ገራገር ፔጅ -Gerager Page

ገራገር ፔጅ -Gerager Page Inspiration does exist, but it must find you working this page is upload any post

24/09/2026

ሞት እንቢ 😀😀

ፍቺ ጠየቀች!..እወደዋለሁ....እሳሳለታለሁ...ልክ እንደ እናት እቅፌ ውስጥ አስገብቼ ፀጉሩን እየደባበስኩ.."ዛሬ ቀንህ እንዴት ነበር አባቴ?""ባክሽ ብዙ ደስ አይልም ወይ ላንለወጥ ነገር ...
22/09/2026

ፍቺ ጠየቀች!
..እወደዋለሁ....እሳሳለታለሁ...ልክ እንደ እናት እቅፌ ውስጥ አስገብቼ ፀጉሩን እየደባበስኩ..

"ዛሬ ቀንህ እንዴት ነበር አባቴ?"
"ባክሽ ብዙ ደስ አይልም ወይ ላንለወጥ ነገር እየደከምን ነው ሌላ አማራጮችን መፈለግ አለብን...መጀመሪያ ቃል እንደገባሁልሽ ቃሌን ማክበር አልቻልኩም...አንደላቅቄ ማኖር አልቻልኩም...ከጓደኞችሽ አሳነስኩሽ...አታይም ፀጉርሽን" ይለኛል የተበጣጠሰ ፀጉሬን ቀና ብሎ በእጁ እየነካካ....

"እኔኮ አፈቅርሀለው ነገ የተሻለ ቀን እንደሚመጣ አውቃለሁ ባይመጣም አፈቅርሀለው ኪስህን አይቼ አይደለም የወደድኩህ ...አንተ ብቻ በርታልኝ አንተ ብቻ ጠንክርልኝ ቢኖርህ እንዴት እንደምታኖረኝ አውቃለሁ"

"ብቻ ነገ ቀን ይውጣልን የኔ እናት" ብሎ ግንባሬን ስሞኝ ከስሬ ይሸጎጣል...ይለፋል ይሰራል እኔም እሰራለሁ ግን ትዳር እንዳሰብነው አልሆነልንም ነበር ከባድ ጊዜ ነበር ....ከጊዜያት በኋላ ሁሉም ነገር መስመር ያዘልን ...ሱቅ ከፈትን...ሀብት አፈራን...ብዙ ነገሮችን ቀየርን....

"ከጓደኞቼ ጋ ራት ፕሮግራም አለብኝ ካመሸሁ አታስቢ አትጠብቂኝ"

"እሺ ራሳችሁን ጠብቁ"
..ከጊዜያት በኋላ ያመጣው ባህሪ ግራ ያጋባል...ያኔ በባዶ ኪስ የነበረን ፍቅር አሁን ገንዘብ ቀይሮታል...ቤቱ ከሚያድርበት ውጪ የሚያድርበት ጊዜ ይበልጣል...እንደበፊቱ መታቀፍን አይፈልግም ...ከእኔጋ ጊዜ ማሳለፍ አይፈልግም...እንደውም ከእኔጋ መታየትንም አይፈልግም...ብዙ ጊዜ ችግሩ ከእኔ ነው ብዬ ራሴን ለመለወጥ ታገልኩ...ኋላ ላይ የገባኝ ችግሩ የኔ እንዳልሆነ ነው ያኔ ዝምታን መረጥኩ....

"መፋታት አለብን በእርግጥ የተፈራረምነው ነገር የለም እንለያይ.."
አለኝ....ለካ አልተፈራረምንም...ያኔ እንፈራረም ስለው" ከወረቀትኮ ልብ ይበልጣል" ነበር ያለኝ የትም አይሄድም ብዬ ስላሰብኩ ከዛ በኋላ ደግሜ አልጠየቅኩትም.....

