GMN ጉራጌ ሚዲያ ኔትዎርክ

GMN  ጉራጌ ሚዲያ ኔትዎርክ የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔር መፍራት ነው

12/07/2026

my people

09/07/2026

#ባህል

09/07/2026

ኢዜማ መንግሥት ለመመሥረት  የሚያበቃ ዕጩ ያስመዘገብኩ ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ብሆንም፣ የምጠብቀውን ውጤት መጥኛለሁ አለ።የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ፣ መጋቢት 19፣...
31/03/2026

ኢዜማ መንግሥት ለመመሥረት የሚያበቃ ዕጩ ያስመዘገብኩ ብቸኛው ተቃዋሚ ፓርቲ ብሆንም፣ የምጠብቀውን ውጤት መጥኛለሁ አለ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ፣ መጋቢት 19፣ 2018 እያካሔደ ባለው የበይነመረብ ስብሰባ፣ መሪው አቶ ኢዮብ መሣፍንት ኢዜማ 299 ዕጩዎችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ዕጩ አድርጎ በማቅረብ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስችል ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ሆኖ ወደ ውድድሩ መግባቱን ገልጸዋል። ሆኖም፣ ባለፈው የ2013 ምርጫ፣ ፓርቲው የተጋነነ ውጤት ጠብቆ እንደነበር አስታውሰው፣ ከዚያ ስህተታችን በመማር በዘንድሮው ምርጫ ግን የተመጠነ ውጤት እንደሚጠብቁ ("managed expectation" እንዳላቸው) ገልጸዋል።

አቶ ኢዮብ አክለውም፣ በዚህ ምርጫ ኢዜማ በፓርላማ መንግሥት መመሥረት የሚያስችል ድምፅ ባያገኝም፣ ያለውን የውክልና ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ፣ በፓርላማ ትልቁ ተቃዋሚ ፓርቲ ለመሆን አልሞ እንደሚንቀሳቀስ ጠቁመዋል። አቶ ኢዮብ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የመገንባት ሒደትን በአጭር ርቀት ሳይሆን በረዥም ርቀት ሩጫ እንደሚመሰል ተናግረዋል። (ምርጫ 2018 – GMN)
INSIDER'S

ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዘፈኑ ዓለም ራሱን አሰናበተ  | ታዋቂው ወጣት ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዓለማዊ ሙዚቃ (ዘፈን)  ሙሉ በሙሉ መውጣቱንና ወደ ቀድሞ መንፈሳዊ ህይወቱ መመለሱን በይፉ አስ...
31/03/2026

ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዘፈኑ ዓለም ራሱን አሰናበተ

| ታዋቂው ወጣት ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ከዓለማዊ ሙዚቃ (ዘፈን) ሙሉ በሙሉ መውጣቱንና ወደ ቀድሞ መንፈሳዊ ህይወቱ መመለሱን በይፉ አስታወቀ።

አርቲስቱ ይህንን ውሳኔውን ያስታወቀው በይፋዊው የፌስቡክ ገጹ ሲሆን፣ የዘፈኑን ዓለም "ውስብስብና አጋንንታዊ አሰራር ያለበት" ሲል ገልጾታል።

አቤል ላለፉት ዓመታት በሙዚቃው ዓለም በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ ከፍተኛ ውስጣዊ ትግል ሲያደርግ እንደነበር ገልጿል። በተለይም ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ዓመታት ሙዚቃን አቁሞ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ ወደ ዘፈኑ ዓለም ዳግም መመለሱ ጸጸት እንደፈጠረበት አልሸሸገም።

"ዓለም ውሸት ነው፤ ዝናም ከንቱ ቆሻሻ ነው! የውሸት መልክና የውሸት ፈገግታ ብቻ!" ሲል አቤል አሁን ያለውን አቋም በጽኑ ቃላት ገልጿል።

ድምፃዊው ለውሳኔው መነሻ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች (2ኛ ጴጥሮስ 2፥22 እና ዕብራውያን 10፥38) በመጥቀስ፣ ወደ ኋላ ማፈግፈግ አብቅቶለታል ብሏል።
ለዚህም ለውጡ የጸለዩለትን ሁሉ አመስግኗል።

አቤል ሙሉጌታ ከዚህ በኋላ ወደ ዘፈኑ ዓለም ዳግም እንደማይመለስና ህይወቱን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠቱን በማረጋገጥ መልዕክቱን አጠቃሏል።

