገልጿል።

✴️ብዙዎቻችን የስማርት ስልካችን ባትሪ ሙሉ በሙሉ ሲያልቅ ቻርጅ ማድረግ እንዳለብን እናምናለን።

✴️በአንዳንዶቻችን ዘንድ ደግሞ ቻርጅ እንደሰካን ሞባይላችንን መጠቀም የባትሪውን አገልግሎት ያራዝማል የሚል አመለካከት አለ።

✴️ይሁን እንጂ የሞባይል ባትሪ እንደ ሰው ልጅ ሁሉ “መጨናነቅን” አይወድም ነው የሚለው ባትሪ ዩኒቨርሲቲ የተሰኘ ኩባንያ።

✴️ስልካችንን ቻርጅ እያደረግን መጠቀም የባትሪውን እድሜ ያሳጥራልም ይላል።

✴️ስለ ስማርት ስልክዎ ባትሪ ከመጨነቅ የሚገላግሉ ናቸው ያላቸውን ነጥቦችም ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በታች አስቀምጧል።

✴️የስልክዎ ባትሪ ሙሉ ቻርጅ ከተደረገ በኋላ ሞባይሉን ከቻርጀሩ ይንቀሉት፡

✴️ኩባንያው እንደሚለው የስማርት ስልካችን ባትሪ ከአቅሙ በላይ ቻርጅ ሲደረግ የረጅም ጊዜ አገልግሎቱ እየወረደ ይመጣል።

✴️ስልካችን 100 ፐርሰንት ቻርጅ ከሆነ በኋላ እንደተሰካ መተው ለከፍተኛ መጨናነቅ በመዳረግ የባትሪውን ሀይል የመያዝ አቅም ይቀንሰዋል።

✴️ (እስከ 100 ፐርሰንት ቻርግ ማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ ካልሆነ አስፈላጊ አይደለም፡

ከአድካሚ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በኋላ ጡንቻዎችን ማፍታታት እንደሚገባ ሁሉ ስልካችንም ሙሉ በሙሉ በሀይል ከተሞላ በኋላ ከቻርጀሩ መንቀል ይገባል።

✴️ባትሪውን ከሙቀት ይጠብቁት
የስማርት ስልክ ባትሪዎች በቀላሉ በሙቀት ይግላሉ።

✴️ለዚህም ነው አፕል ራሱ የአይፎን ስልኮችን ቻርጅ ስታደርጉ መሸፈኛ (ኬዞቹን ብታወጡት በማለት የሚመክረው።

✴️ስለሆነም ስልካችን ቻርጅ ስናደርግ መሞቁን ካስተዋልን ሽፋኑን ማውጣት ይኖርብናል።

✴️የባትሪያችን ጤና ለመጠበቅ ስማርት ስልካችን ቻርጅ የምናደርግበት አካባቢ የፀሀይ ሙቀት የሌለበት ቢሆንም ጥሩ ነው።

✴️100 ፐርሰንት ላይ እስከሚደርስ መጠበቅ የለብንም፡

✴️እንደ ባትሪ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ ከሆነ ከፍተኛ ቮልቴጅ ባትሪውን ስለሚያጨናንቀው ባትሪን መቶ በመቶ ሀይል መሙላት አያስፈልግም።

✴️ስማርት ስልካችን ቀኑን ሙሉ ቻርጅ ማድረግም በባትሪው እድሜ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ብሏል።

ቻርጅ ለማድረግ የባትሪውን ማለቅ አይጠብቁ።

✴️ ስልካችን ቻርጅ ለማድረግ ባትሪው ተሟጦ እስኪያልቅ መጠበቅ የለብንም።

✴️ ባገኘነው አጋጣሚ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን ሀይል ይዞ የመቆየት አቅም ያሳድገዋል።

✴️እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ስልቶች የስማርት ስልካችን ባትሪ ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግል እና ቀኑን ሙሉ ከስጋት ነፃ እንድንሆን ይረዳናል ።

እባክዎን ይህን ጠቃሚ መረጃ ለወገኖ እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩን!