"ያሁሉ ጊዜስ? ያ ሁሉ ፍቅራችንስ? የኔስ እድሜ? በቃ? በቀላሉ እንለያይ አልከኝ? "
"አዎ በቃ እኔም ላንቺ ያለኝ ስሜት ቀንሷል...አንቺም በጊዜ ወደሚወድሽ ሂጂ"..ለካ ነይልኝ ባሉ ማግስት ሂጂም ይባላል...ለእሱ ብዬ ነበር ከቤተሰቦቼ የተለየሁት...አይሆንሽም ሲሉኝ ይወደኛል ይሆነኛል ብዬ ነበር በባዶ ቤቱ የገባሁት....

"አስብበት ግድ የለህም"
"አስቤበታለሁ ውሳኔዬን ነው የነገርኩሽ...ቤተሰቦችሽ ጋ ምትሄጂበትን ቀን ሰአት አሳውቂኝ መኪና እልክልሻለሁ..." ጥሎኝ ወጣ....

ግራ ገባኝ...ከሱጋ ያሳለፍኩት ጊዜ
በሰከንዶች ውስጥ እንደ ትውስታ ታዩኝ...በባዶ ቤት የነበረን ፍቅር ታየኝ...ልቤ ተሰበረ ድምፁ ለእራሴ እስኪሰማኝ ድረስ ከሽ...ከሽ...ይለፍልኝ እንጂ አንቺን እንዴት እንደማኖርሽ አቃለው ብሎኝ አልነበር? ገንዘብ ሲመጣ ፀባይም አብሮ ይቀየራል? ፍቅርም ይጠፋል? ምኔ አስጠልቶት ነው? እንደ እናት ስፍስፍ አልኩበት? የትም እያደረ ሲመጣ ስለማልጠረጥረው ነው? ወይስ ጨቅጫቃ ሚስት መሆን ነበረብኝ? እኔ የችግሩ መወጣጫ ነበርኩ? ብዙ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች..... አብረን የተነሳነው አንድ ፎቶ እንኳን አልነበረንም....ፍቅር አውሮኝ ነበር....እኔ ከዛ ቤት በወጣሁ ማግስት...የምታምር የምታሳሳ ቆንጅዬ ኮረዳ አስገባ...ቅር አላለኝም ...ውበቴ ደብዝዞበት ነው ካለበት ደረጃ ጋ አልመጥነውም ነበር....ቅር አላለኝም....ማፍቀር የራስ ማድረግ ብቻ አይደለም የሚያፈቅሩትን ሰው ምርጫም ማክበር ፍቅር ነው።

" አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳያልፍ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም ተለቀዋል " - ማህበሩበኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ "ቢላ" በሚባለው አካባቢ ከሳምንት በፊት በርካታ ነዳጅ ...
22/09/2026

" አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳያልፍ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም ተለቀዋል " - ማህበሩ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ከተማ "ቢላ" በሚባለው አካባቢ ከሳምንት በፊት በርካታ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ጥቃት ሲቃጠሉ፣ ታግተው ተወስደው የነበሩ አሽከርካሪዎች ከእገታ መለቀቃቸውን የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የእገታና የቃጠሎ ጥቃቱ የተፈጸመው ጳጉሜ 1/2018 ዓ/ም ሲሆን፣ ጉዳዩን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ማብራሪያ የሰጠን ማህበሩ፣ ሾፌሮቹን "በተኩስ ነው ያስቋሟቸው፤ ተሽከርካሪዎቹ ተቃጥለዋል፤ ታጣቂዎቹ አምልጠዋል" ብሎ፣ ዲያው ስልክ ተደውሎለት ጉዳዩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንዳሳወቀ ገልጾልን ነበር።
ጥቃቱ በተፈጸመበት ቦታ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እንዳሉበት፣ አንዱ ሹፌር በወቅቱ ቢያመልጥም፣ ከስምንት በላይ የሚሆኑት ግን መታገታቸውን አስረድቶ ነበር። ከሹፌሮችን ጉዳይ የሚከታተለው የ" " ሹፌሮች አንደበት " የታጋቾችን ቁጥር 14 አድርሶ ነበር።
አሁንስ ምን ተባለ ?
የታጋቾቹ ጉዳይ ከምን ደረሰ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር አመራር፣ " ሁሉም ተለቀዋል። ሁሉም በሰላም ወደ ወደቤታቸው ገብተዋል " ብለዋል።
ታግተው የነበሩት በትክክል ቁጥራቸው ስንት ነው ? የተለቀቁትስ ? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ አመራሩ፣ " የኛ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ዘጠኝ ናቸው። ስሌሎቹ አላወኩም። የኮንስትራክሽን መኪናዎችም አብረው ስለነበሩ ምን ያክል እንደታገቱ መረጃው የለንም " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
የታጋቾቹ ብዛት 14 መሆኑ በወቅቱ ሲነገር ነበር፤ " ሁሉም ተለቀዋል " ሲባል፤ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ብቻ ናቸው ሌሎቹም ሾፌሮችም ተለቀዋል ? ለሚለው ጥያቄ አመራሩ፣ " በወቅቱ ሪፖርቱ የደረሰን የኛ ሾፌሮች ብቻ ነው እንጅ እኮ የኮንስትራክሽን መኪና እና የሌሎች ሾፌሮችም ይኖራሉ፤ ቁጥሩ እስከ 14 ሊደርስ ይችላል " ብለዋል።
የሌሎች ተሽከርካሪዎች ሾፌሮችም ከእገታ መለቀቃቸውን እንደሰሙ ገልጸው፣ " ሁሉም ተለቀቁ ነው የተባለው፤ የሰማሁት እንደዛ ነው። 'ያልተለቀቀ የለም' ነው ያሉኝ " በማለት ነግረውናል።
አሽከርካሪዎቹ ከእገታ የተለቀቁት ከቀናት በፊት መሆኑን ገልጸዋል። ታጋቾቹ የተለቀቁት ገንዘብ ተከፍሎ ነው ወይስ በምን መልኩ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ " እሱን አላውቅም። ይህ ለሚዲያ ትሩፋት መሆን የለበትም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የታጋች ቤተሰቦችን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ባይሳካም እኚሁ የማህበሩ አመራር ግን፣ " ወደ ቤተሰቦቻቸውም እየደወልን እያጣራን ስለነበር ታጋቾቹ ቤታቸው ገብተዋል። ከእገታ የተለቀቁት በምን መልኩ እንደሆነ ግን እኛ መረጃ የለንም " ብለዋል።
ገንዘብ ተከፍሎ ነው የተለቀቁት? የሚለው " ጠቃሚ አይደለም " ያሉት አመራሩ፣ " ዋናው ነገር፥ አሽከርካሪዎቹ ሕይወታቸው ሳያልፍ በቤተሰቦቻቸው ጥረት በሰላም ተለቀዋል " ሲሉም ተናግረዋል።

19/09/2026

አስቸኳይ
የሚሸጥ ፍሪጅ ያላቹህ ሰዎሽ መገበያየት እንችላለን
0945688927 ላይ ደውሉልኝ

19/09/2026

በጵጵስና ስም ተሸፍነዉ ትዉልድን የሚገድሉ እንዲህ አይነት አባቶች ናቸዉ ።
ኮዬ ፈጬ ላይ ብትሄዱ ጉድ ነው እምትሉት ።
ልጂቱ ለማሳየት የፈለገችዉ የደረሰባትን በደል ነው

18/09/2026

😄😄😄😄😄👇

ጉድ ጉድ 😃😃በምጥ ላይ የነበረች አንዲት ሴት የፈፀመችው አነጋጋሪ ድርጊት‎‎በኬንያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ፣በምጥ ላይ የነበረች አንዲት ሴት፣ለባሏ የምትነግረው አስፈላጊ ነገር እንዳለ ...
09/09/2026

