Inform Ethiopia

Inform Ethiopia Ethiopia Forever
(1)

የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis)~~የአጥንት መሳሳት ማለት አጥንቶች ጠንካራነታቸውን እያጡ ስሰና ደካማ መሆናቸውን ለመግለፅ እንጠቀመዋለን። ይህ ችግር ብዙ ጊዜ በእድሜ መጨመር፣ በካል...
24/05/2026

የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis)
~~
የአጥንት መሳሳት ማለት አጥንቶች ጠንካራነታቸውን እያጡ ስሰና ደካማ መሆናቸውን ለመግለፅ እንጠቀመዋለን። ይህ ችግር ብዙ ጊዜ በእድሜ መጨመር፣ በካልሲየምና Vitamin D እጥረት፣ እንዲሁም በእንቅስቃሴ ባለማድረግ ይከሰታል።

አጥንቶች ሲደክሙና ስስ ሲሆነ ቀላል የሆነ መውደቅ እንኳን ለአጥንት መሰበር ሊዳርግ ይችላል።👉 በወገብ፣ በጀርባ እና በእጅ አጥንቶች ላይ ብዙ ጊዜ ይታያል።

**የሚታዩ ምልክቶች • የጀርባ ወይም የአጥንት ህመም
¢_የጀርባ ህመም
¢_በቀላሉ የአጥንት መሰበር
¢_በቀላሉ የድካም ስሜት

መከላከያ፦
¢_ካልሲየም ያለባቸው ምግቦች መመገብ
¢_በቂ የፀሐይ ብርሃን ማግኘት
¢_🚶‍♂️ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ
¢_ሲጋራና አልኮል መጠጥ ማቆም
¢_በሐኪም ምክር ምርመራ ማድረግ ህክምና መጀመር

✅ ጠንካራ አጥንት ለጤናማና ንቁ ሕይወት መሠረት ነው።
👍¢__ጤናዎን ይጠብቁ፤ አጥንቶችዎንም ከኦስቲዎፖሮሲስ (Osteoporosis)ይታደጉ!

  (H***n)  =====☑️  እና ስፖርት - እንደ ጂምናስቲክስ፣ ፈረስ ግልቢያ እና ብስክሌት መንዳት ባሉ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ድንግልና ሽፋን ሊጎዳ ወይም ሊጠፋ ይችላል።☑️  ...
24/05/2026

(H***n)
=====
☑️ እና ስፖርት -

እንደ ጂምናስቲክስ፣ ፈረስ ግልቢያ እና ብስክሌት መንዳት ባሉ ከፍተኛ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ድንግልና ሽፋን ሊጎዳ ወይም ሊጠፋ ይችላል።

☑️ #አደጋዎች -

በብልት አካባቢ ላይ የሚከሰት ድንገተኛ ጉዳት የሾለ ነገር ላይ መውደቅ፣ ወይም በመዋኛ ገንዳ ላይ የሚደርስ አደጋ ሽፋኑ እንዲጎዳ ሊያደርግ ይችላል።

☑️ ነገሮች -

ታምፖን (tampon)፣ የወር አበባ ኩባያ (menstrual cup) ሲጠቀሙ ጣቶች ወደ ብልት መግባት ሽፋኑ እንዲዘረጋ ወይም እንዲቀደድ ሊያደርግ ይችላል።

☑️ -

ማህፀን ምርመራ (pelvic exam) ወይም ሌሎች የውስጥ ምርመራዎች በሚደረጉበት ጊዜ ድንግልና ሽፋን ሊጎዳ ወይም ሊቀደድ ይችላል።

☑️ -

አንዳንድ ሴቶች ድንግልና ሽፋን ሳይኖራቸው ይወለዳሉ፣ ወይም ሽፋኑ በጣም ቀጭን ይሆን እና በራሱ ጊዜሊጎዳ ወይም ሊቀደድ ይችላል።

ይህ አካላዊ ሁኔታ በምንም መልኩ የሴትን ክብር ወይም የግብረ ሥጋ ግንኙነት ታሪክ አያመላክትም።

#ማስታወሻ:

የድንግልና ሽፋን መኖር ወይም አለመኖር አንዲት ሴት ወሲባዊ ግንኙነት እንዳላደረገች ወይም እንዳደረገች የሚያሳይ ትክክለኛ የህክምና ማስረጃ አይደለም።

#ምንጮች (Sources)
=====
1. BMC Women's Health, H***n and virginity

2.Vinmec, Will bleeding from ma********on indicate a torned h***n?

