Daily News Ethiopian

Daily News Ethiopian ethiopia

ፈረንሳይ በአፍሪካ የበቀል ፖለቲካ እድል እየፈለገች ነው ስትል ሩሲያ ከሰሰች።የሩሲያ የውጪ ደህንነት አገልግሎት ቢሮ አገኘሁት ባለው መረጃ ፈረንሳይ በአፍሪካ የዳግም ግኝ ግዛት መፈንቅለ መን...
04/02/2026

ፈረንሳይ በአፍሪካ የበቀል ፖለቲካ እድል እየፈለገች ነው ስትል ሩሲያ ከሰሰች።

የሩሲያ የውጪ ደህንነት አገልግሎት ቢሮ አገኘሁት ባለው መረጃ ፈረንሳይ በአፍሪካ የዳግም ግኝ ግዛት መፈንቅለ መንግስቶችን ለመፈፀምና የፖለቲካ በቀሎችን ለመፈፀም እየተዘጋጀች ነው ብሏል።

ቢሮው በአፍሪካ የህዝብን ጥቅም ያስቀደሙ ጀግኖች በመኖራቸውና የፈረንሳይ ተላላኪ ባለመሆናቸው በአህጉሪቱ ፈረንሳይ ትልቅ ኪሳራ ገጥሟታል በማለት አሜሪካ በማዱሮ ላይ በሰራችው ኦፕሬሽን በመነሳሳት ማክሮን ለልዩ ኃይሉ በአፍሪካ የሚገኙ የማይፈልጋቸውን መሪዎች ለማስወገድ ትዕዛዝ ሰጥቷል ብሏል።

የሩሲያ የውጪ ደህንነት ቢሮ ፈረንሳይ በፈረንጆቹ ጥር 3 በቡርኪናፋሶ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ማድረጓን ገልፆ አላማው የዳግም ቅኝ ግዛትን የሚቃወሙትን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራኦሬን መግደልና የፓን አፍሪካ አስተሳሰብን ማዳከም ነበር ብሏል።

ቢሮው ፈረንሳይ ከዩክሬን ጋር በመሆኑ አሸባሪዎችን ድሮንን ጨምሮ መሳሪያዎችን እያስታጠቀች ነው ብሎ ሲከስ ከብሪክስ ጋር መስራት የሚፈልገውን አዲሱን የማዳጋስካር አስተዳደርም ለማስወገድ እየሰራች ነው ሲል ወንጅሏል።

ዘገባው የታስ ነው።

04/02/2026

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily News Ethiopian posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share