ጉድ ጉድ 😃😃
በምጥ ላይ የነበረች አንዲት ሴት የፈፀመችው አነጋጋሪ ድርጊት
‎
‎በኬንያ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ፣በምጥ ላይ የነበረች አንዲት ሴት፣ለባሏ የምትነግረው አስፈላጊ ነገር እንዳለ በመግለጽ ጆሮውን ወደ እሷ እንዲያቀርብ ከጠየቀችው በኋላ በሀይል ጆሮውን በመንከስ፣ጆሮው ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ማድረሷ ተነግሯል።
‎
‎የባለቤቱን ትፅዛዝ ተከትሎ ልትናገረው የፈለገችውን ነገር ለመስማት ጓጉቶና ተጨንቆ የነበረው ባል፣ባላሰበው ድንገተኛ የሆነ ጥቃት ሲጮህ እና ሲያለቅስ እንደነበር ተገልጿል።
‎
‎በህመም እና በፀፀት እያለቀሰ የነበረው ባል፣ድርጊቱን ለምን እንደፈፀመች በጠየቃት ወቅት "ይህንን እርግዝና ላመጡት ምሽቶች ያንን ደስታ አብረን እንደተጋራነው ሁሉ፣አሁን ደግሞ በዚህ ሰዓት እየተሰማኝ ያለውን ህመም እንዲሁ እንድትጋራው ፈልጌ ነው።" በማለት ምላሽ መስጠቷ ተነግሯል።

ለበዓል ንፁህ ቅቤ ከፈለጋቹህ 0945688927 ላይ ደውሉሉኝ
08/09/2026

ለበዓል ንፁህ ቅቤ ከፈለጋቹህ
0945688927 ላይ ደውሉሉኝ

07/09/2026

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም በጤና አደረሰን
ንፁህ የምግብ ቅቤ ሲፈልጉ እኛ ጋ ያገኛሉ
የተነጠረ በኪሎ=1800 ብር
ያልተነጠር =1200 ብር
አዲስ አበባ በሁሉም ቦታ እንደርሳለን
0945688927 ላይ ቢደውሉ ያገኙናል

8ቱ ያልተፃፉ የቢሮ ህጎችI was too young to be in some rooms, but old enough to learn how people really work because the corporat...
05/09/2026