3. Dr. Nazli Korkmaz, Tearing of the H***n

4. What can make the h***n break?

5. Times of India, H***n breaks only during in*******se

6. Simple English Wikipedia, H***n

7. Gender Links, Virginity revisited

#በቅንነት #ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡

✍️የእባቡ ምስጢር፡ ከጥንቱ የፈውስ ጥበብ እስከ ዓለም ጤና ድርጅት መንበር .....ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) አርማ ላይ የሚታየው በዱላ ላይ የተጠማዘዘው እባብ፣ ለብዙ መቶ ዓመታት...
24/05/2026

✍️የእባቡ ምስጢር፡ ከጥንቱ የፈውስ ጥበብ እስከ ዓለም ጤና ድርጅት መንበር .....

ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት (WHO) አርማ ላይ የሚታየው በዱላ ላይ የተጠማዘዘው እባብ፣ ለብዙ መቶ ዓመታት የሰውን ልጅ አእምሮ ለጥርጣሬ፣ ለጥያቄ እና ለተለያዩ ምስጢራዊ ትርጓሜዎች ሲዳርግ የኖረ ድንቅ ምልክት ነው። ብዙዎች ይህንን ምስል የክፋት፣ የደባ ወይም የድብቅ ማህበራት ሴራ አድርገው ቢመለከቱትም፣ ወደ ታሪክ ጥልቅ ማህደር ስንዘልቅ ግን ከጀርባው እጅግ አስገራሚ፣ ፍልስፍናዊ እና ጥንታዊ የሰው ልጅ የህልውና ጉዞ እናገኝበታለን።

ይህ ምልክት ከጥንት ስልጣኔዎች ጀምሮ እስከ ዛሬው ዘመናዊ የህክምና መንበር ድረስ እንዴት ሊዘልቅ እንደቻለ በጥልቀት እንመርምረው።

✍️የጥንቱ የናስ እባብ እና የፈውስ ምስጢር

ወደ ግሪክ አፈ-ታሪክ ከመሻገራችን በፊት፣ በምስራቃዊው ዓለም እና በጥንታዊ መጻሕፍት ውስጥ እባብ ከፈውስ ጋር የነበረውን ጥልቅ ቁርኝት ማየት ያስፈልጋል። በነቢያት ታሪክ ውስጥ፣ የእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ በነደፏቸው እባቦች ምክንያት በታመሙና በሞቱ ጊዜ፣ ሙሴ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመቀበል የናስ እባብ ሰርቶ በዓላማ (በዱላ) ላይ እንደሰቀለ ይነገራል። ያንን የተሰቀለ የናስ እባብ የተመለከቱ ሁሉ ከመርዝና ከሞት ይድኑ ነበር። ይህም በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እባብ እና ከፍተኛ ዱላ ለፈውስ ምልክትነት በጋራ የቆሙበት ጥንታዊው ክስተት ነው።

✍️የአስክለፒየስ ዱላ እና የግሪክ ፍልስፍና

የዓለም ጤና ድርጅት አርማ በቀጥታ የወሰደው ግን "የአስክለፒየስ ዱላ" በመባል የሚታወቀውን ጥንታዊ የግሪክ ምልክት ነው። አስክለፒየስ በጥንታዊ ግሪካውያን ዘንድ የህክምና እና የፈውስ መለኮት ተደርጎ ይታይ ነበር።

በታሪኩ መሠረት፣ አስክለፒየስ በዱላው እየተመረኮዘ ታማሚዎችን ለማከም ወደ ተለያዩ ስፍራዎች ይጓዝ ነበር። በአንድ ወቅት አንድ እባብ ወደ እሱ ቀርቦ ዱላው ላይ ተጠመጠመ። አስክለፒየስም እባቡ የአፈርንና የዕፅዋትን ምስጢር፣ እንዲሁም የምድርን ድብቅ የፈውስ ኃይል እንደሚያውቅ በመረዳት እባቡ በዱላው ላይ እንዳለ እንዲቀጥል አደረገ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምልክት የህክምና ሳይንስ መለያ ሆነ።

