Amnen Marketing & Promotion

Amnen Marketing & Promotion 🌍 ቱሪዝም | 🎭 መዝናኛ | 📊 የቢዝነስ ትንተና

🌍 Tourism | 🎭 Entertainment | 📊Business

19/03/2026
09/03/2026

የዕለቱ ዓበይት የቢዝነስ ዜናዎች
1. ኢትዮ ቴሌኮም ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የኔትወርክ ማስፋፊያ ስምምነት ፈረመ።
እነዚህ ታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች Ericsson፣ Huawei፣ Nokia፣ ZTE ሲሆኑ በባርሴሎና የተካሄደውን ዓለምአቀፍ የሞባይል ቴክኖሎጂ ኮንግረስ የተሳተፈው የድርጅቱ አመራር ይህንን የኢንተርኔት ፍጥነትን ለማሻሻል እና ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር ይረዳል ተብሎ የሚጠበቀውን ስምምነት ተፈራርሟል።
(Addis Standard)
2. ኢትዮጵያ የካፒታል ገበያዋን ለውጭ ኢንቨስተሮች ክፍት ለማድረግ መቃረቧን ተገልጿል
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የውጭ ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ እንዲሳተፉ የሚያስችል አዲስ መመሪያ እያዘጋጀ መሆኑን ተነግሯል። (capitalethiopia.com)
እርምጃውም የውጭ ካፒታል ወደ ሃገር ውስጥ መግባትን ያበረታታል፣ በገበያው የገንዘብ ፍሰትን ያቀላል፣ የፋይናንስ ሴክተሮች ሊበራላይዜሽን በር ከፋች ይሆናል።
3. የትግራይ ዘርፍ እና ንግድ ምክርቤት የክልሉ ውጥረት በንግድ እና በፋይናንስ ስርዓቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጥፋት አስመልክቶ በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስቧል፤
በጦርነት የተነሳ የብድር ችግር በክልሉ ውስጥ ያሉ ተበዳሪዎችን ወደ ኪሳራ እየገፋ እንደሆነ በመግለፅ ይህ ችግር ከተበዳሪ ነጋዴዎች አልፎ ወደ አጠቃላይ የፋይናንስ ስርዓቱ ሊሰፋ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
እስከ ዛሬ የተደረጉ ጥቂት ቴክኒካዊ መፍትሄዎች እና ከዚህ ቀደም የተደረጉ የክፍያ ጊዜ ማራዘሚያዎች ችግሩን ሊፈቱ አልቻሉም። በመሆኑም በጦርነት የተጎዳ የንግድ ማህበረሰብ እና የተፃፈ የብድር ውል በያዙ ባንኮች መካከል ያለውን ችግር ሊፈታ የሚችለው መንግስት በሚያደርገው ፖለቲካዊ መፍትሄ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
(Addis Fortune)
ሃፍቶም መክሊተይ

07/03/2026

የዚህ ሳምንት ዓበይት የቢዝነስ ዜናዎች
1. ዳንጎቴ ስሚንቶ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሊያስፋፋ ነው
የናይጄሪያው ታላቅ የሲሚንቶ ኩባንያ ዳንጎቴ ስሚንቶ በአፍሪካ ውስጥ የ1 ቢሊዮን ዶላር የማስፋፊያ እቅድ አለው ተብሏል። በዚህ እቅድ ውስጥ ኢትዮጵያ ከተመረጡ አገሮች መካከል አንዷ ናት።
ለማስፋፊያው ካነሳሷቸው ዋና ምክንያቶችም
የኮንስትራክሽን ስራዎች በፍጥነት እየጨመሩ በመምጣታቸው ምክንያት የሲሚንቶ ፍላጎት በጣም መጨመሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ለቢዝነስ ያለው ትርጉምም የሲሚንቶ አቅርቦት ይጨምራል፣ ዋጋውም ሊቀንስ ይችላል።
(Addis Standard)
2. "በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2018" “Invest in Ethiopia 2026” የኢንቨስትመንት ፎረም እንደሚካሄድ
ይህ ትልቅ ኩነት ከመጋቢት 17–18፣ 2018 (March 26–27, 2026) በአዲስ አበባ ይካሄዳል።
በዚህ ፎረም ከተለያዩ የዓለም ሃገራት በርካታ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከፎረሙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ከ2.4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት እንደሚገባም ተገምቷል።
በፎረሙ የሚሳተፉ ተቋማት በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በኢነርጂ፣ በቴክኖሎጂ እና ሌሎችም መሆኑ ተጠቁሟል። (2Merkato)
3. ለቡና ላኪዎች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
በዓለም ገበያ የቡና ዋጋ እየቀነሰ በመምጣቱ ምክንያት የኢትዮጵያ ቡና እና ሻሂ ባለስልጣን ለቡና ላኪዎች በእጃቸው የሚገኝ የቡና ምርት ወደ ውጭ ቶሎ እንዲልኩ እና እንዲሸጡ አስቸኳይ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
የዚህ ምክንያትም ኤክስፖርተሮች አላስፈላጊ ኪሳራ እንዳይደርስባቸው መሆኑ ተነግሯል።
(Capitalethiopia.com)
4. በትግራይ ክልል የነዳጅ እጥረት ንግድን እየጎዳ መሆኑን ተገልጿል
ወደ ክልሉ የሚገባው የነዳጅ አቅርቦት እየቀነሰ መጥቶ በቅርቡ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምክንያት የንግድ እቃዎች ዋጋቸውን ጨምሯል። መጓጓዣ ከቀን ወደ ቀን እየከበደ መጥቷል። (Addis Standard)
የታክሲ እና የትራንስፖርት አገልግሎት ተገድቧል፣ የፋብሪካ እና የንግድ ተቋማት ስራቸውን ቀንሰዋል። የነዳጅ ጉዳይ በዚህ ከቀጠለ በቀጣይ ግዝያት በክልሉ በርካታ የተወሳሰቡ ችግሮች ይከሰታሉ።