መረጃ ሐብት ነው

31/03/2026
30/03/2026

የጉራጌ ማህበረሰብ ተባብሮ የማደግ እሴቶች በማስፋት ዜጎች በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እንዲተገብሯቸው ተጠየቀ።

, የጉራጌ ማህበረሰብ ተባብሮ ለማደግ ከሚጠቀሟቸው እሴቶች አንዱ ደቦ ወይም ጘዝ ሲሆን ዜጎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ያስችላቸዋል።

መረጃ ሀብት ነው

 !!​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጥራትን ለማስጠበቅ ባደረገው ክትትል፣ የሚከተሉት ተቋማት ከዘርፉ እንዲወጡ ተወስኗል።​ተቋማቱ በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ባለመግባታቸው እ...
30/03/2026

!!

​የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጥራትን ለማስጠበቅ ባደረገው ክትትል፣ የሚከተሉት ተቋማት ከዘርፉ እንዲወጡ ተወስኗል።

​ተቋማቱ በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ባለመግባታቸው እና በተደጋጋሚ (በደብዳቤ፣ በስልክና በአካል) የቀረበላቸውን ጥሪ ባለማክበራቸው።

​ ህጋዊነታቸው ተቋርጧል። እነሱም:-

1 አቢሲኒያ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
2 አፍራን ቀሎ ኮሌጅ
3 አገው ምድር ቢዝነስ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
4 አዲስ ፋና ኮሌጅ
5 ቢኤ ኮሌጅ
6 ኡቡንቱ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
7 ፈጣም ኮሌጅ
8 ግሪን የምርምርና የልማት ተቋም
9 ሴንቸሪ ኮሌጅ
10 ኮቻ ኪድማስ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
11 ካንድል ላይት የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
12 ቀይ ባህር ኮሌጅ
13 ማራኪ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ኮሌጅ
14 ኒው ዲፕሎማት ኮሌጅ
15 ፒቢቲ አፍሪካ ኮሌጅ
16 ኳሊቲ ስኮላር ኮሌጅ
17 ራዲካል ኢንተርናሽናል ኮሌጅ
18 ውቅያኖስ ኮሌጅ
19 የኔታ ኢንጅነሪንግ ኮሌ
20 ቪዥነሪስ የድህረ ምረቃ ኮሌጅ
21 ባቱ ግሎባል ኮሌጅ
22 ባህረ ጥበብ ጤናና ቢዝነስ ኮሌጅ
23 ማይክሮ ቢዝነስ ኮሌጅ
24 ማያ ኮሌጅ
25 ትሪፕል ኮሌጅ
26 ቤታሎጎ ኮሌጅ
27 ቤካ ኮሌጅ
28 ቀስተ ደመና ኮሌጅ
29 ብራይት ቪዥን ኮሌጅ
30 ኤ.አር.ቲ ሜዲካል ኮሌጅ
31 ኢሊያስ ኮሌጅ
32 ሳይፕሮ ኮሌጅ
33 ዳይናሚክ ኮሌጅ
34 ግራንድ ማርክ ኮሌጅ
35 ዱርማን ኮሌጅ
36 ህብረት ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
37 አይቤክስ ሆቴልና ቱሪዝም ኮሌጅ
38 አይ ኪው ኮሌጅ
39 ገራይ ኮሌጅ
40 ጋላክሲ ቢዝነስና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
41 ቪዥን ላንድ ኮሌጅ
42 መራ ሄመንገድ ኮሌጅ
43 ዩናይትድ ኦሮሚያ ኮሌጅ
44 ኢንተርናሽናል ሊደርሺፕ ኮሌጅ
45 ሲምለስ የርቀት ትምህርት ኮሌጅ
46 ዛክቦን ኮሌጅ
47 ኤም ኤስ ኤል ጂ ኮሊጅ
48 ስሪሳይ ኮሌጅ
49 ፋም ኮሌጅ
50 ስማርት ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
51 ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ቢዝነስና ሊደርሺፕ
52 ዳሎል የቲክኖሎጂና ቢዝነስ ኮሌጅ

የኢፌዲሪ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን

መረጃ ሀብትሽ ነው

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMN ጉራጌ ሚዲያ ኔትዎርክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to GMN ጉራጌ ሚዲያ ኔትዎርክ:

Shortcuts

Share

Category