የጥንቶቹ ጠቢባን እባብን ለመድኃኒትነት የመረጡበት ምክንያት ሦስት ትልልቅ ምስጢራዊ ፍልስፍናዎች አሉት፦

👉የቆዳ መላላጥ (ዳግም መወለድ)፦ እባብ በየጊዜው አሮጌ ቆዳውን ጥሎ በአዲስ ቆዳ ይተካል። ይህ ሂደት በህክምናው ዓለም አንድ የታመመ ሰው ከበሽታው አገግሞ አዲስ ሕይወት እንደማግኘቱ ይቆጠራል።

👉የመድኃኒት እና የመርዝ ድብቅ ባህሪ፦ የእባብ መርዝ በአግባቡ ካልተያዘ ገዳይ ነው፤ በጥበብና በልክ ከተቀመመ ግን ፈዋሽና ማገገሚያ መድኃኒት ይሆናል። የህክምና ጥበብም ልክ እንደዚሁ የጥንቃቄ እና የዕውቀት ውጤት ነው።

👉የዱላው ፅናት፦ ዱላው የህክምና ባለሙያዎች በበሽታዎች ላይ ያላቸውን ስልጣን፣ እንዲሁም ሕመምተኛው የሚያገኘውን የፅናት ድጋፍ ያመለክታል።

✍️በዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ውስጥ ያለው ድብቅ ስራ

የዓለም ጤና ድርጅት በ1948 ዓ.ም ሲመሰረት አርማውን ባዶ የዓለም ካርታ አድርጎ ብቻ መተው አልፈለገም። ድርጅቱ መላውን የዓለም ህዝብ ከበሽታ የመጠበቅ እና የማዳን ዓላማ እንዳለው ለማሳየት፣ ይህንን ጥንታዊ የፈውስ ምልክት (እባብና ዱላውን) በዓለም ካርታው መሀል ላይ በትክክል አስቀመጠው።

ነገር ግን ይህ ምልክት ለምን በሰዎች ዘንድ እንደ "ድብቅ ሴራ" ሊታይ ቻለ?

1. የባህል እና የሃይማኖት ግጭት፦ በብዙ ባህሎች እና እምነቶች ውስጥ እባብ የሽንገላ፣ የውድቀት እና የክፋት ተምሳሌት ተደርጎ ይወሰዳል። ስለዚህ፣ ሰዎች ይህንን ፍጡር በዓለም አቀፍ የጤና ተቋም አርማ ላይ ሲመለከቱት፣ በስተጀርባው ክፉ "ድብቅ መንግስት" እንዳለ አድርገው እንዲያስቡ በር ከፈተ።

2. ከንግዱ ምልክት ጋር መደባለቅ፦ ብዙ ጊዜ ሰዎች የአስክለፒየስን ዱላ (አንድ እባብ ያለው) እና የካዱኩስን ምልክት (ሁለት እባቦችና ክንፍ ያለው) ያቀላቅሏቸዋል። የሁለቱ እባቦች ምልክት የንግድ፣ የትርፍ እና የኮሙኒኬሽን መለያ ነው። አንዳንድ ተቋማት በስህተት የንግዱን ምልክት ለህክምና ስለተጠቀሙበት ምስጢሩ ይበልጥ የተወሳሰበ እንዲመስል አድርጎታል። ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት የመረጠው የፈውሱን (የአንዱን እባብ) ምልክት ብቻ ነው።

✍️

የዓለም ጤና ድርጅት አርማ ላይ ያለው እባብ የሰውን ልጅ ለመጉዳት ወይም በምስጢር ለመቆጣጠር የተሸሸገ የደባ ምልክት አይደለም። ይልቁንም፣ የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ በሽታን ለማሸነፍ ያደረገውን ተጋድሎ፣ ከተፈጥሮ መርዝ ውስጥ መድኃኒት የቀመመበትን ጥበብ እና እንደ እባብ ቆዳን አድሶ ዳግም የመኖርን ተስፋ የሚያሳይ የታሪክ አሻራ ነው። ዛሬም ድረስ ይህ ምልክት በኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ በአምቡላንሶች እና በፋርማሲዎች ላይ በክብር የሚቀመጠው ለዚሁ የፈውስ ጥበብ እውቅና ለመስጠት ነው።

✍️የመረጃ ምንጮች

🥺 የብሔራዊ ሕክምና ቤተ-መጻሕፍት የጥናት ጽሑፍ ስለ አስክለፒየስ ዱላ ታሪክ

"በብሔር የተጠለፉ የሰራዊት አባላት  ክሕደት ፈጽመው ነበር" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላየጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በትናንትናው እለት እንዲህ ብለዋል፦ "በብሔር...
24/05/2026