ምስጋናችን ከልብ ነው!

Lasta Digital Ads Inc.

የነርቭ ጉዳት ምልክቶች*************************************ሰላም ጤና ይስጥልን!ዛሬ ነርቭ ሲጎዳ ሊኖሩ ስለሚችሉ ምልክቶች እንመለከታለን ተከታታሉን፡-👉👉 መደንዘዝስሜታዊ...
11/02/2020

የነርቭ ጉዳት ምልክቶች
*************************************

ሰላም ጤና ይስጥልን!
ዛሬ ነርቭ ሲጎዳ ሊኖሩ ስለሚችሉ ምልክቶች እንመለከታለን ተከታታሉን፡-

👉👉 መደንዘዝ

ስሜታዊ ነርቮች/sensory nerves/መጎዳታቸውን የምናውቅበት የመጀመሪያው ምልክት የመደንዘዝ እና የመውረር ስሜት በእጅ፣ በጣት፣ በእግር፣ እና በእግር ጣቶች ላይ ሲፈጠር ነው። ስሜታዊ ነርቮች ስራቸው የስሜት መልእክት መላክ ሲሆን ጉዳት ሲያጋጥማቸው ቆይቶ ወደ መደንዘዝ የሚቀየር የመውረር ስሜት ይሰማናል። በጊዜው ተገቢ ህክምና ካላገኘ ይህ ስሜት ወደ ሌሎች የሰውነት አካሎች ሊዛመት ይችላል። ህመሙ ከጊዜ ጋር እየጨመረ የቀን ከቀን ኑሮአችንን ያስተጓጉላል።

እጅ እና እግር ላይ ለሚፈጠር የመደንዘዝ ስሜት ሌሎች መንስኤዎች እግር እና እጅ ላይ የተፈጠረ ከፍተኛ ጫና፣ ለብርድ መጋለጥ፣ እንቅስቃሴ የሌለበት የአኗኗር ዘይቤ እና የቫይታሚን ቢ12 እና ማግኒዚየም እጥረት ናቸው።

👉👉 ህመም

ሌላ የነርቭ ህመም ምልክት የሚሰነጥቅ ወይም የሚያቃጥል የህመም ስሜት ነው። የዚህ አይነት ስሜት እጅ እና እግር ላይ የሚፈጠር ሲሆን ከሌላ የህመም ስሜት ይለያል።

ህመሙ የሚፈጠረው ስሜታዊ ነርቮች ላይ በተፈጠረ ጉዳት ነው። ስሜት በአግባቡ ከአእምሮ ወደ ቆዳ መተላለፍ ካልቻለ የተጎዳው ቦታ ላይ ከፍተኛ ህመም ሊሰማን ይችላል። የህመሙ ቦታ በተጎዳው ክልል ዙሪያ ብቻ ወይንም ሰፊ የሰውነት ክልል ላይ ሊፈጠር ይችላል። ህመሙ ብዙ ጊዜ በምሽት ይባባሳል።

ከነርቭ ጉዳት ውጪ የስኳር በሽታ፣ የቫይታሚን ቢ12 እጥረት ወይም የጀርባ አጥንት ሰረሰር ላይ የተፈጠረ ጉዳት ለከባድ ህመም ያጋልጠናል።

👉👉 የጡንቻ ድካም

ጡንቻ እንዲንቀሳቀስ የሚያደርገውን መልእክት የሚያስተላልፉ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ ድካም ይፈጥራል። አልፎም ጡንቻን የመቆጣጠር ችሎታ ሊያሳጣ ይችላል። ለጡንቻችን የሚላከው መልእክት በአግባቡ ካልተላለፈ መራመድ እንቸገራለን። በእጃችን እቃዎች ለማንሳት እና ጭብጥ አድርጎ መያዝ ይከብደናል።

