አንድ ኢትዮጵያ

አንድ ኢትዮጵያ አንድ ኢትዮጵያን ኑ በጋራ እንገንባ ...

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 በሕዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡ የአሸናፊ ቁጥሮችም  እንደሚከተለው ሆነዋል ፡፡ #አን...
03/01/2023

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2015 በሕዝብ ፊት የወጣ ሲሆን የወጡ የአሸናፊ ቁጥሮችም እንደሚከተለው ሆነዋል ፡፡
#አንድ ኢትዮጵያ

   " የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ...
30/12/2022



" የፈተናውን ውጤት በአጭር ጊዜ እናሳውቃለን " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ ይህ የፈተና ሥራ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ አወንታዊ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈታኞች ደግሞ መልካም ውጤት ተመኝቷል።

" በአጭር ጊዜ ውስጥ የፈተናውን ውጤት የምናሳውቅ ይሆናል " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተፈታኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት አስተላልፏል።

#አንድ ኢትዮጵያ

30/11/2021



ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዶ/ር እሌኒ ገ/መድህን ሰጥቶ የነበረው የክብር ዶክትሬት ሰረዘ።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሰኔ 29 ቀን 2005 ዓ.ም ለዶ/ር እሌኒ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ምርት ገበያን በማቋቋምና በመምራት ላበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) የሰጣቸው መሆኑን አስታውሷል።

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በወቅቱ የክብር ዶክትሬቱን የሰጣቸው የህብረተሰቡ አኗኗር እና የሀገሪቱን የውጭ ንግድ ስርዓት እንዲሻሻል ባበረከቱት መልካም አስተዋጽኦ እና ለወደፊቱም በተሰጣቸው የክብር ዶክትሬት ልክ ሀገራቸውን ያለአድሎና በእኩልነት እንዲያገለግሉ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ነበር ብሏል።

ይሁን እንጅ ዶ/ር እሌኒ ሰሞኑን የዓለም አቀፍ ሰላምና ልማት ማዕከል ተብሎ ይጠራ በነበረው ድርጅት አማካኝነት በድብቅ በተዘጋጀ የበይነመረብ ስብሰባ ላይ ሙያዊነትን ያልጠበቀ፣ አድሏዊ፣ የአንድን ቡድን ፍላጎት ብቻ ያንጸባረቀ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲውን ዋና ዋና እሴቶች የሚፃረር ሀሳብን በማራመዳቸው ዩኒቨርሲቲው ለዶ/ር እሌኒ የሰጠውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በድጋሚ ሲያጤንና ሲመረምር መቆየቱን ገልጿል።

በዚህም መሠረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ህዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለዶ/ር እሌኒ ገብረመድኅን ሰጥቶት የነበረውን የክብር ዶክትሬት ዲግሪ (Honorary Degree of Humane Letters (DHLitt)) እንዲሰረዝ መወሰኑን አሳውቋል።

 #አንድ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ብዙ ተፃራሪ ሀይሎች በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን ለመጫን ደፋቀና እያሉ ነው ቢሆንም ግን እኛ ልጆቿ ልክ እንደዚህ በተጠንቀቅ ልንጠብቃቸዉ ይ...
24/11/2021

#አንድ ኢትዮጵያ
አሁን ላይ ብዙ ተፃራሪ ሀይሎች በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ክንዳቸውን ለመጫን ደፋቀና እያሉ ነው ቢሆንም ግን እኛ ልጆቿ ልክ እንደዚህ በተጠንቀቅ ልንጠብቃቸዉ ይገባል!!
ኢትዮጵያ ታሸንፋለች አንድነቷም በጀግኖች ልጆቿ እንደተጠበቀ ይዘልቃል 💪💪💪💪

24/11/2021

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ Jeune Afrique በተባለ የፈረሳይኛ መፅሄት እና የእንግሊዝኛ ትርጉሙ The Afirca Report ላይ እሳቸውን የተመለከቱ ፅሁፎች መውጣታቸውን መመልከታቸውን ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቷ ከጋዜጠኛው ጋር ተገናኝተው እንደማያውቁ አሳውቀዋል።

ፅሁፉ ዛሬ መውጣቱ የአጋጣሚ ጉዳይ አይመስለኝም ያሉት ፕሬዜዳንቷ " በዚህ ደረጃ በኃላፊዎች መካከል መከፋፈል ያለ ለማስመሰል የተደረገ ሙከራ ነው" ብለውታል።

ይህንን አስመልክተው ተከታዩን ብለዋል፦

"የተለያዩ አገሮች ከገጠማቸው የፖለቲካ ችግሮችና የእርስ በእርስ ጦርነቶች እንዲወጡ የሰራሁ በመሆኔ አገራችን ዛሬ ያለችበትን ሁኔታ በአግባቡ እረዳለሁ። እንደሁላችንም ልቤ ተሰብሯል። የእርስ በእርስ ጦርነት በጣም አስከፊ ነው።

ሌላው መታወቅ ያለበት ከእንደዚህ ያለ ሁኔታ ለመውጣት One size fits all የሚባል ነገር የለም። መላውን መፈለግ የእኛ ፋንታ ነው።

ኢትዮጵያ ካለችበት አስከፊ ሁኔታ ለማውጣት ከምንግዜውም በላይ ሁሉንም ልጆቿን ትሻለች። መንግስትን የሚመሩት ጠ/ሚ አቢይ አህመድ በመሆናቸው ያስቀመጡትን አቅጣጫ ተቀብለን በምናውቀው፣ በሰራንበት፣ በሙያችን እየተረባረብን እንገኛለን።

በግጭት አፈታት ላይ ሰላማዊ መፍትሄ ፍለጋ ሁሌም ያለጉዳይ ነው። በዚያኑ መጠን ሳይወዱ ጦርነት መግባትም እንዳለ መዘንጋት የለበትም። ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ መንግስት ለንግግር ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጡ ይታወሳልና የሰላም ፍለጋው አካል መሆኑ ለእኛ እንግዳ አይደለም።

ብዙ አትናገሪም እባላለሁ። በየአጋጣሚው መናገሬ አልቀረም። ከወር በፊት ፓርላማን ስከፍት ያልኩትን ልድገም እየደማን ነው። ፅጌረዳዋ እንዳትርቀን እንተባበር እንበርታ።"

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አንድ ኢትዮጵያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አንድ ኢትዮጵያ:

Share