"በብሔር የተጠለፉ የሰራዊት አባላት ክሕደት ፈጽመው ነበር" - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በትናንትናው እለት እንዲህ ብለዋል፦

"በብሔር እና በፖለቲካ እሳቤ የተጠለፉ የሰራዊት አባላት ኢትዮጵያ ላይ ክህደት ፈጽመው ነበር፤ ነገር ግን በተሰራው የሪፎርም ስራ ሀገርን ከመፍረስ ታድገናል። ባለፉት አመታት የገጠሙንን ጦርነቶች በድል ተወጥተናል፤ አሁንም የጸረ ሰላም ኃይሎችን አከርካሪ እየሰበርን ነው"

 : ከኮንጎና ከኡጋንዳ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር  የአፍሪካ ሀገራት የኢቦላ ስርጭት ያሰጋቸዋል ተባለ !ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይ...
23/05/2026

: ከኮንጎና ከኡጋንዳ ባሻገር ኢትዮጵያን ጨምሮ አስር የአፍሪካ ሀገራት የኢቦላ ስርጭት ያሰጋቸዋል ተባለ !

ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ኡጋንዳ በተጨማሪ 10 የአፍሪካ ሐገራት የኢቦላ ቫይረስ ሥርጭት እንደሚያሰጋቸው የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን በዝርዝሩ ኢትዮጵያ ተካታለች።

የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ድርጅት የበላይ ኃላፊ ዣን ካሴያን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው የኢቦላ ወረርሽኝ ስጋት አለባቸው ተብለው ከተዘረዘሩት 10 ተጨማሪ ሐገራት ውስጥ ኢትዮጵያ ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ታንዛንያና ዛምቢያ ይገኙባቸዋል ሲል DW ዘግቧል።

የፌስቡክ ባለቤት "ሜታ" 8 ሺህ ሰራተኞችን አባረረ!ሜታ ኩባንያውን ይበልጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ለማስቻል በያዘው ትልቅ መዋቅራዊ ለውጥ ወደ 8,000 የሚ...
23/05/2026

የፌስቡክ ባለቤት "ሜታ" 8 ሺህ ሰራተኞችን አባረረ!

ሜታ ኩባንያውን ይበልጥ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ለማስቻል በያዘው ትልቅ መዋቅራዊ ለውጥ ወደ 8,000 የሚጠጉ ሰራተኞችን ማባረሩ ተዘግቧል።

የኩባንያውን አጠቃላይ አለም አቀፍ የስራ ኃይል 10% ያህል የሚነካው ይህ የስራ ስንብት የመጣው፣ ዋና ስራ አስፈፃሚው ማርክ ዙከርበርግ በ-AI ቴክኖሎጂ ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለማድረግ በመወሰኑ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ ኩባንያው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ከነበሩበት የስራ መደብ በማንሳት ከ-AI ጋር በተያያዙ ፕሮጀክቶች ላይ እንዲመደቡ አድርጓል።

ይህ ድንገተኛ ለውጥ በሰራተኞች መካከል ስለ ስራ ዋስትና፣ በስራ ቦታ ላይ ስላለው የመረጃ አጠቃቀምና በኩባንያው ውስጥ እያደገ ስለመጣው የ-AI ሚና ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት "ጽምዶ" በሚባለው እንቅስቃሴ በኩል "በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣ" ስጋት ቢኖር ስለሚወስደው እርምጃ አገር ውስጥ ለሚገኘው ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ማሳወቁን ...
23/05/2026

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት "ጽምዶ" በሚባለው እንቅስቃሴ በኩል "በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ የሚቃጣ" ስጋት ቢኖር ስለሚወስደው እርምጃ አገር ውስጥ ለሚገኘው ዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ ማሳወቁን ገለጸ።

የመከላከያ የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተር፤ ይህንን እንቅስቃሴ " 'ወደ መሬት እናወርዳን' ብለው ስንዝር እንቅስቃሴ" የሚያደርጉ አካላትን አስጠንቅቀዋል።

ዳይሬክተሩ ሜጀር ጄነራል ተሾመ ገመቹ ይህንን ያስታወቁት ትናንት አርብ ግንቦት 14/2018 ዓ. ም. በብሔራዊ ቴሌቪዥን በተላለፈ ቃለ መጠይቅ ላይ ነው። 21 ደቂቃ ገደማ የፈጀው ቃለ መጠይቅ በሙሉ ያተኮረው "ጽምዶ" በሚለው ስያሜ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ ነው።