ተከታታይ የቢዝነስ እና ሌሎች ዜናዎች ለማግኘት ገፃችንን follow ያድርጉ!!

Welcome to Our Official Page! 🌍 Tourism | 🎭 Entertainment | 📊 Business Analysis✨ Discover destinations.🎶 Experience ente...
28/02/2026

Welcome to Our Official Page!
🌍 Tourism | 🎭 Entertainment | 📊 Business Analysis
✨ Discover destinations.
🎶 Experience entertainment.
💼 Understand business.
We promote opportunities, celebrate culture, and analyze markets that matter.
If you love growth, creativity, and smart insights, you are in the right place!
Follow us. Engage with us. Grow with us.

Amnen Marketing and Promotion
********************************************
እንኳን ወደ ገፃችን በደህና መጡ!
🌍 ቱሪዝም | 🎭 መዝናኛ | 📊 የቢዝነስ ትንተና
✨ መዳረሻዎችን ያግኙ
🎶 በመዝናኛ ይደሰቱ
💼 ስለ ቢዝነስ ግልፅነት ይፍጠሩ
የስራ እድሎች እንፈጥራን፣ ባህልን እናከብራለን፣ ገበያን እንተንተናለን፣ እናስተሳስራለን።
እድገት እና ፈጠራ ምርጫዎ ከሆነ — ትክክለኛው ገፅ ላይ ነዎት!
ይከታተሉን። ይሳተፉ። ከእኛ ጋር ይደጉ!🚀
አምነን ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን

ኣዶናይን ካልኦት ኣሕዋትናን ኣብ ሕፃፅ ዘለው ወገናትና ንምሕጋዝ እትገብርዎ ዘለኹም ምርብራብ ዝናኣድ እዩ። ትካልና Amnen Marketing & Promotion ብወገኑ ናይ Adonay Berh...
23/12/2025

ኣዶናይን ካልኦት ኣሕዋትናን ኣብ ሕፃፅ ዘለው ወገናትና ንምሕጋዝ እትገብርዎ ዘለኹም ምርብራብ ዝናኣድ እዩ። ትካልና Amnen Marketing & Promotion ብወገኑ ናይ Adonay Berhane Hailemichael ቻለንጅ ብምቕባል ብር 50,000 ኣታዊ ገይሩ ኣሎ። ኩላትና በብዝኸኣልናዮ ንረባረብ

እንኳዕ ን2018 ዓ/ም ንብርሃነ-መስቀል ብሰላም ኣብፀሐና!እንኳን ለ2018 ዓ/ም ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
27/09/2025

እንኳዕ ን2018 ዓ/ም ንብርሃነ-መስቀል ብሰላም ኣብፀሐና!
እንኳን ለ2018 ዓ/ም ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!

ሰናይ ሓዱሽ ዓመት 2018 ዓ/ምHappy New Year
10/09/2025

ሰናይ ሓዱሽ ዓመት 2018 ዓ/ም
Happy New Year

03/08/2025

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amnen Marketing & Promotion posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amnen Marketing & Promotion:

Share