በነርቭ ጉዳት ምክንያት ጡንቻ ጥቅም ላይ የሚውልበት ጊዜ ሲቀንስ እራሱ እየደከመ ይመጣል። ጡንቻ መዳከም ከነርቭ ጉዳት ውጪ እንደ ፓርኪንሰን በሽታ፣ የዲስክ መንሸራተት፣ ስትሮክ የመሳሰሉ ህመሞች መንስኤ ይሆናሉ።

👉👉 የጡንቻ መሸማቀቅ

የእንቅስቅሴ ነርቮች ላይ የደረሰ ጉዳት የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ ሊያመጣ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ እና መሳሳብ በራሱ የተጎዱት ነርቮች ላይ በሚፈጥረው እንቅስቃሴ ጉዳቱን ሊያባብስ ይችላል። የጡንቻ መሸማቀቅ የሚፈጠረው የእንቅስቃሴ ነርቮች በብዛት ሲሰሩ ነው። የመሸማቀቅ ስሜት ክብደቱ ቀላል፣ መሃከለኛም ወይንም በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል።

👉👉 የላብ ችግር

የሰውነት አካልን የሚረዱ ነርቮች ሲጎዱ አውቶኖሚክ ኒውሮፓቲ የሚባል ህመም ሊያስከትል ይችላል። አውቶኖሚክ ነርቮች ሲጎዱ የላብ ችግር ሊፈጥር ይችላል። አንዳንድ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ላብ ሲፈጠር ሌሎች ላይ ደግሞ የላብ መቀነስ ይታያል። ላብ በአግባቡ ካልመነጨ ሰውነታችን ሙቀቱን በአግባቡ መቆጣጠር አይችልም። በከፍተኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴ ወቅት ችግሩ ይገዝፋል።

👉👉 ሽንት ቤት መመላለስ

የሽንት ፊኛ ሽንትን በደንብ እንዲይዝ ብዙ ነርቮች አብረው መስራት አለባቸው።
የነርቭ ጉዳት ሲፈጠር የሽንት ፊኛ ሽንትን ቶሎ ቶሎ ለማስወገድ ይሞክራል። የነርቭ ጉዳት የሽንት ፊኛ ጡንቻዎች የሚያደርጉትን መኮማተር እና መላላት በተገቢው መልኩ እንዳያደርጉ ያስተጓጉላል። የሽንት ፊኛ ችግር ሌላ መንስኤ ሊኖረው ይችላል። ልጅ በወለዱ እናቶች እና የስኳር በሽታ ታካሚዎች ላይ የሚፈጠር ችግር ነው።

👉👉 ከባድ ራስ-ምታት

ኤሌክትሪክ ንዝረት የሚመስል አጭር ጊዜ የሚቆይ ከባድ ራስ-ምታት የነርቭ ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል። ህመሙ የኦክሲፒታል ኒውራልጂያ በሽታ ምልክት ሊሆን ይችላል። ኦክሲፒታል ኒውራልጂያ አንገት ላይ ያለ የነርቭ መቆንጠጥ በሽታ ነው። ህመሙ የላይኛው አንገት ክፍል ወይም ጭንቅላት ጀርባ ላይ ይፈጠራል።

👉👉 ሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር

የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር ወይም መንገዳገድ ሌላ የነርቭ ጉዳት ምልክት ነው። ወድቀው ሊጎዱ ስለሚችሉ ይህን ምልክት ችላ ማለት የለብንም።

የነርቭ ጉዳት አእምሮ የሰውነትን እንቅስቃሴ በአግባቡ እንዳይቆጣጠር ያደርጋል። ይህ ሁኔታ ወድቀው እንዲጎዱ ሊያደርግ ይችላል። የሰውነት ሚዛን መጠበቅ መቸገር የፓርኪንሰን ህመም ምልክት ሊሆን ይችላል።
መልካም ጤንነት!!
ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ ላይክ፤ሼር ያድርጉ!!

Lasta Digital Ads Inc.

Address

Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akotet Graphics Design and Digital Marketing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share