የሜጀር ጄነራል ተሾመ ቃለ መጠይቅ የተለላፈው፤ የተለያዩ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች እንዲሁም ከሱዳን እና ኤርትራ እንደሆኑ የተገለጹ ግለሰቦች በሱዳኗ ፖርት ሱዳን ከተማ ስብሰባ አካሂደው እንደነበር የሚያሳይ ቪዲዮ ከተለቀቀ ከቀናት በኋላ ነው።

ዝግጅቱን የሚያሳየው ቪዲዮ የተለቀቀው ከኤርትራ መንግሥት ጋር ግንኙነት ባለው 'ህድሞና ቲቪ' የተባለ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ነው።

ከዚህ ቀደም "ጽምዶ" የሚለው ቃል በህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮች እና በኤርትራ መካከል ይደረጋል የሚባለውን ግንኙነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ ይውል ነበር።

እስካሁን ድረስ ሁለቱም ወገኖች በአመራሮች ደረጃ ግንኙነት ስለመፍጠራቸው በይፋ አልገለጹም።

በትናንቱ ቃለ መጠይቅ ላይ ሜጀር ጄነራል ተሾመ፤ "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጽምዶ የምትባል ነገር የተጀመረችበት ሒደት እንዳለ" ተጠቅሶ ስለ ጉዳዩ ምንነት ተጠይቀዋል። እንቅስቃሴውን "ፀረ ሉዓላዊነት" ሲሉ የገለጹት ሜጀር ጄነራል ተሾመ፤ "ጫንቃቸውን ለፈርኦን ቀንበር" በሰጡ የኢትዮጵያ አካላት እና "አካባቢው ላይ ባሉት ስብስብ" የተፈጠረ ነው ብለዋል።

መከላከያ ሠራዊት "በራሱ ቻናል" ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ "የአታሼ ማኅበረሰብ" አባላት ስለዚህ ጉዳይ "በደንብ እንዲያውቁ እና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሰፊ ሥራ" መከናወኑን አስታውቀዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዳይሬክተሩ እንደገለጹት፤ አገር ውስጥ ላሉ "አታሼዎች ስለ ሁኔታው ማስገንዘብ" ያስፈለገው "ለአምባሳደሮቻቸው ቀዳሚ ሰዎች እና አካላት ስለሆኑ" ነው።

በተጨማሪም "ነገ እንደው እቺን ሐሳብ 'ወደ መሬት እናውርድ' ብሎ የሚሠራ አካል ካለ" የሚሰጠው ምላሽ ለዲፕሎማሲው ማኅበረሰብ "አስቀድሞም የተነገረ ጉዳይ" እንዲሆን በመታሰቡ መሆኑንም አስረድተዋል።

"ከዚህ ሐሳብ ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ነገ ትልቅ [እርምጃ] የሚያስወስድ ጉዳይ ቢነሳ የማንንም ፈቃድ መጠየቅ እንኳ ባያስፈልግ፤ ወዳጆቻችን፣ አብረውን የሚሠሩ ሰዎች የውጪ ሰዎች ይሄን ሐሳብ እንዲገነዘቡ ማድረግ ተገቢ ስለሆነ [ነው]" ሲሉም አብራርተዋል።

ሜጀር ጄነራል ተሾመ፤ የውጭ ጉዳይ ሚስቴርም በዚሁ ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ ሥራ ያከናውናል የሚል እምነት እንዳላቸውም አክለዋል።

ይህ እንቅስቃሴ "ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት አስጊ" ተደርጎ እንደማይወሰድ የተናገሩት ዳይሬክተሩ፤ ሐሳቡን ለመተግበር የሚደረግ እርምጃን በተመለከተ ግን አስጠንቅቀዋል።

"እቺኛዋን የጽምዶ ሐሳብ በተመለከተ ግን፤ ይቺን ቅዠት 'ወደ መሬት እናወርዳታለን' ብለው ስንዝር እንቅስቃሴ ቢያደርጉ፣ እንደ ሉዓላዊ አገር ይሄ ተቋም ደግሞ በመንግሥት ግዳጅ እንደተሰጠው፣ ኃላፊነት እንደተሰጠው፣ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሥራ እንደሚሠራ አካል፤ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ ብለን ነው የምናስበው፣ የምናምነው" ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ለዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ገለጻ እንደሰጠበት የገለጸው "ጽምዶ" ዝግጅት በፖርት ሱዳን የተካሄደው፤ በኢትዮጵያ እና ሱዳን መካከል የተፈጠረው ውጥረት ይፋ በወጣበት ወቅት ነው።