8ቱ ያልተፃፉ የቢሮ ህጎች
I was too young to be in some rooms, but old enough to learn how people really work because the corporate office runs on rules that nobody writes down. (በአንዳንድ የስብሰባ ክፍሎች ውስጥ ለመገኘት እድሜዬ ገና ቢሆንም፣ የኮርፖሬት ቢሮዎች ማንም ሰው በማይጽፋቸው ህጎች የሚመሩ በመሆናቸው ሰዎች እንዴት እንደሚሰሩ ለመማር ግን በቂ ዕድሜ ነበረኝ።)
Office politics isn't about being fake or manipulative; it's simply about understanding human dynamics, strategic communication, and how influence actually works. (የቢሮ ፖለቲካ (Office politics) ማለት አስመሳይ ወይም ሰዎችን ተንኮል መጫወቻ ማድረግ ማለት አይደለም፤ ይልቁንም የሰዎችን ባህሪ፣ ስትራቴጂካዊ ተግባቦትን እና ተፅዕኖ መፍጠር እንዴት እንደሚሰራ በውል መረዳት ነው።)
1️⃣ Visibility Matters (ታይነት ዋጋ አለው)
Doing great work matters, but people need to see it too, so share regular updates and make sure your valuable contributions are never invisible.(ጥሩ ስራ መስራት ትልቅ ነገር ቢሆንም ሰዎች ስራዎን ማየትም ስላለባቸው ዘወትር የስራ ማሻሻያዎችን ያሳውቁ እንዲሁም ያበረከቱት ጠቃሚ አስተዋፅኦ በፍጹም የማይታይ እንዳይሆን ያድርጉ።"
2️⃣ Pick Your Fights (ጦርነቶችዎን በጥንቃቄ ይምረጡ)
Not every disagreement needs to become a battlefield, so you must pick your fights carefully and save your precious energy for things that actually move the needle.(እያንዳንዱ አለመግባባት ወደ ጦርነት መለወጥ የለበትም ስለዚህ የትኛውን ክርክር መግጠም እንዳለብዎ በጥንቃቄ ይምረጡ እና ጉልበትዎን ትርጉም ላላቸውና ለውጥ ለሚያመጡ ነገሮች ብቻ ያስቀምጡ።)
3️⃣ Likability is a Superpower (ተወዳጅነት ትልቅ አቅም ነው)
Being easy to work with matters much more than you think because leaders don't just promote the smartest person, they promote people they trust and enjoy working with.(አብሮ ለመስራት ምቹና ተስማሚ መሆን ከሚያስቡት በላይ እጅግ ወሳኝ ነው፣ ምክንያቱም መሪዎች የሚያሳድጉት በጣም ጎበዙን ሰው ብቻ ሳይሆን የሚያምኑትንና አብረውት መስራት የሚወዱትን ጭምር ነው።)
4️⃣ Manage Up Privately (አለቃዎን በግል ያስረዱ)
Learn what truly matters to your manager and align with their goals, and remember that while you can disagree, you should always do it privately and never publicly.(ለአለቃዎ ምን ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠው ጠንቅቀው ይረዱ እና ከጎላቸው ጋር ይጣጣሙ እንዲሁም ከእነሱ ጋር ባንስማማ እንኳን መቃወም ያለብን ሁልጊዜ በግል እንጂ በሰው ፊት መሆን እንደሌለበት ያስታውሱ።)
5️⃣ The Forward Rule (የመልዕክት ማስተላለፍ ህግ)
Treat every email and text like it could be forwarded to the entire management team, which means you must keep things professional, clear, and respectful at all times.(እያንዳንዱን ኢሜይል ለዋና አመራሮች ሊተላለፍ (forward ሊደረግ) እንደሚችል አስበው ይጻፉ ይህም ማለት የጽሁፍ መልዕክቶችዎን ሁልጊዜ ፕሮፌሽናል፣ ግልጽ እና አክብሮት የተሞሉ ማድረግ አለብዎት ማለት ነው።)
6️⃣ Real Connections (እውነተኛ ግንኙነቶች)
Strong professional relationships are built outside formal meetings, so remember that team lunches, coffee chats, and casual conversations often matter more than calendar invites.(ጠንካራ ሙያዊ ግንኙነቶች የሚገነቡት ከመደበኛ ስብሰባዎች ውጭ ነው፣ ስለዚህ የምሳ ሰዓቶች፣ የቡና ጨዋታዎች እና ተራ ወሬዎች ከቀጠሮ ስብሰባዎች በላይ ትልቅ ዋጋ እንዳላቸው አይዘንጉ።)
7️⃣ Speak Up (ይናገሩ)
If you never speak up, people will simply fill in the blanks for you, so share your ideas and ask strategic questions because your voice shapes your professional reputation.(ሀሳብዎን በጭራሽ የማይናገሩ ከሆነ ሰዎች በራሳቸው መንገድ የተሳሳተ ትርጉም ይሰጡዎታል፣ ስለዚህ ሀሳቦችዎን ያጋሩ እና ስትራቴጂካዊ ጥያቄዎችን ይጠይቁ፤ ምክንያቱም የእርስዎ ድምፅ የሙያ ስምዎን ይገነባል።)
8️⃣ Reputation Follows You (ስምዎ ይቀድምዎታል)
your reputation follows you everywhere and people talk when you're not in the room, so focus on being someone others want to recommend and support.(የሙያ ስምዎ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ይከተልዎታል እንዲሁም በሌሉበት ክፍሎች ውስጥ ሰዎች ስለ እርስዎ ያወራሉ፣ ስለዚህ ሁልጊዜ ሌሎች በደስታ ሊመክሩዎት እና ሊደግፉዎት የሚፈልጉት ሰው ለመሆን ይጣሩ።)
The sooner you learn the unwritten rules of the corporate world, the easier your career growth becomes and the faster you achieve success. እነዚህን ያልተጻፉ የኮርፖሬት ዓለም ህጎች ቀድመው በተረዱ ቁጥር የሙያ እድገትዎ (career growth) ይበልጥ ቀላል ይሆንልዎታል እንዲሁም ስኬት ላይ በፍጥነት ይደርሳሉ።
Which of these 8 unwritten rules took you the longest to learn in your professional career? Let me know in the comments below!

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ገራገር ፔጅ -Gerager Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ገራገር ፔጅ -Gerager Page:

Shortcuts

Share