ባለፈው ሚያዝያ ላይ በጄነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሐን የሚመራው የሱዳን ጦር "ከኢትዮጵያ የተነሱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድሮኖች" ግዛቱ ውስጥ ጥቃት መፈጸማቸውን በመግለጽ ወንጅሎ ነበር።

ይህንን ክስ "መሠረተ ቢስ" በማለት ያጣጣለው የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ፤ ሱዳን "ለተለያዩ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ማዕከል ሆና እያገለገለች" መሆኑን በማንሳት በምላሹ ከስሷል።

“ለህወሃት የጥፋት ሴራ ማገዶ አንሆንም!” -  የትግራይ ሚሊሻዎችበዚህ ወቅት የህልውና ቀውስ ውስጥ የገባው ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን፣ ህጻናትን ሳይቀር በግዳጅ ወደ ጦር ካምፕ እየተማገደ ይገ...
23/05/2026

“ለህወሃት የጥፋት ሴራ ማገዶ አንሆንም!” - የትግራይ ሚሊሻዎች

በዚህ ወቅት የህልውና ቀውስ ውስጥ የገባው ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን፣ ህጻናትን ሳይቀር በግዳጅ ወደ ጦር ካምፕ እየተማገደ ይገኛል። ይሁን እንጂ ይሄንን እኩይ ድርጊት የተገነዘበው የክልሉ ህዝብ ሴራውን በጽኑ እየተቃወመው ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ የቡድኑ ሚሊሻዎች ጭምር የፅንፈኛው የህወሃትን አጀንዳ በመቃወም ትጥቃቸውን እየፈቱ በስፋት እየኮበለሉ መሆኑን የተገኙ ታማኝ መረጃዎች ያመላክታሉ።

በተለይም በደቡብ ምስራቅ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የቡድኑ ሚሊሻዎች የቡድኑን ትዕዛዝ አንቀበልም በማለት፣ በብዛት ወደ “ሃራ ማሬት” እየተቀላቀሉ መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ቡድኑ የገጠመውን ከፍተኛ የሰው ኃይል እጥረት ለመሸፈን ሲል እላይ ታች እያለ ቢሆንም የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ መጋባት ውስጥ ገብቷል።

ይህም ከየአቅጣጫው የሚነሳበትን የህዝብ ቁጣና ተቃውሞ በሃይልና በማስፈራራት ለማፈን እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ህዝቡ ግን በአንድ ድምፅ “ጦርነት በቃን!” በማለት ላይ ነው።

ፅንፈኛው ህወሃት የህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው!

በአለም ከባድ ሙቀት መጨመር ምክንያት የእባቦች የተናዳፊነት ባህሪየሰ እየጨመረ ምጣቱ ተነገረ!📌በአየር ንብረት መዛባት ሳቢያ የመርዛማ እባቦች ፍልሰትና የንክሻ አደጋ በአለም አቀፍ ደረጃ እየ...
22/05/2026

በአለም ከባድ ሙቀት መጨመር ምክንያት የእባቦች የተናዳፊነት ባህሪየሰ እየጨመረ ምጣቱ ተነገረ!

📌በአየር ንብረት መዛባት ሳቢያ የመርዛማ እባቦች ፍልሰትና የንክሻ አደጋ በአለም አቀፍ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት አመለከተ

የአለም ሙቀት መጨመር መርዛማ እባቦች ቀድሞ ከሚኖሩባቸው ስፍራዎች በመውጣት የሰው ልጅ በብዛት ወደሚንቀሳቀስባቸው የእርሻ ቦታዎችና የመኖሪያ መንደሮች እንዲሰደዱ እያደረጋቸው ሲሆን፣ ይህም ከሰዎች ጋር ያላቸውን ንክኪና የአደጋውን መጠን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል።

በጥናቱ መሰረት በተለይም በአፍሪካ የሚገኙት የሚተፉ ዘንዶዎች (Spitting Cobras) እና በእስያ የሚገኙት ክራይቶች (Kraits) የሙቀት ማዕበሉን ለማምለጥ ሰፊ የቦታ ለውጥ እያደረጉ መሆኑ ተረጋግጧል።

ዘ ጋርዲያን የዓለም ጤና ድርጅትን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው፣ አገራት አደጋውን ለመከላከል በገጠራማ አካባቢዎች ለሚገኙ የጤና ተቋማት በቂ የእባብ መርዝ ማክሸፊያ መድኃኒቶችን (Anti-venom) እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል።

የጥራት ደረጃን በኦንላይን የሚያረጋግጥ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ!የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት፥ ሸማቾችና ነጋዴዎች የኪው አር ኮዶችን ሰስካን በማድረግ  የምርቶችን የጥራት...
22/05/2026

የጥራት ደረጃን በኦንላይን የሚያረጋግጥ
አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ተደረገ!

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኢንስቲትዩት፥ ሸማቾችና ነጋዴዎች የኪው አር ኮዶችን ሰስካን በማድረግ የምርቶችን የጥራት ደረጃ እንዲያረጋግጡ የሚያስችል "IES Verifier" የተሰኘ አዲስ የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል፤ ይህም የሀሰተኛ ምርቶችን ስርጭት ለመቀነስና የኢትዮጵያን ምርቶች በቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ገበያዎች ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የመተግበሪያውን መመረቅ አስመልክቶ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትርና የኢንስቲትዩቱ ቦርድ ሰብሳቢ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ይህ ዲጂታል መድረክ የሀገሪቱን የጥራት ማረጋገጫ ስርዓት በማዘመን ለኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር መሰረት በቀለ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ መተግበሪያው ተጠቃሚዎች ምርቶችን በኦንላይን ስርዓት እንዲለዩና እንዲመረምሩ በማስቻል ህዝቡ ከሀሰተኛ ምርቶች ይልቅ ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን እንዲገበይ እንደሚረዳው ጠቁመው፣ አሰራሩ የደረጃዎች ማረጋገጫ ሂደቱን በማቀላጠፍ የሀገሪቱን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ያሳድጋል ብለዋል።

ይህ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ከተመዘገቡ በኋላ ከApp Store እና ከGoogle Play አውርደው መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ ከዚሁ ጎን ለጎን የባለ አምስት ኮከብ ደረጃ ምግብ ቤት፣ የ200 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው የኮንፈረንስ አዳራሽና የኢንስቲትዩቱን ታሪካዊ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚያሳይ የኤግዚቢሽን ማዕከልን ጨምሮ ተቋማዊ መገልገያዎቹን ማደሱን አስታውቋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የታደሙት የአፍሪካ ደረጃዎች ድርጅት የቴክኒክ ዳይሬክተር ሪዩበን ጊሶሬ በበኩላቸው፥ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን በስኬት ለመተግበር ብሔራዊ የጥራት ደረጃዎች ወሳኝ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም የኢትዮጵያን አርአያነት ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኬንያ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን ኤሌክትሪክ ሃይል በእጥፍ ለማሳደግ በመወሰን አስፈላጊውን ተግባር እየከወነች ነው                         🇪🇹🤝🇰🇪ኬንያ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ የም...
22/05/2026

ኬንያ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን ኤሌክትሪክ ሃይል በእጥፍ ለማሳደግ በመወሰን አስፈላጊውን ተግባር እየከወነች ነው
🇪🇹🤝🇰🇪
ኬንያ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ የምትገዛውን 200 ሜጋዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በእጥፍ በማሳደግ 400 ሜጋዋት ለማድረስ አስፈላጊውን ሕጋዊ፣ አስተዳደራዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮች እያጠናቀቀች መሆኑን በማስታወቅ ጠቅላላ ሂደቱን በመጪዎቹ አምስት ወራቶች ለማጠናቀቅ እየሰራች መሆኑን እወቁልኝ ብላለች።

ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ አስተማማኝና እርካሽ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በማቅረብ የምስራቅ አፍሪካ Power House ለመሆን የያዘችው ራዕይ በትክክለኛ መንገድ ላይ ይገኛል።

ጎረቤት ሶማሊያ በዓለም ባንክ የፋይናንስ ድጋፍ ከኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል ለመግዛት በመጨረሻ ምእራፍ ላይ መሆኗን በትናንትናው እለት መዘገባችን ይታወሳል።

Address

Churchil
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Inform Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Inform Ethiopia:

Share

Category